Artist Behailu Menegesha Passed Away

by yeEthiopiaforums

According to Washington DC based Ethiopian newspaper and
website bawza.com report artist Behailu Menegesha passed away today
March 3,2013. Artist Behalu Mengesha was born February 09, 1956 in
Addis Ababa. He was an Actor, Producer and Director in many
Theaters, Films and TV dramas. His burial ceremony will be held at
DEBRE MIHERERT ST. MICHAIL ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH 3010
Earl Pl NE Washington, DC 20018

artist-behailu-mengesha

Artist Behailu
Mengesha

 

Please watch Behailu’s interview below on his artistic life and work with Dereje
desta on ESAT Ye Hager Lij program. 


Read the
Amharic interview with Bawza news paper. በአዲስ አበባ ከተማ የካቲት 8 1948
ዓ.ም ነው ተወለደው። ውልደቱ 6 ኪሎ ቢሆንም እድገቱ ሙሉ በሙሉ ጉለሌ ሩፋኤል አካባቢ ነው። የመጀመሪያና
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም ት/ቤት ነው ያጠናቀቀው። ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ አርቲስት
አለም ፀሐይ ወዳጆ ጓደኛው ስለነበረች ወደ ሃገር ፍቅር ቲያትር ወስዳ ከነ ተስፋዬ አበበና መላኩ አሻግሬ
ጋር አስተዋውቃዋለች።” የቲያትር ሙያ ላይ እንዳተኩር ያደረገችኝ እሷ ናት”ይለናል። በኋላም ሎሬት ፀጋዬ
ገ/መድህን 22ሺ ብር መድቦ አማተር ተዋንያን መልምሎ ሲያሰለጥን ከነ አለምፀሃይ ወዳጆ ፣ አለሙ ገብረአብ
፣ አስራት አንለይ ፣ ሲራክ ታደሰ ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ትሩፋት ገ/ኢየሱስ ፣ አልማዝ ሰይፉ ፣ ተዘራ ውብሽት
፣ መሰለች ከበደና በሃይሉ መንገሻ ሆነው ስልጠናውን ይጀምራል ። በመሃሉ ባገኘው ዕድል ለሁለት ዓመት ወደ
ታንዛንያ ዳሬሰላም ሄዶ ወታደራዊ ሳይንስና ማኔጀርነት ይማራል። በኋላም ሃገሩ ተመልሶ ቲያትር ቤትም እየሰራ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይጀምራል በወቅቱ ” ትግል ይቅደም ትምህርት ይቅደም” የሚባል የፖለቲካ
ትግል ስለ ነበር አቋርጦ ወደ ራሺያ ይሄድና በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ዓመት ቀጥሎም በሞስኮ
የቲያትር ኪነ ጥበብ አካዳሚ አምስት አመት ተኩል ትምህርቱን ተከታትሎ በቴአትር አዘጋጅነት “ዳሬክተር
የማስተር ኦፍ አርት” ማስትሬት ዲግሪውን አግኝትቷል። በሞያው ለበካታ ዓመታት በሃላፊነት በቤሄራዊ ትያትር
፣ በሃገር ፍቅር ቲያትር ፣ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሰርቷል። ከዚህ በተጨማሪ በአዘጋጅነት ፣
በተዋናይነት በርካታ ቲያትሮችን ፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በመስራት ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ
አድርጓል። አርቲስት በሃይሉ መንገሻ። ለአርቲስት በሃይሉ መንገሻ እዚህ ሃገር ከመጣ በኋላ የመስማት ችግር
ስላጋጠመው አንዳንድ ጥያቄዎችን በፅሁፍ አቅርበንለት እንደሚከተለው ምላሽ ሰጥቶን ነበር። ባውዛ፡ አሜሪካ
አመጣጥህ ለምን እና እንዴት ነበር? በኃይሉ ፡ ባለቤቴ ወ/ሮ አለም እሸት ከዱ ቀደም ብላ ወደ አሜሪካ
መጥታ ስለነበር እኔም ወደዚህ መጣሁ። በሶስተኛው ቀን ነው ወደ ሃኪም ቤት የገባሁት። ወዲያው ሁለቱም
ኩላሊትህ ስራ አቁመዋል ተብዬ ዲያልየሲስ “ደሜ ከሰውነቴ ወጥቶ ተጣርቶ መመለስ እንደሚያስፈልገኝ”
ተነገረኝ። ቅድመ ዝግጅት ሰርጀሪ ተደርጌ አስፈላጊዎቹ የላስቲክ ቱቦዎችን ተገጠሙልኝ። ከዚያም ሰነባብተው
አንዱ ኩላሊትህ ካንሰር (develope) እያደረገ ነው ብለው በቀዶ ጥገና አወጡት። እንግዲህ ለተለያዩ
ሕመሞቼ ከምወስዳቸው ኪኒኖች ውስጥ አንዱ በከፍተኛ ፍጥነት ሁለቱም ጆሮዎቼን አደነቆረኝ። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ
ችግር ላይ ወደኩ። ስራመድ ሁሉ መንገዳገድ ጀመርኩ ባለቤቴ ሶስት ወር ያህል ከስራ ቀርታ በየሃኪም ቤቱ
እያሳከመችኝ ለምጠየቀው ጥያቄ መልስ እየሰጠች አስታማ የጆሮዬ ነገር የሞተ ጉዳይ ሆነ። እንግዲህ ካለ
ኢንፎሜሽንና ኮሚኒኬሽን መንቀሳቀስ የማትችልበት አገር በመሆኑ ችግር አለው። በአንጻሩ የመስሚያ መሣሪያ
ተገጥሞልኝ ትንሽ ትንሽ ይረዳኛል። ቲቪ ካፕሽን ስላለው እያነበብኩ እከታተላለሁ ቴክኖሎጂው ህይወትን
ለማቅለል በብዙ መንገድ ይረዳል። በኋላም ልቤን ከሦስት አርትሪዎች ሁለቱ ጠበው ከሁለቱ ደግሞ አንዱ በጣም
ስለጠበበ ቀዶ ህክምና አደረኩ።( እስቴንት) የሚሉት የልቤ አርትሪ ብረት ለቀለበት ገጥመውልኝ አሁን ድህና
ነኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ጓደኞቼ አብሮ አደጎቼ የባለቤቴ ዘመዶች ጓደኞች እየተመላለሱ እየጠየቁኝ
አስታመውኛል እግዚአብሔር ይስጣቸው። ውለታቸው በደስታ ይከፈል እላለሁ ባውዛ፡ መተኪያ ኩላሊት አገኝህ እንዴ
? በኃይሉ ፡ ገና የኩላሊት ትራንስፕላንት እየጠበኩ ነው።ተመዝግቤያለሁ። ከ3-5 ዓመታት ይፈጃል። አገር
ቤትም ሰዉ አግኝቼ ነበር ግን የአሜሪካ አሜምባሴ ቪዛ አልሰጥም አለ። ለሁሉም እግዚአብሔር ቢፈቀደ ጊዜ
አገኝ እሆናለሁ ብዬ እየጠበኩ ነው። ባውዛ፡ ስለ ሥራ ሕይወትህን ጠቅለል አድርገህ ብታጫውተን? በኃይሉ
፡በመሠረቱ ስራዬ የቲያትር አዘጋጅ በመሆኑ ከዚሁ ከሙያው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሥራ ላይ ነው ብዙ አመት
ያገለገልኩት። በብሄራዊ የቴያትር ክፍል ሃላፊ የፕላንና ፕሮግራም የህዝብ ግንኙነትህ ኃላፊ የትያትር ቤቱ
ዋና አዘጋጅና አርቲስቲክ ዳሬክተር በመሆን አገልግያለሁ። ከ984 በኋላ የክልል 4 ባህልና ስፖርት ቢሮ
የሥነ ጥበባት ማስተባበሪያ ቡድን መሪ በመሆን ቴያትርን ሙዚቃን ሥነ ጽሁፍን ስዕልና ቅርጻቅርጽን በሚመለከት
በሃላፊነት ከባለሞያዎች ጋር በመሆን በማደራጀት የሙያ ፈቃድ በመስጠት በመገምገምና የተለያዩ ስልጠናዎች
ጭምር በመስጠት አግለግያለሁ። በቴአትርቤቶች መድረክ ላይ የሚቀርቡትን የቴአትር ቤቶቻችንን የጥበብ ውጤቶች
መገምገም ደረጃቸውን እንዲጠበቁ በመቆጣጠር በመደገፍ በማበረታት በመምራትና ሙያዊ አገልግሎት መስጠት ሌላውን
የስራ ድርሻዬ ነበር። በ 1990 የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት (city hall) የቴአትርና ባህል አዳራሽ
ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን በኋላም የባህልና የማስታወቂያ ቢሮ የቴያትርና የሲኒማ ከፍተኛ ኤክስፐርትነት
ተመድቤ ፈቃድ በመስጠት በማሰልጠን በተለይ እያበበ የመጣውን የቪዲዮ ሲኒማ እየገመገምን በሪፍሌክተር
በቴአተር ቤቶቻችን አዳራሽ እንዲታዩ በመፍቀድ ዘርፉ እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። በአዘጋጅነት
የሎሬት ፀጋዬ ገ.መድኅንን « ጴጥሮስ ያችን ሰዓት » በሃገር ፍቅር ቴአትር “የፊታውራሪ መኮንን ዶሪ“
“የእጮኛው ሚዜ” በብሔራዊ ቴአትር ያስታጥቃቸው ይሁንን “አንቺን አሉ” በብሔራዊ ቴአትር የማክሲም ጎርኪን
በረዳት ፕሮፌሰር አቦነህ አሻግሬ የተተረጎመውን “ቅኝት” በብሔራዊ ቴአትር የሻምበል ታምራት ገበየሁን
”ውጫሌ 7” በብሔራዊ ቴአትር የዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን “ፍቅር በአሜሪካ” በብሔራዊ ቴአትር የሻምበል ፈቃድ
ዮሐንስ “እቡይ ደቀመዝሙር” የተስፋዬ አበበን “የደም ቀለበት” በቴአትርና ባህል አዳራሽ የሰራዊት ፍቅሬን
“የከርቼሌው ዘፋኝ” የአሰፋው አፅማት “የምሽት ፍቅረኞች“ ቴአትሮችን በቲአትር ባህል አድራሽ መድረክ
አቅርቤያለሁ። በተዋንያንነት በሃገር ፍቅር ቲአትር የብርሃኑ ዘሪሁን ” የአርባ ቀኑ መዘዝ” የተስፋዬ አበበ
ሙዚቃዊ ድራማ በሃገር ፍቅር ቲያትር የፀጋዬ.ገ/መድን”ሀሁ በስድስት ወር” ሁለተኛው የገፀ ባህርይ ምድብ
በመሆን የተስፋዬ ሣህሉን ፣ አለሙ ገ/አብ፣ ጠለላ ከበደን ፣ አለምፀሐይ ወዳጆ ፣ አውላቸው ደጀኔን ፣
ሲራክን ታደሰ ፣ ወጋየሁ ንጋቱን ፣ ተክሌ ደስታ ጀምበሬ ጥላሁን ፣ አስራት አንለይ፣ ጌታቸው ይበልጣል ፣
በኃይሉ መንገሻ ፣ በመሆን በኋላ በወጣት ተዋንያን የተገነባውን ቲአትር ይዘን ጅማ ፣ መቱ ፣ አሰላ ፣
ድሬዳዋና ሐረር ፣ አሳይተናችው የፀጋዬ ገ/መድኅን “አቦጊዳ ቀንሶ” በብሔራዊ ቴአትር የፀጋዬ ገ/መድኅን
አፅም ብየገፁና የመቅደላ ሰንበት ብሔራዊ ቴአተር። በቴሌቪዥን የተስፋዬ አበበን “አባ ውቃውና ጋዜጠኛው”
የተሰኘውን ከ1966ጀምሮ የተለያየ የቲቪ ድራማዎችን በፊልም (the adventure of tom sawyer
and hunky berry fin) የአማሪካዊው ክላሲክ ደራሲ የማርክ ትዌይን በሞስኮ – የሲኒማ ኩባንያ
የቀረበው ላይ ፣ የእንግሊዝ ኩባንያ ያቀረበው ላይ ቢቢሲ (channel 4 &carnival films)
ያቀረቡትን ( the big battalions ) የተሰኘው ፊልም ላይ ጎንደር ሲሳይ የተባለ ገፀባህርይ እና
የተለያዩ ፊልሞች ላይ ትንሽ ባህርያትን ተውኛለሁ። ባውዛ፡ የወጣቶችን ሥራ በቴአትሩ ዘርፍ እንዴት
ታየዋለህ? Click Here to Read More from
Bawza.com

Related Posts

Leave a Comment