በውስጥ መስመር ከገሀነም የደረሰኝ መረጃ

User avatar
nebex
Leader
Leader
Posts: 283
Joined: 29 Oct 2009 10:32
Contact:

በውስጥ መስመር ከገሀነም የደረሰኝ መረጃ

Unread post by nebex » 11 Mar 2018 20:36

በውስጥ መስመር ከገሀነም የደረሰኝ መረጃ !!
.
ገሀነም ውስጥ 3G ፣ 4G አረንደውም 5G ሁላ በሳኮኮድ ድርጅት በሁሉም የገሀነም አካባቢዎች በተሟላ ሁኔታ ተገጥሟል በነገራችን ላይ ሳኮኮድ ማለት ሳትናኤል ኮምኒኬሽን ኮፕሬሽን ድርጅት ማለት ነው አሉ !!
.
እናም መለስ ዜናዊ በለሱን እየገመጠ ኦንላየን ሲገባ የአዜብን መታገድ አንብቦ ክፉኛ አዘነ !! (ማነህ እዛ ጋር በለስ ገሀነም ውስጥ ይበቅላል ወይ ነው ያልከኝ ?? እና ገነት ውስጥ ይብቀልልህ ?? እሾህ ያለው ነገር ገነት ውስጥ አይበቅልም!! ) ይቅርታ ወደ ዋናው ጉዳዬ ልመለስ
.
የመለስን ማዘን ሳትናኤል አይቶ ልቡ በሀዘን አነባ ( የመለስ ሀዘን የሳትናኤል ሀዘን ነው ) ይሄን አይነት ሀዘን ብራዘርሊ ይሉታል የገሀነም ሰዎች !! እናም ሳትናኤል በመለስ ሀዘን ምክንያት አንድ መላ ዘየደ !! ለመለስም እንዲህ ሲል ነገረው ባለቤትህ የነበረችው አዜብ መስፍንን ምድር ላይ እንዲህ ከምትሰቀይ ይዤያት ልምጣ እንዴ ??
.
ይሄን ጊዜ መለስ ደነገጠ ደንግጦም አልቀረ ከመቀመጫው ብድግ ብሎ ሳትናኤል ላይ አፈጠጠ አፍጥጦም አልቀረ አንድ ቃል ተናገረ !! ያም ቃል እንዲህ የሚል ነበረ . . .
.
.
.
አንተ የምታቃጥለኝ መች አነሰኝ !!


source: Facebook

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”