የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 05 Jan 2012 14:44

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::


አዲሱን ቤታችንን ያለተቃውሞ ሁላችንም መቀበላችን ተረጋግጥዋል::ሞቅ ደመቅ ለማድረግ እጃንን እያፍታታን ነው::በ እርግጥ ወዳጆቻችን ታገሱ እያሉን ነው::ቤታችን ን የሚወዱ አንባቢዎቻችን ሁሉ
አብረውን እንደሚኖሩና እዚህም ከኛው ጋ እንደሚቀጥሉ እምነቱ አለ::


የመንጌን መጽሃፍ እየለበለብኩት ነው:: መንጌ አሁንም ስልጣን ላይ ያለ ነው የሚመስለው::የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የአረብ ቡችላዎች የሚሉት ቃላቶቹ እንዳሉ ናቸው::
መጽሃፉ ውስጥ የሚገርሙ የሚያስደንቁ የሚያናድዱና መንጌንም ትዝብት ውስጥ የሚከቱ ስራዎች ተካተዋል::
መጽሃፉን ለመጨረሽ ጥቂት ገጾች ስለቀሩኝ ወድፊት ብዙ ለማለት እሞክራለሁ::ጥቂት ካስገረሙኝ ነገሮች አንዱ ስለ ሌ/ኮ አጥናፉ አባተ ያሉት ሲሆን(ገጽ 258)


_ ሌ/ኮ አጥናፉ ውስጣዊ ምኞቱ ምንም ዩሁን ምን በተግባሩ ግን ከኛ እስከተለየበት ቀን ድረስ አብዮታዊ ጓዳችን ነበር::በተግባር የሶስቱም የጦር ሃይሎች ንቅናቄ አባልና ንቁ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን የአብዮታዊ ደርግ ፈጣሪም ነበር::
በየዋህነቱና በክፉ መካሪዎቹ ወደ ኋላ ቃል ኪዳኑን ሳተ::አብዮት ልጆቿን ትበላለች እንደሚባለው ጓድ አጥናፉንም የፈጠረው ደርግ በላው::
ይላሉ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም::


ቸር እንሰንብት!!!

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 05 Jan 2012 15:03

ጤና ይስጥልኝ
በጣም ይገርማል አጠቃላይ ዳታዎቻችንን በተለይም ፎቶግራፍና ቨዲዮ መልሰን ልናያቸው መቻላችን ከልብ አስደስቶኛል ! ታዲያ ኢትዮፎረም ህግ የማስከበር ስራ ሊበዛበት እንደሚችል ገምታለሁ ድጋፋችንም አይለያቸውም:ባጭሩ ከዋርካ ያሸሸንን ጉዳይ እዚህ እንደማናየው አምናለሁ::
ፖስት ለማድረግ ችሎታችሁን ላካፈላችሁን ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ::
ሞፊቲኮ ያንተን ጽሁፍ አይቼ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ ? ፎቶ ፖስት ማድረግ ከተቻለማ ያኔ ወቤ ስጋ ቤት ቆመህ ያነሳህን ፎቶ እንደገና ልናየው ማለት ነው ብዬ ቅቅቅቅቅቅቅ በሳቅ ሙትት አልኩልህ ::
በነገራችን ላይ ስለመንግስቱ መጽሃፍ ስትናገር መጻፉን እንጂ ገበያ መውጣቱን አልሰማሁም ለነገሩ ገና ሳላነበው እንደህንድ ፊልም የሚታወቅ ታሪክ ከመሆን እንደማያልፍ እርግጠኛ መሆን ይቻላል::
ምክንያቱም ብዙም አዲስና አስገራሚ ነገር (ሰርፕራይዝ)ይኖረዋል ብዬ አልጠብቅም::
እስቲ ባክህ ወደ አስገራሚዎቹ ፎቶዎቻችን ልመለስና ልፈትሽ ::
ራስብሩ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 06 Jan 2012 10:12

ሰላም ቤቶች

ከዚህ በታች ያለው ፎቶ የክብረ መንገሥት ሻኪሶ መገናኛ አውራ ጎዳና ነው።


40415_1374742527902_1211989312_30945112_373621_n.jpg
40415_1374742527902_1211989312_30945112_373621_n.jpg (14.37 KiB) Viewed 4794 times

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 06 Jan 2012 16:59

Gosa
Joined: 21 Nov 2011
Posts: 10

Posted: Fri Jan 06, 2012 6:18 pm Post subject:
ሰላም ለሁላችንም !!

መጨረሻ እንደመጣሁ መጨረሻ ብቻዬን መቅረቴ ብያሳዝነኝም ወዴት እንደገባችሁ ስለማላውቅ ያ መከረኛ ሞፊቲ እስኪመጣልኝ እዚሁ አለሁ :: ገና እስከ ዛሬ የተጻጻፋችሁትን እሩቡን እራሱ አንብቤ ስላልጨረስኩ በሱ እራሱ ብዙ እጽናናለሁ :: በቁምነገር ቤቱን ወድጄ ነበር - ዳሩ ግን ብዙ ጊዜ የኔ ነገር ከረፈደ ለምን እንደምሆን አላውቅም ::

ወንድሜ ባለሱቅ 2012 ሱቅህ ገበያ በገበያ የሚሆንበት : እነ አይፋ አጠገብህ ሱቅ ለመክፈት ያሰቡት ሀሳባቸው እውን የማይሆንበት : እነ ሞፊቲ ሰክረው መጥተው ብድር የማይጠይቁበት የበረከት ዘመን እንዲሆንልህ እመኝልሀለሁ ::

ራስ ብሩ እና አዶቆርሳ ደግሞ ያ ከዉስጣችሁ እንደ ምንጭ የሚፈሰው የስነ -ጽሁፍ ስጦታችሁ እንደ ገናሌ ወንዝ ሞልቶ እነ ሞፊቲን ግራ ያጋባቸው :: በጣም አደንቃችኍለሁ ::

ሌሎቻችሁም ያው ምኞታችሁ ይሳካ ::

መልካም ገና !!
brookk
Joined: 11 Nov 2003
Posts: 274
Location: ethiopia
Posted: Fri Jan 06, 2012 6:57 pm Post subject:
የምናነበው የምንፈልገውን ብቻ እንዲሆን ራሳችንን መምራት የምንችለው እኛው ነን -- አርዕስቱን ወይም ስማቸውን አይተን ካልከፈትነው በአብዛኛው መጥፎ ስድባቸውንም ያለማየት እድሉ ይሰፋልናል ::
በርግጥ አንዳንድ ስድብ ከአርዕስቱ ስለሚጀምር ሊያስከፋን ይችላል --- አንዳንዱም በሌላ "ቶፒክ " ውስጥ እየገባ ...

ለማለት የፈለኩት የምንወዳችሁን ያህል ልናጣችሁ መሆኑ በጣሙን ያሳዝናል --- በአሁኑ ወቅት የሚሳደበው እየበዛ ጤነኛው እያነሰና እየራቀ መምጣቱ የዋርካን ኳሊቲና ተፈላጊነት እያሳነሰው መምጣቱም ግልጽ ነው
ይሁን እንጂ ሽሽታችሁ መዳኛችሁ መሆኑ አይታየኝም ---
ዋርካ ትላንት እንደዚህ አልነበረችም
ዛሬ ልትሸሸጉበት የምትሄዱበትም ቦታ እንደዛሬው ዋርካ የማይሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም --
መፍትሄው ችግርን መሸሹ ሳይሆን ሌላ ሊሆን የሚችልበትን በጋራ መፈለጉ ነው -- የሁላችንንም መማረር የሚያዩት ዋርካዎች ወደፊት አንድ ነገር ማድረጋቸው አይቀርም ::
ትላንት እጅግ አስቀያሚ ፎቶዎች ቢያስቸግሩን -- ፎቶዎች እንዳይለጠፉ እንዳደረጉት ሁሉ -- ለዚህኛው ቅጥ ያጣ የሀይማኖት ብልግና ደግሞ - የሆነ ነገር ማድረጋቸው አይቀርም
ካደረጉ አደረጉ --- ባያደርጉ ግን --የራሳችንን - የምንወደውን -- የምንፈልገውን ብቻ ለምን አናደርግም ? ለምን ራሳችንን በነሱ ቶፒክ ውስጥ አስገብተን እናሰቃያለን ? ካላነበባችሁትኮ አያናድዳችሁም --- አይቶ ማለፍምኮ አለ --- እራስን በማይረባ ነገር ውስጥ አስገብቶ ኮንስዩም ከማድረግ ::

ሀይማኖትን ሰበብ አድርጎ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል ሁሉ "ተራ " ነው -- የትኛውንም ሀይማኖት አይወክልም --- ለሀይማኖቱ መሞት የሚፈልግ እድሉ የሰፋ ነውና -- ከኮምፒተር ጀርባ ይውጣና ሄዶ ይፋለም ---- በሀይማኖታቸው ምክንያት የሚያልቁ ስንት ሙስሊሞች አሉ -- ሄዶ ያድናቸው --- በሀይማኖት ምክንያት በእሳት ያለቁ ክርስትያኖች ኢትዮጵያስ አሉ አይደል -- ሄዱ ለምን ደማቸውን አይወጣላቸውም ?

ውድ የክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች -- አስቡበት እንደገና -- ባትሄዱ እመርጣለሁ በበኩሌ (ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ቢሆንም ) :: ከሄዳችሁም እንግዲህ ሚስ እናደርጋችኋለን
ዋርካ የተበላሸችውን ያህል እንደዋርካ የትም አይኖርም (እስከአሁን ባለው )
መልካም እድል

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ከላይ የቀረቡት አስተያየቶች የሚረብሹ ናቸው::ወዳጆቻችን ቅር መሰኘታቸውንና ፍቅራቸውን እየገለጹልን ነው::ምን እንደሚሻል አላውቅም::እንግዲህ ስደቱን ተቀብሎ መጓዝ ወይም
በሽምግልና መመለስ ህሊናን ዳኛ በማድረግ ነው::

ውድ ጎሳ= ያላችሁበትን አላውቅም ነው ያልከው? ለምንኛውም እዚህ ነን::የድሮ ቂምህን ለመወጣት ከፈለክ እዚሁ ተከትልህ አናግረኝ::ዋርካ ላይ የትሳፍከውን ማንም አያነብልህም
ብዬ ወደዚህ ስቤ አምጥቼዋለሁ::
አይፋ ልጅቱን ለማየት ወደ ቦሬ ብቅ እንደምትል ነግራኛላች::እኔም ለሷ የሚሰጥ ደብዳቤ ለኬያታለሁ::አሁን ጉድህ ይፈላል::ደግሞ ብቸኛ ነኝ ትላለህ?የዛን ቀን ስትደውልልኝ
መኝታህ ላይ ሆነህ ቁና ቁና የሚያስተነፍስህ ብቸኝነቱ ነው ወይስ የሚገፋህ ሰው አጠገብህ ነበር?

ቸር እንሰንብት!!!!!

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 07 Jan 2012 02:34

መልካም የገና በዓል ለሁላችሁም እመኛለሁ::

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 07 Jan 2012 08:55

images.jpg
images.jpg (15.39 KiB) Viewed 4747 timesእንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

አዲሱ ዓመት የሰላምና የደስታ እንዲሁም የጤና ዓመት ያድርግላችሁ!!

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 07 Jan 2012 14:29

መልካም ምኞት ለተመኛችሁልን ሁሉ እንኳን አብሮ አደረሰን !
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሆንኩ የሚያሰኝ ቀን ነው ሁላችሁንም በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ !
አጋጣሚ ሆኖ በአሉ ቅዳሜ በመዋሉ ዘንድሮ ገናን በደንብ እንድናከብረው አስችሎናል::
የቤታችንን ወደዚህ ማምጣት በአንዳንድ ወንድሞቻችን ዘንድ ያስነሳውን ቅሬታ እንዳየነው መጥፎ አልነበረም በውነት ለመናገር እኛም
የለመድነውን እና የምናውቀውን ዋርካን ትተን መውጣት ቀላል ሆኖልናል ማለት አልችልም ::
ሆኖም ከኅሊናችን በላይ ማንም ወቃሽ አይኖርምና እኔ በበኩሌ ዋርካን ማሰብ ብቻ እንኳን የሚረብሸኝ ሁኔታ እየሆነ ከመጣ ቆይቶአል::
ከዚ በፊት የምታስታውሱ ከሆነ ኮሎኔል በጣም የሚደንቅ አባባል ተናግረው ነበር ቃል በቃል ባላስታውሰውም ሃሳቡ
( ልጆቻችንን እና ቤተሰቦቻችን እንዲያነቡና እንዲማሩበት ስናደርግ ቆይተን አሁን ግን ልጆቻችን በኛ እያዘኑብን ነው )
ትክክለኛ አባባል ነው እንዲህ ብለው ለዋርካ አድሚኖች በሰጡት ምክር አስጸያፊ ስድብ ወርዶባቸው ዋርካን ጥለው ተሰናብተዋል ::
ወንድማችን ብሩክ ደግሞ (ሽሽታችሁ መዳኛችሁ መሆኑ አይታየኝም ዛሬ ልትሸሸጉ የምትሄዱበት ቦታ እንደዛሬው ዋርካ ከመሆን ሊቀር የሚችል አይመስለኝም )
ሲል ሃሳቡን አካፍሎናል :በእርግጥም ይህም ትክክል ነው ሽሽታችን መዳኛ ላይሆን ይችላል::
ቢቸግረን ራሳችን ዌብ ሳይት ለመገንባትም ሞክረናል ግን እንደዋርካ የተለመደና
ምቹ ለማድረግ ሲባል እዚሁ ቆየን ::
ብሩክ አንተም እንዳልከው መጥፎ ስዕል የሚለጥፉትን ለመቆጣጠር እንዳደረጉት ሁሉ መጥፎ የሚጽፉትንስ በአንድ ክሊክ ማስወገድ ለምን አይቻልም ?
በርግጥ ይሰለቻል እንጂ በየቀኑ ስሙን የሚቀይርና የሚሳደብ ይኖራል ግን ትንሽ ግዜ ትግስት አድርገው ቢቆጣጠሩ ወይም ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን
በቂ ቁጥጥር ቢያደርጉ ችግሩን ይቀንሱታል ብዬ አምናለሁ::
ብሩክ ወንድማችን የሰጠኸን አስተያየት ካለህ አክብሮት የተነሳ ስለሆነ ከልብ ላመሰግንህ ወዳለሁ ::
ቢያንስ በእግዚአብሄር ስም ላይ ጸያፍ ጽሁፎችን ባናይ ዋርካ ቤታችን ነው ::

ጎሳ ደጌላን ታውቀዋለህ ? እኔ ትንሽ ልጅ ሆኜ እሱ ማር ቆራጭ ነው ሲባል እሰማ ነበር አንዴ ብዙ አመት ሳላየው ቆይቼ ጎሳ መግቢያ ላይ ቆሞ
መኪና ሲጠይቅ እኔ ከጓአደኛዬ ጋር ወደ ሻሸመኔ ስንሄድ ተገናኝተን ይዘነው ሄድን ከዛ መንገድ ላይ ስናወራ እየደጋገምኩ ደጌላ ደጌላ ስለው :
በኦሮምኛ አድርጎ ምን ደጌላ ደጌላ ይለኛል እኔም አላቀውም ሲል በደንብ ስላልገባኝ ምናልክ ስለው ? እሱን ድሮ ነው ምታውቀው
አሁን ኤሌማ ስሜ ነው ብሎኝ በጣም አስቆኛል::
እና ጎሳ እሰራለሁ ይበለኝ ወይም እዛ አካባቢ እኖራለሁ ይበለኝ ረሳሁ አንተ ጎሳ ከነበርክ ልታውቀው ትችላለህ ብዬ ነው::
የመጨረሻ ቀልደኛ ነው የሚገርምህ እሱ ግን በፍጹም አይስቅም ::

ራስብሩ


ቦንካ
Posts: 2
Joined: 06 Jan 2012 22:52
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ቦንካ » 07 Jan 2012 21:02

ሰላም ለጀምጀም ልጆች በሙሉ::
በመጀመሪያ መልካም የገና በዓል ለሁላችሁም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::

እኔም እንደሌሎቹ ዋርካ በሚገኘው ቤታችሁ እየገባሁ ለብዙ ጊዜ አነብ ነበር:: የአንዳንዶቻችሁን የስነጽሑፍ ችሎታ በጣም አደንቅም
ነበር:: እንደእውነቱ ከሆነ በዚያ ላለው ጽሑፍ ብትሳሱለት ምንም አያስገርምም:: ልትሳሱለትም ይገባል:: ነገር ግን ዋርካም ሆነ
ኢትዮፎረም ዘላለማዊነት የላቸውም:: ነገ እንደማንኛውም ድረገጽ ጠፍተው ሊቅሩ ይችላሉ:: ከመጥፋታቸውም በፊት ማስጠንቀቂያ
ይሰጡናል ብሎ መገመትም አይቻልም:: ስለዚህ ይህ ከመሆኑ በፊት እያንዳዳችሁ ጽሑፉን save የምታደርጉበትን መንገድ በቅድሚያ
መፈለጉ ብልህነት ነው::

ወደ ዋርካ በምገባበት ጊዜ በቀጥታ ወደናንተ ቤት ዘው ብሎ መግባቱን እንጂ ወዲያ ወዲህ ማለቱን ካቆምኩኝ በዙ ጊዜዬ ነው:: ለመሆኑ
ከእንደዚያ ዓይነቱ ጽሁፍ ምን ይገኛል ተብሎ ወደሌላው ክፍል ይገባል? አርዕስቶቹን ለመመልከት እንክዋን እስከሚከብድ ድረስ
አስጸያፊ ሆነዋል:: ፍጹም morality የጎደለው ብልግናን በማንበብ ጭንቅላትን ማስጨነቅ ትርፉ ምኑ ላይ ነው? እጅግ በጣም የሚገርመኝ
ደግሞ የዋርካ አዘጋጆች ኢትዮጵያውያን ከዚያ ዓይነቱ ጽሑፍ ምን ይማራሉ ብለውስ እነኛን ሰዎች ያስተናግዳሉ? ለኔ እንደዚህ የሚያስቡ
ኢትዮጵያውን መኖራቸውን በማወቄ ለአዕምሮዬ ትልቅ ስድብ ሆኖበታል:: ለካስ እንደዚህ ነን አስብሎታል?

በዚህም ምክንያት ወደ ኢትዮፎረም መቀየራችሁን በጣም ወድጄዋለሁ:: በተጨማሪም pictures and video ማስገባት መቻሉም በቀላሉ
የሚታይ ነገር አይደለም::

ስለዚህም ቤት ለእንቦሳ ብያለሁ::

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”