አዲስ አበባ ፖሊስ 621 አድማ በታኝ ፖሊሶችን አሰልጥኖ አስመረቀ

by ocean

አዲስ አበባ, ግንቦት 1 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) – የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በአድማ ብተና ያሰለጠናቸውን 621 አባላት ትናንት አስመረቀ፡፡

በጦላይ ከፍተኛና የበታች ሽማምንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለአንድ ወር ሥልጠናውን የተከታተሉት በኮሚሽኑ በቋሚ ጥበቃና ተወርዋሪ ኃይል የሚያገለገሉና ከሠራዊቱ የተወጣጡ አባላት ናቸው፡፡

Addis ababa police in Addis ababa university

Addis ababa police in Addis ababa university (photo archive)

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ምክትል ኮሚሽነር ይህድጎ ሥዩም ለተመራቂዎች ባደረጉት ንግግር የአገሪቱም ሆነ የከተማዋ ደህንነት መሠረት የጸጥታና የሰላም ዋነኛ ምንጭ ሕገ መንግሥቱ ነው፡፡

ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አክብሮ በማስከበርና የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳሉት ገልጸው፣ተመራቂዎችም በሥልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀትና ችሎታ ትርጉም የሚኖረው በጸጥታ ማስከበር ሥራ የሚጠበቅባችሁን ውጤት ማስመዝገብ ስትችሉ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም ለአራተኛ ጊዜ በአገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን ተመራቂዎች መንግሥትና ሕዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በተገቢ መንገድ መወጣት እንደሚያስፈልግ ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

የሥልጠናው አስተባባሪ ተመራቂዎቹ ለ167 ሰዓት መሰጠቱንና ሥልጠናው ሙያቸውን ለማሳደፍና ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ ለመወጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ ማስገንዘባቸውን ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡

Source: ENA

Related Posts

8 comments

Selamawit Selassie May 10, 2010 - 6:03 am

oh i think it’s a sign …….

Reply
Haile HillBilly May 10, 2010 - 7:02 am

Dude ur so far away but u get info first hand ! .. how do u do it?

Reply
Alexen Woldu May 10, 2010 - 10:02 am

OMG..we gotta leave this town!

Reply
Alm Tegegne May 10, 2010 - 11:03 am

Oh…that`s real. I saw them from last week to yesterday…..

Reply
Misrie ⎝⏠⏝⏠⎠ Tiyya May 10, 2010 - 12:03 pm

i was just thinking…what in the f would happen if everybody boycotted the ballots and stayed home to watch TV? ya’ll know what the hell is gonna happen-election is just formality and your votes will not count and he’s telling you he’s about to hand your ass back to you kaltedesete…so…just stay home and enjoy some tejj and yabetew izaw balebet yifenda…

Reply
Selamawit Selassie May 11, 2010 - 7:02 am

I defiantly agree with you Misrie people should learn from the past we better sit home and enjoy the move…..

Reply
Jemal Muhe May 12, 2010 - 3:03 am

ag’azi??

Reply
Muluken Kassahun May 16, 2010 - 2:03 pm

gobez tenkek….

Reply

Leave a Comment