”ጠንቋይ” ታምራት ገለታ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተባለ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
Post Reply
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

”ጠንቋይ” ታምራት ገለታ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተባለ

Unread post by ኦሽንoc » 12 Aug 2009 14:43

[center]ዓቃቤ ሕግ በሞት ይቀጣልኝ ሲል ጠየቀ[/center]
(ረቡዕ ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. August 12, 2009)፦”ባለአውሊያ” እና ”ባለከራማ” ነኝ በማለት ከአሥር ዓመት በላይ በጥንቆላ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው አቶ ታምራት ገለታን ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. የዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ”ጥፋተኛ” ያለው ሲሆን፣ ንብረቶቹም ተወርሰው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ ወሰነ። ዓቃቤ ሕግ በሞት ይቀጣልኝ አለ።

"ጠንቋይ" ታምራት ገለታ ከስድስት ግብረአበሮቹ ጋር ተከስሰው የነበሩባቸው ስድስት የተለያዩ ክሶች በዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማጥፋትና የመግደል ሙከራ በማድረግ፣ የሰው ገንዘብና ንብረት በማታለልና በማጭበርበር፣ ሴቶችን በመድፈር በሚሉ ነበር። "ጠንቋይ" ታምራት በተከሰሰባቸው ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብሏል። አንደኛው ተከሳሽ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩ ክሱ ተነስቶ ነበረ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ አምስቱ ተከሳሾችም ጥፋተኛ ተብለዋል።

የጥፋተኝነት ውሳኔውን ፍርድ ቤቱ ካሰማ በኋላ ከሳሽና ተከሳሽ የቅጣት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ አቶ ታምራት በተደራራቢ ወንጀሎች የጥፋተኝነት ውሳኔ መሰጠቱን ገልጾ፤ ተከሳሹ በሞት ፍርድ እንዲቀጣለት ጠይቋል። የተከሳሽ የአቶ ታምራት ገለታ ጠበቃ ደግሞ ደንበኛቸው ከዚህ ቀደም ወንጀል ሠርቶ የማያውቅ መሆኑንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በመግለጽ ቅጣቱ እንዲቀልለት ጠይቋል።

አቶ ታምራት ከጥንቆላ ውጪ ገቢ ያገኝበት የነበረ ሥራ እንዳልነበረው የገለጸው ፍርድ ቤቱ፤ በጥንቆላ ሥራ ያፈራቸው ንብረቶች ሙሉ ለሙሉ ውርስ ሆነው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ በዛሬው ችሎቱ ወስኗል። እንዲወረሱ የተወሰነባቸው 153 ሺህ 351 ብር በአቢሲኒያ ባንክ ዑራኤል ቅርንጫፍ፣ ሁለት መኪኖች፣ በፍቼ ከተማ የሚገኝ ሆቴልና መሬት፣ ወርቅና ልዩ ልዩ በፖሊስ ኤግዚቢትነት የተያዙ በርካታ ንብረቶች መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል።

የከሳሽና የተከሳሽን የቅጣት ሃሳብ ፍርድ ቤቱ ካደመጠ በኋላ፤ ለነሐሴ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ቅጣት ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቷል።
Source:http://www.ethiopiazare.com/the-news/1- ... rat-geleta

ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

Re: ”ጠንቋይ” ታምራት ገለታ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተባለ

Unread post by ኦሽንoc » 12 Aug 2009 15:03

ስለ ጠንቋዩ ታምራት ገለታ ነጠላ ዜማ
እያንጉዋለለ
[youtube]http://www.youtube.com/watch?v=cR59fEn9tHk[/youtube]

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”