‘ጫቱ ላይ ያለውን ተባይ ለማጥፋት እና ጫቱ ‘ሻይን’ እንዲያደርግ፣ እንዲያምር በሚል ዲዲቲ ይረጭበታል

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 591
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

‘ጫቱ ላይ ያለውን ተባይ ለማጥፋት እና ጫቱ ‘ሻይን’ እንዲያደርግ፣ እንዲያምር በሚል ዲዲቲ ይረጭበታል

Unread post by selam sew » 20 Mar 2018 08:05

‘ጫቱ ላይ ያለውን ተባይ ለማጥፋት እና ጫቱ ‘ሻይን’ እንዲያደርግ፣ እንዲያምር በሚል ዲዲቲ ይረጭበታል…’

ጫት ላይ የሚረጨው ዲዲቲ ነገር…

ለወጣ ትንኝ ማጥፊያ በሚል ወደ ሐገራችን የገባው ዲዲቲ በአሁኑ ወቅት በሐገራችን በሕግ የተከለከለ ኬሚካል ቢሆንም ገበሬው ከሕገወጥ ሻጮች እየገዛ ጫት እና የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች ላይ ይረጨዋል ይለናል ይህ የትዕግስት ዘሪሁን ዘገባ…

በተለያዩ ሐገራት የተከለከለው ይህ ኬሚካል ለጉበት፣ ለነርቭ፣ ለካንሰር እና ለመሃንነት እንዲሁም የጤና እክል ያለባቸው ሕፃናት እንዲወለዱ ምክንያት ይሆናል ነው የሚባለው፡፡

ዘገባው እንደሚለው ጭራሽ አንዳንድ ገበሬዎች ለረጅም ጊዜ የሚያስቀምጡት በቆሎ ነቀዝ እንዳይበላው በሚል በዲዲቲ አሽተው ያስቀምጡታል…

ይህን ለጤና አደገኛ የሆነ ኬሚካልን ገበሬዎች እንደማንኛውም ሸቀጥ በቀላሉ ማግኘት መቻላቸውና እንደልባቸው እንደፀረ-ተባይ ኬሚካል መጠቀማቸው ሊያስከትል የሚችለው ማህበራዊ የጤና ጠንቅ የትየለሌ ነው ነው የሚባለው፡፡

16 ሚሊየን ያህል ኢትዮጵያውያን የሚቅሙት ጫት ላይ ዲዲቲ የመረጨቱ ነገር አሳሳቢ ነው የሚለው ዘገባው፤ ጫቱ ላይ ያለውን ተባይ ለማጥፋት እና ጫቱ ‘ሻይን’ እንዲያደርግ፣ እንዲያምር በሚል ዲዲቲ ይረጭበታል ይላል፡፡

በጫቱ ቅጠል ውስጥ ሰርጎ የሚገባው ዲዲቲ ቢታጠብም አይወጣም የሚሉት ባለሞያ መርዛማው ኬሚካል አፈር ውስጥ ከ15 ዓመት፤ ውሃ ውስጥ ደግሞ ከ150 ዓመታት በላይ ይቆያል ይላሉ…

(ትዕግስት ዘሪሁን)

ሙሉውን ያዳምጡ...

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”