Confusion reigns at Ethio Telecom on appointment for positions

by ocean
  • Workers who is not alive and out of the country appointed
  • ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች በአዲሱ ቴሌኮም ላይካተቱ ይችላሉ

By Hayal Alemayehu

Employees of the now phased-out Ethiopian Telecommunications Corporation (ETC) are confused over the appointment of the N-5 category which decides the stake of most of ETC’s workers at the newly structured Ethio Telecom. Posted at the corporation’s head office last Saturday morning, the first phase of the N-5 appointment incorporated about 3333 employees of the former ETC. The parastatal has in excess of 12,000 employees most of which are destined not to make it to newly structured Ethio Telecom.

Following the notice posted at the head office, some of the employees of the corporation told The Reporter that most of ETC’s staffers were “confused” with the appointment which include employees who have passed away and those already living overseas.

Jean-Michel-Latute-ethio_telecom -ceo

Jean Michel Latute ethio telecom ceo

While the criteria for the appointment at the new telecom considers educational background and experience, there are workers appointed at the N-5 category who have not even completed 12 grade in contrast to those who failed to make it to the list even though they are degree and

diploma holders, according to ETC employees.

Although the N-5 category appointment has begin with the first phase that included over 3000 employees of ETC and will continue in the coming months, most employees were “frustrated” by the process as if the first phase appointment is the final one.
“We have only started the first phase appointment of the N-5 category,” Debretsion Gebremichael, Communication and Information Technology minister who oversee the new established Ethio Telecom, told The Reporter. “The appointment will continue in the coming months as I have said earlier and we cannot now tell how many will make it to Ethio Telecom.”

debretsion gebremichael

Debretsion Gebremichael

So far 700 to 800 staffers of ETC are appointed in the N-2, N-3 and N-4 categories while some 3333 are being appointed in the first phase of the N-5 class.

In the mean time, ETC’s labor union and the management of Ethio Teleocm  have failed to reach an agreement over the appointment. Sources disclosed the labor has invited to file their complaints. Head of the ETC’s Labor Union, Addise Bore, has refused to comment on the matter saying that the labor has to wrap up administration issues with the management and the government before it provides information to the press. The Reporter’s attempt to obtain comment from the new management was not successful as well.

Amharic Version

በሕይወት የሌሉና ካገር የወጡ ሰዎች ተመድበዋል
‹‹ምደባውን ጀመርን እንጂ አላጠናቀቅንም›› አቶ ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

በኃያል ዓለማየሁ በአዲስ መልክ በተቋቋመው ኢትዮ ቴሌኮም ከሥራ ምደባ ጋር በተያያዘ ግራ መጋባት መስፈኑን የተለያዩ የድርጅቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በአዲሱ የሥራ አመራር የፍራንስ ቴሌኮም ቡድን የተካሄደው ምደባ በሕይወት የሌሉና ውጭ አገር የሚኖሩ የቀድሞ ሠራተኞች መካተታቸውን የጠቀሱት የቴሌ ሠራተኞች፣ በምደባው ፍትሐዊነትና ግልጽነት ማጣት ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የሥራ አመራር ኤን5 በተባለውና አብዛኛውን የቀድሞውን የቴሌ ሠራተኛ ምደባ በሚያካትተው የሥራ ምድብ የመጀመሪያ ዙር ምደባ የተመደቡትን 3,333 የሚሆኑ ሠራተኞች ዝርዝር ባለፈው ሳምንት ዓርብ ማምሻው ላይ ይፋ ተደርግል፡፡ ምደባው የትምህርት ደረጃንና የሥራ ልምድን ግምት ውስጥ ያስገባ እንደነበር   ለሠራተኞቹ ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እያላቸው ሳይመደቡ የቀሩ እንዳሉ፣ በተቃራኒው አሥራ ሁለተኛ ክፍል ያላጠናቀቁና በድርጅቱ ከወራት በላይ ያላገለገሉ ሠራተኞች በመመደባቸው ምደባው ሠራተኛውን ቅር ከማሰኘቱ በተጨማሪ፣ ግራ ማጋባቱን የድርጅቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኤን5 የመጀመሪያ ዙር ምደባ ይፋ ከሆነ በኋላ በምደባው ያልተካተቱ አብዛኛዎቹ የቀድሞው ቴሌ ሠራተኞች ተስፋ መቁረጣቸውን የገለጹት አንድ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊ፣ ይኼም በቀሪው ሠራተኛ ላይ ስጋትና ድንጋጤ ሳይፈጥር እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡

ከሥራ ምደባው ጋር በተያያዘ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹ምደባው ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም›› ያሉት የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል፣ በመጪዎቹ ወራትም ምደባው እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ምደባው በቀጣይነት የሚካሄድ በመሆኑና በአሁኑ ወቅት ምን ያህል ሠራተኞቹ በአዲሱ ቴሌ እንደሚመደቡ ለማወቅ አይቻልም ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ አብዛኛውን ሠራተኛ የሚያካትተው ምደባ ወራቶችን የሚወስድ መሆኑን ገልጸው፣ ያልተመደቡ ሠራተኞች ከቴሌ ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች እንደሚደራጁ አስታውቀዋል፡፡

እስካሁን ባለው ሒደት በኤን1 ምድብ ያሉት የፍራንስ ቴሌኮም አመራርን ቡድንን ሳይጨምር፣ ከኤን2 እስከ ኤን4 ከ700 እስከ 800 የሚደርሱ የቀድሞ የቴሌ ሥራ ኃላፊዎች የተመደቡ ሲሆን፣ በኤን5 ምድብ 3,333 የሚደርሱ ሠራተኞች መካተታቸውን አንድ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እኚሁ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የኤን5 ምደባ ይቀጥላል ቢባልም፣ በቀጣዩ የሚመደቡት በጣም ጥቂት ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጸው፣ ወደ 13ሺሕ ከሚጠጉት የቴሌ ሠራተኞች ውስጥ ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑት በአዲሱ ቴሌኮም ላይካተቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በሠራተኛ ምደባው ከሥራ አመራሩ ጋር መግባባት ላይ ያልደረሰው የሠራተኛ ማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አዲሴ ቦሬ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን፣ ከቴሌና ከመንግሥት ጋር አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ሳይቋጩ መግለጫ እንደማይሰጡ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

ፍራንስ ቴሌኮም አዲሱን የሥራ አመራር ከተቆጣጠረ በኋላ በሠራተኞች ላይ ስጋትና ጭንቀት ቢፈጠርም፣ ሠራተኞቹ የሚያገኙት ወርኃዊ ደመወዝ እንደማይቋረጥ በተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና በሚኒስትሩ ጭምር መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚሁ በሠራተኛ ምደባ ላይ አዲሱ የሥራ አመራር ለማነጋገር የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

Source: Reporter

Related Posts

1 comment

selam January 8, 2011 - 8:25 pm

They can not be abused in their own country by some western capitalists animals!

Reply

Leave a Comment