የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን የብር ሜዳሊያ እንደማይቀማ አሳወቀ

by Selam

የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የማራቶን ውድድሩን ሲያሸንፍ የተሸለመውን የብር ሜዳሊያ እንደማይቀማ አሳወቀ::

በብራዚል ሪዮ ከተማ በተደረገው የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ በሁለተኛነት በሚያጠናቅቅበት ወቅት እጆቹን በማጣመር በኦሮሚያ እና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በገዢው ስርዓት እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የዜጎች መብት መጣስ በአለም አደባባይ ያጋለጠው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተሸለመው የብር ሜዳሊያ እንደማይቀማ ተረጋግጧል::

የቢቢሲ ጋዜጠኛ ፒርስ ኤድዋርድስ በትዊተር ገጹ እንዳሰፈረው :

የኦሎምፒክ ኮሚቴው ” ከአትሌቱ ጋር ተነጋግረናል እናም የኦሎምፒክ ህጉን ማስታወስ እንዳለበት ገልጸንለታል”

ቢቢሲ: ” እና ጉዳዩ በዚሁ ተዘግቷል?”
ኦሎምፒክ ኮሚቴ: ” አዎ ተዘግቷል”

የኦሎምፒክ ህጉ በውድድር ወቅት የፖለቲካ ምልክቶችን ማሳየት የማይፈቅድ ሲሆን አትሌቶችም በማሸነፍ የተሸለሙትን ሜዳሊያ እንደሚቀሙ ይደነግጋል::

feyisa-lelisa-ethiopia-ioc

feyisa-lelisa-ioc-Piers Edwards