የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ....20 ተሽክርካሪዎች

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
Post Reply
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ....20 ተሽክርካሪዎች

Unread post by ኦሽንoc » 07 Oct 2009 19:18

የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ....20 ተሽክርካሪዎች

እስከ መቼ?
Wednesday, 07 October 2009
(በብርቱካን ፈንታ)

ትናንት ጠዋት እንደወትሮው የጦር ኃይሎች መንገድ በትራፊክ እንደተጨናነቀ ነበር፡፡ በሥራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ላይ የትራፊክ ግርግር የተለመደ በመሆኑ ሁሉም ወደ ስራው ከመጣደፍ በስተቀር የትራፊኩን መጨናነቅ ልብ ያለው አልነበረም፡፡

Image

በግምት ከጠዋቱ 2፡20 ሰዓት ሲሆን ግን ለየት ያለ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ጩኸት በረከተ፡፡ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-09365 ኢት. የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የፈጠረው አደጋ እጅግ ሰቅጣጭ ነበር፡፡

አውቶቡሱ ወደ ሐረር የሚጓዙ መንገደኞችን እንደጫነ ከጦር ኃይሎች ወደ ሶስት ቁጥር ማዞሪያ ሲገሰግስ በተለምዶ ሦስት ቁጥር ማዞሪያ (ቶታል) አደባባዩ አካባቢ ሲደርስ የመጣበትን ፍጥነት መግታት ተሳነው፡፡ እናም አውቶቡሱን ጨምሮ ሌሎች ብዛት ያላቸው ተሸከርካሪዎች በፍጥነት ያሽከረክሩ ስለነበር እርስ በርሳቸው እየተላተሙ ለጉዳት ተዳረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኘኑነት ባለሙያ ዋና ሳጅን አሰፋ መዝገቡ ክስተቱ በ20 ያህል ተሸከርካሪዎች ላይ አደጋን ያስከተለ መሆኑን፣ ከተሽከርካሪዎቹ መካከል 12ቱ ከባድ፣ 8 ያህሉ ደግሞ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል፡፡

እስከ ትናንት ቀትር ድረስ ባለን መረጃ አንድ አሽከርካሪ የሞተ ሲሆን በሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

ዋና ሳጅን አሰፋ እንዳሉት በኢትዮጵያ ደረጃ በአስከፊነቱ ቀዳሚ በሆነው በዚሁ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ሰዎች ብዛት፣ የወደመው ንብረት ትክክለኛ ግምት እስከ ትላንትና ማምሻውን ድረስ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

በቦታው በደረስንበት ሰዓት ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሸከርካሪዎች ተደራርበውና ተጨፈላልቀው አንዳንዶቹም የመኪኖቹን ዓይነት መለየት በሚያዳግት ሁኔታ ተለውጠው ለመመልከት ችለናል፡፡

አደጋው በተከሰተበት ሰዓት በአካባቢው የነበሩ አንዳንድ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት የአደጋው አስከፊነት የሟቾቹን ቁጥር ከዚህ በላይ ከፍ ሊያደርገው ይችላል የሚል ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዋና ሳጅን አሰፋ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ሁኔታውን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የድንገተኛና እሳት አደጋ እንዲሁም የአካባቢው ኅብረተሰብ ላሳዩት ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በቦታው በስራ ላይ የነበሩ ትራፊክ ፖሊሶችም እንደገለፁት የተሽከርካሪዎቹ ፍጥነት አደጋውን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አደጋ ባደረሰው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ የሐረር መንገደኞች እስከ ትላንት ቀትር ድረስ ተለዋጭ ተሸከርካሪ ስላልቀረበላቸው ቅሬታቸውን
ሲገልፁ ተስተውለዋል፡፡

Image
Image
Image
Image
For more Pictures Visit Ethiopian Reporter
Source: Ethiopian Reporter

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ....20 ተሽክርካሪዎች

Unread post by selam » 09 Oct 2009 22:27

እስከ መቼ? E-mail
Wednesday, 07 October 2009

Image(በብርቱካን ፈንታ)

ትናንት ጠዋት እንደወትሮው የጦር ኃይሎች መንገድ በትራፊክ እንደተጨናነቀ ነበር፡፡ በሥራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ላይ የትራፊክ ግርግር የተለመደ በመሆኑ ሁሉም ወደ ስራው ከመጣደፍ በስተቀር የትራፊኩን መጨናነቅ ልብ ያለው አልነበረም፡፡በግምት ከጠዋቱ 2፡20 ሰዓት ሲሆን ግን ለየት ያለ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ጩኸት በረከተ፡፡ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-09365 ኢት. የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የፈጠረው አደጋ እጅግ ሰቅጣጭ ነበር፡፡

አውቶቡሱ ወደ ሐረር የሚጓዙ መንገደኞችን እንደጫነ ከጦር ኃይሎች ወደ ሶስት ቁጥር ማዞሪያ ሲገሰግስ በተለምዶ ሦስት ቁጥር ማዞሪያ (ቶታል) አደባባዩ አካባቢ ሲደርስ የመጣበትን ፍጥነት መግታት ተሳነው፡፡ እናም አውቶቡሱን ጨምሮ ሌሎች ብዛት ያላቸው ተሸከርካሪዎች በፍጥነት ያሽከረክሩ ስለነበር እርስ በርሳቸው እየተላተሙ ለጉዳት ተዳረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኘኑነት ባለሙያ ዋና ሳጅን አሰፋ መዝገቡ ክስተቱ በ20 ያህል ተሸከርካሪዎች ላይ አደጋን ያስከተለ መሆኑን፣ ከተሽከርካሪዎቹ መካከል 12ቱ ከባድ፣ 8 ያህሉ ደግሞ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል፡፡

እስከ ትናንት ቀትር ድረስ ባለን መረጃ አንድ አሽከርካሪ የሞተ ሲሆን በሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

ዋና ሳጅን አሰፋ እንዳሉት በኢትዮጵያ ደረጃ በአስከፊነቱ ቀዳሚ በሆነው በዚሁ የትራፊክ አደጋ የተጎዱ ሰዎች ብዛት፣ የወደመው ንብረት ትክክለኛ ግምት እስከ ትላንትና ማምሻውን ድረስ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

በቦታው በደረስንበት ሰዓት ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሸከርካሪዎች ተደራርበውና ተጨፈላልቀው አንዳንዶቹም የመኪኖቹን ዓይነት መለየት በሚያዳግት ሁኔታ ተለውጠው ለመመልከት ችለናል፡፡

አደጋው በተከሰተበት ሰዓት በአካባቢው የነበሩ አንዳንድ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት የአደጋው አስከፊነት የሟቾቹን ቁጥር ከዚህ በላይ ከፍ ሊያደርገው ይችላል የሚል ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዋና ሳጅን አሰፋ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ሁኔታውን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የድንገተኛና እሳት አደጋ እንዲሁም የአካባቢው ኅብረተሰብ ላሳዩት ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በቦታው በስራ ላይ የነበሩ ትራፊክ ፖሊሶችም እንደገለፁት የተሽከርካሪዎቹ ፍጥነት አደጋውን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አደጋ ባደረሰው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ የሐረር መንገደኞች እስከ ትላንት ቀትር ድረስ ተለዋጭ ተሸከርካሪ ስላልቀረበላቸው ቅሬታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል[img][img][/img][/img]
Last edited by selam on 09 Oct 2009 22:50, edited 1 time in total.

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ....20 ተሽክርካሪዎች

Unread post by selam » 09 Oct 2009 22:42

በዋሽንግተን በርካታ ኢትዮጵያውያንና... E-mail
Wednesday, 07 October 2009

በዋሽንግተን በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በታክሲ ሥራ ፈቃድ ሙስና ተከሰሱ
(በጋዜጣው ሪፖርተር)

አላግባብ በሆነ መንገድ የታክሲ ሥራ ፈቃድ ለማግኘት ሲሉ የዋሽንግተን ከተማ የታክሲ ኮሚሽን ሊቀመንበርን ጉቦ በመስጠት አሲረዋል ያላቸውን 39 ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ትውልድ ባላቸው ላይ አቃቤ ሕግ አርብ ዕለት ክስ መሰረተ፡፡

ወደ 330ዢ000 የአሜሪካ ዶላር ይጠጋል በተባለው በዚህ የጉቦ ቅሌት ዋነኛ አቀነባባሪዎችና መሪዎች ተብለው የተከሰሱት ግለሰቦች የ51 ዓመት ዕድሜ ያለው ይትባረክ ስዩሜ፣ የ47 ዓመት ዕድሜ ያለው ብርሃነ ለገሠና የ53 ዓመቱ አማኑኤል ግርማጽዮን እንደሆኑ በአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር የዋሽንግተን አቃቤ ሕግ ያወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

የተቀሩት 36 ግለሰቦች በከተማዋ የታክሲ አሽከርካሪዎች ሲሆን እነዚህኞቹ የተከሰሱት ደግሞ በነፍስ ወከፍ የታክሲ ባለቤትነት ፈቃድ በጉቦ ለማግኘት በመሞከር ተጠርጥረው ነው፡፡

ከጠቅላላው 330ዢ000 ዶላር ውስጥ 220ዢ000ውን ሶስቱ ግለሰቦች የሰጡ እንደሆነና የተቀረውን 110ዢ000 ዶላር ደግሞ 36 የታክሲ አሽከርካሪዎች እንደሰጡ ሪፖርተር ያገኘው የክስ ቻርጅ ያሳያል፡፡

ግለሰቦቹ ክሱ ሊመሰረትባቸው የቻለው የዋሽንግተን ከተማ የታክሲ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሊዮን ስዌይን ጉዳዩን ከሦስት ዓመት በፊት ለመንግሥት አሳውቀው ከፌዴራሉ የምርምር ቢሮ (FBI) ኤፍ.ቢ.አይ ጋር በስውር በተደረገ ክትትል መሆኑንም የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

በማቀነባበሩ ሂደት የተከሰሰቱትን ሶስቱን ግለሰቦች ጨምሮ 25ቱ ተከሳሾች ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ አይደለንም ብለው የዕምነት ክህደት ቃል ሰጥተዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ፣ ባለፈው ሳምንት የዋሽንግተን ምክር ቤት አባል የጂም ግራሃም፣ ጽህፈት ቤት ሹም ቴዲ ሎዛ ታስረዋል፡፡

ቴዲ ሎዛ ከተከሳሾቹ የ1ዢ500 ዶላር ጉቦ በመቀበል የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥ ሕግን በማስቀየር ሙከራ ወንጀል ተጠርጥረው እንዲታሰሩ ተወስኗል፡፡

"ይህ ክስ በጣም ብርቱና አሳሳቢ ነው፡፡ የታክሲ ኢንዱስትሪያችን መሠረት እያናጋ ያለውን የሙስና ችግር የሚያሳይ ነው፡፡ ሙስናን ከስር መሠረቱ ለመንቀል በአስተዳደራችን ያለውን ቁርጥ አቋቋምም የሚያሳይ ነው" ሲሉ የዋሽንግተን ተጠባባቂ አቃቤ ሕግ ተናግረዋል፡፡

የዋሽንግተን የኤፍ ቢ አይ ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው "የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት የብርና የጉቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የተሣፋሪዎች ደህንነትም ጉዳይ ነው" በማለት የጉዳዩን አሣሣቢነት ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የዋሽንግተን ከተማ ምክር ቤት ተመራጭ የቴዲ ሎዛ አለቃ ጂም ግራሀም በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2004 ለአንድ ወር በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ የጂም ግራሀም ጉብኝት አብዱ ጫሙ በተባሉ ኢትዮጵያዊ የተመቻቸ እንደነበርና የጂም ግራሀም የአውሮፕላን ወጪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቆይታቸው ደግሞ በሸራተን አዲስ እንደተሸፈነ አቶ አብዱ በጊዜው ለጋዜጠኞች ተናግረው እንደነበር ዋሽንግተን ፖስት ይገልፃል፡፡

አብዱ ጫሙ ከጂም ግራሀም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የተለያዩ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

ሐሙስ እለት የኤፍ ቢ አይ ሰዎች የግራሀምን ቤት በርብረው ብዛት ያላቸው ሳጥኖችን ይዘው መውጣታቸውንም የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

ግራሃም ከቴዲ ሎዛ ጋርም ይሁን ከተከሳሾቹ ጋር በወንጀል ሥራ ላይ እንዳለተሳተፉ ተናግረዋል፡፡

"ሚስተር ሎዛ ስለዚህ ጉዳይ አንድም ጊዜ አናግሮኝ አያውቅም፡፡ ጉዳዩ በተነሳበት ስብሰባ ተሳትፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእኔ ግን የታክሲ ፈቃድ አሰጣጥን ሕግ በሚመለከት አንድም ጊዜ አማክሮኝ አያውቅም" ብለዋል ግራሃም፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስለ ጂም ግራሃም ጉብኝት ተጠይቆ "ስለ ጉዳዩ ምንም መረጃ የለኝም" ብለዋል፡፡

"አልመጡም ነው ወይንስ ስለመምጣታቸው መረጃ የለንም ነው የምትሉት?" ለሚለው ጥያቄ የኤምባሲው ምላሽ "ግለሰቦች፣ ተመራጮች እንኳን ቢሆኑ፣ በግላቸው የሚያደርጉት ጉብኝትን በሙሉ አንከታተልም" ነበር፡፡

ሙስናዉን በማቀነባበር የተከሰሱት ሶስት ግለሰቦች የክስ ቻርጅ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የ36ቱን ሌሎች ተከሳሾች የክስ ቻርጅ ከዚህ ያንብቡ

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”