የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 27 Apr 2013 09:45

እንደምን አላቹልኝ
ስለስደት ስታነሱ እኔም ያለኝን ልጣል ብዬ መጣሁና
ሳስበው ግን
እኔ ስለስደት ብናገር ያምርብኛል ወይ... ብዬ አቅማማሁ... እራሴንም ጠየኩት
ልምን ብትሉ
ተሰድጄ አላውቅማ!
... አቤ......ት .. ጉራ... ሲሉ ሰማሁዋቸው..... ጎሳ እና አደቆርሳ

ያው እንግዲህ ተሯሯጡብኝ በብዕራቹ
....................//...........
እናላቹ ምን ልላቹ ፈልጌ መሰላቹ
ስደት
አዎን ስደት... የሃገራችን ስደት... ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ እንደመጣ ነው ሚሰማኝ አሁን አሁን
ቲፒንግ ፖይንት (Tipping Point) ሲባል ሰምታቹ ይሆን.....
አንድ አዲስ ነገር (ለምሳሌ ፋሽን ቀሚስ/ጫማ/ምርጥ ዘር/ማዳበሪያ/አይ-ፓድ/ስደት/)ይመረትና ለገበያ ይቀርባል (ስደት ምርት ነው እንዴ እንዳትሉኝ ብቻ)
የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች... ሪስክ-ቴከር... ወይም አዲስ ነገር ለመሞከር የፈጠኑት ሰዎች ብቻ ይሆናሉ...
እንግዲህ ይህ አዲስ የተፈጠረ ነገር ቀስ እያለ ቀስ እያለ... ይስፋፋና.... የሆነች ቦታ ላይ ሲደርስ (ጃፓኖቹ 10% ሲደርስ ይላሉ... ስለሃገራቸው ገበያ ሲናገሩ).... መመለሻ የለውም.... ጉዳቱ ኖሮት ጉዳቱ መነገር ቢጀምር እንኳን መመለሻ የለውም....
የሚጠፋውና የሚቀዘቅዘው... ሌላ አዲስ ከዚህ የበለጠ ነገር እንደገና ወደ-ገበያ ሲቀርብ ነው.... ይላሉ... ተመራማሪዎች
እንግዲህ ለስደታችን መዳኒቱ... ሰውን እንዳይሰደድ የሚያደር አዲስ ነገር መፍጠር በሃገር ውስጥ... ሊሆን ነው ማለት ነው?
እንዴት ያለ ነገር ቢሉ..... ማንም የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም
አሁን ግን ስደት ሱስ ሆኖዋል በሃገራችን... ቲፒንግ ፖይንቱን ስላለፈ

ምን ገጠመኝ መሰላቹ ባለፈው ለአዲስ አመት ኢትዮጵያ የሄድኩ ጊዜ
አዲሱን አመት ያሳለፍኩት ሸዋ ሮቢት ነው ብያቹ አልነበር.... እስረኞች ሳስፈታ

ከዚያ መልስ .... በሚኒባስ ከኃላ ወንበር አንዲት ትንጭዬ የገጠር ልጅ ተቀምጣ ሳጫውጣት ነው የመጣሁት አላልኳአቹም
እስኪ ትዝ ከሚለኝ ምልልስ ውስጥ በትንጩ ላውጋቹ
> አባትሽ ምንድነው ሚሰሩት
* እረግ... ገበሬ ነዋ... እዛ ገጠር ውስጥ ምን ሊሰራ ብለህ
ድምጽዋ... ለየት ያለ ነው.... የገጠር.... በየአረፍተ-ነገሯ ውስጥ... እረግ... ኃላስ... የሚሉ ቃላቶች አሉበት
> ምን ምን ታመርታላቹ
* እረ አባቴ ጎበዝ ገበሬ ነው... የማያመርተው የለም... ጤፍ ብትል... ዳጉሳ ብትል... ይሄ ደሞ አዲስ የመጣው... አረንጓዴው ምንድነው ስሙ
ከፊት-ለፊታችን ተቀምጦ የነበረ ወጣት ስሙን ነገረን.... አተር የሚመስል አዲስ ምርት ነው... ጥሩ ገበያ ያወጣል አሉ... ገበሬውን ሃብታም በማድረግ የታወቀ... ከጤፍ ቀጥሎ
> እሺ... አባትሽ ሃብታም ገበሬ ነዋ
* ኃላስ
> ቤታቹ እስኪ እንዴት ነው
* እንዴት ማለት.. እንደሰው ነዋ
> ማለቴ ቆርቆሮ ነው
በመገረም አይን እያየችኝ
* ኃላስ.... ሆ ሆ .. ምን ይላል ባካቹ... የሰፈሩ ቤት ሁሉ ቆርቆሮ ነው ስልህ
> አንቺስ ትማሪያለሽ
* ነበር .. ግን ምን ያደርጋል ተምሮ የት ለመድረስ... አቁሜአለሁ
> ምነው ለምን አቆምሽ
* አንዲት ጉዳይ ስላለችኝ
> ቆይ ቆይ ግን አዲስ አመት ገና ሳምንት ሳይሆነው ቤተሰብ ጥለሽ አዲሳባ የምትሄጅው ለምንድነው
* አይ አንዲት ትንሽ ጉዳይ ስልህ
>ምን አይነት
* ፓስፖርት እያወጣሁ ነው
> ለምን
* እንዴ ለምን ይላል እንዴ... ልወጣ ነዋ
> ወዴት
* እንዴ ሰው ሁሉ ወደሚሄድበት አረብ አገር ነዋ
> ቆይ ስንት አመትሽ ነው
እንደማፈር አለችና... ወደ-ውጪው በመስኮት እያየች
* እውነተኛውን ነው ወይስ የፓስፖርቱን
> ምን ማለት ነው
* እውነተኛው 17 ነው ብዬ ነው... የባስፖርቱ ደሞ... 24
ገባኝ ምን እያልች እንደሆነ
> ግን አረብ አገር ያለውን ስቃይ እና መከራ.... ሰምተሻል?
* አዎን ሰምቻለሁ.... የዕድል ጉዳይ ነው... ሰምቻለሁ
> መደፈር አለ... ከፎቅ መወርወር አለ.... ስቃዩ እኮ ብዙ ነው... ለምን ግን መሄድ ፈለግሽ
* ሴት ልጅ ለሚያሰራት ወንድ ፊት ካላሳየችው... ስራዋን ብቻ ከሰራች.. መደፈር የሚባል ነገር.... እውነት አይመስለኝም
> እንዴት እርግጠኛ ልትሆኚ ቻልሽ
* እንጃ ሴትነቴ የሚነግረኝ ስሜት ነው
> ቆይ ቆይ... ግን ቤተሰቦችጭሽ እንዴት ፈቀዱልሽ
* ባይፈቅዱልኝ.. በወልዲያ እህዴ የለ.... አባቴ ቁርጡን ሲያውቅ ነው የፈቀደልኝ
> እንዴት ወልዲያ ምን አለ
* በወልዲያ በኩል አድርጎ በጅቡቲ .. በመርከብ የሚያጫግሩ ሰዎች አሉ.... የኛ ሰፈር ብዙ ሰዎች በዚያ ሄዳለሁ
> የኔ ቆንጆ በመርከብ ሲኬድ እኮ...... ብዙ ሰዎች ሞተዋል
* አውቃለሁ አውቃለሁ
> እያውቅሽ ነው ልትሄጂ የወሰንሽው በመርከብ
* አዎን.... ሞት እንደሆነ እዚህም እዚያም .. ያው ነው... እግዜር በፈቀደልህ ቦታ እና ጊዜ መሄድህ አይቀርም.... እዚህ ስላለሁ አልሞትም እዚያ ከሄድኩ ሞታለሁ ማለት... እግዚአብሄር ዘንድ የለም
> ቆይ ግን የኔ እህት... ካልጨቀጨኩሽ... ለምን መሄድ ፈለግሽ
* እንዴ ሁሉ ይሄድ የለም እንዴ.... እኛ ጎረቤት 12 ቤቶች አሉ... ሁሉም አንድ አንድ ልጅ ልኳል.... እንደውም በቀደም ጎረቤታችን ሁለተኛ ልጃቸውን ልከዋል
እኔ ምንድነኝና ነው እዚህ ተቀምጬ... የማየው.... ምን አለና ነው.... ባል ከማግባት በስተቀር....
እሱን ደሞ እሞታታለሁ እንጂ አላደርገውም
> እና ባል ላለማግባት ነው ምትሄጂው ማለት ነው
* እሱና ... ሁሉም ሰው ስለሚሄድ... እንዴ ምነው አንተ ግን ገረመህ
ብታይ እኮ... እኛ ሰፈር.... እዚያ እነ-እንትና.... ሰፈር ከተራራው በስተጀርባ ያሉትማ.... ሁለት ልጁን ያልላከ የለም
እኔም እሄድና ትንሹ ውነድሜ ትንሽ አደግ ሲል... እንዲመጣ አደርጋለሁ.. አሁን ገና 12 ነው... አልጠነከረም
> የመሄጃ ገንዘብ ግን ማን ይሸፍንልሻል... ግን
* አባቴ 100,000ብር ይሰጠኛል... ትልቁ ወንድሜም የምፈልገውን ያደርግልኛል
> ታላቅ ወንድምም አለሽ... የት ነው ያለው
* ሳውዲ ነዋ... እሱ ጋ እኮ ነው ምሄደው.. እሱም ቶሎ ነይ እያለኝ... ነው ያለ!
ምንም ልናገር አልቻልኩም
> ይሄ እግርጭ ስር ያለው ከረጢት ምንድነው
* ጤፍ
> ለማን
* ለአክስቴ.... እሱዋ ጋር ነው ማርፈው ባስፖርቴን ለመቀበል አዲሳባ ስቆይ
> አዲሳባ የት ነው ያክስትሽ ሰፈር
* ለገጣፎ
> ምን አልሽ
* ለገጣፎ.. ምነው
> እንዴ እንደዚህ የሚባል ሰፈር አለ እንዴ አዲሳባ
ከፊታችን ያለው ልጅ አሁንም ማብራሪያ ሰጠኝ
............... አዲሳባ ለካስ እንደዚህ ሰፍታለች .....
........... እረ ተንቦርቅቃለች ...............

ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት
በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺ አመታት
ይውጡ መአድናት ላገራችን ጥቅም
ህዝቧም ታጥቆ ይስራ በተቻለው አቅም
.................... ድንቄም ግድብ........
በመጀመርታ
ይህ የስደት ጎርፍ ይገደብ
የሙስሊም እምባ ይገደብ
የቃሊቲ በር ይገደብ
የኑሮ ውድነት ይገደብ
የሻኪሶ ወርቅ ይገደብ (አላሙዲ እና ጨሪኮቹ ... የበቃቹዋል)
እንዴ... ወርቅ መአድኑ የተጨጠበት ዋጋ ታውቃላቹ.... 170ምናምን ሚሊዩን ዶላር
አንድ የቢራ ፋብሪካ በቀደም 250ምናምን ሚሊዩን ዶላር እኮ ነው የተጨጠው

እረ ግፍ ነው.. እረ ግፕ ነው... አይን-ያወጣ ግፕ

ከዚህ መአት ይሰውራት አገራችንን

አሚን

..........................//.....................
ቀደድነው ነው ሚባለው ዛሬ
ምናባቱ የአመቱ ቅዳሜ አይደል.... ይቀደድ

በተረፈ
በቸር ያቆየን

ስደቱን በቃ ይበለን... የፈጠረው ትውልድ እራሱ

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 04 May 2013 12:23

ጤና ይስጥልኝ
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ !
መልካም የፋሲካ በዓል ለመላው ወራ አዶላ እመኛለሁ
ራስብሩ

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 04 Jun 2013 15:36

ጤና ይስጥልኝ
የቤታችን ዝምታ እስከመቼ ይሆን ?
በፌስቡክ የ አዶላ ኮፊ ሩም ልጆች ይህንን ሩም ይጎበኛሉ እስካሁን ግን ከአንድ በስተቀር ብቅ ያለ የለም ሆኖም
እንደሚመጡ ተስፋ አለኝ::
' ሴራ በገነተ ልዑል ቤተመንግስት ' ሁለተኛ መጽሃፍ ወደ ህትመት ክፍል ገብቷል !
ደራሲውም ወርቃፈራሁ ከበደ ይህንንው ለማስጨረስ እዚያው ይገኛል መጽሃፉ ገበያ ላይ እንደዋለ ወዲያው አሳውቃችኋለሁ::ዜና እረፍት
ወንድማችን ዳዊት አቦምሳ እና ወንድማችን መምህር ታምራት መርጊያ ከቅርብ ቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ::
በውነት አስደንጋጭ ዜና ነበር የሰማነው ለወንድሞቻቸውና ለእህቶቻቸው እንዲሁም ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው ሁሉ
መጽናናትን እመኛለሁ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን የገነት ያድርግላቸው::

ራስብሩ

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 08 Jun 2013 16:20

ራስብሩ ወዳጄ
መርዶው ደርሶናል... በጣምምም የሚያሳዝን ነው የዳዊት እረፍት....
የዛሬ 2 ወር ገደማ ነው የሰማሁት
መርዶ ማርዳት ስለማልወድ እንጂ..........
.......................//.................

ሰላም ያገር ልጆች
ይሄ ዝምታ ከመሰለቻቸት የመጣ ስለሚመስለኝ..... እኔም ሳልሰለች ውልቅ ብዬ ልጥፋ መሰለኝ

ያቺኑ ሳይበር-ኢትዮጵያን የሙጢን ብል የሚሻል መስሎኛል እንደ....ጎሳ

የሚያናድደው ግን ሳይበር ውስጥ መግባትም አልቻልኩም....
ጎሳ በዚህ እንደምትተባበረኝ አምናለሁ

እዚህ ጭር ያለ ቤት ውስጥ የምለጥፈውን ዝባዝንኬ... ወስደህ ሳይበር ላይ ልጥፍ ብታደርግልኝ ደስታውን አልችለውም
ምክንያቱም አንባቢ አላጣም ብዬ ነው እዛ ቤት ውስጥ
ምን ይመስልሃል???
............................//.......................

እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች
ዛሬ ምን ላወራ መጣሁ መሰላቹ
ስለ-ውሻ
ወይ ውሻ.... ምን ሊወራለት ይሆንንንንንን
...........................//.....................
ከዛሬ 8ወር በፊት ነው ድርጊቱ የተፈጸመው
እኔ እና 4 ጃፓኖች (2ወንድ 2 ሴት)
ስማቸውን ባችህሩ ላስተዋውቃቹ
ሴቶቹ 1ኛ. አይዋ.... 2ኛ ዩሚኮ
ወንዶቹ 1ኛ ሳቶ...... 2ኛ ሱጂ
እና እኔ አይዋ ዩሚኮ ሳቶ እና ሱጂ ... እራት አዘን እየጠበቅን ነው,.... ኡጋንዳ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ.... አርብ እለት
አንዳንድ ቢራ ይዘናል
ስለስራ .. ትንሽ ካወራን በኃላ... የግል እና የጋራ ችሀዋታ ተጀመረ
እንደሚከተለው ይነበባል
> ዩሚኮ........ ባካቹ የማነበው መፃፍ አለቀብኝ.... ካገሬ ስወጣ ብዙ ቆያለሁ ስላላልኩ... ይዤ የመጣሁት መፃፍ ትንሽ ነበር እና.. አለቀብኝ.... ካላቹ አውሱኝ ፕሊስ
* ሳቶ.... እኔ ጋር አንድ ሁለት መጻፍ አለ... ውሰጂ
> ዩሚኮ.... አንተ ጋር ያሉትን አውቃቸዋለሁ.... አንብቤአቸዋለሁ
+ አይዋ.... እኔ ጋር የኢኮኖሚክስ መፃፍ አለልሽ... ትፈልጊያለሽ?
> ዩሚኮ.... እኔ የት/ት መፃፍ አልፈልግም... ልብወለድ መፃፍ ነው ምፈልገው.... አቤት ቅዳሜና እሁዱ ሲደብር መፃፍ ከሌለ..... ምን ይሻለኛል???
የተከፋ እና የደበረው ፊት ታየኝና.. እኔም የሃሳቤን ለመወርወር ... አልኩኝ
..................
*ባለሱቅ.... ለምን ያነበብሽውን መፃፍ ድጋሚ አታነቢውም
> ዩሚኮ.... አንተ ደሞ አይገባህም... ሰው እንዴት ያነበበውን መፃፍ ድጋሚ ያነባል... እኔ በፍጥሱም አላደርገውም.... ሳነብ እያንዳንድዳንድዳዋን ነገር ስለማነብ .. መድገም አያስፈልገኝም
* ባለሱቅ.... እኔ ግን.... ማንም ሰው በመጀመሪያ ጊዜ የሚያነበውን መፃፍ በደንብ የሚያነበው አይመስለኝም.... ዋናው ታሪክ ላይ ብቻ ስለምናተኩር.... ብዙ ሚስ ምናደርገው ነገር አለ
+ አይዋ.... እስኪ በምሳሌ አስረዳን... ምን ለማለት እንደፈለክ
ዋውውውውው
የምፈልገው ይችን አይደል.. ብዬ ቀደዳ ጀመርኩ
.....................//................
10ኛ ክፍል ሳለን
አዎን 10ኛ ክፍል ሳለን.... የአማርኛ አስተማሪያችን (ኬኒያ ማመጫ)... አንብባቹ ገምግሙ ብሎ... የበአሉ ግርማን መጻፍ እንድናነብ አድርጎን ነበር.... ከአድማስ ባሻገር.... ደራሲው..... ትዝ ይሉኛል
ከአድማስ ባሻገር ላይ ያለችውን ሉሊትን... አፍንጫዋን (ቀጥ ብሎ ወርዶ እታች ሲደርስ የሚቀለበሰውን)... ምን ያህል እንደተመራመርንበት ትዝታዬ... ይቀመጥና
ደራሲው የሚለው መፃፉ ላይ የገጠመኝን ነበር ያጫወትኳችው

ደራሲው የሚባለውን መፃፍ... ከሶስት ጊዜ በላይ አንብቤዋለሁ... ከ1984 በፊት....
10ኛ ክፍል
ዘመቻ ጣቢያ
ዩኒቨርሲቲ
ብዬ ጀመርኩላቸው

እዚህ መፃፍ ውስጥ አንድ የሚያላዝን ውሻ አለ.... እረ ትንፋጭ እስኪያጥራቸው የሚያስሉ አሮጊትም ነበሩ እንጂ
አሁን አራቱም ጃፓኖች እያዳመጡኝ ነው
በተለይ አይዋ... በጣም ነበር ምትከታተለኝ
ታሪኩን አራዝሜ አራዝሜ.....
እዛ መፃፍ ላይ ያለው ውሻ ለኔ የታሪኩ አዳማቂ እንጂ.... የራሱ ታሪክ እንዳለው አላውቅም ነበር 3ጊዜ አንብቤው እንኳን .. ሁሌ የሚኦያላዝነው ውሻ ታሪክ እኔን ታይቶኝ አያውቅም ነበር
አንድ ቀን ግን... በ1984 መስከረም 4
ከሆነ ሰው ጋር ስለመፃፍ እያነሳን ስናወራ... ስንቀድና ስንጥል
የሚከተለውን አይነት ምልልስ አደረግን... ከዚያ ሰው ጋር
> ደራሲው የሚለውን መጻፍ አንብበሕዋል?
* አዎን በጣም የምወደው መፃፍ ነው
> የውሻው ታሪክ አያሳዝንም
* የምን ውሻ
> ያ ሚያላዝነው ውሻ
* እንዴ ...ቅቅቅቅ ውሻ ው ደሞ ምን አይነት ታሪክ አለው.... እኔ እኮ ሶስት ጊዜ ነው ያነበብኩት.... ዝም ብሎ የሚያላዝን ውሻ አይደለም እንዴ,... ደራሲውን የሚረብሽ.. እንዳይጽፍ
> ኖ ኖ እንደገና አንብበው.... ውሻው የሚያሳዝን ታሪክ አለው.... አሁን አትጨቃጨቅ...እንደገና አንብበው
በማግስቱ... አነበብኩት እንደገና
ውሻውን ፈልጌ ስለውሻው ብቻ ለማወቅ አነበብኩት.... ለ4ኛ ጊዜ
ያ... የሚያላዝን የደራሲው የጎረቤት ውሻ.... ለካስ... አባቱ ዘመቻ.... ካራማራ ተራራ ላይ ሆኖበት ... እሱን አጥቶ ነበር የሚያላዝነው
እዬዬ ማለቱ ይሆን... አባባባባባ..... እያለ....
የጋሽ በቀለ ውሻ
ጋሽ በቀለ ከዘመቻ የተመለሱ ቀን ግን... ማላዘኑን እንዳቆመ.. ሁሉ .... መፃፉ ላይ ተፅፎአል
በስመ-አብ ወወልድ... ይህንን ሁሉ ታሪክ እንዴት ሳላነብ እና ሳይከሰትልኝ
አቤት ውርደትትትትት በችኮላ ማንበብ

ይህንን ታሪክ እያወራሁላቸው ሳለ....
ዩሚኮ.... እዬዬዋን አቅልጣዋለች ለካስ በእንባዋ
እኔ አላየኃትም ነበር አይዋ ነው የነገረችኝ.... በቃ አቁም ብላ
ምን ተፈጠረ
ዩሚኮን ምን አስለቀሳት

እስኪ እስዋን አባብለን እንመለሳለን

ቸር ቆዩኝ

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 23 Jun 2013 16:59

ጎሳ ወንድሜ
በጣም አመሰግናለሁ ከዚህ ድብርታም ቤት ውስጥ አውጥተህ መልክቴን ስለለጠፍክልኝ... በድሮው ቤታችን
አየህ አይደል እኛን አይታ ያቺ ቀዌ... የግልነሽ እንደመጣች
ገና ትመጣለች... አንተ ብቻ ተባበረኝ እንጂ.... ከዚህ ግርግዳ ነቅለህ.. እዚያኛው ላይ መልክቴን ከለጠፍክልኝ
..................................//.......................
ምን እያወራሁ ነበር ባካቹ,,,,,,,,,,,, አይ እርጅና... ይጫወትብኝ ጀመር ማለት ነው...

ኣዎን ዩሚኮ አለቀሰች ብያቹ ነበር........... ምን አስለቀሳት... ምን ነበር የነገርኳት

አዎን የውሻ ታሪክ.... ደራሲው የሚለው መጽሃፍ ላይ ስለሚያላዝነው ውሻ
አንድ ቀን የውሻው በየጊዜው ማላዘን ያስመረረው ደራሲው (ጋሽ ስብሃት) ... ለስሞታ ጎረቤት ሄደና..ጠየቀ
እናትና ልጅ.... ልጅ የናትየውን ቀሚስ ይዞ... ደራሲውን አይን አይኑን እያየ
በሃሳቡ.... አሁን ምን ልሰራ መጣሁ... እያለ .. በአመጣጡ እያፈረ..... ደራሲው.. ሲራክ
በመጨረሻ... አጫወቱት እማማ.. ሁሉንም......
ባለቤቴ,... ወደ-ኦጋዴን ከዘመተ ጀምሮ ይሄ ውሻ እያላዘነ አስቸገረኝ
አቤት ደራሲውን በዚያች ቅጽበት የታየው..... ጎፈሬውን ያጎፈረ.. ቁምጣ እና ከስክስ የወታደር ጫማ የተጫማ... .... በበረሃ የነደደ ፊቱ የተቆጣ ... ጀግና ወታደር....ካራማራ ተራራው ላይ ቆሞ.. የኢትዮጵያን ባንዲራ በጀግንነት ሲያውለበልብ
ሶስት ጊዜ አንብቤው... ያላየሁት ታሪክ
ይሄ አሁን ምኑ ያስለቅሳል
........................//...........
እንባዋን ጠራርጋ ስትጨርስ ጠየኳት
> ምን አስለቀሰሽ ግን?
+ ውሻው.... ውሻዬ................ እምምምም ትላንትና ከቤት ስልክ ተደውሎልኝ... የልጅነት ጓደኛዬ.. ውሻዬ ሊሞት 10ቀን እንደቀረው ሃኪሙ ለቤተሰቤ ነግሮአቸው....
እንደገና ማልቀስ ስትጀምር... አቆመች
አለቃችን ሳቶ.... እናንተ አገር እንደዚህ አይነት መጻፍ ይጻፋል? አርስቱ ምንድነው.. ማነው የጻፈው... ተተርጉሞዋል?... በጥያቄ አጣደፈኝ
አይዋ ... ዩሚኮን አባበለቻትና ስታበቃ... ወደኔ ዞራ
* የመንደሪኗ ልጅ ናት አይደለም ... እንደገና እንድታነብ ያደረገችህ... አለችኝ
ክውውውውውውውውውው ነው ያልኩት .. በውነት.... እንዴት ልታውቅ ቻለች.... ማን ነገራት.... ይህንን ታሪክ ለሰው አውርቼ አላውቅም እኮ..... የሁሉም ሰው አይን ጆሮ የሆነ ይመስል... ሁሉም አፍጥጦ አየኝ እና የምለውን ሲጠብቅ
> ማን ነገረሽ... እንዴት እንደሱ ልትገመቺ ቻልሽ.. ስላት
*የዛሬ ሶስት አመት ስለዚች ልጅ አጫውተኅኛል... እና እንዲህ አይነት ደስ የሚል ታሪክ ያላት አንተ ህይወት ውስጥ እሷ ብቻ ነው ምትመስለኝ..... ግን እሷ እንዴት ይሄ የውሻ ታሪክ ሊስባት ቻለ
ህምምምምምምምምምምምምምምምም
ታሪኩ ረጅም ነው... ነገር ግን... አባቷን በጣም ትወድ ነበር.... እሱም እንደዚያው.... በልጅነቷ አባቷን ከመውደዷ የተነሳ... እናቷን በጣም ትጠላ ነበር
ምክንያቱም.. ማታ ስትተኛ ካባቷ አጠገብ ሆኖ ሳለ... ጠዋት ስትነሳ.. አባቷን እናቷ አልጋ ላይ ስታገኝ... ቅናት አይሉት ምን... ታለቅስ ነበር..... እርር ድብንንን ብላ
እና ያ በልጅነቷ የምትወደው አባቷ..... የኦጋዴን ጦርነት ካለቀ በኋላ... ወደ-ሰሜን ሄዶ.... ድምጹ ከተሰማ ከአስር አመታት በላይ ተቆጥረዋል
ከዛሬ ነገ ይመጣል እያለች የምትጠብቀው አባት
ይሙት
ይኑር
መንግስትም አልነገራት.... እሷም አላወቀች

አንተ አሞራ... መጥተህ ንገረኝ.. ያብዬን እጣ
የኔ ጀግና .. አልተመለሰም... እንደወጣ

........................//......................
ሱጂ የሚባለው ጃፓናዊ ምርቅንንንን ብሎ ነበር ለካስ ሚያዳምጠኝ.... መዝፈን ጀመረ
አንቺ የመንደሪን አበባ... የሚል ጃፓንኛ ዘፈን.... ሰምቼው አላውቅም... ግን ደሥ የሚል...
ወዲያውም ሁሉም በአንድነት...
ትገናኛላቹ አሁንም ከመንደሪኗ ልጅ ጋር....አሉኝ
እኔ ከመመለሴ በፊት ግን አይዋ ተሽቀዳድማ.... አዎን ይገናኛሉ.. አለች
እኔም እየሳቅኩ.... አዎንታዬን ስነግራቸው
ይደወልላት... እና ይሄ ዘፈን ይዘፈንላት.. ይላክላት
ባንድ አፍ.. ብዬ እኔም ስልኬን አውጥቼ
ቂሪሪሪሪሪሪሪሪሪ

አይበቃም

ቸር ሰንብቱ

አደራ መጻፍ ስታነቡ.... ደጋግማቹ አጣጥሙት... ብዙ ሳናውቅ የምናልፋቸው ታሪኮች ስላሉበት

እንደኔ እንዳትዋረዱ

ቺርስ

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 30 Jun 2013 04:16

ሰላም ቤቶች፣ ኢትዮጵያ ለአንድ ወር ቆይቼ ተመለስኩ። ጥሩ ጊዜ ነበር። ወደ አዋሳ በአውቶቡስ (ስካይ ባስ)ሄድኩ። አዋሳ ግሩም ከተማ ሆናለች። ከአዲስ አበባ መጨናነቅ ጋር ሲያነጻጽሯት አዋሳ ገነት ናት። ራስብሩ እንዳለው "ሤራ! በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት - ሁለተኛ መጽሐፍ" ለህትመት ቀርቧል። "መጽሐፍ አንድ" በብቃት ለአንባቢው ስላልተዳረሰ እንደገና አራት ሺህ እንዲታተም ታዟል፣ በቅርቡ እንደሚወጣ ተነግሮኛል። "መጽሐፍ ሁለት" ከ3 ወር በኋላ ለገበያ ይቀርባል። ከልማት መፋጠን አኳያ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ፕሮግራም (የህንጻዎች፣ የመንገዶች፣ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ወዘተ) አስደናቂ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። እርግጥ ነው ከሰብአዊ መብትና ከንግግር ነጻነት ብዙ ይቀረዋል፣ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደ የኢሕአደግ ፓርቲን የሚስተካከል ነጻነት የላቸውም። ይህ ገና መስተካከል ያለበት ነገር ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለ ብሎ ቢናገርም፣ በአገሪቱ ግን የዲሞክራሲ ሥርዓት ብዙ ይቀረዋል። ለማንኛውም በአዲስ አበባ ሆነ ከአዲስ አበባ ውጭ ብዙ የልማት ሥራዎች እየተካሄዱ ናቸው። የሙስናውን ተግባር ጨርሶ ለማስወገድ ገና ብዙ መሰራት አለበት። የተጀመረው ዘመቻ ግን ተስፋ ሰጪ ነው። ለሁላችሁም የማክበር ሰላምታየ ይድረሳችሁ።


አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 03 Jul 2013 15:04

(ከአዲስ አበባ መጨናነቅ ጋር ሲያነጻጽሯት አዋሳ ገነት ናት።)

መቼም ለምን እንዴት ወዴት አይባልም የአዋሳም የአዲስ አበባም ልዩነቶች ከመጠነኛ መሻሻል ጋር መሆኑን ተገንዝበህ ጠቆም ማድረግህ ተገቢ ነው እላለሁ::
ውድ አንፈራራችን እንኳን በደህና ደርሰህ ተመለስክ !
ሴራ በገነተ ልዑል ቤተመንግሥት .... ሁለተኛ መጽሃፍ ማተሚያ ገባ ሲባል ሰማሁና አንደኛዋን ካለችበት አንስቼ በድጋሚ በሶስት ቀናት ውስጥ ከጥግ እጥግ ተወጣኋት::
የዓለማየሁ ኒኮላስን እና የተዋቡ ደንቦባን የፍቅር ግስጋሴ ለመከታተል መንደርደር እንዲመቸኝ አልያም ማገናዘብ እንዳይቸግረኝ እንደፈረንጆቹ አባባል ሜሞሪዬን update አደረኩት ማለት ነው::
ቀኑ ደርሶ ለማንበብ ያብቃን::
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትና የልማቱን ሁኔታ በቁርኝት ተመልክተህ ልዩነቶቹን አጭርና ግልጽ በሆነ መንገድ አስቀምጠኸዋል ግሩም አገላለጽ ነው::
የልማት እንቅስቃሴው ምንም እንኳን ፍትሃዊነት የሚጎድለው ቢሆንም :- የበጀት ምደባውና የልማት እንቅስቃሴው የሚጣጣም ባይሆንም :- ለልማት የተሰጠው ድርሻና የክንዋኔው እመርታ ከዚህ ቀደም ዓይተን ለማናውቀው እሰየው ከማለት ሌላ ምንም አንልም::
ምናልባት የሙስናን ጉዳይ ስላነሳህ የሚገርመኝ እና የሚያስቀኝ ምን እንደሆን ታውቃለህ ?
ጉቦ የማይበላ :- የኢትዮጵያን ሃብት በሚቻለው መንገድና ሁኔታ የማይዘርፍ:- ከሃገሩና ከህዝቡ ይልቅ የራሱን የግል ኑሮውን ብቻ ብቻ ብቻ የማያሳድድ ኢሃዴግ የሆነም ያልሆነም ማንም በስልጣን ላይ ያለ ሰው አይገኝም::
በየትኛውም ክፍለሃገር ብትሄድ አንድም መስሪያ ቤት ያለጉቦ ጉዳይ ማስፈጸም አይቻልም ይህ ነው በጣም የሚያስገርመኝና የሚያሳዝነኝ::
አሁን የተጀመረው የጸረ ሙስና ፕሮግራም መልካም ሆኖ ሳለ መጀመሪያ ራሳቸው ወያኔዎች ከችግሩ እጃቸውን ካላነሱ ችግሩን መቶ በመቶ ይቀርፉታል ብዬ ከቶም አላምንም::
በብዙ የአፍሪካ ሃገሮች ህዝባቸውን የችግር እስረኛ አድርጎ ያስቀመጠው ሁኔታም ይሄው ነው::
በአንዳንድ ሃገሮች ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያወጡት እቅድ ለአንድ የፓርላማ ባለስልጣን የደለበ ረብጣ ዶላር በየወሩ ማሳቀፍ ነው ብለው አንድ ሰሞን ዓለምን ሲያስቁ ከርመዋል::
እኛም ራሳችንን አሳልፈን ከሰጠናቸው ካመንናቸውና ከጮህንላቸው የህዝብ ልጆች በድንገት የደረሰብንን እፍረት ስናስበው የጥርሳችንን መፋቂያ ማውረድ አቅቶን ቁጭ ብለናል::
ባጭሩ በሃገራችን ያለው የልማት ሁኔታ እንዲሁም ሃገራችን በጥቂቱም ያለችበት እድገት እንዲንጠራራ
እና የባለጉቦ እጆች እንዲቆረጡ የምንጊዜም ምኞቴ ነው::
በማንም ሰው ወይንም ድርጅት ላይ ተስፋ ባይኖረኝም የማያሳፍር ጌታ አለን !
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::


ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

Greenough
Posts: 1
Joined: 12 Jul 2013 01:11
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Greenough » 12 Jul 2013 01:42

with smart choices and hard work, not so much about what you're willing to spend.


gold price rs
buy gold rs

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”