የመጀመርያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሴት ፓይለቶች እነማን ናቸው?

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 558
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የመጀመርያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሴት ፓይለቶች እነማን ናቸው?

Unread post by selam sew » 24 Dec 2015 09:15

ወ/ ሮ ሙሉመቤት እምሩ ከፋሺስት ጣልያን ወረራ በፊት የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን ድሬዳዋ ካጠናቀቁ በሇላ አዲስ አበባ ከሚገኘው ሊሴ ገብረማሪያም ት/ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ መልካም ፍቃድ የበረራ ትምህርት እንዲማሩ ተፈቅዶላቸው ኮሎኔል ሮቢንሰን እና ባህሩ ካባ ታይገር ሞዝ በምትባለው አውሮፕላን እንዳስተማሯቸውና በ1928 ዓም በጣሊያን ፋሺስት ወረራ ምክንያት የበረራ ትምህርታቸውን እንዳቇረጡ ታውቇል። ወይዘሮ ሙሉመቤት በህይወት ሳሉ "መነን" ይባል ለነበረው መፅሄት በጊዜው ስለነበረው የበረራ ትምህርት ቤትና ስለ አብራሪነታቸው ቃለ መጠይቅ አርጎላቸው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

Image
ወይዘሮ ሙሉመቤት እምሩ

ከጠላት ወረራ በሇላ በንጉሰ ነገስቱ የበላይ ጠባቂነት ኢምፔሪያል የአየር ክበብ በመባል አዲስ አበባ ውስጥ ተቇቁሞ የነበረው ክበብ፤ ለበረራ ትምህርት በሰዓት 22.5 ብር እያስከፈለ በሚያስተምርበት ጊዜ ወ/ ሮ አሰገደች አሰፋ በዚህ እድል በመጠቀም ኮሎኔል ሮቢንሰን የበረራ ትምህርት አስተምሯቸው በ1944 ዓም ለብቻቸው ለማብረር ችለዋል።

Image
ወይዘሮ አሰገደች አሰፋ

ሁለቱ ወይዛዝርት ፓይለቶች በአንድ ወቅት ተገናኝተው ስለበረራ ታሪካቸው ሲወያዩ ወ/ ሮ ሙሉመቤት በጦርነት ምክንያት ለብቻቸው ለመብረር ሳይችሉ ትምህርታቸው መቇረጡን እንደነገሯቸው ወ/ ሮ አሰገደች ለዚህ መፅሃፍ ደራሲ አስረድተዋል።

ስለዚህ፣ የመጀመርያዋ በረራ ትምህርት ቤት የገቡት ኢትዮጵያዊት ወይዘሮ ሙሉመቤት እምሩ ሲሆኑ የመጀመሪያይቱ ለብቻቸው አይሮፕላን አብራሪ ለመሆን ደግሞ ወይዘሮ አሰገደች አሰፋ ናቸው።
ምንጭ:
አቪዬሽን በኢትዮጵያ
ካፒቴን መኮንን በሪ

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”