የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 604
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

Unread post by selam sew » 15 Jul 2020 12:37

‼️ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
****************
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ ግድቡን በተመለከተ በሳተላይት የሚታዩ ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።
AddisMedia youtube
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውን ትውልድ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልከ የሚደረግ እንደሆነ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ጨምሮ ከኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ማዳጋስካር እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 11 ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል።

በትእግስት የሻነው
Via EBC

#NileDam #EthiopiaNileRights #GERD

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”