የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 17 Feb 2012 16:03

ካምፓላ መአት የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች አሉ ነው የምትለኝ ? ገሪም ነው !
ይገርምህል በኢትዮጵያ ከነበረው የቀይ ሽብር ዘመቻ እልቂት የባሰ ከሩዋንዳና ቡሩንዲ አካባቢ ተነስቶ እስከ ኡጋንዳ በደረሰ ጊዜ እዛ ስለነበርኩ ብዙ ክፉና የማይረሱ ነገሮችን ተመልክቻለሁ::
እነዚያ ሰዎችና እኛ አፈጣጠራችንም ይለያያል ብዬ ብዙ ግዜ ድምዳሜ ላይ ሁሉ እደርስ ነበር ግን ነገር ሲያልፍ ተረት ይሆናል እንደሚሉት እየሆነ ነው እንጂ እኛም ሃገር በደንብ የተደረገ ነገር ነው::
እናልህ ወንድምዬ መቼም ያንዱ ሞት ላንዱ ሽረት ነው ይባል የለ በእልቂቱ ዘመን ያላሰብኩት ነገር ገጠመኝና እለት ተለት ምግቤም መኝታዬም ሆቴል ነበር ታዲያልህ ያኔ የኢትዮጵያ ምግብ ቁጥር አንድ ተመጋቢ ነበርኩልህ ::ማደሪያ ሳይኖረኝ ማደሪያ ያጣ አስጠግቼ አጠገበኝ :
ሳሙኤል ይባላል ወላጆቹቹ ኡጋንዳውያን ናቸው የተወለደው ግን ሩዋንዳ ነው ኡጋንዳን በጭራሽ አያውቃትም በጣም የተመቻቸ ኑሮ ይኖር ነበር ችግሩ ሲነሳ ሳሙኤል የመጀመሪያው ሰለባ ሊሆን የሚችል መሆኑን ቀድሞ ያውቃል ቢሆንም ሳይታሰብ ነገሩ አስጊ ሆነ ቤተሰቡም በአንድ ሌሊት ተበተነ እሱም መልኩን ለውጦ ከመሃላቸው ያመልጥና ወደ ኡጋንዳ ይመጣል ኡጋንዳ ማንንም አያውቅም : አይገርምህም ኡጋንዳ በገባ በሁለተኛው ቀን ከኔ ጋር ተገናኘን በጥቂት ደቂቃዎች ወሬ በኋላ ሊለየኝ አልፈለገም የዛንው ቀን አብረን ውለን አደርን ሌሊቱን ሙሉ ታሪኩን ሲያጫውተኝ ነጋ::
የጦርነቱን አጀማመር ስለ ኪጋሊ ቤተሰቡና ኑሯቸው ስሎእ ፍልሰታቸውና መበተናቸው ወዘተ
በጣም ተደነቅኩ አከበርኩት ማድረግ ስላለበትም ሁኔታ እና ቤተሰቦቹን እንዴት ማግኘት እንደሚችል በሚያደርገው ትግል ውስጥም ሙሉ አጋሩ ሆንኩኝ በተለይም የትንሿ እህቱ ነገር እረፍት ነሳው ውሎ አድሮ ባደረገው ጥረት እግዚአብሄር ትልቅ ብሥራት አሰማው : ትንሿን እህቱን እዚያው ኡጋንዳ ውስጥ አገኛት ይሄ የሆነው ከኔ ጋር በተገናኘን በወሩ ይሆናል ታዲያ የዛን ቀን ወደማታ ጠራኝና ከዛሬ ጀምሮ እዚህ አናድርም አንተም እኔም ሆቴል እናድራለን እዚህም እያበሰልን አንበላም ሆቴል እንበላለን አለኝ
ይሄ ሰውዬ መቃም ጀመረ እንዴ ? አልኩኝ በሆዴ ቂጣ እየጋገርን በውሃ እያማግን የምንበላ ሰዎች በአንድ ጀምበር ሆቴል እንግባ ይለኛል እንዴ ? ለብሄራዊ ቡድን አልተመረጥን ወይ ዩ ኤን ኤች ሲ አር አልተቀበለን ምንድነው ነገሩ ? አልኩና ገረመኝ ወዲያው መኪና ተኮናተረና በሹፌር እየተነዳን ወደ ደቡብ ኡጋንዳ አመራን ሁለት ሶስት ከተሞችን እንዳለፍን ነገሩ አስተማማኝ ስላልነበረ እኛ ቀረንና ሹፌሩ ሌሊቱን ተጉዞ ልጅቱን እንዲያመጣ ተነገረውና ቀጠለ : እኔ ግን ሳሙኤልን ለዚህ ሹፌር ብር በድንብ ስጠው አልኩት .... እንደዚያ አይነት ሰው አይቼ አላውቅም ብቻ በቆምንባቸው አራት ቦታዎች አራቴ በልቷል ትንሽ እንደሄድን እርቦኛል ይልና ይበላል አሁንም ትንሽ እንደሄድን እራበኝ ይላል ብቻ መብላት መብላት አሁንም መብላት ነው መፈክሩ እንዲሁ እንደበላ ሸኘነውና በማግሥቱ ልጅቷን ይዞ ከተፍ አለ::
የሳሚ ደስታ እስካሁን አይረሳኝም አብሬው ስደሰት ቆየሁና ....እዚህጋ የገረመኝን ልንገርህ ሴት እህቱን በዚያ ቀውጢ ጊዜ ለአንድ ሹፌር ይዘህልኝ ና ብሎ ሲልከው ይጠራጠረዋል አልያም ያስጠነቅቀዋል እያልኩ ብጠብቅ ምንም እንደውም ትዝም አላለውም ነበር እኔ ግን ክፋቴ ይሁን ደንቆሮነቴ አላውቅም ዝም ማለት አቅቶኝ ነበር:: ብታምንም ባታምንም አሁንም ቢሆን እንዲህ ያለ ነገር ቢገጥመኝ እጠራጠራለሁ እነሱኮ ምንም ምንም አይሉም ምናልባት ተናግረው ምንም ስለማያመጡ ይሆናል ብዬ ነው የማምነው እንጂ ንጹህ ስለሆኑ አይደለም እንደውም እስከ ቅርብ ሰዎች ድረስ ዝም የማይባባሉ ሌቦች እንደሆኑ ነው የማውቀው::
ሌላው ደሞ ሹፌሩ እህቱን ሊያመጣ ሲሄድ እኛ ብቻችንን ስለነበርን ልጠይቀው ደጋግሜ የቃጣሁት ነገር ቢኖር ይሄን ያህል መአት ገንዘብ ይዘህ እንዴት ከኔጋር ቂጣ ስትበላ ከረምክ?
የሚል ነበር ነገር ግን በመጨረሻ ትዕግስቴ አስደሰተኝ : ራሱ ነገረኝ እህቴ የት እንደደረሰች ሳላውቅ ምንም ማድረግ አልፈለኩም ነበር አለኝ:ምናልባት ገንዘቤ ቢያልቅና ና እዚህ ነኝ ድረስልኝ ብትለኝና baይኖረኝ ራሴን ከማጥፋት የተሻለ አማራጭ አይኖረኝም በዚህም ላይ ሴት ስለሆነችም በደህና አገኛታለሁ አላልኩም ነበር መታከም እንዳለባትና ከወዲሁ መዘጋጀት ስለነበረብኝ ነው ራሴን መቸገር አለብኝ ብዬ ያስቸገርኩት ብሎ ሲለኝ አደነቅኩት::
አይ የኔ ነገር የጀመርኩትን ትቼ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባሁ ጫፍ ካገኘሁኮ መመለስ አላውቅም::
ግን ደሞ ተናግሬ የሚወጣልኝ ወይንም መናገር የማልችል ሰው ስልሆንኩ ይሆናል መጻፍ ስጀምር አፌ የተፈታ ሁሉ ይመስለኛል
ብቻ ዋናው ነገር ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶችን እለት በእለት መጎብኘት እየመረጥኩ መብላትና ያማረ ልብስ መልበስ የቻልኩት: በዚያው ብዙ ነገሮችም ተቃኑና ሁኔታዎች መልክ መልክ ያዙ ..... ሴትዮዬንም ለስራ መጥታ ሳለ አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ተገናኝተን ለመተዋወቅ ቻልኩ ::
ይሄንን እንኳን ከዚህ ቀደም አጫውቼያችኋለሁ ብቻ ታሪክ ተለወጠ እልሃለሁ::
በተለይ እዚያው ካባላጋላ የሃይልና የተፈጥሮ ፕሮዤ ነበረ ..... ኤጭ ተወኝ እባክህ ወንድሜ አታስለፍልፈኝ::
ፊያሜታን ለማየት ቸኮልኩኝ መሰለኝ ምክንያቱም ካምፓላ የፍቅር ከተማ ናት ሰላማዊ ከተማ ናት በተለይም የቢክቶሪያ ሃይቅ ሰላማዊውን የፍቅር ንፋስ ወደከተማው ያነፍሳል እንደሚባልለት የካምፓላ ፍቅር ዋዛ እንዳይመስልህ ::
ለነገሩ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ሱዳንን የሚያህል የፍቅር ሃገር አለ ብዬ አላምንም የምን አላምንም ነው የለም:: ሱዳን ህዝቡም ባህሉም ልዩ ነውሰስቲ ፊያሜታ ጊላይን ይቅርታ ፊአ ሜታን አስተዋውቀን ::
ቸር ያቆየን


ዋርካ ደርቃለች ነው ጠፈፍ ብላለች የምትለው ፕሮፓጋንዳ ነው እንዴ ?
የአህያዋ ተረት ትዝ አለኝ ነገሩ ትንሽ ባለግ ያለ ተረት ስለሆነ ልተወው ግን አህያ በመጨረሻ
(ካላረገዝኩ አላምንም) ያለችው አስተማሪነት ያለው ቁም ነገር ነው ::
ዋርካም እንደዛ ነው ካሁን በኋላ ያጸዱታል ብዬ አልገምትም ::

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 18 Feb 2012 15:32

ሰላም ሰላም


በጋሽ አስረስ ገዳ ልጅ ላይ የተፈጸመውን አስዛኝ ታሪክ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ይዤ መጥቻለሁ::ዜናውን የሰራው ጋዜጠኛ ቡሬ እያለ ሲሆን ቦሬ በሚለው አስተካክሉት::
Attachments
Screen Shot 2012-02-18 at 1.19.00 PM.png
Screen Shot 2012-02-18 at 1.19.00 PM.png (1.58 MiB) Viewed 2945 times

ሞፊቲ
Jogger
Jogger
Posts: 33
Joined: 03 Jan 2012 14:19
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ሞፊቲ » 18 Feb 2012 15:46

http://www.addisadmassnews.com/index.ph ... Itemid=994


ከላይ ያለው ሊንክ ቀደም ሲል ፖስት ያደረኩተን ዘና የምታገኙበት ነው::በጸዳለ ላይ በደረሰው ነገር ከልብ አዝኛለሁ::የጋሽ አስረስ ልጆች አብሮአደጎቻችን በመሆናቸውም ጭምር በደረሰባቸው ሃዘን
ስሜቴ ተነክቶአል::


እግዜር መትስናናቱን ይስጣቸው::ትሰዳለንም አምላክ ይማራት! ባሏም የቦሬ ልጅ ቢሆንም እስካሁን ላውቅው አልቻልኩም::

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 20 Feb 2012 13:24

እንዴት ያናድዳል በናታቹ
ይህ የሞዛምቢክ ኢንተርኔት
ሁለት ቀን ሙሉ እኮ ነው የሞከርኩት ዋርካ ለመግባት....
አቅሙ አልችል ብሎት እምቢ አለኝ እንጂ
ሂሂሂ አሁን የኮምፒተሬን ህመም የማወራበት ሰአት እንዲኖረኝ ትፈልጋላቹ
ለምን እንደጤፋሁ ማወቅ ነው ወይስ የጀመርኩት የፊአ-ሜታ ታሪክ ማወቅ ነው ምትፈልጉት
የራሳቹ ጉዳይ
እኔው መልሱን ልስጣቹ
እና እንዲህ ልቀጥል
.......................................//..................................
እኔና ፊአ-ሜታ በጣም ብዙ ያወራን ይመስለኛል እዛች ምግብ ቤት ሆነን
ምግቡን ግማሽ ያህል እንደበላሁ ነው ትዝ የሚለኝ
የሆነ ደስስስስስ የሚል ስሜት ተሰምቷቹ ያውቃል....
እና ያ ስሜት የምግብ ፍላጎታቹን ሲዘጋ ተሰምቷቹዋል
እንደዛ ነው የሆንኩት የዛን ቀን
ነርስ ናት
ስራ እየፈለገች ... እና የዛን ቀንም ዪኒሴፍ ቢሮ ሄዳ ስትመለስ ነበር ያገኘኃት
ከአስመራ በሱዳን በኩል እንደወታች ነገረችኝ
የምሰራው ከደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ካለች ትንሽዬ የድንበር ላይ ከተማ እንደሆነ ነገርኳት
ሰአቱ እንዴት ይሮጣል ግን ሰው የመንፈስ ምግብ ልመገብ ብሎ ሲጀምር
ኤኒዌይ
> አንተ መሄድ አለብኝ... ብዙ ቆየሁ... አለችኝ
+ እረ እኔም መሄድ ነበረብኝ... "የያዘኝ ይዞኝ እንጂ" ብዬ ለራሴ አጉተምትሜ...
ሂሳባችንን ከፍለን ወጣን
ሹፌሬ እስከሚጠብቀኝ ቦታ በእግር ሄድንና.... ላርድስሽ አልኳት
> ኖ ኖ ቅርብ ነው ቤት.. በ-ቦዳ ሄዳለሁ.... አለችኝ (ቦዳ = ሞተር-ብስክሊሊት ታክሲ)
+ ተይ ላድርስሽ... ምንም ችግር የለውም እኮ... እግረ-መንገዴን እው እኮ
> አይ ይቅርብኝ... አመሰግናለሁ
አለችኝ እና ተለያየን
መኪና ውስጥ ገብቼ ሳያት,.,,... ፋሲካ-ሆቴል \ፊትለፊት ያለውን መንገድ ተሻግራ ሄደች
ካሁን አሁን ቦዳ ትይዛለች ብዬ ስመለከታት... በእግሯ አቀጠነችው
ቤቷ .. የት እንደሆነ ባላውቅም.. እሩቅ መሰለኝ
መኪናዬ ተነሳች.... ወደ-ስራ ልሄድ ነው
በእግሯ ስትኳትን በርቀት አየኃትና
አይ ያበሻ ነገር ብዬ ታዝቤ እንደመተው
ደወልኩላት
አይ የኔ ነገር... አሁን ተለይታኝ ናፈቀችኝ ማለት ነው
ፍቅር በስተርጅና ... ሲለኝ ሰማሁት ሞፍቲ
> ሄሎ
+ እኔ ነኝ.... ግን ልክ አይደለሽም
> ምነው
+ ቦዳ ይዛለሁ ብለሽ በእግርሽ እየሄድሽ አይደለም.... ? እያየሁሽ እኮ ነው.... ምናለበት ቤትሽ ባደርስሽ
> ዎክ ማድረግ ስለፈልኩ እኮ ነው... ለክፉ አይደለም
+ ኤኒዌይ ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል
> እኔም ብትል
+ ተይ እንጂ..?... ከምርሽ ነው
> ማርያምን!... ምን አስዋሸኝ... ደስ አለኝ ስላወራሁህ
+ ደስ ይላል... ስሜት ሲመሳሰል...
> አደራህን ደውልልኝ
+ እንዳይሰለችሽ እንጂ....
> ውይ ,, በምን እድሌ
+ አንቺ ጣፋጭ ልጅ ነሽ ከምር
> አንተን ነህ ጣፋጭ.. ከምር
ዋውውውውውውውውውው ነፍሴ እፍረት በእፍረት.... ምን አይነቷ ልጅ ናት ባካቹ
ቃላትቶች አለቁብኝ... ወይም ጠፉብኝ
ተሰናበትኳት
አደቆርሳዬ... ገጥሞህ ያውቃል እንዲህ ያለ ነገር
አቤትትትትትትትትትትትት ስንቶቻቹ ይሄዬ...
ይች አጭበርባሪ...
ይሄ... ቅንዝረኛ
እያላቹን እንደሆነ በደንብ ነው የሚታየኝ
እኔም እናንተ ቦታ ላይ ብሆን እንደሱ ነው ምለው
ግን ምናለበት ብንሆንስ!
ዝም ብሎ ሰው ማመን ደስ አይልም?
አንዳንዴ እኮ ጥሩ ነው... ለደቂቃም ቢሆን... በገንዘብ ልታገኘውን የማትችለውን ደስታ ታገኝበታለህ... ዝም ብለህ በእምነት በየዋህነት ሁሉንም መቀበል
ይህ የኔ ፍልስፍና ነው... ይስራ አይስራ የራሱ ጊዳይ
እና ምን ይጠበስ....... ነው ያላቹኝ አይደል
ም......ን.................ም
.........................................//...................................
ካንፓላ ብዙ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት አለ ወይ ያልከኝ አደቆርሳዬ
እኔ ብዙ ወጣ ወጣ የማልለው ባለሱ እንኳን... ሁለት ፋሲካ አንድ አብነት.. አንድ ኢትዮጵያ ቪሌጅ... እንደሁም አራት ወይም አምስት ስማቸን የረሳኃቸው ምግብ ቤቶች አውቃለሁ
እና ብዙ ነን ካምፓላ ውስጥ
እረ ምን ካምፓላ ውስጥ... እኔ ምሰራበት ገጠር ከተማ ውስጥ እንኳን ሁለት የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች አውቃለሁ
እና ብዙ ኤርትራዊ እና ኢትዮጵያዊ እንደሚኖር ይሰማኛል
እረ በ2009 አዲስ አመት አካባቢ... የኦሮሞ ማህረሰቦች ... ቪክቶሪያ ሀይቅ አጠገብ ባህላዊ በአላቸውን ሲያከብሩ በቲቪ እና በጋዜጣ አይቻለሁ
አሁን ሁኔታው ተረስቶኛል እንጂ
ብዙ ያገር ሰው እንዳለ እና ብዙ የንግድ ድርጅቶችም እንዳላቸው ነው የተገነዘብኩት
አንተ በስብስቴ ጊዜ ያየሀት ኡጋንዳ በጣም ተቀይራለች
እርግጤኛ ነኝ ባንተ ጊዜ 6-የስልክ ካምፗኒ እንዳልነበረ ይረዳኛል
አሁን ብታይ..............
ተወኝ አቦ... አታበሳጨኝ... ከጦብያ ጋር እንዳወዳድር እያደረክ
........................................//.........................................
እና
እንደዋወል ጀመርን...
እኔና ፊአሜታ
ካለሁበት ገጠር ሆኜ
እንደገና ለመተያየት በጣም ጓጓን
የስራ ጉዳይ ሆነና ግን....... አልሆነም
በየቀኑ በስልክ ማውራት ... መጠያየቅ ቀጠልን
ከወር ከምናምን በኃላ ግን
ፊአ-ሜታ ጠፋች
ስደውል.. ስልኳ ቢዚ.. ወይም አይመልስም ነው ሚለው
አንደኛ ቀን..... ምናልባት ኔት ዎርክ ይሆናል... ይሄ የአፍሪካ ኔት ዎርክ እኮ... ዘመድ ያለያያል
ሁለተኛ ቀን//// ምናልባት እኮ... ኤየር ታይም Air Time) አልቆባት ይሆናል
ሶስተኛ ቀን..... ምናልባት ስልኳ ተሰርቆባት.....
አራተኛ ቀን ..... ምናልባት እኮ.... ስራ አግኝታ.. ቢዚ ሆና....
ሳምንት ሆነ....
ሁለት ሳምንት... በፍፁም ታማ ይሆናል.. እንጂ....
ምን አረኳት
ምን አጠፋሁ
ኢትዮጵያ ነው የምኖረው ብዬ እንደዋሼኃት ደረሰችበትና... በመዋሼቴ ጣዝባኝ ዘጋችኝ ይሆን
ቢሆንስ... ነግራኝ ብትዘጋኝ አይሻልም
ድውልልልልልልልልልልል
"the number is swiched off"
በቃ ልተዋት ለምን አስቸግራታለሁ
ምናልባት እኮ ቦይ-ፍሬንድ እንዳላት ደብቃኝ... ከኔ ጋር ስታወራ ደርሶበት...............
ምን ይታወቃል
ወር ሞላኝ መሰለኝ.... ሳልደውል
አንድ ቀን ዝም ብሎኝ ነሸጠኝ እና... ደወልኩ
አቃጨለ
እንደገና አቃጨለ
በሶስተኛው ተነሳ....
በትግርኛ
> ውለይ ፅብቅ መአልቲ ማርያም በተፀነሲ.. ወቅባቱ
አለችኝና ዘጋችብኝ
ምን እንዳለችኝ ሳይገባኝ....
ስልኬን ይዤ ፈዝዤ ቀረሁ
አይ ባለሱቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አይበቃቹም?

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 20 Feb 2012 23:06

Copy and Past No. ####
አይበቃቹም.... ስል ሰምቶ አደቆርሳ
አይበቃንምምምምምምምም ጨምር አለኝ
እኔም ቀለሜን በጠዋቱ ይዤ ጭምርርር
........................//....................................
ካምፓላ ጓደኛዬ ጋር ደወልኩ.... አምቼው የበርጫ ጓደኛዬ
> አታ አድጊ... የት ጠፍተህ ነው ባክህ
+ እንዴ እንዴ ባለሱቅ ... ከየት ተገኘህ.... በቀደም መጥተህ ብቻህን ምሳ እንደበላህ ሰማሁ.... ሶሪ ተኝቼ ስለነበር እኮ ነው
> እንዴ ቆይ አንተ... ቀን ቀን ተኝተህ ማታ ማታ የሚስት ስራ ማን ሊሰራልህ ነው?
+ አሀሀሀሀ... አንተ ቀላጅ... ለሱም ጊዝኣ አለ አብሽር.... ቆይ ለመሆኑ መቼ ነው ካምፓላ ምትመጣው
> ፊአ-ሜታን ያገኜህልኝ ቀን
+ ምን አልክ
> ፊአሜታን ታውቃታለህ
+ ነቨር ... ሰምቼ አላውቅም... ካምፓላ?
> አዎን... ሰርቃኝ ጠፋች..... እሷን ካገኘህልኝ ነው ምመጣው
+ ምን ሰረቀችህ ደሞ... ያንተ ነገር
> ትንሹን አንጀቴን
+ ም..ን? አካካካካ.... ማታመጣው የለም እኮ
> ከምር ነው እኮ
+ አትቸገር እሷ ወስዳ ከጠፋች... እዚህ ብዙ አለ...
> እውነት ግን ከምር አታውቃትም
+ ዌል ሳምንታዊ እና ወርሀዊ ስብሰባ ብሄድ ላገኛት እችላለሁ.... ጊዜ ስለሌለኝ ተሳትፌ አላውቅም እንጂ
> ስብሰባ አላቹ
+ አዎን በየወሩ አንዳንዴም በጎጥ በጎጥ በየሳምንቱ
> ምንድነው ምታወሩት
+ የተቸገረን መርዳት... አዲስ መጤን ማለማመድ..... ያለውን የስደተኝነት ፕሮሰስ ማስረዳት.... ባጠቃላይ መረዳዳት
> ዋውውውው.... ከኛ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጣም የላቃቹ ናቹ እናንተ ባክህ
ከምር ቀናሁ.... ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች .መሀከል የሌለ ነገር ስለሆነ.... እኔ ባየኃቸው አገሮች ማለቴ ነው
ድምምምም
+ እኔ ብዙ ጊዜ ስለማይመቸኝ አልሄድም እንጂ... እንሰበሰባለን.... አሁን ነገር አታረሳሳ.... ማናት ፊአሜታ
> ፊያሜታ የሚል ስም አታውቅም
+ ሰምቼ አላውቅም.... ከየት ናት
> ኦሮማይ የሚል መፃፍ አላነበብክም
+ የምን መፃፍ
> ኢትዮጵያ እያለህ
+ ሆ ሆ በ12 አመቴ እኮ ነው አሽቀንጥራቹ የወረወራቹኝ... መፃፍ ለማንበብ አልደረስኩም ከኢትዮጵያ ስወጣ
> ኦ ህ ረሳሁት.... ኤኒዌይ .. በአንድ መፃፍ ላይ ታዋቂ የአስመራ ገፀ-ባህሪ ናት... የምትወደድ
+ እና አሁን እንዴት ትዝ አለችህ
> ባለፈው ካምፓላ የመጣሁ ጊዜ ... አብሬአት ምሳ በላሁ እና....
+ ቅቅቅቅቅቅቅ አንተ አሪፍ ቀልደኛ ነህ.... እሺ
> አሁን ስልኳን ዘግታ ጠፋችብኝ
+ መቼ ነው የመጣችው... ይህች አጭበርባሪ
> አጭበርባሪ አትመስልም.... ምስኪን ነገር ናት.... ከመጣች ገና ሶስት ወሯ መሰለኝ
+ ኦህ... በል ተወው.. ወደ-ደቡብ አፍሪካ ሄዳልሀለች.. ወይም ለመሄድ መንገድ ላይ ናት
> እንዴ እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ
+ ብዙዎቻችን እንደመጣን የምናደርገው ነው.... ታሪኩ ረጅም ነው.... ከተሳካላት እርሳት... ካልተሳካላት ስትመለስ ታገኛታለህ
> ወይ ጉድድድድ... ታዲያ ምነው ብትሰናበተኝ?
+ በድንገት ተነሽ ተብላ ይሆናል... እንግዲህ የስደተኛ ነገር የራሱ ጊዜ እና እቅድ የለውም
> ግን እኮ በቅርብ ስልኳን አንስታ በትግርኛ ሰድባኝ ዘግታብኛለች
+ አሀሀሀሀሀ.... ምን ብላ... እንዴት ስድብ እንደሆነ አወክ
> እንዴ ስድብ ባይሆን መልስ ስትጠብቅ ትዘጋብኛለች?
+ እሷን እንደሆነች በምን አወክ
> በድምጧ
+ በል እንግዲህ ችግር ውስጥ ነው ያለችው ማለት ነው.... ጠብቃት ትደውልልሀለች
> እንዴ አንተ እንዴት አወክ
+ የአስመራ ልጆች እንደዚህ ናቸው.... ቅቅቅቅቅቅ.... ዝም ብለው አይዘጉም.... ከአቅማቸው በላይ የሆነ ችግር ካልገጠማቸው በስተቀር....
> ምን ሊገጥማት ይችላል በ3ወር ውስጥ
+ ብዙ ነገር.... ሀዘን ላይ ልትሆን ትችላለች... ወይ ከቦይ-ፍሬንዷ ጋር ተጣልታ ሊሆን ይችላል.... ለመሆኑ ነግራሀለች እንዳላት
> እንደዚያ አይነት ጨዋታ ውስጥ አልገባንም... የምናወራው ስለሌላ ሌላው ነበር እስከማስታውሰው
+ ዌል እንግዲህ እዚህ ከተማ ካለች ጠብቃት.... አለበለዚያ .. ሄዳለች እድሏን ልትሞክር.... ሳውዝ አፍሪካ..... የኛ አሜሪካ
ህምምምምምምም
እንደዚያ ከሆነ በሄደችበት ይቅናት .... በዚያ በተቦጫጨረው ፊቷ ላይ... በዚያ በሚያምረው አይኗ ውስጥ ያየሁት ጥልቅ ሀዘን.. እና የብቸኝነት አለም... ምን እንደሆነ ማወቅ በጣም ጓጉቼ ነበር

ይቅናሽ በሄድሽበት ይቅናሽ ላንቺ
አይክፋሽ እንደኔ ተደሰቺ
እኔው ልጥቆርልሽ እኔው ልክሳ
ይውረድ በላዬ ላይ ያንቺ አበሳ

የሚል ዘፈን ለምን ትዝ አለኝ ባካቹ

እንመለሳለን ከፊአሜታ ጋር
ትንሿ ነበልባል
ጲርርርርርርርርርር

ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 21 Feb 2012 04:54

ጤና ይስጥልኝ
እንደምን ከረማችሁ ሞፊቲኮ ያቀረብከውን ዜና አነበብኩት በጣም በጣም ነው ያዘንኩት
ምን ዓይነት የሰይጣን መንፈስ እንደሆነ አይገባኝም እንደዚ ያለ ወንጀል በየግዜው ይሰማል ::
የሚገርመው ደሞ ከተማሩና ሁሉንም ማገናዘብ ከሚችሉ ሰዎች እንደዚ ያለ ነገር ማየታችን ነው::
ባለፈው ሰሞን አንዱ እንዲሁ የልጆቹን እናት አሲድ ደፍቶባት ተቃጥላ ተሰቃይታ ሞታለች
ከካሚላት ጀምሮ በተደጋጋሚ የምንሰማው ዜና ሆኗል በውነት ያሳዝናል::
በፍርድ አሰጣጡ በኩል ያለው መላላት ትልቁን ችግር የሚያጎላው ይመስለኛል::
ምክንያቱም ይሄንን ከነፍስ ማጥፋት ጋር አያይዘው አያዩትም::
ወንጀለኞቹን በተለያዩ ምክንያቶች በጣም ከተገቢው ባነሰ ሁኔታ ነው ቅጣት የሚጥሉባቸው ስለዚህ አንዱ ምክንያት ነው ብዬ ገምታለሁ::
የልጅቷ ዓይን ማየት እንደሚችል እና እንደማይችል የሃኪም ውጤት ፖዘቲቭ እንዲሆን ምኞቴ ነው
ለቤተሰቦቿም መጽናናትን እመኛለሁ ::
ወንጀለኛው ትክክለኛና ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኝም እመኛለሁ ቢቻለን የድርሻችንን መወጣት ይገባናል::
በጣም በጣም የሚያሳዝን ነገር ስለሆነ ከልቤ አዝኛለሁ::
ሰላም ሁኑባለሱቅ መቼም አንተ በየሄድክበት የሚያጋጥምህ ሁሉ ጥሩ ጥሩ ነገር ነው አንተም ጥሩ ስለሆንክ ይመስለኛል
ከአጨዋወትህ ጀምሮ አንተን ማንበብ ደስ ይለኛል ሽሜውንም እንደዚሁ ደስ ይለኛል::
ወንድሜ ካምፓላ ውስጥ ከ10 ዓመት በላይ ተቀምጧል አሁን የሚኖረው ሜልበርን ነው ::
ለመሄድና ካምፓላን ለማየት እመኝ ነበር ግን ሳይሳካልኝ ወንድሜ ወጣ ::

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 21 Feb 2012 07:48

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አንዲት {አንቱ የሚባል ነው ለነገሩ) ኮርስ እየወሰድኩ ስለሆነ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ጥናት ላይ ነኝ:: ፈተናየም አርብ እለት ነው:: ለዚህ ነው ብቅ ያላልኩት::

አደቆርሳ በእውነቱ የምትገርም ሰው ነህ:: በዚያች አንዲት ፎቶግራፍ ላይ ተመርኩዘህ ስለ ጉጂዎች አለባበስ የሰጠኸን ታሪካዊ ትምህርት መቼም አይረሳም:: አቦ ተባረክ:: ሌላ ቀን ደግሞ ሌላ ፎቶ ይዤ መጣለሁ ስለሱ ደግሞ ትነግረናለህ::

ሞፊቲ በውነቱ በጣም የሚሰቀጥጥ ሁኔታ ነው በዚያች ሴት ላይ የደረሰባት:: እግዚአብሔር እንዲፈውሳት እጸልያለሁ:: ራስብሩ እንዳልከውም እኔም እስማማለሁ እንደነዚህ ያሉ ወንጀለኞች ከሞት በታች መቀጣት የለባቸውም:: ለምሳሌ ያቺ የአየር መንገድ ሆስቴስዋን አይን ያጠፋው ወንጀለኛ በ14 አመት ቅጣት ብቻ ነው የተላከው: እርስዋ ግን እስከ ህይወትዋ መጨረሻ አይነ ስውር ሆና የሰው እጅ አይታ ቀረች ማለት ነው:: ይህ ትክክል አይደለም::

ባለሱቅ...ወይ ባለሱቅ ወይ ፊያሜታ!! እውነተኛ ስሟ ነው ወይስ አንተ ያወጣህላት ነው? አይዞህ ወንድሜ እንግዲህ እርሷን ፈለጋ መላ አፍሪካን ልታስስ ነው ማለት ነው? ፍቅር ከባድ ነው:: ምናልባት ያ ጓደኛህ እንዳለህ ይኽኔ ቦይፍሬንድ ሊኖራት ይችላል እኮ:: ይልቅ ሌሎች ቆነጃጅቶችን ቃኝ:: ስለ ፊያሜታ እኔ የምሰጥህ ሀሳብ የኤርትራ ኤምባሲዎችን ለምን አትጠይቅም? እነርሱ ይረዱህ ይሆናል:: እስከዚያው ግን በዚህ "ፍያሜታ ጊላ" በሚለው የቭድዮ ዘፈን ተጽናና!! ሶሪ ዘፈኑ ያጽናናህ እንደሆነ ግን እርግጠኛ አይደለሁም:: ቅቅቅቅቅቅ

[dtube]3D7d641f1ec[/dtube]

http://www.diretube.com/hussien-mohamme ... 1f1ec.html

ይቅርታ አሁን ስለተቻኮልኩ መሄድ አለብኝ። ቭዲዮውን በህዋላ አስተካክለዋለሁ። አድራሻው ግን ትክክል ነው።

[This Post edited by ኦሽንoc to fix the video link]
Last edited by አንፈራራ on 21 Feb 2012 10:06, edited 1 time in total.

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 21 Feb 2012 10:02

ተድላ ሀይሉ እንዳለው
አደራ ከሞዛምቢክ ስትመለስ የሾላ ፍሬ ይዘህልን ተመለስ :: ምናልባት የሾላ ዛፎች ካላየህ እኔ ሥፍራውን ልጠቁምህ እችላለሁ
ፕሊስ የት እንደሚገኝ ንገረኝ እና ልቅመሰው.... ወይም ስሙን በፈረንጅኛ አስተምረኝ
በነካካ እጅህ ታዲያ ያ አረንጓዴው ወርቅ (በርጫ) የት እንዳለ ጠቁመኝ
አደራህን
..........................................//........................................
አንድ ከሰአት በኃላ በሞባይሌ ላይ መልክት አገኘሁ
> አለህ ወይ ባገሩ.... ተቀየምከኝ ዎይ.... ይቅርታ በናትህ.... ከቻልክ ደውልልኝ
የሚል መልክት
መልክቱ ሲደርሰኝ.... ቀስስስስ ብላ በለሆሳሳ የምታወራ ነው የመሰለችኝ
እኔም ሳነበው እንደዚያ ነው ያነበብኩት
ገጠር ነበርኩ እና ደወልኩላት
> አንቺ!... በሰላም ነው ወይ የጠፋሽው
+ ወይኔ.... በናትህ ይቅርታ አስጨነኩህ አይደል
> እረ እንኳን ደህና ሆንሽ እንጂ... የኔ ጭንቀት ምንም አይደለም.... ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ የጠፋሽው
+ ብዙ ነው ታሪኩ.... መቼ ትመጣለህ ካምፓላ
> አላውቀውም... የምመጣበትን... ግን ግን ግን በናትሽ ምን ሆነሽ ነው እስኪ ጫፍ ጫፉን ንገሪኝ ምን እንደሆንሽ
+ በናትህ አታስጨንቀኝ.... ስንገናኝ.... ወይኔ ባገኝህ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለህ
> እኔም .... ግን ባለፈው በትግርኛ ሰድበሽኝ ለምን ዘጋሽብኝ
+ ዋእ... እረ ስድብ አይደለም.... ደውልልሀለሁ አሁን ቢዚ ነኝ እኮ ነው ያልኩህ.... ውይ በናትኅኅኅኅኅ
> ቅቅቅቅቅ ገብቶኛል ለነገሩ ግን ትግርኛ እኮ አልችልም....
+ አውቄአለሁ... ግን ስላልተመቸኝ ነው.... በሰአቱ አማርኛም ጠፋብኝ
> ከቦይ ፍሬንድሽ ጋር ስለነበርሽ ነው አይደል?
+ ኖ ኖ እንደሱ አይደለም... ግን ስንገናኝ ብንጫወት ምን ይመስልሀል.... ፕሊስ ደውልልኝ... ደሞ... ከልብህ ይቅርታ አድርግልኝ
> እረ ምን ገዶኝ.... ምንም አላደረግሽም እኮ.... እንዲሁ ስትጤፊ አሳሰበኝ እንጂ
+ አመሰግናለሁ ስላሰብክልኝ.... ፕሊስ ና... ካምፓላ
ውይ ድምፃ ደስ ሲልልልልል
አሁን አሁን ብረር ብረር አሰኘኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አንፈራራ የሚሉት ብሽቅ ልጅ.... ፍቅር ነው ብሎ ስሜን ሲያጠፋ አየሁት በዚያኛው ቤት
ፍቅር እንደፍየል በየመንገዱ ሚይዘኝ ይመስልሀል እንዴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ደሞ በስተርጅና... ልጆቼን እንደማሳደግ... ፍቅር ማባርር ይመስልሀል?
አቤት መሳሳትትትትትትትትት
ኤኒዌይ... እንደምታስበው የሴት እና የወንድ አይነት ፍቅር አይደለም የሚሰማኝ
የሆነ የምትወደውን ስም ስታገኝ እና.... ስለሱ ብዙ ለማወቅ ስትሞክር የምትንገበገበው ግብግብ በሌላው ሰው አተያይ ፍቅር ቢመስል እንጂ....
በፍፁም በምኔም ውስጥ ምንም የለም
እመነኝ... ዝም ብለህ
ያ ቢሆን እዚህ መጥቼ አላወራውም ነበር
የቤታቹ ፎንት ግን አሁንም አስቸግሮኛል....
የደመደምኩት በኔ ኮምፒተር ነውና... አዲሱን ገዝቼ እስከምገላገል....
እዚህም እዚያም ነኝ
ለነገሩ ዋርካ አሁን ፅድትትትትትትትት ብላለች ብታያት
ባዲስ ሞድ የተሰፋ ነጭ በነጭ አድርጋ... ጥለቱ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ... የሆነ አጭር ነጠላዋን ጀርባዋ ላይ ጣል አድርጋ

ሳሙኝ
እቀፉኝ
ውደዱኝ
ጥብቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ጭንቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ትንፋሽ እጥርርርርርርርር እስኪለኝ ድረስ
ስማቹ አሳምሙኝ
እያለቻቹ ነው
ዋርካ የጥንቷ የጠዋቷ
ተድላ ሀይሉም.... እየተጣራ ነው ከሰማቹት


አለበለዚያ እንዳላቃጥለው
ይላቹዋል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እመለሳለሁ እስኪ
ከስራዬ እንዳልባረር

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”