የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 01 Apr 2013 09:12

የምናከብርህና የምንወድህ ወንድማችን አንፈራራ ሰላም ላንተ ይሁን ምክርህና ተግሳጽህ በሰዓቱና በቦታው በመሆኑተንደወትሮው ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርብልሃለሁ::
ብዙ ጊዜ ሊያጋጥም እንድሚችለው አለመግባባት ቢኖርም ስሜታችንን እና ሃሳባችንን በግልጽ መተዋወቅ ግን ክፉ አይደለም::
የምወድህ ጎስሽክም ኢንዴሚን ሲንጀዴ !
ከመድረኩ ወርዳለሁ ስትል ከምር ደብሮኛል ምክንያቱም ያገናኘን ወንድማማችነታችን እንጂ የአመለካከት ልዩነታችን አልነበረማ::
የምወድህ ጎስሽክም በፍቅርና በወንድምነት አጠር አድርጌ ልንገርህና ኦሮሞ ነኝ ከሚል ሰው እንዲህ ያለ ሃሳብ በመንጸባረቁ አልፈልጋችሁም ብለህ መለየትህ በውነት ትክክል አይደለህም
ምክንያቱም እንኳንስ እኔና አንተ የአንድ አባት ልጆችም በሃሳብ ይለያያሉ ይህም ቢሆን ስህተት አይደለም::
ለምሳሌ ባለፈው ናይሮቢ የነበረህን ቆይታ ልንረሳው በማንችለው የፍቅር ታሪክህ ዙሪያ ስታጫውተን በልዩነቶች ላይ አንተ የነበረህ አቋም አሁን ከምናየው ጋር ያለው ልዩነት ትንሽ እንዳልሆነ ነው የምገነዘበው
ሆኖም ይሄ እንኳን በሂደት መማማርን በሃሳብ መግባባትን በልዩነቶች ማመንን ወዘተ የሚያሳይ ሲሆን ሁሉንም በመልካም ጎኑ ነው የምመለከተው::
እኔም ከአስርና ሃያ አመታት በፊት የነበረኝ አቋም አሁን በከፊል የለኝም
ባጭሩ አሁን በሃገራችን በየክልሉ ቋንቋቸው የስራ ቋንቋ የሆነላቸው ሁሉ የሙሉ ዲሞክራሲ ተጠቃሚዎች ሆነዋል ብዬ በጭራሽ አላምንም አይደሉምም ከዚህ የተነሳ በቋንቋ መናገር ብቻውን የዲሞክራሲ ባለቤት
አድርጎናል ብዬም አላምንም አላደረገንም :: በፈለክበት የኢትዮጵያ ስፍራ ብትሄድም ምንም ዲሞክራሲ የለም........
ታዲያ የኔ አመለካከት በቋንቋ መጠቀማችንን በፍጹም አይቃወምምኮ ይደግፋል እንጂ
ልዩነቱ የስራ ቋንቋ እና የመገልገያ ቋንቋ ላይ ነው
ይሄውም አንድ የወላይታ ተወላጅ የሆነ ሰው ኦሮሚያ ሲሄድ ማንኛውንም የስራ ጉዳይ ለማስፈጸም የሚገጥመውን የቋንቋ ችግር እስቲ እናስበው አንድ የኦሮሚያ ተወላጅ የሆነ ሰው ደሞ አማራ ወይንም ሲዳማ ክልል
ሄዶ ጉዳይ ለማስፈጸም የሚገጥመውን ችግር እስቲ እናስበው አስተርጓሚ ጋ ሄዶ በቱርጁማን አስጽፎ በቱርጁማን አናግሮ በቱርጁማን አስፈጽሞ ወዘተ ይሄ ነው እድገትን የሚያመጣው ? እኔ እላለሁ ይሄ ኢሃዴግ
ህዝባችንን አስመስሎ የሚጫወትበት የውሸት ፖለቲካ ነው ::
ብዙ መናገር ባያሻም የአህጉራችን መሰረታዊ ችግር ምንድርነው ብንል መልሱ ሩቅ አይሆንም
ከዚህ አኳያ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ወይንም የአህጉራችንን ችግር በመፍታትና በእድገት ላይ ለመራመድ ያለኝ አቋም እንዲህ ነው::
አንድ ሃገር በሃምሳ ብሄሮች ሃምሳ የስራ ቋንቋ ኖሯት ብሄራዊ እድገት ታድጋለች ማለትን ለኔ የሚገባኝ ነገር አይደለም ስለዚህ ማንም ሰው ከተማረው ትምህርት እና ከሌሎች ሃገሮች ካገኘው ልምድ የተሻለ ዘዴ

ምንም ሊያውቅ አይችልምና አንድ ሃገር የብሄሮች ፍጹም መከባበርና መደጋገፍ መሰረት ሆኖ አንድ ብሄራዊ ቋንቋ ሊኖረው ይገባል ብዬ በጽኑ አምናለሁ::
ይሄ ማለት ደሞ የቋንቋ ጭቆናና አንተ እንዳልከው ተጭኖብን ተገደን ወዘተ የሚል ስሜት በሌለበት በመላው ብሄራዊነት መተማመን ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማረጋገጥ ነው::
ይህ የኔ የአደቆርሳ አቋምና አመለካከት ሆኖ ሳለ ካንተ ጋር በሃሳብ ስለተለያየን መድረኩን ትተህ መሄድህ ለምንድር ነው ?
ይህ ልዩነት የሚቆመው እኔና አንተ በእውነት ተወያይተን ስንስማማ ወይንም ስንተማመን ብቻ አይደል እንዴ ?
እኔ በበኩሌ ከማንም ወንድሞቼ ጋር በሃሳብ ላልግባባ እችላለሁ ባለቺኝ ችሎታ ለመተማመን እወያያለሁ እማራለሁ ከቻልኩም አስተምራለሁ እንጂ በሃሳብ አልያም በአመለካከት ልዩነት ወንድሞቼን አልለያቸውም::
ጎስሽክም በሃሳብ አለመግባባት መለያየትን የሚያመጣ ሊሆን አይገባውም ይልቁንም ለመማማር እንጂ
ይሄ ቤትኮ የአንድ አመለካከት መስመርተኞች ቤት አይደለም የብዙ ወንድማማቾች የጋራ መቻቻልና የፍቅር ቤት ነው ሃገራችንስ እንዲህ ተቻችለን አይደለም እንዴ የምንኖረው ?
ስለዚህ ኢንዴሚን !
ሌላው ኦዶ በተናገረው ላይ ( በነገራችን ላይ ኦዶ ኪያ አመሰግንሃለሁ እንኳን ደህና መጣህ )
አንተ እንደገመትከው አፋን ኦሮሞ ብሄራዊ ቋንቋ ይሁን አላልኩም ኦዶም አጻጻፉ እንደዛ ይመስላል እንጂ አይደለም ምናልባት ስለ ኦሮምኛ ቋንቋ ስፋትና ጥልቀት የጻፍኩትን በማስተዋል ይመስለኛል ::
ስለዚህ ጎስሽክም ቅሬታህን ትተህ ከኛ ከወንድሞችህ ጋር ባትለይ ደስ ይለኛል ምክንያቱም እወድሃለሁ !
አክባሪህ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 01 Apr 2013 12:07

Sorry,my,keyboard,didn't,work.i,will,by,soon.can't,make,space,and,some,of,keys are,not,working.

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 01 Apr 2013 23:09

እናንተ
ዛሬ ተሳካልኝ በአማርኛ መጻፍ ቻልኩ
ወንድሜ አንፈራራ ስለ-አስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ
አደቆርሳሳሳሳ.... እንደምን አለህ ወዳጄ ወንድሜ
አቤት ዛሬ ልወርድብህ ምላሴን አሹዬ ነው የመጣሁት
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቻለው!!
ዛሬም እንደወትሮው ቢዚ ብሆንም.... ውይይታቹ ስቦኝ... ገረፍ ገረፍ አድርጌ አንብቤአቹ ሳበቃ... ይህችን የራሴን እምነት ጣል ባደርግ ብዬ መጣሁ
በቅድሚያ የጎሳን ስሜት እንደምጋራ በአጽኖት እና በግልጽ ልገልጽ እውዳለሁ::
ይህንን የምለው...
“በመላው ሃገሪቱ ያለውን ወጣት ኃይል ወደ አንድ ብሄራዊ የቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ለመመለስ እጅግ ከፍተኛ የቤት ስራ እንደሚሆን ልንጠራጠር አይገባንም::”
የምትለዋን አባባል ካየሁ በሃላ ነው
እኔ በኢትዮጵያ ሁለት ብሄራዊ ቋንቋ ቢኖር የምስማማ ጫጩት ነኝ
ለምን? ብሎ ህዝበ- አንድ አገር አንድ ህዝብ አንድ ቋንቋ አንድ ኃይማኖት... ሲጮህ ተሰማኝ
ለምን ተሰማህ ብትሉኝ.... ብዙ ጊዜ ይህ ጩሀት ሲጮህ..... ካለሁበት አገር ድረስ.... እንደ-የገደል ማሚቱ.... በተራሮች ቅብብል
ከታቦር ተራራ ተነስቶ.... በሃኪም ጋራ አድርጎ... ከዝቋላ ተጋጭቶ.... ራስ-ዳጭን አናቱ ላይ ናኝቶ... ወደ-ኪሊማንጃሮ ጮሆ.... በኤቨረስት ተጋኖ... ድምጹና ጩሀቱ ስለተሰማኝ
አቤት ፍልስምና.. አለች.. ጣይቱ... ተፈላስሜ ሞቻለሁ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ኤኒዌይ... ይህ የኔ እምነትና ሃሳብ ነው
የቋንቋ መብትን... ከዲሞክራሲያዊ መንግስትነት ጋር ማወሻከት ግን አይገባም... ነገር ግን የቋንቋ መብት አንዱ የዲሞክራሲ መብት ነው የሚገለጽበት ባህሪ ይመስለኛል
ብዙሃኑ ሃሳቡን ከደገፈው.... ዲሞክራሲ ማለት ደሞ የብዙሃን ምርጫ ነው ከተባለ....
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደሞ አንድ አንድ ድምጽ አለው ካልን
ውሳኔውን ለህዝቡ ከተውነው
እርግጠኛ ነኝ.... ሃገሪቱ ሁለት ቋንቋ እንደሚያስፈልጋት
አደቆርሳዬ እንዲህ ብልህ ጎሳን ጠይቀሃል
ለመሆኑ አሁን አንተ ያለህበት ሃገር የብዙ ብሄሮች መኖሪያ መሆኑን አታውቅ ይሆን ? ነገር ግን የስራና ብሄራዊ ቋንቋቸው ሥንት ነው ? የዚህን ጥያቄ ሳትመልስልኝ እንዳትቀር አደራ እልሃለሁ ::
ጎሳ ወንድሜ ለምን ይህችን ጥያቄ ሳይመልስ እንዳለፋት አላውቅም እንጂ... እኔው እራሴ ልሞክር
ሄጄ ባላውቅም... ካናዳ ውስጥ ሁለት ቋንቋ (ብሄራዊ) እንደሆነ የሰማሁ መሰለኝ.... ጋሽ ሞፍቲ ዝርዝሩን እና እውነታውን ቁጭ ቢያደርግልን ያስታርቀናል
የኔ ሶርስ እንዲህ ይላል
Canada is officially bilingual under the Official Languages Act and the Constitution of Canada that require the federal government to deliver services in both official languages.
ሄጄ ካየሁባቸው ቦታዎች ዝርዝር ውስጥ ደሞ....
ለምሳሌ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ (ምንም የአሜሪካ ብሄራዊ ቋንቋ እንግሊዘኛ ቢሆንም).... ሌሎች አምስት ቋንዎች የስራ ቋንቋ... እንደሆኑ (አማርኛን ጨምሮ) ያየሁ መሰለኝ
አንፈራራ እስኪ ይህችን አብራራ
In the United States, at the federal level, there is no official language, although there have been efforts to make English the official language. ተሳስቼ ይሆን
ደቡብ አፍሪካ ደሞ ብትሄድ... ወደ-9 ቋንቋዎች ኦፊሺያል የስራ ቋንቋ ናቸው.... ብሄራዊ ቋንቋ ስለመሆናቸው ባላውቅም...
እንላቹ... ለማለት የፈለኩት
ስለዲሞክራሲ... ሰባዊ መብት... ቅብርጥሶ ጉዳይ የምንስማማ ከሆነ
በተጨማሪ አንድ ሰው አንድ ድምጽ አለው ካልን
ይህ አርስት ይህንን ያህል የሚያጋጨን አይሆንም ይመስለኛል
አይመስላቹም
ጎሲቲ... በዚች የተነሳ... ይህንን የሞቀ ቤት ጥለህ ብትወጣ..... ዋርካ ላይ ያለበስኩህን ቡሉኮ ነው ምገፍህ (የትልቅነት ማዕረግ)
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በተረፈ
እንዲህ ሲመቸን እየመጣን... እናጋጫለን
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሌሎች ባይሊንጉዋ ሃገሮች ደሞ
Paraguay, 48% of its population is bilingual in Guaraní and Spanish (both official languages of the Republic),
Puerto Rico's official languages are Spanish and English, yet 85 percent of its inhabitants reported that they did not speak English "very well."
Belgium has three official languages:
Cameroon : English & French (official)
Chad : Arabic & French (official)
Djibouti : Arabic & French (official) + Somali & Afar.
Somalia : Somali & Arabic (official).
South Africa : Afrikaans, English, Ndebele, Northern Sotho, Sotho, Tswana, Swati, Tsonga, Venda, Xhosa, Zulu and immigrant languages from Asia, Africa and Europe.
እያለ ይቀጥላል
ስለዚህ በዲሞክራሲ መብቶች ከተስማማን... የቋንቋ ቁጥር መብዛት አያጣላንም
የቀኝ ወይም የግራ አክራሪ ሆነን እራሳችንን ካላቀረብን
ይህ የባለሱቅ አቋም ነው
ለሃገሩ የሚመኘውም ይህንኑ ነው
ቺርስ

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 02 Apr 2013 04:23

የምወድህ ባለሱቅ ያቀረብከው ሃሳብ እውነታን ከመረጃ ያዋሃደ ነው
ግን ለምድር ነው ካናዳ ውስጥ ፍሬንች የሚነገረው ? ማለቴ ከቅኝ ጋር የተያያዘ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ስለመጣብኝ ነው

እኔ የሚመስለኝ ካናዳ ሙሉ በሙሉ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ እንደሆነች ነበር ::
በነገራችን ላይ ፍሬንች በሌሎች በየትኞቹ ሃገሮችስ ይነገራል ? እባካችሁ መልሱልኝ
ምናልባት በተለይም በአፍሪካ የፈረንሳይ ቅኝ በሆኑ ሃገሮች የሚነገርባቸውን ሳይመለከት ማለቴ ነው::
ባለሱቅ በድጋሚ ከልብ አመሰግናለሁ::ወዳጅህ አደቆርሳ

ጎሳ
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 13 Mar 2013 02:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ጎሳ » 02 Apr 2013 06:56

ሰላም ለሁላችንም!
ውድ አንፈራራችን ስለ በሳል መልዕክትህ እጅግ አመስግኜሀለሁ:: በእርግጥ እንዳልከውም በሁለት ሰዎች መካከል ትንሽ አለመግባባት ሲኖር ምንም እንኳ የተሳሳተው ሰው በግልጽ ቢታወቅህም በዚያን ጊዜ ዘለህ ገብተህ ተሳስተሀል ብትለው ንገሮችን ከማቀዝቀዝ አንጻር ብዙ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ተገንዝበህ ተረጋግተህ ጉዳዩን በትዕግስት ተከታትለህ መናገር የሚገባህን ሰዐት መርጠህ መልዕክትህን ማንንም በማያስቀይም መልኩ መናገርህ ብስለትህን ነው የሚያሳየው እላለሁ:: በድጋሚ እግዚአብሔር ይስጥልኝ::
የተወለድኩት ከቦሬ ከተማ ትንሽ ወጣ ብላ በምትገኘው አኖ ዋቴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው:: የአስራ ሁለት አመት ልጅ ሆኜ ነበር ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ጎሳ የገባሁት:: እዚያም ሞፊቲ እንደሚያውቀው ውሎ አዳራችን ከከተማ መጥተው እዚያ ክሊኒክ ውስጥ ከሚሰሩት ከከተማ (የአማራው ብሔር ተወላጆች) ልጆች ጋር ነበር:: ከዚያም አዋሳ አዲስ አበባ ሮቤ እና ናይሮቢ አውስትራሊያ:: ይህንን ታሪክ ከዚህ በፊት የጻፍኩት ስለሆነ ብዙዎቻችሁ ታስታውሱት ይሆናል::
ቦሬ አንደኛ ክፍል ስገባ አንድም የአማርኛ ቃል አላውቅም ነበር:: የህጻንነት ዕድሜዬም ተደምሮበት ቋንቋውን አለመቻሌ አንደኛ ክፍልን ለመድገም ተገደድኩኝ:: በሁለተኛውም አመት በግፊ አይነት እንዳለፍኩኝ ያኔ ስም ጠሪዬ የነበረው ወንድሜ ካደኩ በኌላ አጫውቶኛል:: ሶስተኛ እና አራተኛ ክፍልን በመካከለኛ ውጤት እያለፍኩ አራት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ክፍሎች ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ነበር ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የገባሁት:: ይህንን እዚሁ ላይ ልተው::
ባለፈው ጊዜ ያጫወትኳችሁን የጽጌን ታሪክ በመጽሀፍ መልክ ለማሳተም ሳስብ ረቂቁን እንዲያነቡልኝ ለተወሰኑ ሰዎች ሰጥቼ ነበር:: ያለቀውን ባይሆንም እስከተወሰነ ቦታ የጻፍኩትን ከመካከላችሁ ለተወሰኑት ሰዎች ልኬ አስተያየታችሁን ጠይቄ ያመናችሁበትን ጠቁማችሁኛል:: ከዋርካ ውጭ በግል ለማውቃቸው ሙያው አላቸው ብዬ ላመንኩባቸው ሰዎችም ረቂቁን ሰጥቼ አስተያየት ጠይቄ ነበር:: ከእነኚህ ሰዎች መሀል ሁለቱ ከተማ ተወልደው ያደጉ የሀይስኩል የቋንቋ መምህራን ሲሆኑ አንዱ ከምንም ፖለቲካ ነጻ ሆኖ በራሱ አለም የሚኖር በቋንቋም ሆነ በባህል ዕውቀት ከኔ ይሻላል ብዬ ላመንኩት ለአስተማሪው ወንድሜ እና አንድ ግብርና ውስጥ ለሚሰራው ጓደኛው ነበር የላኩኝ:: ሁለቱ የከተማ ልጆች(መምህራን) ከአንዳንድ የቋንቋ እርምት በስተቀር እንዳለ እንዲታተም ሲመክሩኝ የወንድሜ እና የጓደኛው ሀሳብ ደግሞ ለየት ያለ ነበር:: በፍቅር ታሪክነቱ ቢወዱትም ባለፈው ስርአት እዚያ ቦሬ አካባቢ በሚኖሩት የጉጂ ህብረተሰብ ላይ ምንም እንዳልደረሰ አድርጌ ያቀረብኩት ሀሳብ ልክ እንዳልነበር ሲነግሩኝ እኔም ያልጠበኩት ነገር ነበር የሆነብኝ:: በተለይ ወንድሜ "አንተ ትላንት ከከተማ ልጆች ጋር በየሻይ ቤቱ የምትገባበዙትን አይተህ ነው እንጂ ከነበረው እውነታ ተነስተህ አይደለም:: እኔ ያኔ በኢህአፓ ስም ልገደል ከሞት አፋፍ ከተረፍኩ ወዲህ ስለ ፖለቲካ ምንም ማውራት ስለማልፈልግ ግባና አጎትህን ወይንም እናትህን ጠይቅ: ምን ያህል ነገር ውስጥ እንዳለፉ " ሲለኝ ልክ በቅርብ የተደረገ ትልቅ ነገር እንዳለ አይነት ነበር የደነገጥኩኝ:: በጭራሽ ያላሰብኩት ነገር ነበር:: ከፍርሀት እና ከአክብሮትም ጋር ከዚህ በላይ ከወንድሜ ጋር ማውራት ስላልቻልኩ ረቂቁን ተቀብዬው ወደ ቤት አመራሁ::
ከሰአት በኌላ ነው...ከእናቴ ጋር የምትኖረው ባለቤቴ ቡና እያፈላችልን ነው:: አራት ብቻ ነን ቤት ውስጥ ንጉሤ ከሚባል በዕድሜ ብዙ ከማንበላለጥ ወንድሜ ጭምር:: ዝር የሚል ልጅ የለም ባከባቢው...የሆነ ርካሽ ኳስ ገዝቼላቸው ስለነበር ጨፌ ሊጫወቱ ሄዷል:: ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ ስላመንኩ ወንድሜ ጠይቃት ያለኝን ጠየኳት
"አዮ....እሲ አማርት ዱር ጉጂ ራክቴ ቤቲ? አቲ ማን ቃባታ? "
"ሆኦ ቁባ....አማ ማን ጎቻፍ ናጋፋታ? ዻጤ(dhaxxee) ዺጋ(dhiiga) ባሳታ? " ብላ ሳቀችብኝ:: እንደምንም አግባብቼያት ትነግረኝ ጀመር::
መጀመሪያ ላይ የነገረችኝ አጠቃላይ የሆነ ነገር ነበር:: ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ባካባቢው ሲታይ ወይ ከብት ሊወስዱ ወይ ሰው ሊያስሩ እንጂ በሰላም እንደማይመጡ:: እኔ አሁን የነገረችኝን በዝርዝር አላስቀምጥም:: ታላላቅ የከተማው አባቶች ናቸው የተባሉት ሁሉ ስልጣን እንክዋን ሳይኖራቸው ህዝቡን ይዘርፉ ይገርፉ እንደነበር...ከሁሉም ከሁሉም ባለፈው ያነሳሁት የባሪሶ ቶኖሪ( አጎቴ ነው) ገንቦ አሸክመውት በጀርባው ጠላ እየተጠመቀ አዲስ አበባ ድረስ የነዱት እና ተመልሶ ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ሚስቱ ልትወልድ እየተጠበቀች ድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ሊነዱት ሲይዙት ሚስቱ እንባ አፍስሳ ራቁት ሆዷን ገልጣ እያሳየቻቸው ስትለምናቸው ገፍትረዋት ጀርባዋን በጉማሬ መትተው እየገፈተሯት እንዳባረሯት ስትነግረን ከኔ ቀድማ አማራዋ ባለቤቴ ነበረች ያለቀሰችው:: ስለፖለቲካ ምንም ግድ የሌለው ንጉሴ እንክዋን የተናገረውን እዚህ ላይ ብጽፍ ሞፊቲ አያምነኝም::
እኛ በህይወት እያሉ ለተሰቃዩት ይህን ያህል አዝነን እንባ ካፈሰስን ዘመድ ወዳጆቻቸው በግፍ የተገደለባቸው የሌሎች አከባቢዎች ኦሮሞዎች ከዚህ ህዝብ ጋር ምንም ላለመነካካት ቢፈልጉ ይደንቃችሁ ይሆን? ይገርመን ይሆናል:: ምክንያቱም ጊዜው ረዥም ነዋ:: የዚያን ስርአት አራማጆች አሁን በህይወት ላይኖሩ ይችላል:: ግን ደግሞ አንድ ስህተት ተሰራ...ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኌላ የራሱን ህይወት ለማቆየትም ይሁን ለተገፋው ህዝብ በማሰብ ያንን ሊደርቅ የተቃረበ ቁስል መልሶ ነካካው:: ለረጅም ጊዜ ሳይሰሙ የቆዩትን ዘግናኝ ታሪኮችን ሆን ብሎ በማውጣት ህዝቡ ያለፈውን እያስታወሰ ድጋሚ እንዲያለቅስ አደረገ:: ተረጋግቶ የነበረው የሰው ስሜት ድጋሚ ተሸበረ:: በዚህ መሀል እንደ ኦነግ አይነቶቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሞ ህዝብ አዕምሮ ውስጥ ትንኝ እንኳን የማይሞትበትን ኦሮሞዎች በኦሮሞዎች ብቻ የሚተዳደሩባትን ከገነት የማታንስ ሉአላዊት ኦሮሚያን በሰፊው ገነቡላቸው:: ለዚህም እንዲመቻቸው እነሱም የራሳቸውን የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት ጀመሩ:: በየስብሰባው በየአዳራሹ የምኒሊክ እና ሀይለስላሴ የግፍ ታሪክ ይነበብ ጀመር:: ያ ዘመን ዛሬም ያለ ይመስል ሰው ነጻነትን ቶሎ ሊቀዳጅ ቸኮለ:: ታዲያ ሰው እዚያ ደረጃ ላይ ሲደርስ ጎሳ ከምንም አልነበረም:: ያኔ..1984 አንድ ጓደኛዬ የሙዚቃ ዝግጅት አለ ብሎኝ አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ይዞኝ ሲሄድ ያየሁትን ማመን ነበር ያቃተኝ...ዘፈን ሲዘፈን ተያይዞ በጅምላ የሚላቀስ ህዝብ:: ምን እንደሚያስለቅሳቸው ስላልገባኝ ፈራሁ...ጓደኛየም አይኑን ይጠራርጋል:: ወጥቼ ወደ ቤቴ ተሸበለልኩ:: ድጋሚ እዚያች ቦታ ላለመድረስ ለራሴ ቃል ገባሁ:: ታዲያ እናቴ ይህንን ካጫወተችኝ በኌላ ያ የተግባረ ዕዱ ለቅሶ ነበር ወለል ብሎ የታየኝ:: ለምን ያለቅሱ እንደነበር በመጠኑም ቢሆን ተረዳኌቸው::
ወደ አውስታራሊያ ስመለስ ስለ ኦሮሞ የተጻፉትን ታሪኮች እንተርኔት ውስጥ ፈልጌ ማንበብ ጀመርኩ:: ግማሾቹ ጸሀፊዎች ልክ እንደ እኔው ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው በሀይለ ቃል ይጀምራሉ:: እነሱን ብዙ አላነብም:: በተቻለኝ መጠን ገለልተኛ ነው ብዬ ያመንኩባቸውን የተወሰነውን ያህል አነብና መቀጠል አቅቶኝ እተዋለሁ:: ባለፈው ታሪክ የተነሳ ድፍን ጥላቻ ውስጥ እንዳልገባ በመፍራት ማንበቡን አቆምኩኝ::
ሰዎች... እንደ ዴሞክራቶች ሆነን ማሰብ እና መወሰን ብዙ ላይከብድ ይችላል:: ነገር ግን when you put yourself in their shoes, things are different. የነሱ ህመም ይሰማሀል:: ችግራቸውን ትረዳለህ:: ሰው ነሀና አስተሳሰብህ ይቀየራል:: ታዝንላቸዋለህም::አይደለም ሌላ ነገር በኦነግ ላይ የነበረኝን አስተያየት እንኳ በመጠኑም ቢሆን ለመቀየር ተገድጃለሁ:: በትልቅ ጭቆና ውስጥ ያለፈን ህዝብ ከዚያ ግፍ አወጣለሁ ብሎ ጫካ ቢገባ ጥፋተኛ አትለውም:: እኔ ባልደግፈውም መገንጠል በመፈለጉ ዳግም አልፈርድበትም ከመገንጠሉ ይልቅ የሁሉም ሰው መብት ተከብሮ አብሮ መኖሩ እንደሚሻል ለማሳመን የበኩሌን እጥራለሁ እንጂ:: እና በዚህ ሙድ ውስጥ ሆኜ ነው የአደቆርሳ የአንድ ብሄራዊ ቋንቋ ትምህርት ጉዳይ ያየሁኝ:: ስለ ናይሮቢ እና ጽጌም ጉዳይ ስጽፍ አንድም ቀን በአንድ ቋንቋ አምናለሁ ብየ አላውቅም:: ስብከቴም በመከባበር እና በመቻቻል ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን መመስረት እንጂ የአንዱ ቋንቋ ተረግጦ ያንዱን ይዘን የምንዘልቅበትን ኢትዮጵያን አልሰበኩም:: በአስተሳሰብ ደረጃ መለያየቶች እንዳሉ ባምንም እውነቴን ነው ባሁኑ ጊዜ ባንድ ቋንቋ የሚያምን ሰፋ ያለ አስተሳሰብ ያለው ኦሮሞ ስላላጋጠመኝ የአደቆርሳ ሀሳብ በጣም ነበር የገረመኝ:: እዚህ ላይ መናገር የማይገባኝን ነገር በደም ፍላት ተነሳስቼ በመናገሬ ወንድሜ አደቆርሳንም ሆነ ቤቱን ይቅርታ ለመጠየቅ እገደዳለሁ:: አንዳንዴ የዘር ጉዳይ ዛርህን ያስነሳብሀል ቅቅቅ:: ስለመልካም ስነምግባሩ ደግሞ ወንድሜ አደቆርሳን ላመሰግነው እወዳለሁ::
መጨመር የምፈልገው ሌላው ጉዳይ ... ዛሬ በየብሎግ ሩም እና ፎረሙ ለኦሮሞ ህዝብ የሚናገር ሰው የሚወርድበትን ስድብ ለማየት ቀላል ነው:: ስንት ነገር የደረሰበት ህዝብ ዛሬ ቀን ወጥቶለት( ሙሉ ዴሞክራሲ አግኝቷል ማለቴ አይደለም) ቢያንስ ልጆቹ በቋንቋው ሲማሩ እንደ ትልቅ ነገር መቆጠር የለበትም:: ዋርካ ፖለቲካ ውስጥ ተድላ ሀይሉ በመባል ኒክ የሚታወቅ እና የክብረመንግስቱም ቤት ውስጥ ትልቅ አክብሮት የምንሰጠው ሰው አፋን ኦሮሞ በቁቤ እንዲጻፍ አስተዋወቀ ብሎ ያመነውን ሰው ብቻ ሳይሆን በድሮ ጊዜ በኦሮሚያ አካባቢ ትምህርት ቤት በመክፈት ዘር እንኳ ሳይለዩ ያስተማሩትን ሚሺነሪዎች በናዚነት ነበር የፈረጃቸው:: ስንቶቻችሁ አሁንም በአንድ ቋንቋ እንደምታምኑ አላውቅም:: እኔ ግን ሌላው ዴሞክራሲ ቢቀርባቸው የኦሮሞ ልጆች ቢያንስ በቋንቋቸው የመማር መብታቸው መቼም ሊነፈጉ አይገባም ብዬ አምናለሁ:: ከላይ የጠቀስኩት የአንደኛ ክፍል ታሪኬን እዚህ ላይ ላንሳ:: በእርግጥ በራሱ ቋንቋ እየተማረ የሚወድቅ ተማሪ የለም ማለቴ አይደለም:: እርግጥኛ ሆኜ የምናገረው እኔ ግን የሚባለውን ነገር ብሰማ እና በሚገባኝ ቋንቋ ብማር አልወድቅም ነበር እላለሁ:: የአንደኛ ደረጃ መምህርም ሆኜ ለአጭር ጊዜ ሱኬ ላፍቶ አስተምሬያለሁ:: ጥያቄ ሲጠየቁ ምን ያህል ያለፍርሀት እንደሚመልሱ አይቻለሁ:: እኔ ያኔ ተማሪ ሆኜ አስተማሪ አንድ ጥያቄ ሲጠይቅ መልሱን እያወቅኩኝ አማርኛ ተሳስቼ ይሳቅብኝ ይሆናል ብዬ ብዙ ጊዜ እጅ ላውጣ አላውጣ እያልኩ ልቤ በፍርሀት ከበሮ እንደመታ ነበር የምውለው:: የእንግሊዘኛ ጊዜ ሲሆን ግን የሚስቅብኝ ሰው ስለማይኖር እና የምሳሳተውም ነገር ስለማይኖር መልስ ለመመለስ አንድ ቁጥር እጅ የማወጣው እኔ እንደሆንኩ አንድ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠን የተማርን እህታችን አይፋ ለእውነት ትመሰክርልኛለች ብዬ አምናለሁ ይህንን ሩም ገብታ ካነበበች:: የምትችለው እንግሊዝኛ ብቻ ስለሆነ ነው እንዳትሉኝ ሁሌ በደረጃ እንደማልፍም አይፋ እራሷ ትመሰክርልኛለች:: እና በራስ ቋንቋ መማርን የመሰለ ነገር የለም:: በራስ የመተማመን ስሜትን ይሰጥሀል::
ከአንፈራራችን በሳል ምክር በተጨማሪ ያረጋጋኝ እና ወደዚህ ቤት የመለሰኝ ነገር የባለሱቅ መልዕክት ነው:: ያለበሰኝን ካባ ከገፈፈኝ በጣም ቀልዬ በየመንገዱ የምንከራተት ነው የመሰለኝ ቅቅቅ:: ወንድሜ ባለሱቅ እኔ የረሳሁትን ጥያቄ በመመለስህ ገበያህ ይብዛልህ ሌላ ምን እላለሁ:: እኔም መመለሱ አቅቶኝ ሳይሆን በተረጋጋ ስሜት አልነበረም እጽፍ የነበረው:: ፖለቲካ ሼይጣን ነው ቅቅቅ:: አንተ ባልከው ላይ ትንሽ ብጨምር
ቤልጅየም : Dutch, French & German
ስዊዘርላንድ: German, French, Italian & Romansh
ስንጋፖር English, Chinese, Malay & Tamil
ስፔይን : Catalan/Valencian, Basque, Galician & Aranese
ፊንላንድ Finnish and Swedish
የታላቋ ዴሞክራሲ አገር ህንድ ስፍር ቁጥር የለውም: ሀያ ሁለት በህግ የተደነገጉ ኦፊሽያል ቋንቋዎች አሏት:
ኔዘርላንድስ Dutch, Frisian
እነኚህ እንግዲህ ከህንድ በስተቀር ሁሉም ከበለጸጉ አገሮች የሚመደቡ ናቸው:: ያልበለጸጉትን ትቼያቸዋለሁ:: እንግዲህ ሀሳቤ ይህንን ይመስላል:: መቼም ቢሆን ተመችቷቸው በኦሮሚኛ የሚማሩት ህጻናት ያንን ዕድል እንዳይነጠቁ ምኞቴ ነው::
ተባረኩልኝ::

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 02 Apr 2013 14:47

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::
በቅድምያ ውድ ባለሱቅ እንኳን በሰላም መጣህ::

በዚህ ሁሉ ውይይት ውስጥ ያለመቀላቀሌ ቁጭት ውስጥ ከቶኛል::ኬይቦርዴ ውስጥ ልጆች ውሃ ደፍተውበት ለመጻፍ ቸግሮኝ ነበር::
አሁንም በብድር ኮምፒውተር ነው የምጽፈው::ባለቤቴ ብትሞት የሷን መጻፍያ አታስነካኝም::ኢሳት voa ዶቾቬሌና ሌሎችም የፖለቲካ ጩሀቶች ስለሰለቻት የራሷ ኮፒውተር ላይ የሚቀሩ እየመሰለታ
እዛው ያንተን አፈንዳው ብላ በዚህ ከተለያየን ቆይተናል::አሁን እሷ ወጣ ስትልልኝ ሳብ አድርጌ እየጻፍኩ ነው::

የነጎሳ ውይይት በኔ አስተያይ ለመግባባት ይረዳናል እንጂ ይህን ያህል የሚያራርቅ እንዳልሆነ ግልጥ ነው::እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች እንደመፈጠራቸው መጠን በሰል ብሎ በረጋ መንፈስ
መነጋገሩ አውቂነትና ብልህነት ነው::

የአደቆርሳን ሃሳብ እኔም ቆየት ባሉት ግዜያቶች ያንጸባረኩ ሲሆን በዚህ ነገር ብዙ ውይይቶች ማድረጋችንም ይታወሰኛል::አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ግን የህዝቦች ዲሞክራሳዊ መብት
እንደፍላጎቱ መከበር እንዳለበት እስካመንን በቋንቋው የመናገር የመጻፍና የመስራትን መብትም
እንደፍላጎቱ መጠበቅ ይገባናል ባይ ነኝ::እዚህ ላይ አደቆርሳም ልዩነት አለማሳየቱን ተረድቻለሁ::የስራ ቋንቋ በሚለው ነገር ብቻ ላይ ነው መግባባቱ ያልታየው::

ይህም ቢሆን አሁን ከምናየው አንጻር ብዙም ችግር የሚያመጣ መስሎ አይታየኝም::እዚህ ያለሁበት ሃገር ሁለት የስራ ቋንቋ እንዳለ እናንተም ገልጻችሁታል::
የኪዩቤክ ግዛቶች በፍሬንች ቋንቋ የሚጠቀሙ ሲሆን ቀሪው የካናዳ ግዛት እንግሊዘኛውን ይሰራበታል::ያም ሆኖ ግን መንግስትም ሆነ የስራና የተለያዩ ማመልከቻዎችን ለማቅረብ የትኛውም ግዛት ላይ በራስህ ምርጫ ቋንቋውን መጠቀም ትችላለህ::ለምሳሌ ፍሬንች ተናጋሪዎቹ የኩቤክ ግዛት ሄደህ ስራ
ለመስራት ብትፈልግ ና እንግሊዘኛ ብቻ የምታውቅ ከሆነ ማመልከቻህን በ እንግሊዘኛ ማቅረብ ትችላለህ ማለት ነው::ችግሩ ፍሬንች ተናጋሪዎች ጋ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ሆነህ ስራ ታገኛለህ ወይ? የሚለው ነው::
በመሆኑም የካናዳ መንግስት ሁለቱንም ቋንቋአዎች እንድታውቅለት ያበረታታል::እንግሊዘኛ ተናጋሪ በሆኑ ግዛቶችም ትምህርት ቤቶች በ ኢለመንተሪ ደረጃ መሰረታዊ የሆነ የፍሬንች ቋንቋን ማስተማራቸውም ይህን ችግር ለመቅረፍ ይመስላል::
ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም በጥልቅ ሁለቱንም ቋንቋ ልጆቻቸው እንዲማሩ (በፍሬንች አካባቢ እንግሊዘኛን በ እንግሊዘኛው አካባቢ ደግሞ ፍሬንችን) ይሞክራሉ::
ባጠቃላይ ግን የተመቻቸ ሁኔታ ስላለ በስራም ሆነ በመሳሰሉት ሁኔታዎች ሰዎች በሁለቱም ቋንቋ ተናጋሪዎች የመኖር ና የመስራት መብት አላቸው::

የኦሮሞ ልጆች በቋንቋቸው መናገር መጻፍ የመሳሱሉት ሁሉ መብቶች እንዲኖራቸው ሙሉ ፍላጎታቸው በመሆኑ ይህ ያለምንም ተጽኖ ሊኖራቸው ይገባል::
ቀደም ሲል ስንነጋግረበትም የነበረው የፖለቲካ ትርፍ እንዳይሆን በሚል እንጂ ይህማ ለዲሞክራሲ የሚታገል ሁሉ ሊቀበለው የሚገባና የህዝቦችን መብት የማክበርም
ሃይል ጭምር ነው::

ውድ ጎሳ በመጨረሻው ላይ የጻፍከውን አይቼ ግራ ግብት ነው ያለኝ::ምክንያቱም አንተ ከተማ ውስጥ ሻይ እየጠጣህ ምን ታውቃለህ ብለው ነገሩኝ ያልከው ነው::እኔም ብሆን በፍቅር ተከባብረን ተዋደን ቤተሰቦቻችንም እንደዚሁ ተዋደውና ተከባብረው መኖራቸውን እንጂ አንተ አሁን እንደምትለው የከፋ ነገር አልሰማሁም::
በ እውነት ለመናገር አንተ እራስህ ከማውቅህ በላይ ፍጽም ተቀይረህብኛል::ያለምክንያት እንዳልሆነም የተረዳሁት ይህን ጽሁፍህን ካየሁ በኋላ ነው::ንጉሴም የሆነ ነገር አለ ስትለኝ እራሱ በጣም ነው የደነገጥኩት::
ለማንኛው የሆኑና የተደረጉ ነገሮች ካሉ የዚህ ዘመን ልጆች ቂምን በመርሳት አንድ ሆነን በፍቅር የምንኖርበትን መንገድ መያዝ ይኖርብናል::
አንድ ነገር ትዝ አለኝ::እኛ ቤትም ጭሰኞች የሚባሉት እንደነበሩሰሰማለሁ::በመጨረሻ የደረስኩባቸው ነበሩ::ባላንበራስ ጃሎ ቤት ከጉጂም ከ አማራም ከወላይታም ነበሩ::
በተለይ ጋሽ ቡቴን እንእም ስለደረስኩበት የስጋ ዘመድ ያህል እወደዋለሁ::ጋሽ ቡቴ ከወላይታ ብሄር ነው::የባልቻ አባነፍሶ አሽከር ነበር ይባላል::በኋላ ላይ ነው ባልንበራስ ጋ የመጣው::በዛ እድሜው የማይልከውና የማያሰራው የቤትሰብ አካል አልነበረም::
እሱም ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ይሰራል ይለፋል አያማርርም::አባቴ በጣም ይወደው ነበር::ባላንበራስም ከሞቱ በኋላ በሴት አያቴ ስር ነበር::በኋላ ጋሽ ቡቴ ከኛ ቤት ከወጣ በኋላ በልመና ይተዳደር ነበር::
ሲሞትም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የአካል ችግር ደርሶበትም ነበር::ሁላችንንም አሳድጎናል::ከ አባቴ ትውል ጭምር ማለቴ ነው::እድሜውም የትየለሌ ነበር::
ብዙ እዚህ ማልናገራቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ::ስራቱ የሚፈቅድልህ ነገር አለ::የህዝቦችን መብት የሚያስከብረው ማ እከላዊ መንግስት ቢሆንም ህዝቦችም ለመብታቸው መናገር መጮህ
እምቢኝ ማለት አለባቸው::
የጋሽ ቡቴን ታሪክ ያመጣሁልህ የነበረው ስራት ከፍና ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ ሌሎችም ብሄሮች ተጎጂዎች ነበሩ ለማለት ነው::

ባጠቃላይ ግን ዛሬም ሃገሬ የሚያስፈልጋት ደረጃ ላይ አልደረሰችም ብዬ አምናለሁ::ሙሉ የመናገር የመጻፍ ነጻነት እንዲመጣና ዘረኝነት እንዲጠፋ እታገላለሁ::ብዙ ማያቸውብ አሳፍሪ ነገሮች
በሃገሬ ላይ ስላሉ እነሱ ጠርተው ለማየት ምኞቴ ነው::ይህ መድረክ እነዛን ነገሮች ለማውራት የሚፈቅድ ባለመሆኑ በተገቢው ቦታ እንወያይበታለን::

አንዳንዴ በቤታችን ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሲፈጠሩ ለወደፊትም ቢሆን በረጋ መንፈስ ብናያቸው መልካም ነው::ካልሆነም አለመወያየቱ ይመረጣል::

አደቆርሳ ስለ ጉጂ ብሄረሰብ ባህል እንዳንተ እዚህ ቤት ውስጥ የጻፈ አላየሁም::በዛም ብዙ ትምህርት አግኝተናል::በጎሳም በኩል በመጣው ሃሳብ ረጋ ብለህ በወንድምነት ለሰጠሀው ምላሽ ከምወድህ በላይ እንድወድህ አድርጎኛል::

ወንድሜ ጎሳ? የጋሽ አየለን ጉቦ መብ
ላት ለጸግሼት ነግሬ
ልህ (አማቹ ስለሆነ) አንተና እንኳ ቢያጣ ንጉሴንም ቢሆን እንደማይልቀው አስጠንቅቆሃል??????

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 03 Apr 2013 10:00

በጣም ደስ የሚል መንፈስ ተመለሰ በቤቱ

እሰይ ያገሬ ልጆች.... እንዲህ ነው መስማማት በልዩነት

ተመስገንንንንንንንን የናንተ ያረገኝ ጌታ

አደቆርሳዬ.... ካናዳ ለምን ፈረንሳይኛ ይነገራል ላልከው.... ብዙ ባላውቅም.... ለነገሩ ጉግል ብናደርግ ትክክለኛ ምክንያቱን እናውቃለን... ነገር ግን .. ሰሞኑን ከማነበው መጻፍ ጫፍጫፉን እንደተረዳሁት....
ካናዳን በቅድሚያ..... "አገኘኃት!... ባትጋሩኝ".... ያለችው ወይም.... የካናዳ ምድር ላይ መስፈር የጀመሩት አውሮፓውያን... በቅድሚያ ፈረንሳዮች ነበሩ..... ፀሐይ የማይጠልቅባት ታላቋ ብሪታንያ... እግርዋን ከአሜሪካ ወደላይ ዘርግታ..... እኔም ይገባኛል.... ማለት ከመጀመሯ በፊት....
በዚያ ዘመን.... አፍሪካን እንቀራመት ማለት ከመጀመራቸው በፊት
ከዚህ በላይ ምንም ልልህ አልችልም.... ነገር ግን ለመጨመር ያህል.... ፈረንሳይኛ... አንዱ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ እንደሆነ ... መቸም ሳታውቅ የምትቀር አይመስለኝም

አይበቃም

ጎሲና!..... አቤት ብንገናኝ የምናወራው ወሬ መመሳሰሉ......
ነገር ግን.... በሰአቱ የነበረውን እና ስራቱ የፈጠረውን ሲስተም.... በቤተሰቦቻችንና ባለፉት አባቶቻችን ላይ ሳይሆን...እንዲሁም በዚህና በዚያኛው ብሄረሰብ ላይ ሳይሆን
ሁኔታውን በፈጠረው እና . በነበረው የመንግስት ሲስተም ላይ ሊሆን ይገባል ይመስለኛል.....
ያ ሲስተም እንዳይደገም... ነው መታገል ያለብን
አንድ ህዝብ... አንድ አገር... አንድ ቋንቋ.. አንድ ኃይማኖት... አንድ ምናምን የሚባለውን አስተሳሰብ ነው በቅድሚያ .. ከውስጣችን እና ከውስጣቸው ማሰወገድ አለብን... በግልጽ በመነጋገር

አይመስልህም

ሞፍቲኮ ኪያ
ይገርምሃል..እንዳንተ አይነት ሰዎች ብዙ ገጥመውኛል.... በዚህኛውም በዚያኛውም ወገን
1993/4 ገደማ.... አንዱ የልጅነት ጓደኛዬ ምን አለኝ መሰልህ
ከዛሬ ጀምሮ ሁለተኛ በባዕድ ቋንቋ (አማርኛ) አላወራህም.... አልፅፍልህም (ደብዳቤ በጣም እንጻጻፍ ነበር).... የሚል ደብዳቤ በእንግሊዘኛ ጽፎ ሲልክልኝደንግጬ ነበር.... በሰአቱ....
ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በሓላ .... የነፍሱን ስሜት ላዳምጥለት ችያለሁ..... እናም አልፈረድኩበትም....
ዛሬ ግን ብታየው ያ ስሜቱ ተለሳልሶ.... በጋራ ሊያስማማን በሚችለው ሃሳብ ላይ ባንድ ባቡር ሃዲድ መሄድ እየቻልን እንደሆነ ሳስብ ደስ ይለኛል.... ምንም እንኳንባንዳንድ ሁኔታዎች አሁንም ባንስማማም

እንዳንተም ያለ ... አንድ ኃይማኖት አንድ ቋንቋ... አንድ ዶላር.... የሚል አክራሪ ማንነት በኢትዮጵያዊነት ስም ገጥሞኛል..... ማይ ዌይ ኦር ዘ ሃይ ዌይ.... አይነት
ለሃገር እየተቆረቆሩ.... ሃገርን እይወደዱ... (እንትናቸው እስከሚንቀጠቀጥ) ..ነገር ግን በውስጡ ያሉትን ህዝቦች ፍላጎት መብትና ጥያቄ.. በኢትዮጵያውነት ጭምብል ጨፍልቆ.. በአንድነት ስም... መደፍጠጥ.... ሃገር መውደድ አይባልም
ስለኤርትራ ሳስብ... ሰው አንገቱ ተቆርጦ እንዴት ይኖራል እያለ የኢትዮጵያን ካርታ እያሳየን.... እውር ድንብራችንን እንድንግዋዝ ያደረገንን የዝንባቡዌውን መንግስቱ ያስታውሰኛል.... እዲህ ያለ ችህፍን ፍቅር ይቅርብኝ
በልዩነታችን ተግባብተንና ተከባብረን ቁንጅናችንን በአንድነታችን ማሳመር ነው የኔ ህልምና ምኞት

አይመስላቹም?

ከእንጨት መርጦ ለታቦት
ከሰው መርጦ ለሹመት....

ያለው ማነው ባካቹ....??.....ሲገርም ግን
ይህ አባባል ይዞ ይጓዝ የነበርውን እምነት እና በሰው ላይ ፈጥሮት የነበረውን ሴንቲሜንት ሳስበው እና የገጠመኝን ገጠመኞች... ሳውጠነጥን..... ግርምምምምምምምም ይለኝ ነበር

ለማንኛውም

ዶ/ር ብርሃኑ.... ስለ-አንድነት... ዜግነት.... መብት እና ምናምን... መቼ እንደሆነ እንጃ.. የሰጠውን ማብራሪያ (ምሁራዊ ትምህርት ልበለው).... እንደገና አግኝቼ ባዳምጠው እንዴት በወደድኩ ነበር
ሁላቹም እንድታዳምጡት ግን በዚህ አጋጣሚ እጋብዛቹዋለሁ.... ነገሩ የቆየ ቢሆንም.... ተደጋግሞ ሊሰማ የሚገባው ቁም ነገር ነው ... ይመስለኛል

ስንመለስ..... ወሬአችንን ቀየር አድርገን.... እንመጣለን
መንገድ ከመጀመራችን በፊት

ቺርሥሥሥሥሥሥ
በክብር
ለሁላቹም

ጎሳ
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 8
Joined: 13 Mar 2013 02:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ጎሳ » 03 Apr 2013 18:29

ሰላም ለሁላችንም!
ጋሽ ሞፊቲ በመጀመሪያ ምን አስቸኩሎህ ጸግሼት ጋር ደውለህ እዚህ በምስጢር የጻፍኩትን የአማቹን ጉዳይ እንደነገርከው አልገባኝም:: በል በቃ ምናልባት ትንሽ ያረጋጋው እንደሆነ ይህንንም ሹክ በለዋ...ጎሳ ላይ ትንሽ ቅምጥ ነገር እንደነበራቸው:: አንተስ ታውቅ ይሆን ጉዳዩን? ለነገሩ አንተ ያኔ በጣም ልጅ ስለነበርክ ላታውቅ ትችላለህ:: እኛም እንደዚህ አይነት ያሉትን ጉዳዮች ከልጆች ጋር ስለማናወራ ላንተም የነገርንህ አይመስለኝም:: በል ባክህ የሰውን ምስጢር እዚህ አደባባይ ላይ አስዘርግፈኽኝ አታቅለኝ በዚህ ዕድሜዬ:: ጽግሸት እንኳ ዛሬም የቲሸርቶቹን ጉዳይ የምናነሳበት እየመሰለው ምክንያት ይፈልግብናል እንጂ ሰዎቹም ከተፋቱ ቆዩ አይደል እንዴ? ካልሰማ ንገረው ባክህ..ወይም ቁጥሩን ስጠኝና ልደውልለት::
“ውድ ጎሳ በመጨረሻው ላይ የጻፍከውን አይቼ ግራ ግብት ነው ያለኝ::ምክንያቱም አንተ ከተማ ውስጥ ሻይ እየጠጣህ ምን ታውቃለህ ብለው ነገሩኝ ያልከው ነው::እኔም ብሆን በፍቅር ተከባብረን ተዋደን ቤተሰቦቻችንም እንደዚሁ ተዋደውና ተከባብረው መኖራቸውን እንጂ አንተ አሁን እንደምትለው የከፋ ነገር አልሰማሁም::
በ እውነት ለመናገር አንተ እራስህ ከማውቅህ በላይ ፍጽም ተቀይረህብኛል::ያለምክንያት እንዳልሆነም የተረዳሁት ይህን ጽሁፍህን ካየሁ በኋላ ነው::ንጉሴም የሆነ ነገር አለ ስትለኝ እራሱ በ\ጣም ነው የደነገጥኩት::
ለማንኛው የሆኑና የተደረጉ ነገሮች ካሉ የዚህ ዘመን ልጆች ቂምን በመርሳት አንድ ሆነን በፍቅር የምንኖርበትን መንገድ መያዝ ይኖርብናል::”

ያነሳኽው የቡቴ ታሪክ በጣም ነው ያሳዘነኝ:: ምን ታደርገዋለህ...ይቅር::


ሞፊቲ ኪያ በፊት የማላውቃቸውን አንዳንድ ነገሮችን በመስማቴ ከዚያ ስርአት ጋር ምንም ግንኙነት ያልነበራቸውን አብሮ አደግ ጓደኞቼን ለመበቀል ተነሳስቼ ባንተም ላይ የተለወጥኩብህ ከመሰለህ እንደ እብድ ቆጥረኽኛልና ይቅርታ እንድትጠይቀኝ እፈልጋለሁ:: ሙት የምሬን ነው ;) :: የማልክደው ነገር...እራሴን የታዘብኩት...ድሮ ምንም የማይመስሉኝ አንዳንድ አነጋገሮች ወይንም ቀልዶች ዛሬ ጠቅ ያደርጉኛል:: ያናድዱኛል:: ጌታ ይገስጸው ያንን መንፈስ! ቅቅቅ ያንን ለምን እንዳልኩ ታስታውስ ይሆን? ስለ ፌስቡክ ፎቶዎች.....ወዲያው የመጣልኝ የአንድ ሀይማኖቱ ጉዳይ ነበርና ያልኩትን አልኩ:: ከዚህ ውጪ ጋሽ ሞፊቲ አንተ እራስህ የመኩሪያን አይነት ሆቴል ቦሬ ላይ ልትከፍት አስበህ የምታገኘውን ሳንቲም ሁሉ ትራስ ስር እየከከርክ ሁለት ዱሩሪ አውጥተህ ካርድ ገዝተህ መደወል ሲያቅትህ ጎሳ ተለወጠብኝ ትላለህ:: ስንቴ ስልክ ስቀጠቅጥልህ ነበር እኔ? ብቻ በግል እንወቃቀሳለን:: ለማጠቃለል ያህል ችግሬ በአንድነት ስም የሌላውን ህዝብ መብት ለመጫን ባለሱቃችን እንዳስቀመጠው ዛሬም "አንድ ህዝብ... አንድ አገር... አንድ ቋንቋ.. አንድ ኃይማኖት... አንድ ምናምን" ከሚሉት ጋር ነው እንጂ አማራ ይሁኑ ጉጂ ብሔራቸው እንኳ ትዝ በማይላቸው በነጸግሼት አይነቶቹ ላይ አይደለም ቅቅቅ:: እሱም ተለውጦ ፖለቲከኛ ሆኗል እንዳትለኝ ብቻ:: አርፈህ ቀበቶህን ሽጥ ብሎሃል በልልኝ:: እኔም አንድነቱን ስለምጠላው ሳይሆን የሌላውን ሰው መብት በተለይ ቋንቋ ሀይማኖት እና ባህል የሚጫነው አንድነት መቼም ስለማይመቸኝ ነው::
“ ጎሲና!..... አቤት ብንገናኝ የምናወራው ወሬ መመሳሰሉ......
ነገር ግን.... በሰአቱ የነበረውን እና ስራቱ የፈጠረውን ሲስተም.... በቤተሰቦቻችንና ባለፉት አባቶቻችን ላይ ሳይሆን...እንዲሁም በዚህና በዚያኛው ብሄረሰብ ላይ ሳይሆን
ሁኔታውን በፈጠረው እና . በነበረው የመንግስት ሲስተም ላይ ሊሆን ይገባል ይመስለኛል.....
ያ ሲስተም እንዳይደገም... ነው መታገል ያለብን
አንድ ህዝብ... አንድ አገር... አንድ ቋንቋ.. አንድ ኃይማኖት... አንድ ምናምን የሚባለውን አስተሳሰብ ነው በቅድሚያ .. ከውስጣችን እና ከውስጣቸው ማሰወገድ አለብን... በግልጽ በመነጋገር
አይመስልህም”
ባለሱቃችን.... ለመሆኑ ይህንን ያህል ጊዜ የት ከርመህ ነው ብቅ የምትለው? ለየት ያለ የአጻጻፍ ስልትህን የማይናፍቅ ሰው ያለ አይመስለኝም....ቁምነገር እያወራህ በመሀል የማይገናኝ ቀልድ ትቀላቅላለህ:: ውበት በውበት ያደርገዋል ጽሁፍህን:: ኧረ እኔና አንተ ብንገናኝ ስንት የምናወራው ጉዳይ ይኖራል መሰለህ...ብዙ አስተሳሰቦቻችን የሚገናኝ ይመስለኛል....በፖለቲካ ዙሪያ ተነጋግረን አንድ ፓርቲ መመስረት ቢያቅተን ቢያንስ ሞፊቲን እንቦጭቀዋለን:: የሆነ ራስታ ጸጉር'ኮ ነው ቅቅቅ:: እናልህ...ቀልዱስ ቀልድ ነው....ባለሱቃችን እኔም ከላይ እንደገለጽኩት...እንተም እንዳስቀመጥከው "አንድ ህዝብ... አንድ አገር... አንድ ቋንቋ.. አንድ ኃይማኖት... አንድ ምናምን የሚባለውን አስተሳሰብ ነው በቅድሚያ .. ከውስጣችን እና ከውስጣቸው ማሰወገድ አለብን... በግልጽ በመነጋገር " ባልከው አምናለሁ እንጂ ባሁኑ ትውልድ ላይ የጅምላ ጥላቻ የለኝም:: ከእንግዲህ ስሜታዊ ላለመሆንም እጥራለሁ:: ይመችህ ወንድሜ!

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”