ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!! ከዋርካ የመጣ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
Locked
User Ads
Leader
Leader
Posts: 110
Joined: 27 May 2010 20:33
Contact:

ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!! ከዋርካ የመጣ

Unread post by User Ads » 19 Jan 2012 00:31

ይህ ርዕስ የጀምጀም ልጆች ወይም በዋርካ ስማቸው የይድረስ "ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!" በሚል ርዕስ የተወያዩትን በተሳታፊዎቹ ጥያቄ ወደ ኢትዮ ፎረም የመጣ ነው

ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
560

PostPosted: Wed Aug 31, 2005 10:58 am Post subject: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
አያልቅበት ሌሊት ሌሊት መኪና ተራ የወጪ ከመጠየቅ በቀር በየቤቱ ልመና አያውቅም ነበር !!የሸዋን መኩዋንንት ስላስቸገረ በእኔ ትዕዛዝ የአዶላን አካፋ እንዲያነሳ ተገደደ ::በሁዋላም አቅሙ እየደከመ ሲመጣ ወደ /መንግስት መጣና የሌሊት ገጣሚ ሆነ ::የሚገርመው በረንዳ አዳሪም ሆኖ አገዛዙን በጣም ይዋጋ ነበር ::
ሰላምታዬ ከያላችሁበት ይድረሳችሁ !!!
This is Ras Biru Woldegabriel.
ውድ የአዶላ ልጆች ይህቺን ጥሪ ሳቀርብ የክብረመንግሥት ልጆቸ እንድንሰባሰብ በማሰብ ነው ::
ያቺ እኛን ያስተማረች /ቤት አሁን አርጅታ ፈራርሳለች :: ዲፕሎማት ሚኒስትርና ሳይንቲስት ለመሆን የበቁ ታላላቅ ሰዎችን ያፈራች ያቺ ትንሽዋ ራስ ብሩ /ገብርኤል /ቤት ዛሬ በአጥንትዋ ቀርታለች ::የዋርካን አምድ ላዘጋጁልን ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለቦሬ ለሻኪሶና ለክ /መንግስት ልጆች ሁሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ :: /ቤታችንን እናድሳት !!
በመጀመርያ ግን መገናኘቱ አስፈላጊ ነውና : የካምቦ የፈረንጅ ውሀ ,የአራዳ ,የሜጫ ,የኩሚና ;የገበያ ክፍል ኩቾና ሌሎችም ተሰባሰቡ :ተገናኘተን እንኩዋን ትዝታችንን እናውጋ ::
.በሉ በቸር ይግጠመን :: ወዳጃችሁ ራስ ብሩ ነኝ ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!!!!
http://www.adola-kibremengst.com/articl ... School.php

Last edited by ራስብሩ on Sun Aug 31, 2008 4:18 pm; edited 11 times in total
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
Back to topአደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
746
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Aug 31, 2005 11:38 am Post subject: መንግስቱ ሀይለማርያም ከሸዋ ሲነሳ ያዶላ መኩዋንንት ኩንታል ኩንታል ፈሳ !!!
ወንድሜ / / ራስብሩ ሰላምታዬ ይድረስህ !ጽሁፍህን ሳነብ ምን እንደተሰማኝ ወዩ ታውቃለች !!ታዲያልህ እዛ 02 ቀበሌ አሰጋኸኝ ወፍጮ ከመድረስህ በፊት ካለችው ድልድይ ወይም እነ ግርማ ጥንቅሹና እነ ቡጡ እሽቴ ሰፈር የነበሩ አንድ አባት ጦር ሁሌ ክራር ከጃቸው የማይለይ አስታወስካቸው ? እሳቸው በአንድ ወቅት የገጠሙትን ነው ርዕስ ያረኩት .አያልቅበትን አስታውሰዋለሁ ግን ምንም ለማለት አልችልም በጣም ትንሽ ነበርኩ ::ከሀሳብህ ስረዳ The US ወይም Europe ነው ያለኸው : ጅማሬህ እጅግ የሚደነቅ ነው አምላክ ይርዳህ !!ሁላችንም እንድንገናኝ እና እንደችሎታችን ራስ ብሩን ለመርዳት እኔ ቃል እገባለሁ ::አሜሪካን እና አውሮፓ ቢያንስ በስልክ ቅርብ ናቸውና ከሌሎቹም ለመገናኘት ሞክር ::
_________________

kibremengist
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
Back to topቀልቤለጌ

አዲስ

Joined: 31 Aug 2005
35
Location: UAE

PostPosted: Wed Aug 31, 2005 2:03 pm Post subject: መጣና ባመቱ ............ሰነበቱ .
የአባባ እልፍነህ ጉደታን ማሳ የሚያውቅ ቀልቤን ያውቃል !እንዴት ከረማችሁ /መዎች ::የካምቦው ቀልቤ ለጌ ነኝ :ጽሁፎቹን ሳይ በቃ መቼስ ምን ልበላችሁ :አንዴየግራዋ አንዴየወደሬ አንዴ ደሞ የተዋበች መስቀላ ጠጅ በቃ ተጭበረበረብኝ :: አደቆርሳ እኒያ ገጣሚው ሰውዬ 10 አለቃ ጸጋዬ ይባላሉ :: ለሁሉም በመገናኘታችን ደስታዬ ብዙ ነው :
ሰሞኑን በሙሉ ትዝታ እስክንገናኝ ቸር ያቆየን ::
_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
Back to topደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
4981
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Aug 31, 2005 11:05 pm Post subject: Re: አዶላ ወርቅ ናት በየወንዛወንዙ : እንደድመት ግልገል ሹሞቹ ባይበዙ !!
ራስብሩ እንደጻፈ():
.... ኢሉ ባነታን ...???

...ኢሉ ??? ኢሉ ማለት አስተዳዳሪ ነበር ልበል የቦረና ...?? እሱ ይሆን ጦር ይዞ አገር ሰላም ላይ ወያኔን ለመውጋት መጥቶ የነበረው ...?? ያብቱ ስም ግን ትዝ አይለኝም ....Sad
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
Back to top
_____________________________________________________________________

ቅሩንፉድ

ኮትኳች

Joined: 15 Apr 2005
454
Location: germany

PostPosted: Wed Aug 31, 2005 11:15 pm Post subject: ቅዱስ ሀሳብ
ወንድሜ ራስ ብሩ ስላምታዬ በአለህበት ይድረስህ ::
አያልቅበትን እኔም ትንሽ ትንሽ አስታውስዋለሁ በደንብ የማስታወስው ወፉን ነው :: ራስ ብሩ ስንቱን አስተምራ እንዲህ መዳከሟ ከልቤ አሳዘነኝ ::እናማ ያስብከው ጥሩ ነው :: ያስተማረችንን ትምህርት ቤት ከወደቀችበት በምንችለው አቅም እናንሳት :: አደቆርሳ መልክት ደርሶኛል አመሰግናለሁ ከጠራአችው ልጆች የማውቀቸው : አልማዝ በርሄን ካናዳ ነው ያለችው :: ጸጋአዛብ ሲዊድን ነው : ተስፉ ለንደን ነው ያለው :: ሰይድ ናጂ የት እንዳለ አላውቅም :: እንዲያውም እህቱ ጓደኛዬ ናት :: በሉ ቸር ይግጠመን የአገር ልጆች Exclamation
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ባለሱቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2004
962
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 01, 2005 6:35 am Post subject: ያዶላ ወዩ ልጆችችችችችችችች
እንዴት ከረማቹ ወገኖቼ !
እናንተን በማግኘቴ መቸም ምን ብዬ እንደምናገር አላቅምምምምም ... ራስ -ብሩን ቢሎ አዶላ አደቆርሳ .. እነዚያ የሚያማምሩ / ቤቶች .... ደርቀዋልልልልልል
ማርያም መዳህኒያለም ሚካኤል እና ስላሴ ... ጫካቸው ተራቁቶ ከአጂፕ ሆነው ሲያዩት ግርማ ሞገስ የነበረው የማርያም ዳገት አሁን የኔን መላጣ መስሏል ... እረ ጎበዝዝዝዝዝዝዝዝ ... ያንን ሁሉ ዛፍ ጨርሰው ሲያበቁ ራቁቷን አስቀርተው አሁን ወደ ባሌ ተሻግረዋል እነ ጆቫኒ -ጊቢ ዘምባባ አባሎ ሀጂ -ኢብራሂም .. የእንጨት መሰንጠቂያዎች .... አሁን ዝግባ ለስም እንጂ አይታይምምምም
ዶቅማ እንጆሪ አውጥ የሾላ ፍሬ ,, እንደድሮ ወጣ ብሎ መልቀም የለም ...
አሬራ ዳቦሸዌ ወተት ገፉማ ... ስሙ እንጂ የለም አሉኝ ዘመዶቼ ...
የሚያምረው የጉጂ ከንፈር .. በቅቤ እብድድድድድ ያለው አሞጥሙጤ .. ድርቅ መታው አሉኝ .. እረ መቼ ነው ሄጄ የማየውውውው ...
የጋሽ እርሶም ወፍጮ ያሰጋኸኝ የሀጂ -ከድር እና ሌሎቹም ወፍጮ ቤቶች ጦማቸውን ነው የሚያድሩት አሉ .. የሚፈጭ ጠፍቶ ...
መቸም ወፍጮ ቤት ለጠበሳም ቢሆን ... ማስፈጨቱ ቢቀር ለጠበሳም ቢሆን ሳይሄድ የቀረ ያለ አይመስለኝም ... እስኪ ተሰባስበን ስለዛች የወርቅ ሀገር .. ስለዛች የመንግስት ክብር ስለሆነች አገር እናውራ ...
ይሄ ማርያም ዳገት .. ሚካኤል ስለሰራነው ነገር መጠየቅ የተከለከለ ነው ... አፍራልከሁና
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እወዳቹዋለሁ ያገሬ ልጆች ...
ለአዶላ / ቤት የሚሆን መፃፍ ለማሰባሰብ እቅዱ አለኝ ... እስኪ እንመካከር ...
ሸንኮራ እየበላን
የዶሌን ጫት ይዘን
ወደ ኩቾ በር ወይም አደቆርሳ መንገድ ወጣ ብለን ዛፎቹ ስር ተቀምጠን እንጨዋወት ...
01 ቀበሌ እፈራለሁ ፖሊስ ጣቢያውንና ወህኒ ቤት ድሮ ድሮ ብዙ ብዙ ስለተመላለስኩ .... በኢሀፓ ጊዜ ዘመዶቼ ታስረውብኝ ....
እኔ ግን ወረቀት አልበተንኩም ... ሻለቃ ደስታ መሸሻን ስለምፈራ .... እረ የት ገቡ !
አራጁ ከንቲባ አዋሳ አየሁት ... ተገለማምጠን ተላለፍን ...ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም እንሰንብት .. ምስጥሬን አውርቼ እንዳልጨርስ

እምምጷ
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
_____________________________________________________________________--

የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
768
Location: united states

PostPosted: Thu Sep 01, 2005 7:27 am Post subject:
ስላም ለናተ ይሁን የወዩ ልጆቸ መቺም እኒ ስለ /መንገስት በተነሳ ቁጥርር እንባዩ ነው የሚቀድመውው ከየት አንስቺ እንደማወራ ባላቅምም እስኪ ከማክስኞና ቅዳሚ ገበያ ልጀምርር የወተት , የቅቢው , የጢፍ , የቦቆሎው , በገናሊ ጉጂ እየተጫነ / የሚመጣውው ትልቁ ገበያቸንን በነሱ ተሞልታ እረ ምን ጠፈቶ / ጉጁ ወተት ሲያጠጣን በአቡጀዲ ከልሎ አረ ስንቱ ቀይ አፈርር ውይይይ በጣምም ነው ደስስ ያለኝኝ በዋርካ ስር መስባስባቸንን የራስብሩ ( ያዶላ /ቢት ) በዛቸ በቀዳዳ አጥር ሽቦ እየሾለክንን የምንገባባት በመጨረሻውው ደወል ደክማለቸ ራስ ብሩ መርዳት አለብንን እኒ በበኩሊ ልረዳ ዝግጅ ነኝ ራስ ብሩ /ቢቲንን አስተምራ አሳድጋ ለዚህ ያደረስቸኝ ናትና በሉ ሁላቸንምም በሉ እንበርታ እንግዲህ ከግዚር እርዳታ ጋርር የናተው የወዩ ልጅጅጅጅ ነኝኝኝ
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
560

PostPosted: Thu Sep 01, 2005 12:59 pm Post subject:
ወንድሜ ደጉ ስለ ኢሉ ባነታ ያስታወስከው ትክክል ነው ::
እንግዲህ ጥሪዬን ሰምታችሁ ከያላችሁበት መልስ ለሰጣችሁኝ የወዩ ልጆች እጅግ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳሁ !!!!!!አደቆርሳ የቅርብ ጉዋደኛዬ እንደነበርክ እገምታለሁ :ወንድሜ ባለሱቅ ጨዋታህ በትዝታ ጠያራ እዚያው ያልክበት ከድር ዶሌ ማሳ ወስዶ ጣለኝ :የግልነሽ ባጥር ሾልከህ ሾላ ስትበላ ጋሽ ክብረት አይተው በዚያች አሳምሚት .................. ! አሁን ያቺን የቀደድካትን አጥር መልሰህ አሳጥራት ::እንግዲህ እየተሰባሰብን ነው በርቱ ሌሎቹንም እየጋበዝን እንጨዋወት :ወንድማችሁ ራስ ብሩ ነኝ ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!!!!
http://www.adola-kibremengst.com/articl ... School.php
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ዝምታ !

መንገደኛ

Joined: 01 Sep 2005
6
Location: sweden

PostPosted: Thu Sep 01, 2005 6:56 pm Post subject: በስህተት ነው ......እርማት !!.
Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed ለእናንተ የጻፍኩት እንደ አዲስ ርእስ ሌላ ቦታ በመሄዱ .. "እንዲይ እንዲያ ነው ወጣ ውጣ በሉ እንጂ " የሚለውን ርእስ ላይ አንብቡ ::
አመሰግናለሁ
_________________
Peace!!
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ቀልቤለጌ

አዲስ

Joined: 31 Aug 2005
35
Location: UAE

PostPosted: Thu Sep 01, 2005 7:09 pm Post subject: የራስ ብሩ ትዝታ
ባለሱቅ ያንተን ጽሁፍ አንብቤ ሥራ መስራት አልቻልኩም :ይገርማል የኢሀአፓን ግዜ በመጥቀስህ ስንቱን አስታወስኩ መሰለህ :እስሩ ሲጀመር ባላስታውስም በመሀሉ የነበረውን አልረሳም . አራጅ ያልከው ሆዳም ከንቲባ አሁን ከስቶ አዋሳ ጨንጌ ይቅማል :የዚያን ጊዜ የወዩ ጠላቶች ሁሉ አሁን ፈስቶባቸዋል .......... አሁን አሜሪካ ያለ አንድ ጉዋደኛዬ ለአንዱዋ የአራዳ ልጅ የፍቅር ደብዳቤ ለመጻፍ ፈልጎ የሱ ጽሁፍ እንዳይታወቅ ብሎ እኔን እንድጽፍለት ይጠይቀኛል (ደብዳቤው ልብ ይነካል ) ከዚያም እኔው እንድሰጥለት ይለምነኝና በዚህ ተስማምተን ልሰጣት ሄጄ በደንብ ሳያት ......ሳልሰጣት ተመለስኩልህእና በሱፋንታ የራሴን ስም ጽፌ በማግስቱ መስጠት .......አዬ ከዝያማ ቢሮ አስጠራቺኛ ......የራስ በሩ ትዝታዬ ብዙ ነው ::
ከአማርኛ አስተማሪዎች .ገረመው ነጋሸና ትቸር እሸቱ ይመር : አስተምረውኛል :ሞላ የሚባል ገራፊ ሳይንስ አስተምሮኛል : እስቲ አንዳንድ በሉ ቸር ይግጠመን ::
_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
768
Location: united states

PostPosted: Fri Sep 02, 2005 2:36 am Post subject: ስላም ለናተ ይሁን ራስ ብሩና የወዩዎቸ
አረ እንደው በናትህ ቀልቢለጊ ምን አይነት ትዝታ ወስጥጥ እንደከተትከኝኝ ብታወቅቅ ዛሪ በተለይም ስለ ገረመውነጋሽና እሽቱ ይመር የጻፈከውው ይገርምሀል ገረመው ነጋሽ ማለትት የአባቲ በጣምም ጋደኛውው ነውው አሁንን ግንን የትት እንዳለ አላውቅምም አረ ሊሎቸ አስተማሪዎቺምም አክሊሎ አንጀሎ , ተስፋዪ ቃጩር , ለማ ካሳዩ , ሽዋሎል ባውሎጂ ትቸርር በአሁኑ ስአት የት ናቸውው የሚያውቅቅ ካለ ይንገረኝኝ እስቲ አረ ሊሎቸምም የሲትት ጋደኞቺ የሆናቸውው እስቲ ብቅቅ ብቅ በሉ ራስ ብሩ እያስባስበንን ነውው እንገናኝኝ ቅድስት , አስፋ ጸሀይ አስፋ , ሶሎሚ /ትንሳኢ , አስቲር አባተ ,
ሊሎቸም ወንዶቸም ብቅ በሎ እስቲ እንጫወት ቦቸራ ገላን , እነ ኪዳኒ ገዳሙ እስቲ ብቅቅ በሎ እንገናኝኝ እንጫወትት እናዋራውው ትዝታቸንን በተረፈ እንግዲህ በቸርር ይግጠመንን እወዳቸዋለውው የወዩ ልጆቸ .........................

የወዩዋ የግል ነኝኝኝ
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

አፈ -ጉባኤ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Mar 2005
566
Location: united states

PostPosted: Fri Sep 02, 2005 4:30 pm Post subject: ትዝታው ተቀሰቀሰብኝ !
"የቋጥኙ ላይ እሬሳ
የዚያ አምበሳ የካሳ
በመቶ አመቱ ቢያገሳ
ስንቱን ስንቱን ቀሰቀሰውሳ " ሰይፉ መታፈሪያ

ወዩ ራስ ብሩ እንደመይሳው በመቶ አመታቸው ቢያገሱ ስንቶቻችን ተቀሰቀስን ? ክብረ መንግስት ካመታት በፊት በስራ ሳቢያ ተቀምጬባት ስለነበር ማለፊያ ጽሁፎቻችሁ ባሳብ ይዘውኝ ነጎዱ ::

ቀድሞ ኢሰፓ /ቤት ከነበረው ወይም ጤና ጣቢያው ፊት ለፊት ካለው (ምናልባት ከነበረው ሆኖ ይሆናል ) ትልቅ የወዩ ዋርካ ስር ጉጂዎች አብዛኛው በእግሩ ከፊሉ በፈረስ ጦር ይዘው የክት ለብሰው አድባሯን በድምቀት ሲዘክሩ ትዝ ይለኛል ::

በቆራዝማ የታጠነ ወተት ቤተልሄም እነ ትእግስት ፍሬ ሆቴል ውስጥ እንጠጣ የነበረው ጣእሙ ዛሬም ይታወሰኛል :: ዙሪያውን የከበበው ደን ካመት አመት ልምላሜ እሚታይበት መልካ ምድር ዛሬም ይደቀንብኛል :: ማራኪ ደን ተመንጥሯል አላችሁ ? አለመታደል ነው :: ከሩቅ እሚሸተው ጉጂዎች እሚለቀለቁት ቅቤም ድሮ ቀረ ? እኒያ የከተሜ ጠረን ሲሸታቸው ሊተናኮሉ እሚቃጡ ከብቶችም ተመናመኑ ?

ኸረ ጎበዝ ጉች ጉች ያለ ጡት ተረሳ ነው እምትሉት ? እንዲያውም በወቅቱ በልጃገረዶቹ ጡት ማራኪነትና ጥጣሬ በጣም በመደመሜ ለጓደኛዬ በጻፍኩት ደብዳቤ ላይ
"አሁን የኔ አሟሟት አሟሟት ነወይ (2)
ጉች ጉች ያለ ጡት አንድ ቀን ሳላይ
እድሜዬን በከንቱ ላጠፋ ነወይ ?" ብሎ ለሚማረረው ድምጻዊ ውብሸት ፍስሀ እድሜው በከንቱ እንዳይባክን ካሰበ ክብረ . ብቅ እንዲል ንገረው ብዬው ነበር :: ድምጻዊው ባለበት ወይም . . ሄዶ አይኑን ሳያጠግብ ከሆነ ከዚህ አለም የተለየው ያሳዝናል :: ስንቱ ይወሳል ?

የፈረንጅ ውሀን ከቀመሱት አንዱ
አፈ -ጉባኤ
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
746
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Sep 02, 2005 6:08 pm Post subject: ዋርካ (ወዩ )
ወንድሜ አፈጉባኤ በመጀመሪያ እንኩዋን ደህና መጣህ ! ::የወዩን ዋርካ ስታነሳ እኔም ትዝታው ገባኝ :ያቺ ትልቋ ዋርካ የነበረችው በቤተመንግስቱ ግቢ ውስጥ ነበር :የትኛው ቤተ መንግስት ? እንዳትለኝ አሁን እነ ገረዝጌር ጦር ሜዳ ያስመሰሉት :: ቀድሞ ትልቅ ቤተ መንግስት ነበር :: ከፊት ለፊት በግራ በኩል :ጥልያን ከገነባው (በፊት የአገረገዢው /ቤት Smileከቀኝ ደሞ ግምጃ ቤት (አሁን ገንዘብ .)ጥግለጥግ ሲያዋስኑት : ከሁዋላ እስከ ኮሎኔል ደስታ አጥር ድረስ ይዋሰናል ::ታዲያልህ ዋርካዋ እዚያ ቤተ . .ግቢ ውስጥ
ነበረች : እንዳልከው አሁን ያላቸው ርቀትና ይዞታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል :አውራ መንገዱ እንኳን የሚጀምረው ከዚሁ ቤተ መንግስት ነበር ::እነ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ : እነ ፊታውራሪ ማሞ ስዩም : እነ ፊታውራሪ ወልደሀዋርያት ኢዮብ :ሌላው ይቅር ሻለቃ ደስታ መሸሻ በነበሩ ግዜ እንኩዋን የቤተ መንግስቱ ዉበት የከተማዋ ግርማ ነበር ::ቸር ያቆየን ::
_________________

kibremengist
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ቅሩንፉድ

ኮትኳች

Joined: 15 Apr 2005
454
Location: germany

PostPosted: Sat Sep 03, 2005 3:55 pm Post subject: አዶላ መሬት ላይ ወድቄ ብነሳ አካላቴ ሁሉ ወርቅ ይዞ ተነሳ
የወዩ ልጆች እንዴት ናችሁ Question ትዝታቹሁን ካነበብኩት ወዲህ በጣም ተረብሻለሁ :: እባካችሁ አትጥፉ አድባርዋ አስባስባ እንዳስደገችን አሁንም እንደገና ታሰባስበን ይሆናል :: ወይ ምን ይታወቃል ከላንጋኖ ጀምሮ እያቀለጥነው ተስባስበን እንሄድ ይሆናል :: ወደ ክብረ መንግስት ስትሄዱ ዝዋይ ላይ አሳ : አዳር ሻሽመኔ ክብረ መንግስት ሆቴል : ቁርስ አለታ ወንዶ አናናስ ገምጬ : የቦሬዋን ቆሎ ዘግኜ ገባሁ ወደ ቤቴ :: ሌላም ሌላም ስንቱ ተዘርዝሮ ::

ባለሱቅም በጣም ደስ የሚል ትዝታ ነው የጻፍከው :: የግልነስ አንቺ እንዲያውም ጓደኛዬ ሳትሆኚ አትቀሪም :: ለማንኛውም በግል ጽፌልሻለሁና መልሱን እጠብቃለሁ ::

አክባሪያችሁ ቅሩንፉድ
__________________________________________________________________________________________________________________________________________
_____________________________________________________________________
----------------------------

ቅሩንፉድ

ኮትኳች

Joined: 15 Apr 2005
454
Location: germany

PostPosted: Sun Sep 04, 2005 9:22 am Post subject:
የግል ነስ መልክትሽ ደርሶኛል Exclamation በጣም ነው የተደሰትኩት :: በይ ላስታወስሽ ጀርመን የመጣሽ ጊዜ የልዃንዳ ስፈር ልጅ አላገኝሽም ወይ Question
እነቅድስት አስፋን ስትጠሪ ወዲያው ነው ያወቁሽ ቅሩንፉድ የሚለው ስም ብዙ ሰው የወንድ ይመስለዋል ::እነ ሶሎሜ እነስናይት እዛው አንቺ ያልሽበት ነው ያሉት ለምን አትፈላለጉም Question
በይ ከአርስት እንዳልወጣ በግል ጽፈልሻለሁ ሰለሁሉም ነገር Exclamation

User Ads
Leader
Leader
Posts: 110
Joined: 27 May 2010 20:33
Contact:

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!! ከዋርካ የመጣ

Unread post by User Ads » 20 Jan 2012 00:38

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
: 962
Location: ethiopia
Posted: Sun Sep 04, 2005 8:51 pm Post subject: ሰላሙልኝ
________________________________________
ሀገርሽ የት ነው ቀዘባ
ተራራ ሜዳ ሀገር አንባ
አቤት ቁንጅና ውበቷ
የጀምጀም ላይጉጂ ልጅቷ
..
እንካ ብላ አልችኝ ደረቁን እንጀራ
እሷ በጣፈጠው በራሰው ልትበላ
ዲሲ ላይ ተኝቼ በልሜ የታየችኝ
የሲዳሞ ጉጂ አንጀቴን በላችኝ
....
እያለ ይዘፍን ነበር ገልቹ ኃይሉሸምቦ ... ነፍሱን ይማረውና ... በጊታሩ !...
በስራ ተወጥሬ ጠፋሁ አቦ !....
እንደምን አላቹ የወዩ ልጆች ....
ሰላምታዬን በጉጂ ቱልቱማ ልጀምር ፈለኩና ... ገና ጠጅ አልጠጣሁ ... እረ ባፌ ወተትም አልዞረ ...
አዮ ... አሬራን ቀባ !
ሜ አስ ፊዲ !
ሜቃ !
ሱሙና ሰዲ !... ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ
ትንሽ ቀመስ ቀመስ ....
ከቢራን ቀቡ ?
አስ ፊዲ መሌ ......
...
ሄ ... ጉርባን ኩን ማሊፍ ጀዻ !
.........

በደበዳ ሀሬ ... ኢልመን ሀጠሺ !....

ወዩን ከራ ሀገዽኡ ....

ምናባት ጠፋብኝ እኮ .... አቤት ሲሰዳደቡ ... አቤትትት ዋጋ ለመቀነስ የምከራከረው .... አቤትትትት ለቅምሻ እያልኩ የምጠጣው ወተት .... ስሙና -ሰዲ ሲጠፋ .... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንዴ የሰማሁት ነው ..... የቅዳሜ ገበያ አልቆ ... ጉጆቹ ጠጅ እየጠጡ ነበር .... ሰፈሩንና ነገሩን አልጥቀሰውና .. ብቻ አንዱ ጉጂ ጩኸቱን አቀለጠው ... በር ላይ ወጥቶ .... ፖሊስ መጥቶ ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ምን እንዳለ ታቃላቹ ....
....
ይሄ እንትና ... (ስሙን አልነግራቹም )....
ይሄ እንትና ... ልጃገረዲቷን ሀሬዬን ... ሰላብኝ .... .....
....
ቁመቱ እንዴት እንደደረሰለት ጌታ ይወቅ ... ለነገሩ ልምድ ነበረው አሉኝ .... አሁን የት ይሆን ያለውውውውውውው ...
.....
በተረፈ ... እስኪ ትንሽ ፋታ ሳገኝ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አሉኝ .. እዛች አገር ውስጥ .... እንዲሁ እንዲሁ እየተጨዋወትን ያንን ያልኳችሁን የመፃፉን ጉዳይም እንድንነጋገርበት እወዳለሁ ....
የጌታ ፍቃድ ከሆነ በኦክቶበር አሜሪካ ሄጄ በማርች ወደ አዶላ ላቀና አስቤአለሁ .... የሚጠረቃቀም ነገር ካለ ... መፃፍ መፃፍ መፃፍ ... እስኪ ሁላችንም በያለንበት እንዘጋጅ ... ከልብ .. በየዋህነት ....
ማትሪክ ስፈተን አንዲትም መፃፍ ለማንበብ አልታደልኩም ነበር .... ጌታ ምስክሬ ነው .... ታናናሽ ወንድሞቻችንና ወገኖቻችን እኛ ያጣነውን ባያጡ ... መልካም ምኞቴ ነውና ...
በህብረታችን የድርሻችንንና የፍቅራችንን ለወዩ አንዲት ነገር እናኑር
አደራ በምድር በሰማይ ...

ባለሱቅ ከትርፍ ሌላ ምንም አይቅም ብላቹ ወደ - "ትርፍ ካወጣች ኤርትራም ትሸጥ " ጎራ እንዳትመድቡኝ ... አደራ
ያንፈራራው ሀጂ -ገሪገሪ የቢሉው ሼ -አሊፋሪስ ... የ 01ዱ ስላሴ የ 04 ሚካኤል ከነደባሉ ... መድሀኒአለምና ማርያም ይታዘቡኛል ... ብዋሽ ...
.....
ወይ ጉድ ወሬኛ ሆንኩ "ኮ
ሆሆ
እስኪ ቸር ይግጠመን
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ትትና
Joined: 23 Feb 2005
: 1474
Location: united states
Posted: Mon Sep 05, 2005 12:14 am Post subject: ቁጭ አድርጋችሁ አዋላችሁኝ እኮ
________________________________________
ይቅርታ አድርጉልኝ ግን ሳልጠራ በመግባቴ :: ውይ ደስስስ ስትሉ እንዴት እንደምታስቀኑ !!! እግዚአብሄር ሀሳባችሁን ይሙላላችሁ :: በሉ እንግዲህ ለቁም ነገር አብቁት መሰባሰባችሁን ::
እኔም አንድ ቀን የትውልድ መንደራችሁን ለማየት ያብቃኝ ::

አክባሪያችሁ
ትትና
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

የግልነስ
Joined: 03 Feb 2005
: 768
Location: united states
Posted: Mon Sep 05, 2005 2:45 am Post subject: የጀምጀሙ ጉጂ የኒ ባለሱቅ
________________________________________
ውይይይይ እንዲት ድስስስ ይላል የዛሪው ግጥምህ በተለይምም የጉጂ ጭውውትትህ ከምር ገበያ ክፍል ካለውው ትልቁ ገበያ መሀል ነው ያንቀዋለልከኝኝኝ ታውቃለህ ሁሊምም ያንተንን ጫወታ አልጠግበውምም ካወኩህ ጀምሮ ቅርንፍድድ ባክሽንን ሚሲጅሽንን እየጠበኩኝኝ ነውው ላኪልኝኝ እስቲ እናውራ እኒምም ቺካጎ ላሉት ወዩዎቸ መልክቲንን አስተላልፋያለውው በራስ ብሩ ተዛዝ መስረት በሉ እስቲ ለዛሪ ልስናበታቸውው የናተዋ የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቅሩንፉድ
Joined: 15 Apr 2005
: 454
Location: germany
Posted: Mon Sep 05, 2005 11:26 am Post subject:
________________________________________
ትህትናዬ ስለአድናቆትሽ አመስግንሻለው ሲዳሞ ማለት በጣም የሚናፈቅ አገር ነው ::እንደው በዝና ከሆነ የምታውቂው አንድ ቀን እንጋብዝሻለን መቼም ወረድ አላልሽ ይሆናል እንጂ ላንጋኖን ወንዶገነትን የምታውቂው ይመስለኛል ::በዚያው መስመር ነው ይቺ ትንሽ ከተማችን የአዋራዋ ትዝታ ከፊት አይጠፋም ::ስውም በጣም ሰለሚዋደድ ነው መሰለኝ ::
በይ ቸር ይግጠመን
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
: 962
Location: ethiopia
Posted: Tue Sep 06, 2005 11:53 am Post subject: ለትትና
________________________________________
ወተት ከናፈቀሽ ... በቆራስማ ቅል
እሸቱን በቆሎ በገፉማ ሙልሙል
ባዶላ ወርቅ ጌጥ ካማረሽ መሽቀርቀር
ምጭና ተደሰች ጀምጀም ለሽርሽር ::

በቦሬ ነጭ ማር በጀምጀሟ ቅቤ
በገብስማ ቆሎ በእንሰት ተከብቤ
እጠብቅሻለሁ ምርጥ አቀራርቤ ::

ለጁስ አሬራችን ለኬክ ዳቦ -ሸዌ
ሀሪቲ ለሽታ ጤናዳም ለደዌ
ጠጁን ለመዝናኛ ቦርዴ ለቁርሳችን
ሁሉም ይዘጋጃል ነይ ነይ አዶላችን
እንጠብቅሻለን ዘርግተን እጃችን

ታዲያ እዛች ወዩ ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል የስሙኒ ቅቤ ገዝተሽ መምጣት እንዳትረሺ .... አድባሯ ቅቤ ትወዳለችና

ሰላም ክረሚ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቀልቤለጌ
Joined: 31 Aug 2005
: 35
Location: UAE
Posted: Tue Sep 06, 2005 3:09 pm Post subject: ሸጌ ነይነይ ...................ላይ :
________________________________________
እንዴ ............ሹፍ ቀልቤ የሞኬ ወንዲም ...347..አታቁም .....ዬኛ ከፍቶች ...ሹፍ ..ወንዲሜ ..ኢስቲ 1 ብሩ አምጣ ......::
እኔ የራሴን ሳወራ ግዜ አጠፋሁ ወገኖቼ እንዴት ከረማችሁ ! ተበራክታሁ የለም እንዴ :: (ትናንት ከሻለቃ ደስታ ጋር ነው ያደርኩት "ቢያስ ......ንም ጮማ ይሻላል " አለች ብርሀኔ )ጊዜዬን ከናንተጋ ባጠፋ ና ሁሉም ቢቀርስ ::የቀድሞ ክ /መንግስትን ሳስታውስ በተለይ አራዳ .አዲሴ -ሌቴ -ሲዴ -ጸጋዬ ሳንታ ሌሎችም በጣም ትዝ ይሉኛል ::ጻዲቄ እና በጠሶቀጠሶንማ ሁኔታቸው ሁሉ አይረሳኝም ::
_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
: 746
Location: ethiopia
Posted: Tue Sep 06, 2005 4:43 pm Post subject: ጉም ጉም
________________________________________
አካም ነጉማ ፈዩማ
አካም ነጉማ ፈዩማ ...ኑ ነጋ ቀብና ጋሩማ
አካም ነጉማ ፈዩማ ...
ይርጋለም አዋሳን ጌዴኦንም ዞሬ
ነጌሌ ቦረናን ክብረመንግሥት ዞሬ
ውብ ቆንጆ ፍለጋ ይርባ ላይ አድሬ
ከገብስ እሸት መሀል አገኘዃት ቦሬ ::

መወለድ እንዳንቺ ሺሻ ገረምባው ሥር
ማደግስ እንዳንቺ አዋሳ ሀይቅ ዳር
መተኛት እንዳንቺ አንጥፎ አሹባ
መልበስስ እንዳንቺ ቆዳ ፍቆ ቱባ
ያለታ ብርቱካን የወንዶ አበባ
የአዶላ ቆንጆ ነይ የኔ ቀዘባ ::

አላብዱና ማቲ ሆኩ ነው እድገቷ
ትዝ አለቺኝ አዮ ያንፈራራይቷ
ጉች ጉች ያለ ነው ጡቷ እንደደመና
ትናፍቀኛለች አጠገቤ ሆና !!!!እስቲ ማነሽ የግልነሽ ማነሽ ቅሩንፉድዬ እጣኑን ጨስጨስ አርጉት እንጂ ::
አዎ እንዲያ ነው አቦ !................
ዝናዬ አሰጋኸኝ ባለህበት ሰላምታዬ ይድረስህ እነዚያ በርሲሳ ጋሎ የጻፍካቸው ግጥሞችህ ያቺን የጉጂ ባርኔጣ የደፋች ልጃገረድ ከነ ቡክቡካዋ ከተቆራሰመ የወተት ቡቄዋ ጋር እንዴት በግጥምህ እንደሳልካት :ትዝ አለና አቦ ::አንድ የማውቀውን ልበላችሁ ግዜው አብዮት ነው :01ቀበሌ ፍ /ቤት ግቢ ውስጥ ስብሰባ ላይ :አብዮተኛ ሲናገር ሌላው አብዮተኛ (ብርሀኑ ደበላ )ወደኦሮምኛ ያስተረጉማል :በመሀል ተናጋሪው "የዛሩ መንግስት "ሲል አስተርጓሚው በኦሮምኛ ለመግለጽ ጥቂት ዝም ማለት : ሻምበል ባሻ ክፈለው ገዳ (ነፍሳቸውን ይማረውና ) ጊዜም አልፈጀባቸው ወደ አስተርጓሚው ዞር ብለው "ሼጣና መንጊስቲ "ኢንጀቱ በማለት የሰለቸውን ህዝብ አዝናኑት :: ቸር ያቆየን ::
_________________

kibremengist
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ወቤ (ጃሎ )
Joined: 28 Jul 2004
: 199
Posted: Wed Sep 07, 2005 12:29 pm Post subject:
________________________________________
በእውነቱ ስለ አዶላ (ክ /መ )በማንሳታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል ::የቦሬ ልጅ ብሆንም ክ /መን ከቦሬ ባልተናነሰ እወዳታለሁ : ራስ ብሩም በአንድ ወቅት 7ና 8 ን ዉብሸት ምንድጌ የሚባል ዳይሪክተር በነበረበት ጊዜ ተምሬአለሁ ::በጣም ብዙ ትዝታ አለኝ ሚ /ር ባክስቸር (አሜሪካዊ )አስተማሪ ;ያሽልንግዬ ያሽልንግዬ ጉጂን ጉጂ ጂቤ ገብሬ መላጥዬ : --የሚለው መዝሙር ;በዚያን ጊዜ የነበረ ኳስ (የመሰንጠቂያና ሌሎች ክለቦች ) ወንድሙ ሳንታ ;ሲሳይ ሳንታ ;የወቅቱ አርቲስት አህመድ ሺፋ ;እፍሬም ጎርፉ :ትዝ ይሉኛል ::በተለይ 3ኛው ዙር መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሬጂ እብሮኝ ዘማች የነበረው ጓደኛዬ ወንደሰን ገድሌ ሁሌም አስታውሰዋለሁ ::በተረፈ በርቱ እኔም ት /ቤቴን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ ::እዚህ በምኖርበት እንግሊዝ ብዙ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ ::ለማስተባበር በጀምጀም ወዩ ስም ቃል
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ወቤ (ጃሎ )
Joined: 28 Jul 2004
: 199
Posted: Wed Sep 07, 2005 12:50 pm Post subject:
________________________________________
ቃል እገባለሁ ::በተለይ ትዝ የሚለኝ ሸዋ ሻይ ቤት በስሙኒ የስጋ ወጥ የምንበላው ;የባላንበራስ መኮንን ሽንኮራ ;የአሮሬሳ ልጆች እነ ካሱ አለማየሁ ና ሌሎች የክ /መ አላዛር ጻዲቅ ;ፍሰሀ ;በተለይ በቀይ ሽብር የተገደለው እሱባለው ሳህሉ ጓደኛዬም ጎረቤቴም ነበር ::የናንተው አብነት ጂሎ ኢጆሌ ቦሬ ከኢንግሊዝ
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቀልቤለጌ
Joined: 31 Aug 2005
: 35
Location: UAE
Posted: Wed Sep 07, 2005 5:14 pm Post subject:
________________________________________
አንተ ወቤጃሎ እንዴት ከረምክ ጃል !አደቆርሳ ያቺን አዮ ቦሬ ከገብሱ እሸት መሀል አገኘሁአት ሲል አምጣ የኔ ናት ለማለት ብቅ አልክ ብዬ ........ ነበር :ዳሩ አንተም የራስብሩ ሆነህ በመምጣትህ ደስ ብሎናል ::
ግን ከነዚያ የወቅቱ አርቲስት ካልካቸው ልጆች ውስጥ አህመድ ሺፋን አስታውሰህ ዘሜ ዓሊን መዘንጋትህ ገርሞኛል (የመጀመርያዋ ዳንሴሪ )ነበረቻ ....:
ገሚሻ አሁንም ያው ነው :ደራርቱ የዘመዶቹን እርጎ እየጠጣ ነው ::ከጠቀስካቸው ውስጥ ኤፍሬም ጎርፌና ወንድሙ ሳንታ አሁን በህይወት የሉም ::በነገራችን ላይ የኢሀፓ እልቂት ሲጀመር በዚያው በጨምቤ በኩል እግሬ አውጪኝ ያሉ የወዩ ልጆች አሁን የት እንዳሉ የሚያውቅ አለ ???ተከስተ ሀብቴ ከረዥም ግዜ በሁዋላ ተመልሶ አሁን ያለው ክ /መ .ነው .እነ ሳህሉና ሀብቱ ኪዳኔ :ስለሺ ተስፋዬ .ከዚያ ደሞ እነ ተስፋዬ ሀ /ጊዮርጊስ (ጨጎና ),አስቴር በተላ ,የት ይሆኑ ?እስቲ የሚያውቅ ካለ እጁን ያውጣ ::
_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቅሩንፉድ
Joined: 15 Apr 2005
: 454
Location: germany
Posted: Wed Sep 07, 2005 8:46 pm Post subject: የወዩ ልጆች እንዴት ከረማቹሁ
________________________________________
ባለሱቅና አደቆርሳ በዚህች ግጥም እኔም የማይረሳ ትዝታ አለኝ :: በተለይ ከነዜማው ሲጫወተው ዝምነው :: እንዲያወም የወንድሜ ጎደኛ ስለነበረ እጣኑንም ስንት ቀን አጭሻለሁ መስለህ :: በነገራችን ላይ ራስ ብሩ የነስመኝን ሻይ ቤትን የሚያስታውስ የለም :: አቤት ብድር ደብተር ላይ የምናጽፈው :: ቀልቤለጌ ወፉንስ አታስታወስውም :: እንዲያውም የማልረሳው ሁልጊዜ ቡና ሲፈላ ጠዋት ጠዋት ቤታችን ይመጣል :: አቀማመጡ ራሱ ከፊቴ አይጠፋም :: ኩርምትምት ብሎ ተቀምጦ ላየው በሳቅ ነው የሚገድለው :: ሌላ ጊዜ እስቲ ስለሱ ጨምሬ እጽፋለሁ :: የምታውቁት ጨማምሩበት ::
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቀልቤለጌ
Joined: 31 Aug 2005
: 35
Location: UAE
Posted: Thu Sep 08, 2005 11:22 am Post subject: ወፉ ????
________________________________________
ሠላም ቅሩንፉድ በጽሁፍሽ የነስመኝ አለማየሁን ሻይቤት ስታስታውሽን ወይኔ ....እረፍት ሆኖ እዚያ ለመሄድ .......በጣም እጅግ በጣም ትልቅ የልጅነት ትዝታ ቀሰቀስሽ አቦ !!!!! ወፉን በሚገባ አስታውሰዋለሁ እንጂ ....እንደውም ወፉን በጣም የሚወዱት ጋሽ ርዕሶም እና ጋሽ ከድሮ ስይድ ነበሩ ::ጋሽ ከድሮ ሱቅ ሄዶ ያቺን ልብስ ..?ብሎ ወፉ ከጠየቀው ያቺንው ነበር አውርዶ የሚሰጠው ::ግን ከዚያች ቀን በላይ ወፉላይ የለችም ::ጋሽ ርዕሶምም አንዳንዴ አመት በዓል ወይም (specialdays)ሲሆን ቂቅ አድርጎ አልብሶት እጁን ይዞ ወደከተማ ይወጣ ነበር ::ወፉግን በአጠቃላይ ልብስ መልበስ አይወድም ::""ያም ትመጣለህ ""የሚለው የዘወትር አባባሉም አይረሳኝም :: መላጣውስ ?
ሌላው ቁምቢ ሮቢ እና ቢሆኔም ትዝ ይሉኛል ::እነ ሀና ሀብቴ በረንዳ የሚያድረው አደፍርስም የኛ ሰፈር የካምቦ ልጅ ነበር ::ስለ ወፉ ጨምራለሁ ባልሽው ላይ ሌላም ጨማምረሽ በትዝታ አዝናኚና አቦ !!
ወንዱ ጫካም ሌላውን ወፉ ሆኖ ነበርኮ !!!!!!
_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ወቤ (ጃሎ )
Joined: 28 Jul 2004
: 199
Posted: Thu Sep 08, 2005 1:06 pm Post subject:
________________________________________
ወንድሜ ቀለቤለጌ በጣም የሚገርመው ትናንት የጻፍኩት በድንገት ነበር :ሆኖም ማታ ተኝቼ ሁሉም ነገር ፊቴ ላይ ተደቀነ :ዘሜ አሊን በታሪክ አልረሳትም ድንቅ ዳንሰኛ ነበረች :: ዛሬ ላነሳት ስል ቀደምከኝ ::ሌላው ,የሱማሌው የጃማ ሻይ ቤትእና ቆጪ አጠገብ ያለው ትልቅ ቤት የነበረ ሳምቡሳ ና ብስኩት ትዝ ይሉኛል ::በአንድ ወቅት ገበያ ክፍል ኬላው አጠገብ ያለው ሀምሌ 19 (የግራዝማች ደመቀ ) ሆቴል ነበር ባልሳሳት :የቦሬ ልጆች አልቤርጎዉን ተካራይተው (ለትምህርት መጥተው )ይኖሩ ነበር : አንድቀን እኔም ነበርኩ ከድር ከማል የተባለ ልጅ ወደጓሮ ሄዶ የተጣለች አሮጌ መኪና ስር የተኛች ትልቅ ሚዳቋ አይቶ ጠርቶን ይዘናት በማታ ከጆቫኒ መሰንጠቂያ ፊትለፊት ካለው ትልቅ ቤት ለሚኖረው አሜሪካዊ አስተማሪ ሚ /ር ባክስቸር በ 14 ብር ሸጠን ያደረግነው ሰርግና ምላሽ አይረሳኝም ::ሌላው የልጅነት ትዝታዬ ስለሆነ ና ያለፈ ታሪክም ስለሆነ ለምን ስለ <ሀዳ ፉሪ ቤት >አናወራም መቼም በዚያን ወቅት መዝናኛችን ,መለማመጃችን ---ላኪ አቦ ----ኢጆሌ ቦሬ ነኝ ቸር ይግጠመን ::
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ፖስታቢትሰፈረ
Joined: 08 Sep 2005
: 36
Location: ethiopia
Posted: Thu Sep 08, 2005 2:49 pm Post subject:
________________________________________
አባ ጮማ ሰፈር ትወልደን አድገን
እነ ወንዱ ጫካን አይተን ቀንትን
ከነ ቦችራ ጋራ ካስ ተጫወትን

ምንም ቢደፈርስ ጎርፍ ቢገባበት
የሳህሉ ውሀ ልብስ ቢታብበት
ያልተጎንጨው ማን አለ ተወልዶ አድጎ ክብረመንግስት

እንደምን ከርማቹሀል የወዩ ልጆት በመጀመሪያ እራሲን ላስተዋውቅ ተወልጂ ያደጉት አዶላ ሲሆን ሰፈሪም አዲሱ ፖስታ በት ወይም የድሮው ቆጭ ሰፈር ነው

አዶላ ወዩ ማህበር በአሚሪካ ስለመመስርቱ ታውካላቹ 15-20 አባል ያለው የሚገውም በቺካጎ ሲሆን እኒም ክመስራቾቹ አንዱ ነን

ሳህሉና አብቱ ኪዳነ የሚኖሩት ቺካጎ ነው
____________________________________________________________________________________________________________________________________________

ፖስታቢትሰፈረ
Joined: 08 Sep 2005
: 36
Location: ethiopia
Posted: Thu Sep 08, 2005 3:03 pm Post subject:
________________________________________
በታም ደስ የምትለን አቆጭ ጉልት
ገበያተናው ሲህድ ወደ በት
በእግራችን ተራርገን ያፈላልግናት
ለናተፋት ሂድን ጀማል ቆቆር ቢት
ደግሞ ያራዳ ልጆት ከየ ሱቅ ባንኮኒያቸውየወስዱትን
ውስደው ያትፋታል ጃማ ሳይ በት

ስለ ራስ ብሩ ትምርት ቢት ስትፉ ቂጂላ ዘበጝ ትዝ አለጝ

______________________________________________________________________________________________________________________

ራስብሩ
Joined: 25 Aug 2005
Posts: 560
Posted: Thu Sep 08, 2005 7:46 pm Post subject: መተር መተር አርጎ ይበላል ጉበት : ዞርበል አንፈራራ ሸዋን ልይበት !!!
________________________________________
አያልቅበት የሚናገረው ሁሌ በግጥም ነው :ላስተዋላቸው ግርም ይላሉ ! ሰላም ወዩዎች እንዴት ከረማችሁ ::ዛሬ ከደረሱ ትዝታዎች :በ አሜሪካ ቺካጎ የምትገኙ የራስ ብሩ ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ !ማህበራችሁ እንዲያድግ ምኞታችን ነው
በርቱ ::ፖስታቤትሰፈሬ በጣም አመሰግንሀለሁ ::እግረ መንገድህን የራስ ብሩን ነገር ለማህበርተኞችህ አስታውቀህ በዚሁ የዋርካ ገጽ ሥር እንድንገናኝና አንድ ነገር እንደናረግ አደራዬ የበረታ ነው ::ሌላው ለአምዳችን ዕድምተኞች የትዝታ ጥያቄዎች --:የክ /መንግስት ራስብሩ ወልደገብርኤል ተማሪ የነበሩና በስፖርት ጥሩ ደረጃ የነበራቸው /ያላቸው /አሁን ያሉበት ደረጃና ሁኔታ :የምታስታውሱትን /የምታውቁትን /አጫውቱን ::
ቸር ይግጠመን !
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!!!!
http://www.adola-kibremengst.com/articl ... School.php

________________________________________

የግልነስ
Joined: 03 Feb 2005
Posts: 768
Location: united states
Posted: Thu Sep 08, 2005 11:41 pm Post subject: ስላምና ጢና ለወዩ ልጆቸ
________________________________________
እንዲት ከረማቸሁልኝኝ የወዩ አዶላ ልጆቸ እኒም ባለሁበት ደህና ነኝኝ የያንዳዳቸውን ጽሁፍና ግጥምም ባነበኩኝ ቁጥርርር በቁሚ ህልም ይዞኝ ጭልጥ ይላል ወደ ክ /መ ካገሪ ከወጣሁኝ ብቆይም 2ት ጊዚ ሂጃለሁኝ ሆኖምም ምን ጊዚም ይናፈቅቀኛል ሀገሪ ወዩ በተለይም ያቺ ከነዘገዩ ቢት ተነስታቸው (ከ 01 ቀበሊ ) ተነስታ የፈረንጅ ወሀን አሻግራ የምትወስደው መንገድ ጠባብ ዳገታማ መንገድ ወደ ራስ ብሩ የምታደረስንን መንገድ ባብዛኛው በህልሚ አያታለው ይገርመኛል በጣም እናም ወደ ሚካኢል ቢተ /ክርስቲያን አካባቢ ነውው የማየውው እስቲ ቅርንፍድዩ ሊላስ ሻይቢት አታስታውሽምም ቁጢ ሻይ ቢት ገበትንን ሻይ ጠጥተን የበስለ ኮክ ስብስበንን የምነወጣበት የወሮ ውቢቱ የ 10ሳንቲም ዳቦስ ቅቅቅቅቅቅ በረፍት ሳት የነበረው ግርግር የነስመኝ አለማየው ቢትማ ብድር አይወራ ቅቅቅቅቅ ሊላው ቺካጎ ላይ የተቃቃመው የክ /መ ልጆቸ ማህበር ሁላቸንንም ከያለንበት ሳያገናኝን አይቀርም የሚል ግምት አለኝኝኝ እኒምም በቅርቡ በስልክክ እያገኝሀቸው ነውው እና በጣም ደስ የሚል ነውው ሞራል ያስፈልጋቸዋልል ባይነኝኝ በተረፍ እንግዲህ እንዲሁ እስካገኛቸውው የወዩ አድባር አትለዩንን ቁጥራቸንን ከፍ ታድርግልን እላለው የናተው የወዩዋ የግል ነኝኝኝ
እምምምምጷ
________________________________________
ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 09, 2005 5:13 am Post subject:
________________________________________
ይህ ዝምታ በስተት ሌላ ቦታ ፖስት ያደረገው ነው .... ሁላችንም , ማንበብ ስላለብን ነው ያለደራሲው ፍቃድ እዚህ ያመጣሁት ...

ፅሁፉም ደስ ብሎኛል ... ብዙ ብዙ ወርቅ ልጆች አሉንሳ !.. ያገር ልጆች ... ወዩ ትጠብቃቹ ...

የሉፍ ጫት እጋብዛቹዋለሁ .. አውቶቡስ ተራ ከመጣቹ ... 02 ቀበሌ !...

በጠሶ -ቀጠሶ ... ቢሆነኝ ... ሞት -እምቢ ... ወፉ (አንዴ ቦቅሶኛል ) ... ብርሀኔ ፃድቃን ... ሸተለኮ ...(ከጃማ ቤት ጠዋት ጤዋት ዳቦ ይዞ ይሰጠኝ ነበር )... እና ስለሌሎቹም በሰፊው እንጨዋወታለን ...

የበጠሶ -ቀጠሶ አካሄድ ግን አሁን ፋሽን ሆኖዋል አሉ ... የምታቋት ልጆች እንግዲህ በሀሳብ ከበጠሶ -ቀጠሶ ጋር ወደማርያም ሜዳ ሂዱና ተዝናኑ ...
አባ -ቡሉኮን ሚያቅ ማነው ... ሜጫ ሰፈር .... ከነዲሞትፈራቸው .. ሽፍታና ኢሀፓ ገዳይ ...
ቡ ቡ .. ቡ ቡ ....
የሰማይ ልቡ ....

እስኪ በሌላ ጊዜ ብቅ ልበል መሰለኝ ... ቦታ እንዳላጣብብ

እወዳቹዋለሁ
Author Message
ዝምታ !Joined: 01 Sep 2005
Posts: 2
Location: sweden
Posted: Thu Sep 01, 2005 5:40 pm Post subject: እንዲያ እንዲያ ነው ! ወጣ ወጣ በሉ እንጂ ....

--------------------------------------------------------------------------------

መቼም ራስ ብሩ ሲጠራና ቀጥሎ ወዩን በማስከተል ንግግር ሲሞቅ እንኩዋን የተኛውን ቀርቶ የሞተውንም ሳይቀስቅስ የሚቀር አይመስለኝም ::
እንደምን ሰነበታችሁ በማለት ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ ::አዎ እኔም በዚችው ምስኪን ትምህርት ቤት ተምሬ አሁን ያለሁበት ያደረሰቺኝ የራስ ብሩ ው /ገብራኤል ት /ቤትናት ::ሰለሆነም እኔም ለዚች ት /ቤት ባለእዳ ነኝና ከእናንተ ጋር ለመቆም ፈቃደኛ መሆኔን በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ ይፈቀድልኝ ::
በተረፈ ራስብሩ :አዶቆርሳ :ቀልቤለጌ :ቅሩንፉድ :ባለሱቅ ና የግልነስ ሁላችሁም ስለ አዶላ ወዩ ስታነሱና ስትጫወቱ እያነበብኩኝ ለተወሰነች ሰከንድ -(ደቂቃም ሊሆን ይችላል ) ሰውነቴ ነው እንጂ እኔ መሀል አራዳ መሀል ቆሜ የማስተውል ሆኜ ነው ያገኝሁት ::ከጥንት ከጠዋቱ ከነ አያልቅበት ና ወፉ ጀምሮ ከዚያም የጋሼ ክብረትን ቅጣት እንዲሁም በጣም የማውቀውን የአባባ እልፍንህን ማሳ አካባቢ ሲነሳ ደግሞ ፍርክርክ ነው ያልኩት ::እኔ ከወጣሁኝ ትንሽ በመቆየቴም ምክንያት ሆኖም ይሆናል ::መቼም እግዜር ብሎ ወዩ እዚህም ብታሰባስበን ና ከጫወታውም ባሻገር ሌላም ቁም ነገሮችንም ለወዩና ለነዋሪው የሚጠቅም መስራት የምንችልበትን በተወያየን በነበር :: እንግዲህ ማሰባሰብ የመጀመሪያ ስራችን ይሁንና ... እንቅጥል ::እዚህም እኔ አካባቢ ፈቃደኝነታቸውን በምጠየቅ ለማሰባሰብ ሞክራለሁ ::

ደህና ቆዩ
_________________
Peace!!

Back to top ይህ ጽሁፍ መሰረዝ አለበት

ራስብሩJoined: 25 Aug 2005
Posts: 6
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 02, 2005 11:45 am Post subject: እንኩዋን ደህና መጣህ !

--------------------------------------------------------------------------------

በመጀመሪያ ጥሪውን ተቀብለህ በመምጣትህ እና በሰጠኸው አስተያየት ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ ::ባለህበት ስላሉት ሁሉ በማሳሰብ :እድሜያችን ወደ Retirment ከመግባቱ በፊት ለተማርንበትና ላደግንበት አሁን ትንሽ ነገር እናድርግ ::በዚሁ ከተሰባሰበን በሁዋላ ስለሁሉም እገልጽለሀለሁ ::
በሀሳቤ አራዳ መሀል ቆምኩ አልክ :የአራዳዎቹን እነ ጋሽ ተስፋዬ መርጊያን አበራ ክፈለውን እና አበበ ኦጋን በደንብ አስታውሳለሁ :በተለይ እነ ሸምሱ መሀመድ እና እንድሪስ ሀሰን (ሸምሱ አሁን በህይወት የለም እንድሪስ የት እንዳለ አላውቅም )ካሱ አለማየሁ (ለጠምባ )አሁን የኢት .ብሄራዊ አትሌቲክስ ም /አሰልጣኝ በት /ቤት የታወቁ ረብሸኞች ነበሩ ::ያኔ የራስብሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ በተላ በዛብህ እማማ አምሳለ ደሞ የጅ ስራ አስተማሪ ::በል በቸር ይግጠመን ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 09, 2005 12:00 pm Post subject: ከኤፍሬም ጎርፉ ትዝታ
________________________________________
ኦቶቡሲ ማሞ ካቻ
የት ትሄዳለህ ቀብረ -ጉራቻ
ምን ልታሜጣ ማር በስልቻ
ትርፉ ስንት ነው ስልቻ ብቻ

ማሞ ካቻ ... እራሳቾ
ሹፌር ናቾ
በኛ በኩል ... መስመራላቾ

ግን ግን ግን ግን

ቱ ሀዻራው .. ቡሽቲ ናቾ
...........................................

ቡሽቲ ግን ምን ማለት ነው ?

ሰላም ሰንብቱ !
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
________________________________________

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
Posts: 746
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 09, 2005 3:49 pm Post subject: Thank you Rasbiru
________________________________________
ትናንት ጽሁፍህን ካነበብኩ በኋላ የማውቃቸውን ስፖርተኞች ሳስብ አደርኩ :
እኔ ከማውቃቸው የመጀመርያዋ በዓለም ታዋቂ የክብረ መንግሥት ልጅ እስከ 2002 በ 800mt.እና በ 1500mt. ተደጋጋሚ የድል ባለቤት የነበረች አሁን ከአትሌቲክሱ መንደር የራቀች ::
አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ :ወንድሟ አዱላ ዱለቻ (የ ጁኒየር አስተማሪ ) ያስተማራችሁ ካላችሁ ታውቁታላችሁ :
2-አትሌት ዱቤ ጅሎ በመካከለኛና ረዥም ርቀት በ አለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት የነበረ :አሁን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ መምሪያ ሀላፊ ::
3-ካሱ አለማየሁ :የደቡብ ኢትዮጵያ የ 10,000mt. ሻምፒዮን የነበረ :አሁን የባንኮች ስፖርት ክለብ አትሌቲክስ አሰልጣኝ :: እሱ ለደረጃ ካበቃቸው አትሌቶች መሀል =አሰፋ መዝገቡ
ሚልዮን ወልዴ
ወርቅነሽ ኪዳኔ እና የአሁንዋ የሀገራችን ዕንቁ አትሌት መሰረት ደፋር እና ሌሎችም ::
ሌላው በፉትቦል አክሊሉ ተስፋዬ ቢራቱ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይጫወት የነበረ (አሁን ሀይስኩል ቲቸር ):ሳሙኤል አቦምሳ ዳባ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወጣቶች ምርጥ የነበረ (አሁን በግብርና የልማት ኤክስፐርት ):ቦቸራ ገላን የመድን አጥቂ አሁን ካልተሳሳትኩ በቺካጎ የወዩ ልጆች ማህበር አባል )
እነ ረይሶ .....,መኮንን ታደሰ ,ተሾመ ተፈራ (ጅቦ ),አዳነ በቀለ ,እነ ጥላሁን ከበደ /ባርባ / ቡጡ እሸቴ ,ወንዱ ጫካ ,ሸምሱ እና ሰበታ አህመድ ,ዮሀንስ አለማየሁ ::ከአራዳ ደሞ የማነ ርዕሶም እና ተስፉ አለማየሁን አብዶ የሚችላቸው አልነበረም ::ፍቃዱ አቦምሳ /አፈኔ /አብዶሼ ሀጂከድር እና እንግዳወርቅ ጸጋዬ ሐይሉ በረኞች ነበሩ ..አቤት ስንቱን አልኩት በሆዴ የቀረ የለም ::የረሳሁት ካለግን እስቲ አስታውሱን ::
_________________

kibremengist
________________________________________

ፖስታቢትሰፈረ
Joined: 08 Sep 2005
Posts: 36
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 09, 2005 10:21 pm Post subject: የግልነስ በጣም ከልቤ አመሰግናለው
________________________________________
የአዶላ ወዩ ልጆች ሀሳብ , ትዝታ , ያሳልፉብትን ሁኒታ ,የሚውያዩብትን መድረክ ፔጅ ስለሰጠሽን ከልቤ አመሰግናለው .

በተለይ አዶቆርሳ , ባለሱቅ , ቀልቤለጊ የሞኬ ወንድም የምትፅፉት ከአስድሳችነት አልፎ በትዝታ ወደ ክብረመንግስት ይዞኝ ጭልጥ .

ራስ ብሩ ትምህርት ቤት ለምርዳት ያንሳቹት ሀሳብ የሜደግፍ ሴሆን በግሌ የሚቻለኝ ከማድረግ ወድዋላ አልልም . ባሜሪካና በአውሮፓ ለሚገኙ የክብረመንግስት ለጆች ስለ ራስብሩ ትምህርት ቤት ወቅታዊ ቪዲኦ ሰላለን ደፕሉኬት አርገን ለንልክላቹ እችላለው . በጣም በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነው . if you gays see that Video, you wil cry. we should have to help to fix at least Window. there is no window each class.
________________________________________

ቅሩንፉድ
Joined: 15 Apr 2005
Posts: 454
Location: germany
Posted: Fri Sep 09, 2005 11:51 pm Post subject:
________________________________________
ውድ የወዩ ልጆች እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ !

አምላክ መጪውን ዓመት ለሀገራችንና ህዝቦቿ የሰላም የደስታና የብልጽግና ዘመን ያድርግላቸው ::

እዚህ ምስሉ ላይ ጠቆም አድርጉ ::

http://www.123greetings.com/eventsnew/e ... wf#560#380

ውድ እህታችሁ ቅሩንፉድ !
________________________________________

ፖስታቢትሰፈረ
Joined: 08 Sep 2005
Posts: 36
Location: ethiopia
Posted: Sat Sep 10, 2005 12:30 am Post subject: ባለሱቅ
________________________________________
በመጀመሪያ እንካን ለመገናኘት አበቃን
በመጀምሪያ የጠቀስከው ስም የውንድሜን ሲሆን የመጨረቫ እኔው ንኝ . I just found your email adress from Hara white page and i wrote to you,but it wasn't delivered to you.i will write by your privet email. thank you
________________________________________
የግልነስ
Joined: 03 Feb 2005
Posts: 768
Location: united states
Posted: Sat Sep 10, 2005 6:00 am Post subject: አሚንንንንንን የኒ ቆንጆ
________________________________________
ላንቺምምም መልካም አዲስ አመትት ይሁንልሽሽ ቅርንፍድዩ በጣም ከልቢ አመስግናለውውው ያውው የሻምፓኙን ጽዋ የወዩ ልጆቸ ተስባስበንን ቸርስስ እንበልላት ላዲስ አመትትትትት መልካም አዲስ አመትት ይሁንልንንን ለሁላቸንምምም መጪው ጊዚ የስላም የፍቅርር ያዲስ ህይወት ግንባታ እናም የወዩ ልጆቸ በራስብሩ አስባሳቢነት የተዘጋጀውንን እቅዳቸንን ያሳካልንን ዘንድድ በዳላ ወዩ ስምም ጸልያለውው አያለየንንን አሚንንንንንንንንን
የናተውውው የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ
________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Sat Sep 10, 2005 9:03 am Post subject: ፖስታቤትሰፈር
________________________________________
ወንድሜ ያገሬ ልጅ ...
አመሰግናለሁ እንዳወከኝ ሁሉ አውቄሀለሁ ...
የሀረር ሆምፔጅ ውስጥ ያለው ኢ -ሜል አድራሻዬ ተለውጧል ... ሌላ አድራሻ ነው ያለኝ ....
እስኪ ልክልሀለሁ ...
ለተወዳጁ ወንድምህ ሰላምታዬን አቅርብልኝ ..

ስልክ ደውላለሁ እያልኩ ስላልተመቸኝ ነው በለው .. መቸም አያምንም እሱ እንደሆነ ....
ባለፈው ከዲሲ ተደዋውለን አናግሬዋለሁ ....
የሉፍ ጫት እየቃመ እንደነበር አጫውቶኛል ...

የምወዳቸው እናትህ እና እህትህ እንዴት ናቸው ...

እስኪ በሰፊው እንጨዋወታለን ....
መጥቼ አያቹዋለሁ ...

ኢንሻላህ !!!

መልካም አዲስ አመት እመኝላቹዋለሁ

ቻዎ !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
________________________________________
ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Sat Sep 10, 2005 9:18 am Post subject: ትንሽዬ ትዝታ
________________________________________
አደቆርሳ ... የሰው ስም ዝርዝር ደርድረህ በትዝታ አንበሸበሽከኝ እኮ ....

የፍቃዱ አቦምሳ ኩርኩም ያልቀመሰ ... የኔ ባች የ 02 ቀበሌ ልጅ ይኖር ይሆንንንንንንንንንንን ....

አንዴ ምን አደረገኝ መሰላቹ ... 7ኛ ክፍል ሳለሁ .... እዛች ነጯ በድንጋይ የተሰራችው ክፍል ውስጥ ነበር የተማርኩት ... እነ ፍቃዱ አቦምሳ ደሞ 8ኛ ክፍል ነበሩ መሰለኝ ... በእንጨት የተሰሩ ክፍሎች ትዝ ይሉኛል .....
ከነጀማል ሀሰን ጋር ሲያጠኑ እላላክ ነበር .... የሀጂ ሀሰን የኪስ ክፍል አለች .. ከጎን ተለጥፋ የተሰራች .... ታቋት ይሆን ????... ኤኒዌይ እየተላላኩ አብሬአቸው የተወረወረ ጫትና ገራባ እያቃምኩ ሳጠና ይመስላኛል .... ትንሽ ትንሽ ጎበዝ ነበርኩ መሰለኝ
"አንተ ነገ ልትደርስብን ነው እንዴ ብሎ የመታኝ ኩርኩም አይረሳኝም "..... ለኔ ግን ብርታት ነበር የሰጠኝ ...
ሳላመሰግነው አላልፍም በዚህ አጋጣሚ ....

በቡጡ እሸቴ ላይ ደሞ ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም .... በዚያን ዘመን አንድ ወንድ ከሴት ጋር ተያይዞ መሄድ ማለት ነውር ነበር ... አይተን አናቅማ .... ባለጌ እያልን .... ልጅቷን ልቀቃት እያልነው ተከታትለን ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም የ 02 ልጆች ጫጩቶ ብል ይሻለኛል .. ተሰባስበን ከቆጪ ገባያ አንስተን በማርያም ዳገት አድርገን ... በኳስ ሜዳ ድረስ እየተከተልነው .. ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም ... ልጅቱ ደሞ የሻኪሶ ልጅ ነበረች .... እሱ ደሞ የተደነቀ የተጨበጨበለት አብዶ ሰሪ ... ዋውውውው ...
አሁን እህት ኖሮኝ ብክሰው ደስ ይለኝ ነበር .... ግን ቆንጆ እህት የለኝም .... ቅቅቅቅቅ

ግፉ ግን በኔም ላይ ደርሶብኛል አሰላ ሳለሁ ... አሁን አይነገርም ... ኡስስስስስስስስስስስስስስ

ባለፈው ሄጄ ያየሁት ጊዜ ያፈርኩት እፍረት ... እሱ ረስቶት ይሆናል .. እኔ ግን ሁሌ ባየሁት ወይም ባስታወስኩት ቁጥር አፍራለሁ ...
አይ ልጅነትትትት ....
አይ ሞኝነትትትት ....

በሚቀጥለው ጊዜ ሲኖር .... አባባ ክብረት ከአሳምነው (አሳምሚት ) ጋር ያስተዋወቁበትን የልጅነት ትዝታዬ አወጋችዋለሁ ...
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
________________________________________
ትትና
Joined: 23 Feb 2005
Posts: 1474
Location: united states
Posted: Sat Sep 10, 2005 9:40 am Post subject: ቅሩንፉድዮ
________________________________________
እግዚአብሔር ያክብርልኝ ለግብዣው ! ተቀብያለሁ እመጣለሁ !! እናንተ ብቻ ተሰባስባችሁ በአንድ ተጠናከሩ እኛ ወገኖቻችሁ ደሞ አለን ከጎናችሁ !!!

አክባሪህ
ቅሩንፉድ እንደጻፈ(ች)ው:
ትህትናዬ ስለአድናቆትሽ አመስግንሻለው ሲዳሞ ማለት በጣም የሚናፈቅ አገር ነው ::እንደው በዝና ከሆነ የምታውቂው አንድ ቀን እንጋብዝሻለን መቼም ወረድ አላልሽ ይሆናል እንጂ ላንጋኖን ወንዶገነትን የምታውቂው ይመስለኛል ::በዚያው መስመር ነው ይቺ ትንሽ ከተማችን የአዋራዋ ትዝታ ከፊት አይጠፋም ::ስውም በጣም ሰለሚዋደድ ነው መሰለኝ ::
በይ ቸር ይግጠመን

________________________________________
ትትና
Joined: 23 Feb 2005
Posts: 1474
Location: united states
Posted: Sat Sep 10, 2005 9:43 am Post subject: Re: ለትትና
________________________________________
ባለሱቅዮ ሙት አስጎመጀህኝ !!! የቆራስማዋን ወተት ወደ ሀረር ስለማውቃት ምራቄን ነው ያስዋጥከኝ በጾሙ !!! እመጣለሁ በጉሎ ቅጠል ተጠቅልላ የምትሸጠዋን ቅቤም አልረሳም !! አደራ እናንተ ያገር ልጆች ስትገናኙ እንዳትረሱኝ እንጂ !!!

አክባሪያችሁ
ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
ወተት ከናፈቀሽ ... በቆራስማ ቅል
እሸቱን በቆሎ በገፉማ ሙልሙል
ባዶላ ወርቅ ጌጥ ካማረሽ መሽቀርቀር
ምጭና ተደሰች ጀምጀም ለሽርሽር ::

በቦሬ ነጭ ማር በጀምጀሟ ቅቤ
በገብስማ ቆሎ በእንሰት ተከብቤ
እጠብቅሻለሁ ምርጥ አቀራርቤ ::

ለጁስ አሬራችን ለኬክ ዳቦ -ሸዌ
ሀሪቲ ለሽታ ጤናዳም ለደዌ
ጠጁን ለመዝናኛ ቦርዴ ለቁርሳችን
ሁሉም ይዘጋጃል ነይ ነይ አዶላችን
እንጠብቅሻለን ዘርግተን እጃችን

ታዲያ እዛች ወዩ ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል የስሙኒ ቅቤ ገዝተሽ መምጣት እንዳትረሺ .... አድባሯ ቅቤ ትወዳለችና

ሰላም ክረሚባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Sun Sep 11, 2005 12:22 pm Post subject: እንኳን አደረሳቹ
________________________________________
ለአዶላ ክብረ -መንግስት ልጆችና .. ለመላው ያገሬ ልጆችችችችች

እንኳን ለ 1998 አመት አዲስ አመት በሰላም አደረሳቹ ..

ይህ አመት የሰላም የፍቅር የተድላና የደስታ እንዲሆንላቹ ከልቤ እመኝላቹዋለሁ !!!!

ሱቅ መጥታቹ አትጡኝ ....

ያለናንተ ማን አለኝ

ገበያዬዬዬዬ
ገንዘቤቤቤቤ

ባዲስ አመት አዲስ ብዙ ነገር ይዤ እጠብቃቹዋለሁ

ሰላም ሁኑ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
Posts: 746
Location: ethiopia
Posted: Mon Sep 12, 2005 1:16 pm Post subject: እንኳን አብሮ !!!!!!
________________________________________
እንኳን አብሮ አደረሰን ወገኖቼ !!!
ወንድሜ ወቤጃሎ በቀደም በጻፍከው ትዝታ እስካሁን እንስቃለን :ያቺን ዱኩላ ለሚስተር ባክስተር ለመሸጥ ሀሳቡን ያመጣው ማነው ?በነገራችን ላይ ሚ /ር ባክስተርን እና ሚስቱን ሚሲዝ ባክስተርን አስታውሳቸዋለሁ :እሷ ሁሌ ጠዋት ጠዋት የት /ቤቱ ደረጃ ላይ ቁጭ ብላ ሲጋራዋን ስታጨስ እኔና አምዶም ሀብተማርያም /አምላክ ነፍሱን ይማረው /ሰልፍ ላይ ሆነን እጅግ በጣም እየገረመን እናያት ነበር (በዚያን ግዜ ሴትና ሲጋራ ...)ወደጨዋታዬ ልመለስና ሚዳቆ እና ድኩላ ማደን ክ /መንድስት እንዴት እንደተጀመረ ባላስታውስም :እኔ ሳውቅ በዚያን ግዜ ጥሩ አዳኝ ከነበሩት :ሳህሉ ኪዳኔን ሲሳይ ሳንታን መስፍንሞልቶታል /አባቡታ /: አስታውሳለሁ : (ወርቃፈራሁ /ቀኬ / እና ታፈሰ ዳዲ አሁን በህይወት የሉም )ሳህሉ ኪዳኔ የወረወረው ጦር መሬት አይወድቅም ነበር ::አደን መጀመሪያ የወጣሁት ከሳህሉ ኪዳኔ ጋር ነበር :የአጥናፌን ቁልቁለት ሽቅብ ወጥተን ዳገቱን ድኩላ መፈንጫ የሚባለው ቦታ :ማዶ ደሞ እነቀልቤ ለጌ /እነ ስመኝ እልፍነህ / ማሳ ያለ ድኩላ በሬ ነበር የሚያክለው ::አንዳንዱም የተወጋበትን ጦር ይዞ ይጠፋ ነበር ::ካሳዬ በርሄ ዘይት ከጋሽ በርሄ ሱቅ /ጋሽ ገብሬን / አታሎ በ 20 ሳንቲም ግማሽ ሊትር ይዞ ይመጣና ሳህሉ መቼም ሲያርድም ፈጣን ነው :እዚያው ጠባብሰን እምሽክ .............. ነበር ::እኔ ያኔ በዕድሜ ከነሱ ታናሽ ስለነበርኩ ብዙም ስራ አይሰጠኝም ነበር ቢሆንም ሳህሉን ተከትዬ በየጥሻው ስፈናጠር የዋዛ አልነበርኩም ::
ወቤ ጃሎ ምስጋናዬ ይድረስህ በትዝታ ከ አውሮፕላን ማረፊያ ማርያም ዳገት ስላሴን እና ሚካኤልን አገሩን ቀዬውን ያሉትን የሌሉትን ወንድሞቼን ስንቱን አስታወስከኝ አቦ ::
_________________

kibremengist

ቀልቤለጌ

Joined: 31 Aug 2005
Posts: 35
Location: UAE
Posted: Mon Sep 12, 2005 2:55 pm Post subject: Re: ትንሽዬ ትዝታ
________________________________________
እኔ ደሞ ኩርኩም የማውቀው የሀብቱ ኪዳኔን ነው ::ሀብቱ ሲኮረኩም እጁን ይጨብጥና የመሀል ረዥሙን ጣቱን በምራቁ አስነክቶ መሬት አሸዋላይ ጠቀስ ያረጋታል ;ያቺ ምራቅ የነካት ቦታ ይዛ የመትነሳው አሸዋ መሀል አናት ላይ ስታርፍ አቤት .........ግማሽ ቀን ታሳብዳለች ::እናልህ ፍቃዱም መኮርኮም የጀመረው በሀብቱ ኩርኩም እልሁን ከጨረሰ በኋላ ነው ::ለነገሩ ሀብቱ እኔን ኮርኩሞኝ አያውቅም ::ለምን ?እንዳትለኝ ::ቸር ያቆየን ::ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
አደቆርሳ ... የሰው ስም ዝርዝር ደርድረህ በትዝታ አንበሸበሽከኝ እኮ ....

የፍቃዱ አቦምሳ ኩርኩም ያልቀመሰ ... የኔ ባች የ 02 ቀበሌ ልጅ ይኖር ይሆንንንንንንንንንንን ....

አንዴ ምን አደረገኝ መሰላቹ ... 7ኛ ክፍል ሳለሁ .... እዛች ነጯ በድንጋይ የተሰራችው ክፍል ውስጥ ነበር የተማርኩት ... እነ ፍቃዱ አቦምሳ ደሞ 8ኛ ክፍል ነበሩ መሰለኝ ... በእንጨት የተሰሩ ክፍሎች ትዝ ይሉኛል .....
ከነጀማል ሀሰን ጋር ሲያጠኑ እላላክ ነበር .... የሀጂ ሀሰን የኪስ ክፍል አለች .. ከጎን ተለጥፋ የተሰራች .... ታቋት ይሆን ????... ኤኒዌይ እየተላላኩ አብሬአቸው የተወረወረ ጫትና ገራባ እያቃምኩ ሳጠና ይመስላኛል .... ትንሽ ትንሽ ጎበዝ ነበርኩ መሰለኝ
"አንተ ነገ ልትደርስብን ነው እንዴ ብሎ የመታኝ ኩርኩም አይረሳኝም "..... ለኔ ግን ብርታት ነበር የሰጠኝ ...
ሳላመሰግነው አላልፍም በዚህ አጋጣሚ ....

በቡጡ እሸቴ ላይ ደሞ ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም .... በዚያን ዘመን አንድ ወንድ ከሴት ጋር ተያይዞ መሄድ ማለት ነውር ነበር ... አይተን አናቅማ .... ባለጌ እያልን .... ልጅቷን ልቀቃት እያልነው ተከታትለን ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም የ 02 ልጆች ጫጩቶ ብል ይሻለኛል .. ተሰባስበን ከቆጪ ገባያ አንስተን በማርያም ዳገት አድርገን ... በኳስ ሜዳ ድረስ እየተከተልነው .. ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም ... ልጅቱ ደሞ የሻኪሶ ልጅ ነበረች .... እሱ ደሞ የተደነቀ የተጨበጨበለት አብዶ ሰሪ ... ዋውውውው ...
አሁን እህት ኖሮኝ ብክሰው ደስ ይለኝ ነበር .... ግን ቆንጆ እህት የለኝም .... ቅቅቅቅቅ

ግፉ ግን በኔም ላይ ደርሶብኛል አሰላ ሳለሁ ... አሁን አይነገርም ... ኡስስስስስስስስስስስስስስ

ባለፈው ሄጄ ያየሁት ጊዜ ያፈርኩት እፍረት ... እሱ ረስቶት ይሆናል .. እኔ ግን ሁሌ ባየሁት ወይም ባስታወስኩት ቁጥር አፍራለሁ ...
አይ ልጅነትትትት ....
አይ ሞኝነትትትት ....

በሚቀጥለው ጊዜ ሲኖር .... አባባ ክብረት ከአሳምነው (አሳምሚት ) ጋር ያስተዋወቁበትን የልጅነት ትዝታዬ አወጋችዋለሁ ...

_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
_________________________________________________________________________________________________________________________________________
ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Tue Sep 13, 2005 6:44 am Post subject: ከትዝታዎቻቹ ማህደር
________________________________________
ሰላም ቀልቤ -ለጌ እና አደቆርሳ

ብዙ ብዙ የምታነሷቸው ሰዎችን በስም እንጂ በአካልና በድርጊት አላቃቸውም .... የጀነሬሽን ጋፕ ይሆን ወይስ ... ሳላቃቸው ቀርቼ አላቅም ...
ግን ደስስ ይላል ትዝታቹ በሙሉ ...

ድኩላ .. ሚዳቋ አደን ሲወራ እንጂ እድሉ አልገጠመኝም ....
ትዝ የሚለኝና በኔ ጊዜ የነበረው ልጅና ወጣት ያደርግ የነበረው .... ያቺ የማርያም ወንዝ ውስጥ መዋኘት .... እዛ ለጥጥጥ ያለ ሜዳ ላይ ... ሌሊት ተነስተን የምንሰራው አክሮባት ... ቀን ቀን ት /ት ከሌለ በርጫችንን ይዘን ማርያም ዳገት ላይ ቁጭ ብለን ... ወይም ወደ ኩቾ በር .. ወይም ወደ ጅሪንቲቲ ተራራ .. ዛፎቹ ውስጥ በዚያ በሚቀዘቅዘውና የነፍስን ስሜት በሰላማዊ ደስታ ወጥሮ በሚያዝናናው ቀዝቃዛ አየር ውስጥ የምንቅመው በርጫ ነው ትዝ የሚለኝ .... የኛዎቹ ልጆች አደን የሚያድን ጉልበት አልነበረንም መሰለኝ ....
ምን ይደረግ ከላያችን ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ተሰደው ታስረው ተገለው ... እኛ ምን ከማን እንማር .... እውር ድንብራችንን ነበር የምንጓዘው ማለት እችላለሁ ....
ላካፈላቹን ትዝታ ግን ከልቤ አመሰግናለሁ ....
ምናለ ባልሞታቹና ከናንተ ብዙ ብዙ በተማርን .... በዚያን ዘመን የሚቃጠል ሽፍታ ወይም ፀረ -አብዮተኛ ወጥታቹ እዩ ስንባልና ስናይ ትዝ ይለኛል ... አቤት የህፃን ጭንቅላት ውስጥ የሚፈጥረው ስሜት ....
ይኸው ፈሪ ትውልድ ሆነን ቀርተናል ... ሚዳቋ እንኳን ማደን የማይደፍር ትውልድ ነን ...

ቀናሁባቹ አቦ !

እስኪ ብዙ ብዙ ንገሩን ስለብዙዎቹ ያገሬ ልጆች ... እራሴንም መለስ ብዬ እንዳይበት

ቸር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
Posts: 746
Location: ethiopia
Posted: Tue Sep 13, 2005 2:15 pm Post subject:
________________________________________
ባለሱቅ ሰላም ይሁንልህ :ይገርምሀል ዛሬ ጠዋት ሥራ ከመግባቴ በፊት ታናሽ ወንድሜ ደወለና በዚያው ሰለራስ ብሩ ጥሪ አንስተን ምን አለኝ መሰለህ
/አደቆርሳ ጽሁፎቹ ደስ ይላሉ ግን ከሚጠቅሳቸው ስሞች አንዳንዶቹን ጨርሶ አላውቃቸውም /በባለሱቅ ጽሁፍ ትዝታ ግን ....................ብሎኛል ::ታድያ ኮምፒዩተሩን አስነስቼ ወደዚሁ ገጽ አመራሁና ያንተን ጽሁፍ ሳነብ በጣም ገረመኝ ::ስለ አባባልህ እና ስለ ልዩነታችን በቅርቡ የ እስርቤት ትዝታችንን የሚዳስስ ሌላ ትዝታ ይዤ ስለምመጣ ምናልባት እዚያ ላይ አንዳንድ ነገሮች ለግንዛቤ ይረዱህ ይሆናል ::በዚህ ላይ የማስታወስ ችሎታም አንዱ ኅይል ነው ::በነገራችን ላይ በጣም ልጅ ሳለን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እያንዳንዱን ነገር ሳይረሳ በጣም የማስታወስ ችሎታው ልዩ ነው የምንለው ልጅ ምናልባት ታውቀው ይሆን አላውቅም ::የሚኖረው በምድረ ስካንዲኔቪያንስ ነው ::እኔም እንደሱ አልሆንም እንጂ ከቄስ ት /ቤት እስከ 8ተኛ ክፍል የነበረውን ዘመን ስለምወደው በጣም አስታውሰዋለሁ ::ዳሩ ትዝታችንም እኮ ያ ዘመን ነው :ከዚያ በኋላማ ምን ትዝታ ሊኖር ........................የሚገርምህ እኒያ በአደን ከጠቀስኩልህ ሁሉ አሁን ብዙዎቹ ካገር ወጥተዋል ከፊሎቹም አልፈዋል እስካሁን እዚያው ክ /መንግስት ያለ ሲሳይ ሳንታ ብቻ ነው ::ያኔኮ ደሞ ሁላችንም (Juniour) የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ነበርን .........ይህ የማያልቅ ታሪክ ስለሆነ :ወደ አምዳችን እንመለስ ::ሰሞኑን ደሞ ቤቱ ጭር ብሏል :ቅሩንፉድ በዚህ አመት ብቅም አላለችም :
ያቺ የግሏ ደሞ ያንን የፈረንጅ ውሀ መንገድ እያነሳች ያለሁበት ቦታ ባህርዛፍ ባህርዛፍ እስኪሸተኝ ድረስ በትዝታ የምታፍነከንከኝ :ምንድነው ነገሩ :በኍላ ሌላ ነገር እንዳታመጪ እኔ በዛ መንገድ ዋ !!!:
ወንድሜም ሊያውቅህ ይፈልጋል እንግዲህ ይጽፍልህ ይሆናል ::ዛሬ ምናልባት አደቆርሳ ማን እንደሆነ ሲያውቅ የሚለኝን ደሞ እጠብቃለሁ ::
አንተ ፖስታቤትሰፈሬ ምነው ጠፋህሳ ?ግምቴ ልክ ከሆነ ""ድንጋይ በኪስህ ይዘህ የተማሪ ደብተር የምታስጥለው ትዝ ይልሀል ወይ በልልኝ ግምቴ ልክ ካልሆነም አላወቅሁህም ) ማለት ነውና :ቸር ይግጠመን ::ወንድማችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ !!
_________________

kibremengist
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቅሩንፉድ
Joined: 15 Apr 2005
Posts: 454
Location: germany
Posted: Tue Sep 13, 2005 9:36 pm Post subject: ሰላም ወዮዎች አመትበዓል እንዴት ነበር ?
________________________________________
በኔ በኩል እንግዲህ የልኳንዳ ስፈርን ስጋ አስመጥቼ ስከታትፈው ነው በሀሳቤ የመጣብኝ :: ምነው እንአደቆርሳ ሴክቴን ጠጥታችሁ ሙዚቃዬን አዳምጣችሁ : አሜን ያላላችሁ :: የግልዬን አይመለከትም ::

ቀልቤለጌ ስለወፉ አንድ ነገር ትዝ አለኝ :: አንድ ጊዜ እማዬ ቡና ስታፈላ መጥቶ ቁጭ ብሎ ጠጣ ጠጣና : ሊወጣ ሲል እህቴን ሳታስበው ድርግም አርጎ ሳማት :: ከዛ ቱፍ ቱፍ እያለች የዘለለችው አይረሳኝም :: ያም ትመጣለህ የሚለውን ነገር እኔም አልረሳውም :: የቺካጎ ማህበር ጥሩ ነው :: እኔም ዘመዶች አሉኝ እዚያ :: የእነፍርዬ ገዳም ቤተስቦች ናቸው ::

በሉ እንግዲህ እስከሚቀጥለው ::

አክባሪያችሁ
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

የግልነስ
Joined: 03 Feb 2005
Posts: 768
Location: united states
Posted: Wed Sep 14, 2005 1:22 am Post subject: አዲስ አመትማ በክ /መንግስት ትዝታ አለፍ
________________________________________
ስላምምም ለሁላቸውው ተጠፋፋንን አይደልልል አንዳንዲምም ትዝታ ይዞ ይጠፋልል እኮ እኒምም ቢዚ ነበርኩ ራስ ብሩ የስጠኝኝን የስራ ድርሻ ለመወጣትት ባቅራቢያዩ ላሉትት የወዩ ልጆቸ የዋርካንን ሆም ፒጅ እየደዋወልኩኝኝ እየስጠሁኝኝ ነውው ሚገርማቸውው አንዲት ጋደኛዩ ጋ ስደውልል ሀዋ አደምን አገኛሀት ለሳምምም የክ /መ ልጆቸ ኦን ላይን ላይ እየተገናኝንን ስላትት በጣምም ነውው ደስስ ያላትት የቺካጎውን የክ /መ መሀበርር ስነግራት ደስታዋ መጠንን አልነበረውምም ለወንድማም እንደምትነገረውው ነግራኛለቸ ቀድሞ ይህንን ፒጅጅ ካላገኝውው እንግዲህ እንበርታ ቀልቢ ለጊና አደቆርሳ የምትናገሩትት ትዝታ ባለሱቅቅ እንዳለውምም ባላልፈበትም በዛንን ጊዚ የነበረውው የቀይሽብርር ሁኒታ በልጅነት አይምሮዩ ውስጥ ይታዩኛልል አባቡታና አስታወሳለውው , ከምን እንደድረስም ባላውቅቅ , ያቆብ ደስታምም ቦሪ ነውው ሂኖክክ ወንድሙም አዲስአባ ነበር ከማስታወሳቸውውበሉ እንግዲህ አይለይንን በርቱልኝኝኝ ቁርንፍድዩ በይ በርቺልኝኝ አንቺምም ባለሽብትት የናተውው የወዩዋ የግልል ነኝኝኝኝ
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

Ellenie
Joined: 27 Jul 2005
Posts: 1086
Location: ethiopia
Posted: Wed Sep 14, 2005 2:15 am Post subject: የግል ቅቅቅ
________________________________________
ምነው ልጄ በሳቅ ትገይኝ እንደዚ ! ቅቅቅ እነኛ የተደጋገሙት ፊደሎች ከ ቻት ሩም ሸሽተው ነው ? ውይ ኧረ ብሳቅ ገደልሽኝ ቅቅቅ ልሞት ነው ምንም እኮ አልገባኝም ጽሑፉ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
Smile
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Wed Sep 14, 2005 4:52 am Post subject: የማስታወስ ችሎት
________________________________________
በትክክል ተመልሷል ::
በውነት ነው ምልህ አደቆርሳ ... የማስታወስ ችሎታዬ እየቀነሰ እየጠፋ እየተስለመለመ አሁን ያለሁበት ደረጃ ደርሷል .... መቸ እንደጀመረኝ ባላውቅም ... ወይም በተፈጥሮ ሆኖ የማስታወስ ችሎታ የለኝም ይሆን እንጃ ...
ይገርምሀል የጎረቤቶቼን ስም ጠቅሰው ሲያወሩ እንኳን .... ማነው እሱ ያልኩበት ጊዜ አለ ... እንዳልከው ሁላችንም የተለያየ የማስታወስ ችሎታ አለን .... ለዚያም ይሆናል ኃላ የቀረሁት ...
ግን በሙሉ ፅሁፍህን ወድጄልሀለሁ ... ቀንቼብምሀለሁ ..... ቅቅቅ አዲስ አማርኛ ፈጠርክ እንዳትለኝ ብቻ ... እንደመጣልኝ ስለማወራ ይቅርታ ...

ምናልባት ታናሽ ወንድምህ በደንብ ያቀኝ ይሆናል ... እስኪ የክ /መንግስት ሀይስኩል አንዲት የዱርዬ ትዝታዬን ላውጋቹ ...
የበቆሎ ተከሉ ዘመቻ ነበር .... እኔና ጓደኛዬ የተሰጠንን መስመር ይዘን ሁለት ሁለት ፍሬ እየተከልን ሄድን ብዙ ብዙ .... እኔ በመርዝ የተነከረ በቆሎ ይዣለሁ ጓደኛዬ ከኔ እየወሰደ ቆፈር ቆፈር እያደረገ ይተክላል .... ወደመጨረሻ አካባቢ ልንደርስ ስንል ... በቃ ተመለሱ የሚል ትዕዛዝ ተላለፈ ... በእጄ የቀረ ብዙ የበቆሎ ፍሬዎች ነበር ... ጓደኛዬም .. አለ
ባክህ ማን ይዞ ይመለሳል ... አስገባው እዙህ ጉድጓድ ውስጥ
..ቆፈር ቆፈር ....
ክትትትትት ወደ 40ፍሬ ይሁኑ ይሆን .... ቅብርርር አደረኩት
ታዲያ ይህንን ስናደርግ የሚያይ አንድ ልጅ ነበር .... ከጎናችን ካለው መስመር እየተከለ ይሄድ የነበር ....
ነፍሱን ይማረውና የአበራ በሪ ልጅ .... ምስራቅ አበራ ...
ጓድ ሊቀመንበራችን መንግስቱ ኃ /ማርያም ክ /መንግስት ለጉብኝት መጥቶ ዘንባባ ካንፕ አሰርቶ ያደረ ጊዜ ... ምግብ አቅራቢ አበራበሪ ሆቴል ነበር ... ስራ ሊያግዝ ሄዶ ነው አሉ ... ልክፍት መትቶት ባንድ ቀን በሽታ ያረፈው መሰለኝ ...
እናላቹ ... ይህ ጓደኛችን .. ሄዶ ላባጦር ... ንግር ...
እንትናና እንትና አንድ እፍኝ በቆሎ ጉድጓድ ውስጥ ከተቱ .. ብሎ .... ምስኪንንን .. ትክክል ነበር መናገሩ ... ግን ጦሱ ለብዙ ነገር ዳረገን እንጂ ...
ተጠቁሞብን ሊይዙን ሲመጡ .. በሌላ ቀን ማለት ነው ... ጓደኛዬ (ታላቄ ነው መሰለኝ )... እግር አውጪኝ ብሎ በአጥር ዘሎ ሄደ .... እንደሄደ በዚያው ቀረ ... ውትድርና ...
እኔ አንድ ግማሽ ቀን ታሰርኩና ... በማግስቱ ጠዋት በተማሪዎች ፊትለፊት ንግግር እንዳደርግ ... የይቅርታ ንግግር ... ተደርጌ ገባሁ
ያ ውትድርና የሄደው ግዋደኛዬ ወንድሙ ግን ምስራቅን ሊደበድበው እቅድ ነበረው ... ቀድሞ ሞተ እንጂ .... አምላክ ነፍሱን በፀጋ ይቀበለው ...

ታዲያ ይህች የበቆሎ ታሪኬ 11ኛ ክፍል ተከትላኛለች ...
ከድሪርሳ (የምወደው የሀይስኩል ዳይሬክተር .. ምስጋና ለሱ ይገባዋል .. አሁን አለሁበት ደረጃ ያደረሰኝ የሱ ቁንጥጫ ነው ).... ከድሪርሳ ጋርም አጋጭታኛለች .... 11ኛ ክፍል ላይ .... የሆነች ስተት ሰርተን 4ተማሪዎች ከት /ት ቤት ተባረን .... ከጊቢዬ ውጣለኝ ፖሊስ ሳልጠራልህ ሁሉ ተብዬ ከ 3ሳምንት በኃላ ለናቴ ነግሬአት ይዛኝ ልትለምንልኝ ሄደን ቢሮው ውስጥ እያግባባነው እያለ ... አባጦር በመሀል ይገቡና .... ይሄ ይሄ የሀገር ጠር ... አገር ምድር በርሀብ ሲቆላ እሱ አንድ እፍኝ በቆሎ ....ም ,ናምን ምናምን .... 9ኛ ክፍል እያለ ብለው ሊራራልኝ የነበረውን ሰውዬ ... ምን ብዬ ልናገር ...
አቤትትትት ልጅነት .. ሞኝነት ...

እስኪ ደሞ ሻፊ ሻይ ቤት ቆቆር እየበላን የራስ -ብሩን ትዝታዬን እንጨዋወታለን

ቸር ይግጠመን

አንቺ የግል ለምንድነው ምትጠፊው ... የአዲስ አመት ካርድ ልከልሽ አመሰግናለሁ እንኳን አይባልም እንዴ ?.. ቆይይይ ባልቆነጥጥሽ ..

ቅሩንፉድዬ ... ያ ልኳንዳ አሁን ቀዝቅዞ ይሆን .... ከአለማየሁ ባንቲ መኖሪያ ቤት በላይ ያለው ልኳንዳ .. ባይኔ ላይ ዞረ እኮ .... የሰዎቹ ወጠምሻነት ... ይህንን ስጋ ነርተው ነርተው ... ዋውውው ሲያስፈሩ ... ሰክረው ሲጣሉማ ... ተዋበች ጠጅ ቤት ጎራ ብለው ....

ያም ትመጣለህ !!!!!... አለ ወፉ .. በቦቅስ ሲነርተኝ

ችር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
Posts: 746
Location: ethiopia
Posted: Wed Sep 14, 2005 6:37 pm Post subject: አይ ልጅነት
________________________________________
እንዴት ዋላችሁ ?
ቅሩንፉድዬ ያንን የልኳንዳ ጮማ (የነገነት እሸቱን :ቤት የጎድን ጥብስ የ 10 አለቃ ተሰማንቤት ጭቅና የነ አገኘሁ ዱባለንቤት ሽንጥ ባንቺ ቢኖ እያወራረድኩ በዚህላይ በባለሱቅ ትዝታ አዶላን እያስተዋልኩ ባንቺና በሌሎቹም የልጅነት ወግ .........ምን ልበልሽ ዓውዳመቱን እንደኔ የተደሰተበት አለ ብለሽ ነው ?
በይ ምስጋናዬ ይድረስሽ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
የግልነሽ ሀዋ አደምን አገኘሁዋት ስትል እኔም አሊ አደምን አስታወስኩ ::አሊ የት /ቤት ጓደኛዬ ነው ::ት /ቤት እኩል ባንገባም 3ተኛ A ክፍል አብረን ነበርን አስተማሪያችን ቲቸር ዘሪሁን ይባላል (ቀይ ቀጭን ረዥም )ዓሊ የሩቅ ሰፈር ልጅ ቢሆንም አንድ ክፍል ስለነበርን በኳስ እንግባባ ነበር ::ዓሊ በባዶ እግሩ በፑንት የሚመታት ኳስ ለበረኛው ለአብዶሼ አሳር ነበረች ::ሰኔ 30 ደርሶ ከየክፍሉ ከ 1-3ተኛ የወጡ :ከሆልሴክሽን ከ 1-3 የወጡና በተለያዩ ሳብጀክቶች ቶፕ ውጤት ያላቸው ሁሉ ብቻ ያኔ ሽልማት ብዙ ነበር ::ታድያ በዚያ የወላጆች ቀን ወላጆች በልጆቻቸው የሚደሰቱበት እና የሚያዝኑበት በመሆኑ ትልቅ ቀን ነው ::እኔም አሊም እንደምናልፍ አረጋግጠን ነበርና :ዝግጅቱን (ሥነስርዓቱን )ትተን ወደ ኳስ ጨዋታችን እንድንሄድ ዓሊ ግድ አለኝ :እኔም ሌላ 3ኛ ክፍል የነበረ ወንድሜን ጠርቼ ተያይዘን ከት /ቤቱ በስተምዕራብ ባለችው የኳስ ሜዳ ስንራገጥ ቆይተን ስንመለስ ዝግጅቱ ተጠናቋል ::አባታችን ሽልማታችንን ተቀብሎ በኛም ያልጠበቀው ሁነታ በጣም ተናዶ ተመልሷል ::እቤት ስንደርስ የዋልንበትን ያቺ አንድ አይነት ፍራቢ ሸራ ጫማችን ትመሰክራለች : ለወላጆች ቀን አጥበን ነበር ያረግናት )ገና ስንገባ እንደምንገረፍ አውቀን ነበርና እኔ ዓሊ ዓሊ ነው እያልኩ ወንድሜ ደሞ በኔ እያመኻኘ ነበር ከዚያማ ተያዝና :እናታችን ባትረዳን ...
አልቆልን ነበር ::በጣም የሚገርመው ግን ዓሊ አደምም ተሸላሚ ነበር ::ትልቁ ወንድማቸው ጋሼ ያደረገውን እስካሁን ያስታውሳል ::እስካሁን ሳገኘው ወቅሰዋለሁ ::
የግሏ አመሰግናለሁ ::የወላጆች ቀን የስፖርት ትርዕይት ታስታውሻለሽ ?ግርማ ይስሀቅን ፍቃዱ አቦምሳን ሽብሩ ግርጃን ወዘተ .
ቸር ይግጠመን ::
_________________

kibremengist
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Thu Sep 15, 2005 5:02 pm Post subject: አደቆርሳ
________________________________________
የትዝታ ኮሮጆ የሰው ስም ማትረሳ
የቦታ ገጠመኝ ሁሉን ምታነሳ
በናፍቆት ሰቀቀን ጥለህ ምታስነሳ
ከ 04 ወዲያ ስምህ አደቆርሳ
ላንተ አድናቆቴን እስኪ አኔም ላውሳ :
በብዕሬ ቅለም ትንሽ ልጠቃቅሳ !::

ሆ ሆ .... ይገርማል የሉካንዳ ሰፈር ሰዎችን ስም ስታነሳ እያንዳንዱን ሰው አቀዋለሁ ... ግን ለብቻኅ ጥራቸው ብትለኝ ... በፍፅም ነው መልሴ ..... እንዴ ነው ግን የሰው ስም ማትረሳው ጃል ...
በተለይ አገኘው ዱባለን ስጠራው ግርምምም ነው ያለኝ ... ምክንያቱም አውቀዋለሁና .... ባንድ አመት መሰለኝ በክፍል ምንለያየው ... ደሞ የሰፈሬ የቀበሌዬ ልጅ ነው እንጂ ... አንተ ካዶቆርሳ መጥተህ የሱን ስም አስታውሰህ እኔ ስረሳ ... እራሴን እንድታዘብ ነው ያድረከኝ ...

እረ ስሞትልህ ስለአንዳርጌ ቤተሰቦች የምታቀውን አጫውተኝ .... ያንዳርጌን መኪና ብዙ ጊዜ ተሳፍሬዋለሁ ... ቢሉ ት /ት ቤት ስማር ....
አንዲት ልጁን ደሞ .... ቅቅቅቅ ወድጃት ሞቼ ነው የተነሳሁት .... ሚስጢር ነው .... ወይ ፍቅርርርርርርርርር .. ባዶቆርሳ ት /ት ቤት ጊቢ .....

በነገራችን ላይ ቢሉ ት /ት ቤት የተከልኵት ዛፍ አለች በሄድኩ ቁጥር የማያት ... እንዴት አድጋለች መሰለህ ... ስወዳትትትትትት

በል ፕሊስ ከትዝታዎችህ ብዙ ብዙ አካፍለኝ ... ወድጄልሀለሁ ያንተን ጨዋታና የማስታወስ ችሎታ ...

በቅናት ልሞት ነው ስልህ ግን ሌላ ሰው እንዳይሰማ እያፈርኩ ነው .... ምክንያቱም የ 02 ልጅ ነኛ !... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አቤትትት የ 02 እና የ 04 ቀበሌ የእግርኳስ ጨዋታ ያለ ጊዜ ያለው ፉክክርና ድብድብ ... መቸም አይረሳኝም ...
አንድ ጊዜ ተሸንፈን ግን ,,,, ዋንጫዋን በድንጋይ ሰብረናታል ... በእንጨት መሰንጠቂያ መኪና ላይ እየጨፈሩ ሲሄዱ ... ተናደን ድንጋይ ወርውረን ... ስይድ ከድሮ አንዱ ድንጋይ ወርዋሪ ነበር .. 01 ቀበለኤ ይሁን እንጂ እኛን ነበር ሚያግዝው መሰልኝ ....

እረ ሮዛ ከድሮን ሚያቅ ማነው ... ቁንጅናዋ .... የኢድ ቀን እሷን ለማየት የምንንጋጋው ትዝ እያለኝ ግርምምምም ይለኛል ... ኒውዮርክ እንዳለች ተነግሮኛል ግን ያው አሁንም በጭንቅላታችን ውበቷ ተስሎ እንዳለ እንድታቅልን ይነገርልን ..ንጎረቤቶቿ አደራቹን አርሱልንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንን

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቸር ይግጠመን አቦ
\
አደቆርሳን አያሳጣን ... የትዝታችን ማህደር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA

Last edited by ባለሱቅ on Sat Dec 23, 2006 2:30 pm; edited 1 time in total
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

አደቆርሳ
Joined: 03 Aug 2005
Posts: 746
Location: ethiopia
Posted: Thu Sep 15, 2005 8:12 pm Post subject:
________________________________________
ትዝታ ለብቻ ከሆነኮ ህመም ነው :ከወዳጅ ጋር ግን እነሆ ትዝታ ነው ::እንዴት ከረምክ ወዳጄ ባለሱቅ :: አድናቆትህን ከፍ ካለ ምስጋና ጋር ተቀብያለሁ ::ወደ ልኳንዳ የወሰደቺኝማ ቅሩንፉድ ነቻ ወፉ እህቴን ግጥም አድርጎ ሳመ ስትል ቀኑን ሙሉ ስስቅ አይደል እንዴ የዋልኩት :: ወይ ጉድ !!
ጠላትህ ይሙት እኔ ስለ ጋሽ አንዳርጌ ቤተሰብ አላውቅም ::የማውቀው ያንን አመለ ሸጋ , ጂኒየስ ,ቀልደኛና የዋህ አድማሱ አንዳርጌን ነው ::የማይረሳኝ አንድ የሚወዳት እና ካፉ የማትጠፋ ዘፈን ነበረችው :(Thebirds........flying...)ምንታረገዋለህ :""ስብሀት
ለእግዚአብሄር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ "":እንዳለ ሉቃስ :2:14 የክርስቶስ መወለድ ለሙታን ትንሳኤ ባይሆን ኖሮ በእነዚያ ሰማዕት በሰው ክፋት ለሞቱ ወጣቶች ዛሬ
የኛ ስራ በቀል ብቻ ነበር ::ነገር ግን በቀል የእግዚአብሄር እንጂ .....::ወዳጄ ሆዴ ባለሱቅ እንደው ወዳላሰብኩት ወሰድከኝ :ይልቅ ወደ ኳስ ጨዋታችን እንመለስና :የ 04 በረኛ የነበረው ተስፋዬ ለማ በዚያን አንተ በምትለው ግዜ ኮከብ ነበር ::ከ 02 ጌታቸው ይርዳውን አልረሳውም ::ከአስተማሪ ስፖርተኞች ማን ማንን ታስታውሳለህ ?ምናልባት እነ ኮርማ ዱግዳ እነሙሉጌታ አስመላሽን ታውቃቸዋለህ ?
እናንተ ቀበሌስ ዮሀንስ አለማየሁ ያሰለጥናቸው ከነበሩ
ልጆች አሁን ጥሩ ደረጃ ደርሰዋል የመትላቸው አሉ ?
ክብሮምስ (ክብሪት )የት ነው ያለው ?ከሴቶች ጥሩ ስፖርተኛስ ?
በል ለዛሬ በዚሁ ይብቃን ቸር ይግጠመን ::
_________________

kibremengist
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ቅሩንፉድ
Joined: 15 Apr 2005
Posts: 454
Location: germany
Posted: Thu Sep 15, 2005 8:42 pm Post subject: ስላም አዶላዎች
________________________________________
አዶቆርሳ እና ባለሱቅ መቼም ትዝታ አያልቅባችሁም :: ክብረ መንግስት እንደስሟ ትናፍቃለች :: ገንዬ ጎደኛዬ ነበረች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ነበር የተማርነው :: እነሶሎሜ ገብረትንሳዬንስ የሚያስታውስ አለ :: አንድ ጊዜ ያዕቆብ የወይነሽት ምትኬን እህት ትንሿን : እህቶቿ አዲስ አበባ ሄደው ነበር ያኔ : መንገድ ላይ ያገኛትና ነይ እስቲ አንቺ ቡና አፍይ ይላታል :: አፍልታለት ቡናው በድንብ አልደቀቀም መስለኝ ቱፍ እያለ ጠጣና : አቦ አንቺስ ቡና ቦርድ ነሽ አላት :: በሌላ ቀን ደግሞ እንዲሁ በይ ዛሬ እስቲ ነይ ወተት አፍይልኝ ብሏት : ወተቱን ደግሞ ስኳር አበዛችበት መሰለኝ : አንቺስ ቡና ቦርድ ብቻ አይደለሽም : ወተት ቦርድም ነሽ ይላታል :: አይ ያኔ የሳቅነው ሳቅ ! ቂቂቂ

የግልዬ እንዴት ነሽ ነብሷ የወዩ ልጅ ! ደውይልኝ !
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

እንግዳ ነኝ
Joined: 15 Sep 2005
Posts: 1
Location: united states
Posted: Thu Sep 15, 2005 11:34 pm Post subject: እንግዳ ነኝ
________________________________________
ታዲያስ የወዩ ልጆች

እንዳው ትገርማላቹ ምንም እንካን ፍቅራችሁ ቢያስቀናም ይሄን ያህል ለዚች አመዳም ከተማቹ (እንዳው ከተማ ልበለው ስሙን አሳምሬ )
ክ /መንግስት ማለት አበዛቹ ::

ቂቂቂቂቂ ...........
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 16, 2005 4:03 am Post subject: አቤትትትትትትት
________________________________________
አደቆርሳ ጥያቄ በጥያቄ አደረከኝ አቦ ...
ብዙ ብዙ ሰው አስታውሳለሁ ስም ግን ጥራ አትበለኝ ... ምክንያቱም ቅድም እንዳልኩህ ጭንቅራቴ በልዟል ....
ከአስተማሪዎች ... ያ ! የቦሬ ልጅ ረጅሙ ... ናስር ነው መሰለኝ ስሙ .... ኮርማ ዱግዳ ስሙን ታላቅ እህታችን ስታነሳ ትዝ ይለኛል .. አጭር ፈጣን ተጫዋች ነበር መሰለኝ ... ዝነኛ አብዶ ሰሪ ...
ያልከውን የ 04 በረኛ ዋውውውው በጣም ነው ማስታውሰው ... አሞራው ነው አይደል ... ሲወረወር እኮ ጭልፊት ነበር .. አቦ .....
ግን ግን አሞራው የ 03 በረኛ ይሆን .. ፀጉሩ ረጅም አጭር ተወርዋሪ .... ተስፋዬ ያልከው ረጅም መሰለኝ ... አቦ ተምታታብኝ እኮ ...
ክብሮም ኃይለዝጊ ጓደኛዬ ነው ... ክብሪት .... መሀመድ ረሺድን ታቀው ይሆን ... ነፍሱን ይማረውና ... እሱ ደሞ ወንድሜ ነው ..... ወይ ጉድ ራሴን አጋለጥኩ እኮ ...
አቦ አንድ ጊዜ እኔ ሀብቱ ተወልዴ ... ግርማ ርዕሶም ክብሮም ኃይለዝጊ ኤፍሬም ኃለዝጊ (ነፍሱን ይማረው ) ሆነን የሉፍ ጫት ገዝተን በጠዋት በእግራችን ሻኪሶ ድረስ በእግር ወክ ያደረግነው አይረሳኝም ....
ጀብዱ ነበር ለኛ 20 ምናምን ኪ .ሜ ... ወክ ማድረግ ... የፈራነው አባሎ አካባቢ ያሉትን ዝንጀሮዎች ነበር ... ሰው ከዛፍ ጋር አስረው በጉንዳን ያስበሉታል የሚባል ወሬ ማን እንዳወራ አናቅም ... በፍራት ነበር ያለፍናት ያቺን መንገድ ... አይ ልጅነትትት

የሴት እስፖርተኞች አልከኝ ... የእጅ ኳስ ነበር ትዝ የሚለኝ .. እዛ ቆጭ ገበያ ካለው የስፖርት ሜዳ ላይ ... ሴቶች ሲጫወቱ ... የ 02 ቀበሌ የሜጫ ሰፈር ልጅ ስሟ ጤፋብኝ ... 01ቀበሌም ጎበዝ ልጆች ነበሩ ... እረ ስም መርሳት በሽታ መዳኒቱ ምን ይሆን ....

ቅሩንፉድዬ የባላምበራስ ገ /ትንሳኤ ቤተሰቦች የምወዳቸው ቤተሰቦቼ ናቸው ... አሁን በብዛት አሜሪካ ነው ያሉት ... ሌሎቹም አዲሳባ ..... ያቆብ ገ /ትንሳኤ ተንኮለኛ ነበር ማለት ነው .... ቅቅቅቅ

ለእንግዳ ነኝ
እናመሰግናለህ ላድናቆትህና ለትችትህ ... ስለህንፃው ድልድዩ ድንጋዩና ተራራው እያወራን አይደለም ... ስለ ሰው ነው ምናወራው ... ሰው ደሞ ከምንም ነገር በላይ የተከበረ ፍጡር ነውና .... የትም ተወለድ የትም እደግ ... ቅመምህ የሰውነት መለኪያህ ... ህብረትህና ፍቅርህ ነው ዋናው ያንድ አገር ቅመሙ ..... እንጂ ህንፃው መንገዱ አስፋልቱ አዋራው አይደለም .... ስለዚህ ሳቅህን ውጠህ በመጣህበት እግርህ ብትመለስ ደስ ይለናል
እናመሰግናለን
ፊርማ የማይነበብ
የክብረመንግስት ልጆች
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
_________________________________________________________________________________________________________________________________________

ባለሱቅ
Joined: 27 Sep 2004
Posts: 962
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 16, 2005 4:13 am Post subject: ቅሩንፉድዬ
________________________________________
ወይኔ እንደገና ሳነብሽ ምን እንዳየሁ ታውቂያለሽ .... የወይንሸት ምትኬ !,,,, ዋውውውውውውውውው አውቃታለሁ እኮ .. ወይንሸትን .... ወፍራሟ ናት አይደል .... ውይይይይ 6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ወድቃ ያለቀሰችው አይረሳኝም ... ቅቅቅቅቅቅ ግን በስተት ነው ተብሎ ተስተካክሎላታል መሰለኝ .... የኔ ባች ናት .... ከማህደረ ገ /ትንሳኤ ጋር ሆነን ... ብዙ ብዙ ትዝታ አለን ... ከወይንሸት ጋር
የት ይሆን ያለችውውውውውውው
እረ ያለማየሁ ባንቲ ልጆችስ ... እነ ኤልሳ ትግስት ወዘተ ... እስኪ የሚያውቃቸው ይተንፍስብንንንንንን

ቸር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA

_________________________________________________________________________________________________________________________________________
የግልነስ
Joined: 03 Feb 2005
Posts: 768
Location: united states
Posted: Fri Sep 16, 2005 5:34 am Post subject: ስላምምም ለክ /መንግስቶቸ
________________________________________
አደቆርሳና ባለሱቅቅ በትዝታ ይዛቸሁኝኝ ወደ ወዩ ነጎዳቸውው ባለሱቅቅ የጠፋቸብህ የሲት ስፓርተኛ ዝነኛዎ ከካስ ሚዳ የማትጠፋው ለመለም በረሂ ናት አሁንን ያለቸው ጀረምን ነው ሊላዋ በአክሮባት የታወቀቸው ባልሳሳት ምህረት ርሶም ናት እስቲ ቁርንፍድዩ እርጂኝኝ ባክሽ ሊሎቸንንም ሶሪ ልቢ በዚህ አምድ ላይ ጠፈቶ ስልክክ መደወል ረሳው ስሞኑን ደውላለው በጣም ነው ድምፅሽንን ለመስማት የጋጋሁት ብታዩ ቀልቢ ለጊ , ዝምታ , ፖስታ ቢት ስፈሪ ምነው አደፈጣቸውው ብቅ በሉና እንጫውት የወዩንን ትዝታ ከዛም አንድ ቀንን ሆ ብለንን ተነስተን ያቺን ራስብሩ እናቀናለንን በተረፍ እንግዲህ ባለሱቅና አደቆርሳ አትለዩን ቁርንፍድዩም እንደዛው
በርቱልኝኝ ካይን ያውጣንን የወዩ አምላክክ
የናተውው የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ

Locked

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”