የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 22 Jul 2013 11:32

ጤና ይስጥልኝ
አንፈራራችን መልካም ዜና ነው ያሰማኸን እንደዚህ ከሆነ ብትጠፋም አይከፋንም ማለት ነው :
ስራህ የተዋጣ እንዲሆንልህ ከልብ እመኛለሁ::
ሽሜው ምነው የእድሜ ነገር ሲነሳ ቁጣ ቁጣ ይልሃል ? ደሞ አንተ ነህ እንጂ የእድሜ ነገር የምትፈራ
ጌታቸው ጅሩ አስተምሮኛል እያልክ እንደገና የነራስብሩ ክላስሜት ነኝ ስትል ዝም ስላልኩህ ነው ?
አርፈህ ቁጭ በል አለበለዚያ ዋ !
ግንድሬን ማስታወስህ ገርሞኛል ለነገሩ አንተ ነገር ማስታወስ አንደኛ ነህ ለዚያውም ቅጽል ስም::
በቅርቡ እሱ አዲስ አበባ ነበር ማንንም አላየሁም አለኝ ብዙ ስለቆየም ስለረሳም ወደክብረመንግስትም ሄዶ አያውቅም ከአዲስ አበባ ነው የሚመለሰው::
ዲሲ ሁለት አሪፍ ቀናት አብረን አሳለፍን ከዚያ በተረፈ እኔ ትንሽ ዞር ዞር አልኩኝ::
ኔቫዳ (ላስቬጋስ) እዮብ ደሳለኝ ጋ ሄጄ ስድስት ቀን አብረን አሳለፍን ስድስቱም ቀን አልበቃ ብሎን በስንት ትግል ነው የተለያየነው ::
ከእዮብ ጋር ከአዲስ አበባ ስነጥበብ ትምህርት ቤት በኋላ አልተያየንም ነበር ይህም ማለት ከሃያ ዓመት
በላይ ሆኖታል::
እዮብ ጋር ብዙ ስለቆየሁ መኮንን ገብሬ ጋ ዳላስ የነበረኝን ፕላን ሰረዝኩ ::
ቬጋስ በነበረኝ ቆይታ ያየሁትን ሁሉ ላጫውታችሁ ብል መሽቶ ይነጋል.::
ከተማው በረሃማ ሲሆን እጅግ በጣም ንጹህና ውብ ነው : ቬጋስና ካዚኖ መችም አንድ ናቸው አንዱ ቁማር ቤት ገብቼ እንደው የሚነካውን ባላቅም ለመሞከር ብዬ ማሽኑን አምስት ዶላር
ሳጎርሰው እጥፍ አደረገልኛ ደስ አሰኘኝ : ትንሽም ሳይቆይ ጥቅልል አረገኝ በዚያው ተለያየን ከካዚኖ ጋር::
በተረፈ ከ እዮብ ጋር በጣም ደስ የሚል ጊዜ በማሳለፌ እረፍቴን በጣም አሪፍ አድርጎልኛል::
ሌላ ከጓደኞቻችን መሃል ከሃና ሃብቴ ጋር ቨርጂንያ ጥሩ ጊዜ አሳለፍን ሃናን ስላገኘኋት በጣም ነው የተደሰትኩት ምክንያቱም ተጠፋፍተን ነበር ::
ከሷም ጋር ከወጣሁ ጀምሮ አልተገናኘንም ነበር ሃና በጣም ጥሩ ነው ያለችው ከሃና ጋር ከልጅነት ጀምሮ በጣም የቅርብ ጓደኛሞች ነን:: በዛ ወቅት ብስራት ሃብቴ ኢትዮጵያ ሄዶ ነበር አላገኘሁትም::
የግልዬን ያለችበት ሰፈሯ ድረስ ሄጄ ነው ያየኋት ከክንዴ ጋር ለመገናኘት የያዝነው ቀጠሮ ሳይሳካ ቀርቶ ሳላየው ተመለስኩ::
ምናልባት ያ ቀጠሮ ቢሳካ ኖሮ መልካሙ ተበጀን የማግኘት አጋጣሚ ነበረኝ ምን ታረገዋለህ ::
ማህሙድን እና ስለሺ ተስፋዬን በቴሌፎን ብቻ ነው ያገኘኋቸው ማህሙድ ብዙ ልጆችን በቴሌፎንም ቢሆን እንዳገኝ ስለረዳኝ ምስጋናዬ ከልብ የመነጨ ነው::

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 22 Jul 2013 13:18

ውድ ወገኖች
የባላምበራስ ዓለማየሁ በንቲ ማረፍ ሁላችንንም አሳዝኗል:: ለሁላችንም ደግ አባት ነበሩ:: አንዴ ከርሳቸው ጋር ከአለታ ወንዶ ወደ ቦረና ነጌሌ አብረን ሄደናል::-


ነገሩ እንዲህ ነው: እኔና አንድ ሌላ የክ/መ ልጅ (አርአያ አብርሃም)ከአዋሳ ተነስተን (በአንዲት ቮልስዋገን) ወንዶ በቀለ አብዲ ሆቴል አደርን:: አዋሳ ላይ ሌላ የክ/መ ልጅ (አበራ የማነ አብ) ጉዳይ ስለነበረው እዚያው ትተነው ሄድን::


ጠዋት ከአልጋ ወርደን ቁርስ ለመብላት ስንዘጋጅ ባላምበራስ ዓለማየሁን አገኝናቸው:: በጣም ደስ አለን:: እርሳቸው አውቶቡስ ይጠብቁ ስለነበር ከኛ ጋር አብረው እንዲሄዱ ጠየቅናቸው:: ከዚያም ወደ ክ/መ አብረን ሄድን:: እዚያም ጥቂት ሰዐዓታት ካሳለፍን በኋላ "ነጌሌ ቦረና እንሂድ" ብለውን እዚያ የሚገኘው ሆቴላቸው አደርን:: በጣም ጥሩ ጊዜ አሳለፍን::


እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ታኑር:: ለልጆቻቸው አንዲሁም ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው አምላክ መጽናናትን ይስጣቸው::


አደቆርሳ አንተም እንደምትወደን እኛም እንወድሃለን:: ከጂግሳ ጋር ስትነጋገሩ ሶሮ ያልከው ግን ምኑም አልገባኝም:: ሰምቼው አላውቅም:: የበሽታ ዓይነት ነው? በውይይት ስለ መስማማትና አለመስማማት ያነሳኸውም ጉዳይ እውነት ነው:: እዚህ ቤት በፖለቲካ ሆነ በሃይማኖት እምነታችን የተለያየ ቢሆንም "የኔ ካንተ ይሻላል" በሚል ምክንያት ልንጣላ ወይም ልንወቃቀስ እንኳን አይገባም:: ላለመስማማት እየተስማማን ኖረናል::


ባለሱቅንና ራስብሩን ሳያችሁ ደስ ነው ያለኝ:: እስቲ ይልመድባችሁ:: ኣረ ሞፊቲ የት ጠፋ? የሚገርም ነው:: በተረፈ ለሁላችሁም ለአደቆርሳ ራስብሩ ሞፊቲ ባለሱቅ ጂግሳ ጎሳ የግል ቦሪቲ ኦዶሻኪሶ እንዲሁም ሌሎቹ የአክብሮት ሰላምታየ ይድረሳችሁ::

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 23 Jul 2013 13:07

ሶሮ ማለት ቃሉ የኦሮምኛ ነው
አገላለጹም ጥቃቅን የጠብታ መጠን ያለው ሆኖ ነገር ግን ችም ችም ብሎ ረዥም ሰዓታት የሚዘንም ዝናም አልያም ረዥም ሰአታት መዝነብ የሚችል ዝናብ ሶሮ ይባላል:: ( ዝናም የሚል ቃል የተጠቀምኩት ቀዳሚ ቃሉ ስለሆነ ሲሆን እኛ ዝናብ እንለዋለን) ወይንም ዧ ብሎ የማይዘንብ ነገር ግን ቀስ እያለ እያረፈም ቀኑን ሙሉ የሚዘንብ ዝናብ ሶሮ ይባላል::
/እንደ አዲስ አበባ ዝናብ ችክ አትበል!/ ሲባል በፊት በፊት ይገርመኝ ነበር
እኔ እንደምረዳው ግን አዲስ አበባ የተለየ ዝናብ ሆኖ ሳይሆን አዲስ አበባ ብዙ የእንቅስቃሴ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ዝናብ ሲዘንም ብዙ ሰዎች ከሩጫቸው ይታገዳሉ ከቤታቸው ሳይወጡ ለመቀመጥ ይገደዳሉ ስለዚህ ክረምትነቱን ሳይቀበሉት ችክ ያለ ይመስላቸዋል ::
የአፍሪካ ሃገሮች ብዙዎቹ የ rain forest region አብዛኛው የክረምት ወራቶቻቸው ዝናባማ ናቸው ሶሮ በነዚህ አካባቢዎች በጣም የታወቀ ነው ምናልባት ምን ተብሎ እንደሚጠራ ነው የማናውቀው::
የኢትዮጵያ የአየር ጸባይ ከ30 ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በረሃማነቱ ከ እጥፍ በላይ መጨመሩን በርካታ መረጃዎች ያሳዩናል::
ለምሳሌ ሶሮ ብዙው ደቡባዊና ምዕራባዊው የኢትዮጵያ ክፍል የክረምት መገለጫ ከመሆኑም በላይ በክረምት ሶሮ ባይኖር እንኳን አየሩ በከፍተኛ ደረጃ ውሃ አዘል /humid/ እንደምንለው ነበር : አሁን አሁን በነዚህ አካባቢዎች ውሃ አዘል ወይንም እርጥብ አየር የለም እስከማለት ተደርሷል በክረምትም እንኳን ዓየሩ ደረቅ ነው ::
ባጠቃላይ ሶሮ ማለት ችክ ያለ ነገር ግን የሚዘንብ የማይመስል ሆኖም የሚዘንብ ደቃቅ ዝናብ ነው::
ስለ ባላምባራስ ዓለማየሁ ጥሩ ትውስታ ነበረህ ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች አንስተናቸዋል በተለይ በአሁን ጊዜ በክብረመንግሥት በሚያድጉት እነዚያ የእግዚአብሄር ፍጡራን ትልቅ ተስፋ ከሆኑትና ዋና ረዳቶቻቸው ከሆኑት ውስጥ የሳቸው የባላምባራስ ልጆች ሰፊ ድርሻ አላቸው::
ልጅ ያባቱን ይወርሳል ይሏል እንዲህ ነው ሰው ከወላጆቹ የሚወርሰው ሃብትና ገንዘብ ብቻ አይደለም ለጋስነትን አዛኝነትን: ረዳትነትን: ጀግንነትን: ሃገር ወዳድነትን: ሰው አክባሪነትን : ቆራጥነትን ወዘተርፈ ........ እነዚያም ምስኪን ልጆች ሲያድጉ የተደረገላቸውን ያደርጋሉ ከእኛም የሚማሩት የሚወርሱትም ይህንንው ነው::
እነዚያን ልጆች ሳነሳ ምንጊዜም ልቦናዬ የሚጎተጉተኝ ነገር አለ ቀኑ ሲደርስ እተነፍሰዋለሁ::
የሚሰማኝ ስሜት ትልቅ ደስታ ነው ልቤ ሃሴትን ታደርጋለች: የራሴ ልጆች ይመስሉኛል: ሳላያቸው እወዳቸዋለሁ: ስዕላቸው ፊቴ ላይ ይመጣል በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር አስበዋለሁ በእውነት እርሱም ያስባቸዋል::
ከዚህም የተነሳ ይህንን ቤትና እናንተን ሁልጊዜ እንድወዳችሁና እንዳከብራችሁ እሆናለሁ::
እግዚአብሄር እርሱ ያክብራችሁ !
"በጻድቅ ስም ጥርኝ ውሃ ያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው ዓይጠፋበትም "
ብሎናልና ዋጋችሁ ይጠብቃችኋል::
ራስ ግንድሬ እዚህ መጥቶ እንደሚመለስ እኔም አውቃለሁ ማንንም አያገኝም ስላልከው አግኝቶ ቢሆንስ ?
ስለ ላስቬጋስ አንዳንዴ ምን አለ መሰለህ እኔ በተፈጥሮዬ በአእምሮዬ የምስለውና የማየው ነገር ብዙ ልዩነት ነው የሚኖረው ለምን እንደሆነ አላውቅም::
ላስቬጋስ ብዙ ባለፍራንኮች አረቦች ወዘተ እየሄዱ የሚዝናኑባት መሆኗን በምሰማ ጊዜ እኔም ሄጄ እዛው ልዝናና ይሆን ? ብዬ ስንቴ አስቤያለሁ መሰለህ ...
ቅቅቅ (በማለት ሼህ አላሙዲን ተናገሩ ብዬ ብጨርሰውስ ምን ይለኛል )
ምን መስለህ እኔ የሚገርመኝ ነገር ለምሳሌ አንተና እዮብ እንዴት እንደሆናችሁ አውቃለሁ ግን ሃያ ዓመት አልተያየንም ስትሉ በቃ ምን ብዬ ልንገርህ ፎጋሪዎች ነው የምትመስሉኝ ለምን መሰለህ እኔ ብሆን እላለሁ .... እኔ ብሆን የምወደው ጓደኛዬ የትም ይሁን የት መቼም ከዓለም አይወጣ ስለዚህ ያለበት ሄጄ ወይም እሱ እየመጣ በደንብ እንጠያየቃለን ብዬ አስባለሁ::
ወም የወዩ ልጆች ከያለንበት እየተሰባሰብን አብረን በአላትን አዲስ አመትን ወዘተ እናሳልፋለን እያልኩ በግሌ አንዳንዴ ማሰቤ አይቀርም::
አይሆንም እንጂ ማይክል ጃክሰን እንደሞተ ሰሞን አንዷ ጓደኛችን "" ጌታ ሆይ ማይክልን መንግስተ ሰማይ አስገባው ብዬ ጸለይኩ አለቺኝ ለምን ብዬ ብላት እኔም ለመግባት እጸልይና እዛ አየዋለሁ ብላኝ አረፈች ..........
የኔም ሃሳብ እንዲሁ የማይደረስ ይሆንብኛል::
ፕሊስ አልጨረስኩም ቶሎ ለመመለስ ሞክራለሁ

Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa » 05 Aug 2013 11:34

አደቆርሳ፣ ራስ ብሩ፤ ባለ ሱቅ፣ ጎሳ …… ቀሪዎች ሁላችሁም
በያላችሁበት ሰላምታዬ ይድረሳችሁ
አደቆርሳና ራስ ብሩ የተጨዋወታችሁት ነገር ትክዝ አደረገኝ፡፡
ልጅነቴን አስታወስኩበት…. አንድ ስም ሲጠራ ጆሮዬ ውስጥ ኪሊሊሊ ብሎ የሆነ ነገር አስታወሰኝ ፡፡ ኢዮብ ጎረቤቴ ነበር፡፡ ግን በጣም የኔ ሲኒየር ነው፡፡ በቆርቆሮ የተሰራችው የአጥራቸው በር፡፤ በሰማያዊ ቀለም በወፍራም ብሩሽ የተጻፈች ..ኢዮብ ና.. የምትል ጽሁፍ…. አቤት የጊዜው ፍጥነት……..

አሁን እንኳን ቤተሰባቸው ሁሉ ቤት ንብረታውን ሸጠው አዶላን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ምናልባት እኔ ካየሁት 30 አመት የሆነኝ ይመስለኛል (በግምት)፡፡ኢዮብ ካነበብከው ሰላም ብዬሃለው፡፡አሜሪካ እንዳለህ እንኳን አላቅም ነበር፡፡ ለካ ደሞ አታውቀኝም፡፡ በጣም ጩጬ ነበርኩኛ ያኔ፡፡!
በቅርቡ አዶላ ሄጄ ነበር፡፡ እናቴን ልጠይቅ፡፡ ለነገሩ ጉራ ስነዛ ነው እንጂ መኖሪያዬስ መች እሩቅ ሆነና;! እናንተ ቬጋስ ሄጄ ምናምን ስትሉ አኔም መቶ ምናምን ኪሎሜትር ተጉዤ አዶላ ሄጄ…ምናምን እያልኩ አወራለው፡፡ በህገ መንግስታችን ---አንቀጽ ላይ የሰፈረው ዴሞክራሲያዊ መብቴ ነዋ፡፡ የሰውን መብት ካልነካሁኝ…. ጉራ ብነዛ ምን አገባው አዳሜ…. እናም ዞር ዞር ብዬ የዛሬ 25 እና 30 አመት ገደማ ከብቶች ያገድኩበትን…. በሬዎች ጠምጄ ያረስኩበትን ዶቅማ ለመልቀም ስንጠለጠል ወድቄ ጉድ የሆንኩበትን… ማሳችንን፤ ሜዳችንን፤ ዛፎቻችንን..( ግራሮቹን ፤ዋንዛዎቹን፤ ዶቅማዎቹን፤ ብሳናዎቹን)….ለማየት…. ግን ይገርማል ያየሁትን ለማማን እጅግ ከበደኝ፡፡ መንገዶቹ ሙሉ በሙሉ ጠፍተው ተቀይረዋል፤ ዛፎቹ ለምልክት የሉም፡፡ ጉቶአቸው እንኳን የለም፡፡ አዝንኩኝ ፤ተከዝኩኝ፤ የሚገርመው ክረምት በመጣ ቁጥር እንጉዳይ እለቅምበት የነበረች ማሳችን መሃል የነበረች አንዲት ጉብታ ነበረች፡፡ አሁን ግን የለችም፡፡ ዛፉንስ ጠገራ ቆረጠው፡፡ ጉብታዋን ምን በላት… ወይ ጊዜ!!!! ሚዳቆና ቆቅ በተደጋጋሚ አጥምደን የያዝንበት የጣልያን ምሽግ ደን…. ለምልክት የሚሆን ቁጥቋጦ የለውም!!!

የውስጤን ስሜት ሳደምጠው ብዙ የምጽፍ መስሎኝ ነበር! ግን በፍጹም አልቻልኩም፡፡በፍጹም!!!

ቸር እንሰንብት…..

Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa » 06 Aug 2013 08:14

መቼም የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አንጀት የሚያርስ ነው (እንደ ቅቤ ሳይሆን እንደ ማረሻ ቅቅቅቅቅቅቅ) እናም የሆነ ፎቶ ልለጥፍ ብዬ ብዙ ሞክሬ እምቢ ቢለኝ ጽሁፉን ብቻ ላኩላችሁ፡፡

ምሳሌነቱ ሩቅ የሚያስኬድ ነው፡፡ በግሌ ለብዙዎቻችን ትምህርት የሚሆንና ልናጠናክረው የሚገባ ብርቱ ጉዳይ ነው ባይ ነኝ፡፡
ባለፈው ሐምሌ ገብርኤል በነጌሌ ቦረና ከተማ እየተሰራ የነበረው የቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ስራ ተጠናቆ ከሩቅም ከቅርብም የመጡ ብዙ ምእመና በተገኙበት ጽላቱ አዲሱ ህንጻ ገብተዋል፡፡
ዋናው ቁም ነገሩ መሰራቱ አይደለም፡፡ ዛሬ ብዙ በሚነገርበትና ብዙ በሚሰማበት ጊዜ በከተማው የሚገኙ ሙስለሊሞች ለዚህ ህንጻ ቤተክርስቲያን ስራ ቢያንስ ከ30000 (ሰላሳ ሺህ ብር በላይ) አዋጥተው የሰጡ ሲሆን በወቅቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ደወል ቤት የሚመጥን ደወል በቅርብ ማግኘት ባለመቻሉ በምረቃው ወቅት ተሰቅሎ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በከተማው ከሚገኘው መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በውሰት የተገኘ ደወል ነበር፡፡

በውኑ ይህ ህብር እንዲጠፋ የሚፈቅድ ማነው?!

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 07 Aug 2013 16:45

ክብር ለ እግዚአብሄር ይሁን !
ጂግሳ አስቀድሜ ሰላም እልሃለሁ ! እንደምን አለህ ?
ፎቶ መለጠፍ ለኔም ቀላል አልሆነልኝም አንፈራራ ባለፈው አንድ ነገር ነግሮን ለጥፎም አሳይቶን ነበር ብቻ ረሳሁት መልሶ ቢረዳን ያሰብከውን ታሳየን ነበር::
የሆነው ሆኖ ያቀረብካት አጭርና ንጹህ መልክት አንጀቴን ስላራሰችው / በምን እንዳትለኝ እንዳንተ በቂቤ ይሁን በማረሻ አላውቅም/ ብቻ አንጀቴ ርሷል ::
እንዲህ ያለው የወትሮ ፍቅርና አንድነት ተመልሶ እንድናይ የቦረና ህዝብ ጥሩ ምሳሌ ሆኗል::
ይህ የሃይማኖት አዲስ አመለካከት ችግር በአሁን ወቅት በኛ ሃገር ብቻ ሳሆን አንድ እምነት ብቻ ወይንም አንድ ሃይማኖት ብቻ በሚያመልኩ ሃገርና ህብረተሰብ መካከልም በጣም ጎልቶ የሚታይ ችግር ከሆነ ሰንበት ብሏል::
እንዳልከው አሁን አሁን በሃገራችንም የምንሰማውና የምናየው አዳዲስ ሁኔታዎች ከመፈጠራቸው በፊት ማለትም እኛ ልጆች በነበርንበት ከዛሬ ሃያና ሰላሳ ዓመታት በፊት የነቢዩ መሃመድ መውሊድ ሲከበር አልያም ታቦተ ንግስ ሲሆን መላው የራስብሩ ተማሪ በሰልፍ እየሄድን እናከብር ነበር እንጂ አንድም ልዩነት አልነበረንም ልዩነት መኖሩንም አናውቅም ነበር::
መስጊድ ሲሰራ አልያም ቤተክርስቲያን ሲገነባ እስላምና ክርስቲያን የሚል ልዩነት በፍጹም አልነበረም ይህ ማለት ደግሞ ሩቅ ጊዜ አይደለም በጣም ቅርብ ጊዜ ነው ::
በእርግጥ አሁንም የለም ሆኖም እንዲህ ያለውን ጥሩ ማህበረሰብ የሚያምሱ አንዳንድ ችግሮች አልፎ አልፎ ሲከሰቱ እናያለን ይህንንም በእግዚአብሄር ኃይል በፍቅርና በአንድነት መኖር የሚወደው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደመልካምነቱ እንደሚለውጠው ምንም ጥርጥር የለኝም::
ፎቶዋን እንደምንም ብለህ ብትለጥፋት ደስ ይለኛል::
ባለፈው ቀን የጻፍካትንም ዛሬ ነው ያየኋት እዮብ ና ... ብላ የምትጣራ አጥራቸው ላይ የነበረች ጽሁፍ ብለህ ማስታወስህ እጅግ በጣም ነው ደስ የሚለው : ማለቴ የማስታወስ ችሎታህ አስደነቀኝ
እዮብ ጥሩ ጸሃፊ እንደነበረ አውቃለሁ ቤታቸውንም አካባቢውን እንጂ ሄጄ አይቼው ግን አላውቅም::
ግን ምን ትዝ አለኝ መሰለህ ? ደጀኔ ቱራ የሚባል የኛ በደንብ ሲኒየር የሆነ ልጅ ነበር እና የቤታቸው የጓሮ በር ላይ Be a Rock & Ice to your misery . ብሎ የጻፋትን ጽሁፍ እስካሁን ድረስ እንደትናንት አስታውሳታለሁ:: የተጻፈው በምስማር ነገር እንጨቱ እየተቦረቦረ ስለሆነ እስካሁንም ይኖራል ብዬ ገምታለሁ::
የጽሁፉ ትርጉም የገባኝም እሱ ከሞተ ከአመታት በኋላ ነው ምናልባት ሃይስኩል ከገባሁ በኋላ::
ጂዮቫኒ ጊቢ አጥሩ ላይ ደሞ ለረዥም አመታት የኖረ በስኪሪፕቶ የተጻፈ ጽሁፍ ነበር < መሬት ለምን ትዞራለች ? > የሚል :: መልሱን እስካሁንም ሞክሬ አላውቅም ባውቅም እኔ ምናውቃለሁ ! ነው የምለው::

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 07 Aug 2013 21:11

St Gabriel, Negelle, Borena.jpg
St Gabriel, Negelle, Borena.jpg (64.97 KiB) Viewed 6268 times


Negelle Borena.jpg
Negelle Borena.jpg (87.97 KiB) Viewed 6268 times

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 08 Aug 2013 06:20

ሰው ሁሉ አደግድጎ እግዚአብሄርን ፈርቶ ስመለከት የሚሰጠኝ የህይወት እርካታ በምንም የሚተካ አይደለም ራሴንም ሆኖ ማየት የምሻው እንደዚሁ ነው !
በጣም ነው ደስ የሚለው
በአውሮፓና በሌሎች አካባቢዎች ቤተክርስቲያናት የሚያመልክባቸው አጥተው ለገበያ ሲቀርቡ የኛ ሃገር ገና በመገንባት ላይ መገኘቷ የአለምን ልዩነት
ከማየት ባሻገር ህዝባችን አምላኩን ወዳጅ እንደሆነ እናይበታለን::
በርግጥ ይሄ በአውሮፓውያን የቤተክርስቲያናት ከአገልግሎት ውጪ መሆንና መሸጥ ማንንም ደስ የሚያሰኝ ሁኔታ አይደለም ሊሆንም አይችልም ::
በአለም ቀዳሚ የነበሩት አማኞች ዛሬ ልጆቻቸውን ማስተማሪያ ጊዜ አጥተው እግዚአብሄር ማነው ? የሚሉና ያለተፈጥሮ ግቢያ ሰዶምና ገሞራ
እንደገና የሚነድባቸው መሆናቸው አስደናቂው የዘመናችን ድራማ ሆኗል ::
ችግሩም ለሌሎች ተርፎ አሁን አሁን እኛም ብዙ ብዙ ማየት ችለናል::
የዚህች አለም ገዢ ወደ ወንበሩ እየወጣ መሆኑንም ማጤን ይገባል
ጎበዝ ዛሬ የሰዎች ሁሉ ፍላጎትና ሩጫ ወደ ገንዘብ ብቻ መሆኑንም አስተውሉ !
ማንንም ቆሞ አታዩም ሁሉ ወደብር ብርርር ይላል ::
ያለ ገንዘብም ዓለም እንዳትሰራ ያደረጋትም ያው ባለቤቱ ሲሆን አህዛቡን ወደ እርሱ ሲጠራ ሁላችን እየተጋፋን እየገሰገስን ነን ::
ቆየት ብሎም ታላላቆቹም የአለም ግዙፎቹ የንግድ ተቋማት እየተጣመሩ አንድ እየሆኑ እየመጡ ነው
ከዚህም የተነሳ የገንዘቡ ባለቤትና አዛዥም አንድ እየሆነ ሲመጣ በግልጽ እናያለን
በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ ቀደም ብዙ ብዙ የተነጋገርን ቢሆንም ሁሌም እንዲህ ያለውን ነገር ብንወያይበት የሚከፋ ነው ብዬ አላምንም::
የሰለጠነው ዓለም ይሄንን የቴክኒዎሎጂ እድገት የወለደው የሚለውን አሰራር ሊጠቀምበት ግድ ነው !
ጎበዝ ልብ በሉ የባንኮችንም አካሄድ ተመልከቱ በዚህ አካሄድ ስንረዳው ቀስ ብሎ ቢዛና ክሬዲት የሚሏቸው ካርዶች ወደ አዲሱ የቴክኒዎሎጂ
አሰራር ሲስተም ይቀየራሉ ያኔ ጥቂት ማሰብ ግድ ይሆናል::
በአለም ላይ ጦርና ጦርነት ነግሷል ለቅሶና ዋይታም የእለት ተለት ክንዋኔ ሆኗል :
ዓለም በተቃውሞ ታጭቃለችስለዚህ ማሰብ ይገባናል::
ስለ ሃገራችንም ስለህዝቡም በጣም ልናስብ የሚገባን አሁን ይመስለኛል
ይህ ሁሉ ጥፋት ሊመጣብን የሚችለው ከምንም በላይ በምንወደው በገንዘብ ምክንያት ብቻ ነው::
አንድነትና ፍቅር ይጠበቅብናል ህብረትና ስምምነት ይጠበቅብናል ሰላምና መዋደድ ይፈለግብናል
መቻቻልና መታገስን ልንሰንቅ ይገባናል ኢትዮጵያ በዚህ የታደለች ሃገር ናት ክብር ለ እግዚአብሄር ይሁን !
ኢትዮጵያ ታበጽዕ ህደዊአ ሃበ እግዚአብሄር !


ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”