ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል 14ኛ ዓመቱን በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብራል

by Zelalem

Tayitu 14th

ላለፉት በርካታ ዓመታት በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሥነጥበብ ድግሱን ያለማቋረጥ ሲያቀርብ የቆየው ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል እነሆ 14ኛ ዓመቱን ኖቬምበር 2 ቀን 2014 ከ 4:00 PM ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያከብራል::
በዕለቱም ታዋቂዎቹ ተክሌ ደስታ ፥ ዓለምፀሃይ ወዳጆ ፥ተስፋዬ ሲማ ፥ተመስገን አፈወርቅ እና ሌሎች  አንጋፋ የሆኑ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የቴያትር ዝግጅት፣ ግጥሞች፣ ቀልዶችና ጭውውቶች ይቀርባሉ:: ጣይቱ የባህል ማዕከልም ይህን ዝግጅት ከወዳጅ ዘመድ ጋር በመሆን እንዲካፈሉ እና  የሁላችንም የሆነውን በዓል በጋራ እንድናከብረው ጥሪውን ያቀርባል::

 
ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ:-

  • ወርሃዊ የሥነፅሁፍ ምሽቶችን ለዋሺንግተንና ለአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በቋሚነት አቅርቧል::
  • በርካታ ጭውውቶችንና የቴያትር ዝግጅቶችን በተለያዩ የአሜሪካ ክፍለግዛቶች፣ በካናዳና በአውሮፓ ከተሞች ተዘዋውሮ አሳይቷል::
  • አንጋፋና ወጣት የሥነፅሁፍ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ለህትመት እንዲያበቁ አበረታቷል፣ ረድቷል:: ልዩ ፕሮግራሞችን በማሰናዳትም ከተደራሲያን ጋር እንዲተዋወቁ አድርጓል::
  • ዓመታዊ የውይይትና የሥልጠና መርሃግብሮችን (ወርክሾፖችን) በማዘጋጀት የሥነጥበብ ባለሙያዎችና ታዳሚዎች እውቀታቸውን እንዲያሳድጉና ተሞክሯቸውን እንዲለዋወጡ መድረኮችን ፈጥሯል::
  • ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት በርካታ አፍሪካውያንን በማሰባሰብ የአህጉሪቱን የሥነፅሁፍ ቅርስ ያስተዋወቀበትን የመስከረም ወር የሥነ ግጥም ምሽት አዘጋጅቷል።
  • በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች ለተደራጁ መሰል የሥነ-ጥበብ ክበባትና ማህበራት የሙያ ድጋፍና ማበረታቻ ሰጥቷል።
  • ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ወጣት የሥነጥበብ ባለሙያዎችን በማስተባበር ላለፉት ሶስት ዓመታት የጋራ የሥነፅሁፍ ምሽቶች በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይና በተመሳሳይ ቀን እንዲካሄዱ አድርጓል። የዝግጅት ወጪያቸውንም ሸፍኗል።
  • በዋሺንግተን ከተማ የንባብ ቤት በማቋቋም ከሃገሩ የራቀው ወገን ከባህሉና ከታሪኩ እንዲሁም ከማንነቱ እንዳይርቅ የበኩሉን አስተዋፅዎ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የባህል ማዕከሉ ሌሎች በርካታ ተግባራትን የፈጸመ ሲሆን በመጪው አመታትም ከጥበብ አፍቃሪ ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የሃገራችን የቋንቋ እና ስነ-ጽሁፍ እንዲዳብር እና ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ ያላሰለሰ ጥረቱን ይቀጥላል ።
 የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ይምጡና ከማዕከሉ አባላትና ደጋፊዎች ጋር እየተዝናናን በዓሉን በጋራ እናክብር እያለ ጥሪውን ያቀርባል !

አድራሻ፣    Tifereth Israel Congregation,
               7701  16th St.  NW Washington, DC 20012

ለተጨማሪ መረጃ በ (202) 667-0077 ይደውሉ
Like Tayitu Cultural Center in Facebook. Share with your friends who you think they shouldn’t miss this event.

https://www.facebook.com/events/1493705564244277/

 


Click Like to Get updated News Everyday.

Related News

Comments

comments

Related Posts

Leave a Comment