የሰውለሰው ድራማ እና ኢቲቪ ፍጥጫ

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
selam sew
Leader
Leader
Posts: 604
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የሰውለሰው ድራማ እና ኢቲቪ ፍጥጫ

Unread post by selam sew » 01 Mar 2014 14:37

የሰውለሰው ድራማ እና ኢቲቪ ፍጥጫ

ዘወትር ረቡዕ ምሽት በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ሰው ለሰው አሁን በአዘጋጆቹና ድራማውን በሚሰራጨው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ድራማው ሳይጠናቀቅ ከስርጭት ይቋረጥ ይሆን የሚለው ድራማውን በቅርበት በሚከታተሉ ወገኖች ዘንድ ስጋት ፈጥሮአል፡፡

ለ124 ክፍሎች እንደተወደደ መዝለቅ የቻለው
ይህ ተከታታይ ድራማ ሊጠናቀቅ ጥቂት ክፍሎች ብቻ በቀሩት በዚህ ወቅት የድራማው አዘጋጆች ‹‹ኢቲቪ መጋቢት 13 ድራማውን አጠናቁ ብሎናል›› በማለት ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን ድራማውን የታሪክ ፍሰቱን እንደጠበቀ ለመጨረስ እስከ ግንቦት መጨረሻ ልንጠበቅ ይገባናል ባዮች ናቸው፡፡

‹‹ኢቲቪ አስገድዶን መጋቢት 13 አጠናቁ የሚለን ከሆነ ግን የድራማውን ታሪክ ባለበት ለማቆም እንገደዳለን እንጂ ለማጠናቀቅ ብለን ድራማውን ከታሪክ ፍሰቱ ውጭ አናስኬደውም ብለዋል የድሬ ቲዩብ የድራማው አዘጋጆች ምንጮች፡፡

Image

ከዚህ በተጨማሪም ለአዲስ አመት ዝግጅት የተላለፈው የድራማ ክፍል ክፍያ ላለፉት ሰባት ወራት እንዳልተከፋላቸው እና እንዲከፈላቸውም በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም የመዝናኛ ክፍል ሃላፊዎች ክፍያውን ለመፈፀም ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህንን የአዘጋጆቹን ጥያቄ ይዘን የኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅር ይልቃልን አነጋግረነው በሰጠን ምላሽ አንድ ድራማ በኢቲቪ ለመታየት የሚሰጠው የግዜ ገደብ 52 ሳምንታት ወይም አንድ አመት መሆኑን ፤ነገር ግን የህዝቡ ተቀባይነት ታይቶ የመታያ ግዜው ሊጨመር እንደሚችል ገልጾልናል፡፡

የሰው ለሰውን ጉዳይ በተመለከት፤ ባለው የህዝብ ፍቅር የተነሳ ለ3 ዓመታት መቆየቱን፤ ነገር ግን ባለፈው መስከረም 2006 ዓ.ም ድራማው በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ምን ያህል ግዜ እንደሚያስፈልግ ከድራማው አዘጋጆች ጋር ባደረጉት ውይይት የ6 ወራት ግዜ እንደሚበቃ ስምምነት ላይ መደረሳቸውን እና ኢቲቪም በዚሁ ስምምነት መሰረት መጋቢት 13 ቀን 2006 ዓ.ም ድራማው እልባት ያገኛል ብሎ እንደሚጠብቅ የገለጸ ሲሆን እስካሁን ግን የግዜ ማራዘም ጥያቄ እንዳልቀረበ ተናግሯል፡፡

ይህ ማለት ግን ድራማው የግዴታ በተባለው ቀን ያልቃል ወይም እንዲጨርሱ ይገደዳሉ ማለት እንዳልሆነ የጠቀሰው ፍቅር ይልቃል የድራማው አለመሰልቸት እንዲሁም ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች ታይተው ተጨማሪ ግዜ የመጨመር እድሉ መቶ በመቶ ዝግ አይደለም ብሏል፡፡

ክፍያው አልተፈፀመልንም ለሚለው ጥያቄ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት መረጃ እንደሌለው እና ጉዳዩን በቀጥታ የሚመለከተው የድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል መሆኑን ጠቁሟል ታማኝ ምንጮቻችን ግን የድርጅቱ የቀድሞ ስራ አስኪያጅ 4ት ጊዜ ያህል ክፍያው እንዲፈፀም ትዕዛዝ ለመዝናኛ ክፍል ማስተላለፋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ድራማው ተተርጉሞ በዲኤስ ቲቪ እንዲተላለፍ የተጀመረው ጥረት በኢቲቪ ሀላፊዎች የቀረበውን ፕሮፖዛል በፍጥነት ምላሽ መስጠት ባለመቻላቸው እና በጎ ምላሽ ባለማግኘቱ እስካሁን አልተሳካም ቢባልም የኢቲቪ ምክትል ስራ አስኪጅ የሆነው አቶ ፍቅር ይልቃል የድራማው ፕሮዳክሽን ባለመጠናቀቁ በዲኤስ ቲቪ ሊቀርብ አለመቻሉን እና ኢቲቪም ድራማው በዲኤስ ቲቪ እንዲታይ ሙሉ ፍላጎት እንዳለው እና ወደፊት ይቀርባል የሚል ሙሉ እምነት እንዳለው ተናግሯል፡፡

ሪፖርተር ቢኒያም ገ/ክርስቶስ

Source: Facebook


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”