በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ግጭት ተቀሰቀሰ… 24 ተማሪዎች ተጎድተዋል

by ocean

መንግስታዊው ETV መነሻው በአንድ ተማሪ ሞባይል ስልክ መጥፋት ምክንያት ነው በሚለው እና የግል ጋዜጦች ምክንያቱ ክመጪው ምርጫ ጋር በተገናኘ አለመግባባት ነው በሚሉት የአዲስ አበባው ስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ግጭት እንደ ETV ዘገባ በ 24 ተማሪዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል::

Addis ababa university

Addis ababa university


የአዲስ አበባ ፖሊስ ሃይል በዩንቨርሲቲው በመግባት ግጭቱን በቁጥጥር ስል ማዋሉን እና ግቢውም በጸጥታ
ሃይሎች እስካሁንም ድረስ እየተጠበቀ ነው ተብሏል::
የግል ጋዜጣ ንብረት የሆነው አውራምባ ታይምስ ግጭቱን
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ ሲተላለፍ በነበረው የቴሌቭዥን ክርክር ገዢው ፓርቲ ‹‹ተቃዋሚዎች አገር መምራት አይችሉም›› ሲል በተደጋጋሚ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ያሉ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች የመድረክ ደጋፊ ለሆኑ ተማሪዎች ይህንኑ አባባል በመድገማቸው ትናንት ምሽት ከባድ ግጭት መቀስቀሱና ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተማሪዎችም ለጉዳት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ወደ ቅጥር ግቢው በመግባቱ ሁኔታዎች ሊረጋጉ መቻላቸውን የገለጹት የአይን ምስክሮች በርካታ ተማሪዎች ከካምፓሱ በመሸሽ በአካባቢው በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ተጠግተው ለማደር መገደዳቸውን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ የተከሰቱ መጠነሰፊ ተቃውሞዎች መነሻቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ምርጫም በአገሪቱ የተቀጣጠሉ መጠነ ሰፊ ተቃውሞዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንደተጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህ ዜና እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ ዩኒቨርስቲው በከባድ ጥበቃ ላይ መሆኑን የአውራምባ ታይምስ ዘጋቢ እቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጧል፡፡
ሲል ዘግቦታል::

Related Posts

9 comments

sew negn May 5, 2010 - 8:08 pm

“yemayimesil neger lemistih atinger” ale yagere sew. The reason could not be due to someones mobile phone. So many students have lost their phones before, but it would never been a reason for a strike.

Reply
sew negn May 5, 2010 - 8:09 pm

uffffffff meta degmo yihe fake mircha libetebiten! yet heden eniref?

Reply
Selamsew Teshome May 6, 2010 - 12:03 am

Ay ETV endachiberebe yinoral..eski ahun man yimut be mobile metfat mikiniyat ya hulu sew yidebadebal…Ketilowim grade yelelachew temariwoch bemesebaseb ale, woy mealti, …tegebi tiyake sinesa kelela neger ga mayayaz yetelemede guday hono mekretu betam yasazinal! Yasazinal!!

Reply
Mulugeta Tesfamariam May 6, 2010 - 8:04 am

u seems to b have no, or blind information. try to b informative not only open talk….

Reply
Mark Ebrahim May 6, 2010 - 10:03 am

@Mulugeta, did u mean that this thing didnt happen? or what?

Reply
Selamsew Teshome May 6, 2010 - 11:04 am

Muluget, don’t tell me what I know abt! I had gone through all such processes and can witness on in a very fairly balaced way the story, relationship, of AAU and State Media…But, if u still hv the inside stroy, please tell us and let’s see ur perspective coz nothing weaken ur argument except personalizing. Cheers!

Reply
samroon May 6, 2010 - 12:44 pm

aye etv zelalemun endewashe yeminor tultula. be 1 mobile metfat mekneyat? yemaymesel neger ale…hahahaha ere atasekugn.

Reply
Yabi Molla May 6, 2010 - 5:02 pm

@ Mulugeta pls don’t be this much positive thinker. And ETV Don’t teach us lying!

Reply
Mulugeta Tesfamariam May 13, 2010 - 1:02 pm

mark ebrahim, yabi molla,selamsew, / yes guys really! u didn realize that’s why we are breazing freely. things are no hapening,.

Reply

Leave a Comment