የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
ራስብሩ
Starter
Starter
Posts: 23
Joined: 03 Jan 2012 09:45
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by ራስብሩ » 12 Feb 2012 12:17

ጤና ይስጥልኝ
ድምጽህን ስሠማ የሆነ ነገር እንደጠጣ ሰው ሞቅ ይለኛል ቅቅቅቅቅ በጣም የሚያስቅ አባባል ነው ::
መቼም ከጊዜ መጥበብ ጋር ተያይዞ ምናምን ምናምን ተደማምሮ እንደድሮው ቶሎ ቶሎ ብቅ አለማለት
ልምድ እንዳይሆን እየፈራሁ ነበር ::
በቤታችን በጣም የሚወደደውን ስፖርት እንኳን የአፍሪካ ዋንጫ እየተካሄደ ልክ እንደ አዘጋጆቹ ሃገር ስታዲየም ምንም ታዛቢ ሲጠፋ በውነት ደንግጫለሁ ::
ለማንኛውም ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የመጨረሻው የዋንጫ ግጥሚያ ይካሄዳል ዛምቢያና አይቮሪ ኮስት እንቅልፍ ሳይተኙ እንዳደሩ እገምታለሁ::
መቼም ዋንጫው የማን ይሆናል የሚለው ብዙ ግምት ቢነሳም ዛምቢያዎች ከአመታት በፊት ሙሉ ብሄራዊ ቡድኗን በአውሮፕላን አደጋ ያጣች ሃገር ስለሆነች ህዝቧ ይሄንን ዋንጫ ለመታሰቢያነት አምጡልን እያሏቸው ነው::
በሌላም በኩል ዲዲየር ድሮግባ የመጨረሻው ዘመኑ ላይ ያለ ተጫዋች እንደመሆኑ ለሃገሩ ሁለተኛ የሚሆነውን እና የራሱን አንድ ትልቅ ታሪክ ማቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል::
እንግዲህ ጨዋታው ከባድ ግምት የሚሰጠው ታሪካዊ የዋንጫ ፍልሚያ ይሆናል ማለት ነው::
በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከታዘብኩት አጠቃላይ ሁኔታዎች ውስጥ
የሱዳን ያልተጠበቀ ብቃት :
ጥሩና ከመቼውም ግዜ የበለጠ የኳስ ጥበብ :
የተዋጣለት የኳስ ዳኝነት የታየበት ውድድር:
እንዲሁም የአፍሪካ ስታዲየሞች ዜሮ ተመልካች መሆናቸው ጥቂቶቹ ናቸው::
የሱዳንን የኳስ ብቃትና የቡድናቸውን ከፍተኛ አቅም ስንመለከት ኢትዮጵያውያኖቹን ከመታዘብ ሌላ ምንም የሚባል ነገር የለም::
መቼ በአፍሪካ ዋንጫ ሜዳዎች ላይ የኢትዮጵያን ማሊያ እንደምናይ እናፍቃለሁ::
የጋናን የኳስ ችሎታና ቅመም የሆነ ቅመራ እንዲሁም የመናበብ ሁኔታ ከና ከመጀመሪያው የዋንጫ ባለቤት ናቸው ብሎ መላው አፍሪካ እስኪያምን ድረስ የተሰጣቸው ግምት ወደኋላ ላይ አፈር በልቷል ሞፊቲኮ ባለፈው ገርሞኝ እንደጠቀስኩልህ ከቱኒዝያ ጋር ያደረጉት ጨዋታ አስፈርቶኝ ነበር ግምቴም ትክክል ሆነ::
ለነገሩ ከዛምቢያ ጋር ሲጫወቱ በጨዋታው 75 ለ 25 ፐርሰንት ያህል ነበር ችሎታቸው ጋና ብልጫ ተጫውቶ በጣም ብዙ የግብ ሙከራዎችን አድርጎ ምንም ሊሳካለት አልቻለም ዛምቢያዎች ችሎታቸው ምንም እንደጋና ባይሆንም በእድል ብዛት አሸንፈው ጋናን ማሰናበት ችለዋል::
የቱኒዝያ አጥቂዎችም በጨዋታ ችሎታቸው የተዋጣላቸው ቢሆኑም በተለይ ከጋና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ብዙ የዲሲፕሊን ጉድለት አሳይተዋል::ባጠቃላይ ዘንድሮ የታየው የአፍሪካን ዋንጫ ጨዋታ በጣም ያደገና ልዩ ችሎታ የታየበት መሆኑን ጀርመናውያን የስፖርት ጋዜጠኞች ጨዋታውን ሲመሩ ከሚሰጡት አስተያየት ለመረዳት ችለናል::
በአፍሪካ የስፖርት እድገት እያለ ባዶ ስታዲየም መታየቱ ግን ለምን እንደሆነ ግራ የሚገባ ነው መክፈል አይችሉም እንዳይባል መንግስታቸው ሄንን ያላገናዘበ ክፍያ ይጠየቃል ብዬ አልገምትም : በውነት በጣም ነው የሚገርመው የአፍሪካን ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ውድድር በግማሽ ስታዲየም ::
በውነት ስታዲየም የለንም እንጂ ጨዋታው እኛ ሃገር ቢሆን ቦታ አይገኝም ነበር::
አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እዚህ ጀርመን ካርልስሮይ የሚካሄድ የአትሌቲክስ ውድድር ስላለ
እመለከታለሁ በዚያውም የዋንጫው ጨዋታ ይቀጥላል::
በመጨረሻም የራሴን ግምት ለመናገር ያህል ኮት ዲቯር ባላቸው የተቻዋቾች ብቃት የኳስ ልምድና ችሎታ ዋንጫውን ያስቀራሉ ብዬ ባምንም ዛምቢያዎች በአደጋ ላጧቸው ብሄራዊ ቡድናቸው መታሰቢያ ሊያደርጉ በማሰባቸው በተለይም የህዝቡ ጥያቄ ስለሆነ ድጋፌ ለነሱ ነው::


ሞፊቲ ፕሊስ ያንተን አስተያየት መስማት አፈልጋለሁና አንድ በልመልካም እድል ለ ካሉሺያ ቡዋሊያ

ራስብሩDole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 12 Feb 2012 20:59

Copy and Paste

አደቆርሳ እንዳለው
በሌላው የክ/ት ልጆች ቤት ውስጥ
የበር ላይ እንጨት አንች አሰናካይ
ወይ ነደሽ አትሞቂ ልመና ከልካይ
እያጉረመረመ እንደሰኔ ለማኝ
ሞገደኛው ነፋስ ድምጽሽን ያሰማኝ


እንደው ድምጽህን ሰሠማ የሆነ ነገር እንደጠጣ ሰው ቶሎ ሞቅ ይለኛል ለምን እንደሆነ አላውቅም :
ደስ አለኝ ስል ምን ትዝ አለኝ መሰለህ የዛሬን አያርገውና ድሮ በጠበሳ ዘበን ቀጠሮ ካለኝ ደስ ደስ ሲለኝ ይውልና ልክ ሰዓቱ
ሲደርስ ጭንቅ ጭንቅ የሚለኝ ነገር ነበረኝ ለምን እንደሆነ እስካሁንም አይገባኝም ::
ግን ባለሱቅ ለምን እንደሆነ የማይገባህ ነገር ለምን እንደሆነ ይገባሃል ? እኔ ግን በጭራሽ ::
ቆይ ቆይ ይሄ ሰውዬህ አዲስ አበባ ብርድ ገደለኝ ያለህ ከዛሬ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ ሚስትህን ይዘህ ና ብለውሃል በለው ::
ገና አፍሪካ በረዶ አውሮፓ ደሞ ግለት ይሆናል በለው : ዘመዶችህ የአቶም ዝቃጭ እያመጡ እዚህ የኛ ምድር ላይ ሲቀብሩ የናንተ
እድሜ እስኪያልፍ ድረስ ብቻ ነው ቀጣዩ ትውልድ ምን ዕጣ ይዞ እንደሚፈጠር ዛሬ ላይ ሆናችሁ ታውቁት የለም ወይ ? በለው ::
ለጊዜው ብቻ ያደሩ የአፍሪካ መሪያት የዳጎሰ ጉርሻ እያመነዠኩ የፋብሪካ መርዝ በምድራቸው ላይ ያስቀብራሉ : ይሁን እንጂ ችግሩ
ቀድሞ የሚጎዳው እናንተንው ነው በልልኝ ባክህ ::
ይልቁንስ ናይጄሪያዊው የተናገረው ትክክል ነው የሆነው ሆኖ እንደነሱ ከሳንጃና በጎራዴ ከመተራረድ በፈሪሃ እግዚአብሄር የታቀበ ህዝብ የተሻለ ነው :
የአፍሪካ ባህል ይመስል ጎሳ ለጎሳ ዘር ለዘር ሲተራረዱ ቆይተው አሁን ደግሞ በሃይማኖት መነካነክ ጀምረዋል አምላክ ኢትዮጵያን ከዚህ ይሰውራት::
ስለ ፈገግታ ያነሳልህ ነጥብ ግን በውነት ትክክል ታዝቧል ያሰኛል ::
ግን እንዴት ይህንን ነገር ሊታዘብ ቻለ ብዬ ገረመኝ ምክንያቱም እናንተ ሃገር ሰዉ እንኳንስ መንገድ ላይ ሊስቅ ይቅርና ቤታቸውስ ቢሆን
መቼ ፈገግ ይሉና ነው ? ጧት ማታ ሩጫ አይደል እንዴ ?
እንዴት እዚህ መቶ ሊገርመው ቻለ ? ዳሩ ህዝቡስ ከየት አምጥቶ ፈገግ ይበል ? በምኑ ፈገግ ይበል ? ፈገግታ እኮ ከውስጥ ደስታ ከወደፊት
ተስፋ አልያም ካለፈ መልካም ትዝታ ነው : እስቲ እግዚአብሄር ያሳያችሁ ከዛሬ አርባ ዓመታት ጀምሮ መከራ... ሞት... ስቃይ.. ረሃብ.. እስር.. ችግር ..ወደኋላ ብትል ወደፊት ምን አለና ህዝቡ ደስ ይለዋል ?
እንደውም ሳቅ ከመጥፋቱ የተነሳ በአጋጣሚ ስትስቅ ፌዴራል ካየህ በማን ላይ ነው የምትስቀው ተብለህ ሸቤ መግባትህ ነው
ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ሳቅ በልክ ነው ........
በዚህም ላይ አጅሬዎቹ ስራቸው እንደሚያስቅ ስለሚያውቁ ሰው ሲስቅ ደስ እንደማይላቸው ግልጽ አይደል ?
አስፋልቱን ግን ይሰሩታል ነው የሚባለው !
መቼም ሰው ማናዘዝ ትችልበታለህ ለመሆኑ የት ከርመህ ነው እንደዚህ የጠፋከው ?
ሚስት አገባህ ? ልጅ ወለድክ ? ይቅርታ ልጆች ወለድክ ወይ ማለቴ ነው ?
ስለ ልጅ ሲነሳ እኔኮ አንድ ሚስጥር ልነግርህ እፈልግና ሰነዱን ከጄ ለማውጣት እፈራለሁ የዘንድሮ ሰነድ መቼም መቆሚያ የለው ::
ሞፊቲን አታይም ከቦሬ ተነስቶ አንዴ ክብረመንግስት አንዴ ዲላ እንደገና ደሞ አዲስ አበባን እንደዚያ እያሰሰ ምንም ነገር ትንፍሽ አይልም :
አደቆርሳ ታዲያ ምን በወጣው አዋጅ ይናገራል እንደውም በቃ ትቼዋለሁ::
የምወድህ አንፈራራችን
ካገኘሃቸው የክ/መ ልጆች የአባባ መድሃኔ ድራር ቤተሰብ ውስጥ በጣም የማውቃቸው ሃና መድሃኔን እና አስፋው መድሃኔን ነው ::
ሃና መድሃኔ ፍጹም ለስላሳ እና ተጫዋች ልጅ እንደነበረች አስታውሳለሁ በጣም ተጫዋች መሳቅ የምትወድ እና ተግባቢ ልጅ ነች::
ብዙዎቹን ልጆች በደንብ አውቃቸዋለሁ እንጂ አውርቻቸው ወይንም ተነጋግረን የማናውቅ ልጆች ብዙ ነን ለምሳሌ ሃናን አብረን
ተማርን እንጂ አናግሬያት አላውቅም እርግጠኛ ነኝ ከነስሜ ብነግራት አታውቀኝም ምክንያቱም እኔ ያኔ ማናገር ቀርቶ መናገርም
የምችል አልነበርኩም::
አስፋውን በኳስ ነው የማውቀው እሱና አክሊለ በርሄ አሪፍ ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ ትልቁ ወንድማቸው በርሄ መድሃኔም ታዋቂ ነበር ::
ጋሼ ዘውዴ አበሩ ቀደምት ከነበሩ በቅጡ ከተማሩና አውራጃውን ከሚያስተዳድሩ ሰዎች ውስጥ ቀዳሚው ናቸው : ብዙ ግዜ ደጋግመን
እንዳስታወስናቸው በክብረመንግሥት የመጀመሪያው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ መምህር የነበሩ ሲሆን በጀምጀም አውራጃ
እንደራሴነትም ትልቅ ታሪክ ካላቸው የልማት ሰዎች ውስጥ ዘውዴ አበሩ አንዱ ናቸው ::
ፍቅሩ ተወልደ አብሮን የተማረ ልጅ ነው በእድሜ ግን እኔ እልቀዋለሁ እስከማውቀው ድረስ እንደውም እስከ በጣም ቅርብ ግዜ ሁሉ
እዚሁ እንደነበረ አውቃለሁ እንኳን ደስ ያለህ ! ብያለሁ ::
ታዲያ በል ቶሎ ብቅ በል ትፈለጋለህ በልልኝ.....
አቶ ገዳም ተስፋሚካኤል የኛ ትውልድ ሁሌም ሲዘክረው የሚኖር መልካም ታሪክ ያለው ሰው ነው !
ስለ ዋርካ የተናገርከው በጣም ትክክል ነው እኔም እንደዋርካ የሚመቸኝ የለም ነገር ግን ገና ስከፍተው ወዲያው የሚታዩት ጽሁፎች
ወይንም ርዕሶች ቀጣዩን ገጽ ለመክፈት ሞራልን ይሰብራሉ::
በውነት ከእናንተም ጋር መገናነት ይቀራል እንጂ እንደዚያ ያለ መልክት በሚስተናገድበት ቦታ ምንጨነቀኝ ብሎ መልሶ መልሶ መምጣት
ኅሊናን መሸጥ ኸረ የምን ህሊና እግዚአብሄርን መካድ ይሆናል ::
ዘግዚአብሄርን ወይንም ደግሞ አላህን በአስጸያፊ ቃላት መናገር ምን ማለት እንደሆነ አዕምሮአችን ለኛ ሊያስተምረን ይገባል ::
ያንን ቃላት ተመልክቼ ቀኑን ሙሉ ጥሩ ስሜት ሳይኖረኝ እውላለሁ ስለዚህ ይህ እንዲሆን ለራሴ መፍቀድ የለብኝም ::
ማየት ያለብን ብዙ መልካም ነገር አለና እንደዚህ ካለው ስፍራ መራቅ አለብን::ባለሱቅ ወንድሜ እንደተረዳሁህ አሁንም እዚያው አለህ ....
ወንድሜ ሆይ ይቅርብህ ያ ቦታ ያንተ ቦታ አይደለም::
አይ እዛ ለምን እንገባለን የራሳችንን ብቻ እንክፈት የሚባል ነገር የለም ዓይን ያያል ልብም ያስተውላል ውጤቱ ደግ አይድለም :: አንዴ ያየኽውን
ነገር ከኅሊናህ ማውጣት አይቻልም ስለዚህ ክፋቱ ማየት ነውና እንዳናይ እዚይ መሄድ ይቅርብን እላለሁ ::
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ
አድዬ አድነት አዱካ አደቆርሳዬ
አቤት ስምህ ለማቆላመጥ ሲመች
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አደቆርሲት እንዳጸማኝ እና እንምዳትቧጭረኝ... ትሴ መስያት
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደለችኝ
ኤኒዌይ እዚህ ቤት እንዳልመጣ እየመከርከኝ ነው
ምክርህን ተቀብዬ ብቀር ይኸው አንተ የጥሣፍከውን እንኳን ማንበብ ላልችል ነውና
ዋርካ ጀነራል ላይ የሚፃፈውን ናቅ አድርጌ... አይቶ እንዳላየ ሆኜ... ለታማሚዎች ፀሎቴን አድርሼ
የአማርኛ ፎንቴ እስኪስተካከል ድረስ መገናኛችን ይህችው ትሆናለች ማለት ነው
እንግዲህ ሊረዱኝ ሰዎች እየተረባረቡ እንደሆነ ደርሼበታለሁ.... አስተባባሪ ዋደራ (ኣንፈራራ) ማለት ነው ትርጉሙ
እናልህ
ሰውዬው እንዴት ፈገግታ ፈልጎ እንዳጣ ለጠየከኝ ጥያቄ
በስራ ምክንያት ብዙ የአፍሪካ ሀገሮችን ጎብኝቷል ብዬህ ነበር
እና ያውቃል ያጠግበዋልም ይህ ንፁህ የሆነ የተፈጥሮ ፈገግታ
ሀገሩ ያጣውን የመንፈስ ምግብ የሚመገበው አፍሪካ ውስጥ ሲመጣ ብቻ ነው
እና አዲሳባ ያንን ሲያጣ
ከምር ነው የምልህ ምርርርርር ብሎት ነበር የሚናገረው
ማጋነን ባይሆንብኝ.... ለሁለተኛ ዙር ለስራው መሄድ ነበረበት...
ነገር ግን አልሄድም ብሎ ሌላ ሰው ተተካ
እሱ ኒጀር ሊሄድ እያኮበኮበ ነው አሁን
ሚስት ያገባውም ከአፍሪካ ነው
ስለአፍሪካ የተፈጥሮ ውበት ከባለቤቱ የበለጠ ነው ሚያውቀው
ለዚህ ነው ያየውን አስቀያሚ ብርድ የመታው ፊት እኔ እንዳይ ያደረገኝ
እልሀለሁ
........................ አሁን ይህንን ፍሬከርስኪ ወሬ እዚህ ላይ ልቋጭልህና....................
ሌላ ፍሬከርስኪ ወሬ ልጋብዝህ....................
ናይ አስመሪና
ሸኮሪና
ሰሜናይት ኮኮብ
በኡጋንዳ
ጠብቀኝ እመለሳለሁ
መቸም አንተ ብቻ ነህ ምታነበኝና የመልስ ምት ምትሰጠኝ
ሌላውማ...
ዝምምምምምምምምም ነው
ብሽቅ ጉጂ ሁላ
እመለሳለሁ
በፍቅር

አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 13 Feb 2012 16:20

የጀምጀም ቆነጃጅት.jpg
የጀምጀም ቆነጃጅት.jpg (16.3 KiB) Viewed 2845 times

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 14 Feb 2012 12:11

ሙሽሪት ዋና ስትዋኝ ቀኑን ሙሉ ቀኑን ሙሉ
ሙሽሪት አሳ ነባሪ ዋጣት አሉ ዋጣት አሉ
...... ዋጣት አሉ ኸረ ዋጣት አሉ
ሙሽሪት አሸበረቀች ትዳር አምሯት ትዳር አምሯት
ሙሽሪት የመርከብ ጉዞ ላታውቅበት ላታውቅበት
ማን ነበር ዘፋኙ እስኪ አስታውሱኝ ... እኔ ትዝ የሚለኝ ግዛው አበበ የሚባል የሰፈራችን ልጅ
ሲዘፍነው ነው ስድስተኛ ክፍል ከግዛው ጋር አንድ ክፍል ነበርን::
መቼም ጉብዝናው አይነሳ ሁሌም አንደኛ ነው የሚወጣው አቤት ስጠምደው ... ሁሌ አንደኛ ብቻ የሚወጣ ጎበዝ ልጅ አልወድም ነበር
አንዳንዴም ወረድ የሚል ልጅ ደስ ይለኛል:: ለነገሩ እኔም አንደኛ ነው የምወጣ ብያችሁ የለ ከትምህርት ቤት ስንለቀቅ .....
ባለፈው ሰሞን አበበ ግዛው የሚባል ዑጋንዳ የማውቀው ልጅ አግብቶ ሰርጉን ታድሜ ነበር ::
ባለሱቅዬ ወንድሜ ስለ ካምፓላ ስታነሳ ብዙ ነገር አስታወስከኝና ቀልቤን በታተንከው
የካምፓላ ወጣት እና የአዲስ አበባ ወጣት በጣም ልዩነት አላቸው::
ካምፓላ አርብና ቅዳሜ ወጣቱ አካሉን የራሱ አድርጎ አይቆጥረውም ::
ሴቷም ብትሆን ነገሯ ሁሉ የራሷ አይመስላትም::
አንዳንዴ ከሶማሊያዊያን ጋር የሚመሳሰሉበት ነገር የሚመስለኝ ለነገ አለማወቃቸው ነው::
እውነት ለመናገር የግዚአብሄርም ቃል እንደሚለን (( ዘ እለት ለእለትነ )) ነው::
እነሱጋ ነገ የሚባል ነገር የለም ያላቸውን በሙሉ ጭጭ አድርገው በደስታ ነው የሚመለሱት::
እኛ ደግሞ ያላሰብነውን ወይንም የከከርነውን ሁሉ በሞቅታ እንደመስስና በማግስቱ የቁጭት ሰዎች ነነ:
ሌላው ይቅር ያደረግነው ነገር ሁሉ በማግስቱ የሚቆጨን ሰዎች ነን::
የካምፓላ ልጆች ከቤት ሲወጡ ሁሉንም ነገር እንዳገኙት ለማድረግ ወስነው ስለሚወጡ አይቆጩም ::
እኛ ቅዳሜ ታጥበን ታጥነን ወደ ቂማ እንሄዳለን ማታ ድራፍት ላይ እንጣድና በምርቃናው ቁልፍ ሶስት አራት እስክንጨልጥ አንነጋገርም አምስት ስንደርስ ሞቅታው አልፎ ምናባህ ታየኛለህ ይመጣል::
ካምፓላ አርብ ከምሳ ሰዓት ጀምሮ ቅምቀማ ላይ ይጣዳሉ እሁድ ነው ወደየቤታቸው የሚገቡት ሁለት ቀን ይጠጣሉ ችሎታችን ራሱ ይለያያል ::
ለገንዘብ ያላቸውም አመለካከት በጣም ይገርመኛል ያለውም አይደብቅም የሌለውም ዝም አይልም በቃ መጠጣት መጠጣት መጨፈር መጨፈር መደሰት ነው::ደስታቸው ግን አንዳንዴ የጤናም አይመስልም ምንም ሃሳብ ያለባቸው ሰዎች አይመስሉም:: ሰኞ በየጉዳያቸው ላይ በትክክል ይገኛሉ እንደሚመስለኝ እኛ ለነገ እናስባለን እንዲሁም ያለንን ሙልጭ አድርገን አናጠፋም ብናጠፋ ደሞ ቁጭትትት ይለናል::
ድህነት ነው እንዳልለው እነሱም ሃብታም አይደሉም ነገር ግን የሃገሩ ዘይቤ ይመስለኛል::
ምናልባት የነሱን ዘይቤ በመልካምነት ብቻም ለመፈረጅ እቸገራለሁ ምክንያቱም እኛ መቸገር አንፈልግም
ስለዚህ ከውድቀት ለመዳን ቀድመን መንቃታችን ይመስለኛል : ነገሩ በራሴ ኪስ አስቤው እንደሁ እንጂ ያውም ቢሆን በበቂ ፕላን መመራት አዋቂነት ይመስለኛል::
እነሱጋ ይሄ የለም ብዙ ያለውም ይዞ ይመጣል ጥቂት ያለውም ይዞ ይመጣል ነገ የራሱ ጉዳይ ነው::
በዚህ አንጻር ሳየው የኛ የሚከፋ አይደለም::
እግረመንገድህን ካባላጋላ የኢትዮጵያ ቅምቀማ ቤት አለ እስካሁንም የሚኖሩ ይመስለኛል ሰዎቹ ጥሩ ሰዎች ናቸው በአካባቢውም ሰዎች በጣም ይወደዳሉ ጎብኛቸው : ታዲያ እንዳልኩህ ዊኬንድ ላይ ብቅ ብትል ሁሉንም እዛው መታዘብ ትችላለህ ትዝብትህንም እስክንሰማ ቸር ይመልስህ
ፔሬድ......... እቀጥላለሁ

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 16 Feb 2012 15:00

አንፈራራችን ከጻፍኩ በኋላ የሆነ ቁልፍ ነክቼ መጻፊያው ገጽ በአዲስ ተተካብኝ ::
እንደሚመስለኝ መልስ በሚለውን ፋንታ ለመጻፍ የሚለውን ስነካው ነው የጻፍኩት የጠፋብኝ
ያሳዝናል ስንትና ስንት ጊዜና ገንዘብብብብብብብብ አዪዪዪዪዪዪዪ

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 16 Feb 2012 15:04

ውድ አንፈራራችን
ያቀረብካቸው የአዶላ ቆንጅዬዎች የለበሱት ልብስ በጣም ደስ ብሎኛል
ሁለቱ የለበሱት አረንጓዴ ቀለም ያለው ጨርቅ በጉጂ ብሄረሰብ ውስጥ በሴቶች ቀሚስነት በስፋት የሚለበስ ሲሆን በይበልጥ የሚታወቀው ከጀምጀም ይልቅ በቦረና አካባቢ ነው::
ሶስቱ የለበሱት ግን ቦሮ (ሲነበብ ጠበቅ ይላል) ነው :: ቦሮ በጉጂ ብሄረሰብ ውስጥ በሁሉም እድሜ ደረጃ እንዲሁም በሴቶችም በወንዶችም በደንብ የሚለበስ ልብስ ነው::
ቦሮ በተለይም ሽማግሌዎች ሲለብሱት ከአለባበሳቸው ጋር እይታው ማራኪ ነው ::
ቦሮ ጨርቁን ገና በቅድሚያ ሲሰሩት ለትንሽ ለትልቅ ለሱሪ ለአላባሽ ለሴት ለወንድ ወዘተ ታስቦ ስለሚዘጋጅ ተጠቃሚው ለሚፈልገው ልብስ አይነት መግዛት ይኖርበታል ::
እኔ አንድ የሚገርመኝ አንድ የወንዶች ብትን ቦሮ (ጨርቅ)የስፌት መኪና ሳያየው ሱሪ መሆን መቻሉ ነው:: ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ግዜ ጠንቃቃ ለባሽ ያስፈልገዋል የሚል ግምት ነገር ነበረኝ ነገር ግን በደንብ እንዳየሁት በቀበቶ የታጠቁት ሱሪ እንኳን እንደቦሮ አይጠብቅም::
ቦሮ ሲለበስ ወገባቸውን የሚያስሩበት ሰቅ በጉጂ ውስጥ ትልቅ ታሪክ ያለው ነው ትዝ ይለኛል ስለጉጂ ባህልና ልማድ ስንነጋገር ወቤ (ጃሎ) አንድ ጥሩ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር::
በጉጂ ብሄረሰብ ውስጥ ባል ቀበቶውን በር ላይ ካጋደመ ሚስት ውጭ መቆም አለባት ተራምዳ ከገባች አለቀላት ........ አይፋም ያሳቀቺኝ አይረሳኝም .. ቆይ እስቲ እኔ በር ላይ አጋድሜ ሞክራለሁ ብላ !!
ቦሮ ተወዳጅ ልብስ ከመሆኑም በላይ ከጉጂ አልፎ በሲዳማም የተለመደ ልብስ ነውኆኖም ግን አጠራሩ እንደየሃገሩና ህዝቡ ይለያያል ለምሳሌ በወላይታ የህዝቡ መለያ እስከሚሆን ድረስ ልብሳቸው ይታወቃል ሆኖም ግን ጨርቁም አሰራሩም ጥራቱም ጥበቡም በስፋት ይለያያል::
በወላይታ ልብሳቸው በተለያየ የጥራት ደረጃ ሲሰራ በጉጂ ይዘቱም ጥራቱም አንድ አይነት ብቻ ነው::
ምናልባት አሁን አሁን አላውቅም በፊት ግን ቦሮ ደረጃው አንድ ዓይነት ብቻ ነበር::
በቀለም ደረጃም ተቀራራቢነት አላቸው ቢሆንም ቦሮ ኦሪጅናሉ ጥቁርና ነጭ ብቻ ነው::
ቦሮን በዘመናዊ ሞድ አሰፍቶ መልበስ የተጀመረው በ1970 አካባቢ ነው ትዝ ይለኛል ለመጀመሪያ ግዜ ከቦሮ የተሰራ ሱሪ ለብሶ ያየሁት መሃመድ ፋራ የሚባል ልጅ ነው:: ከዚያ በኋላ ብዙዎች በብዙ አይነት ለብሰውታል ምናልባት ቦሮ ያለበስኩት እኔ ብቻ ነኝ አቅም ስላልነበረኝ::
መሃመድ ፋራን እኔ መጀመሪያ ስላየሁት የመጀመሪያው ሞድ ለባሽ አድርጌ አስበዋለሁ እንጂ ከሱ በፊት የለበሱ ሊኖሩ እንደሚችሉም እገምታለሁ ብቻዐስካሁን አይምሮዬ ውስጥ ትዝ የሚለኝ እሱ ነው::
ፎቶዋቸውን ያሳየኸንን የወዩ ልጆች በዚህ እድሜያቸው የሃገራቸውን የባህል ልብስ ለብሰው ደምቀው ብቅ በማለታቸው የተሰማኝን ልባዊ አክብሮት አድርስልኝ ::
ቸር ያቆየን ወዳጅህ አደቆርሳ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 17 Feb 2012 00:08

ሱሪ ባንገት የሆነ ስራ ይዤ
ጥያቹ ጠፋሁ
ሶሪ
ዝባዝንኪ ሳላበዛ ቀጥታ ወደ- ካባላጋላ
2011 ጁላይ በአንዱ ቀን
እንጀራ አማረኝ
ክፉ---------ኛ ነው ያማረኝ
እንደ-እርጉዝ ሴት
ሽታው... አፍንጫዬ አወደኝ
የወጡ አይነት አይኔ ላይ ተደረደረ
የለመድኩት ምግብ አስጠላኝ
ያገሬ ልጆች ናፈቁኝ
አይናቸው... አይናፋርነታቸው,... ፈገግታቸው
ኡ ኡ ኡ ኡ እንደዚህ እንጀራ አምሯቹ ያውቃል
አላውቅም
ቆይ ከዚያ በፊት ስለነበርኩበት ሁኔታ ትንሽ ላጫውታቹ
እንዲጋባባቹ ስሜቴ
ለ4 ወር ገደማ ጫካ ነበርኩ.... የኡጋንዳ ገጠር
በዚያ ላይ ቁርስ ምሳ እራት ሁልቀን ከተመሳሳይ ሰዎች - የስራ ባልደረቦቼ.. ጋር ነው የነበርኩት
ገጠርም እንውጣ.. ካምፓላ እንምጣ.... መለያየት አንችልም
ለምን እንደሆነ አይገባኝም እንጂ... የራሴ የምለው ጊዜ ሊኖረኝ በፍፁም አልቻልኩ
ማንም ከልክሎኝ አይደልም... ሁኔታው ግን ያስገድድሀል.. ሳትፈልገው
እንጃ ምን ያህል እንደገባቹ አላውቅም
ኤኒዌይ
ለውጥ አስፈለገኝ... ካለሁበት ሁኔታ መራቅ
እንጀራም መብላት አማረኝ
ያገሬን ልጆችም ማየት ፈለኩ
ለነገሩ እንጀራ አብረን እንበላለን እኮ.... ቢያንስ በ15 ቀን አንዴ
እንደው ምክንያት ፈልጌ ከነሱ መለየቴ ይሆናል....
አንድ እሮብ እለት... ካምፓላ ለምሳ ስንዘጋጅ.... በድንገት
> እኔ ዛሬ እንጀራ መብላት አምሮኛል.... አልኩኝ
ማንም የተቃወመኝ የለም... ሊቃወሙም አይችሉምና.... ነገር ግን
ከቦምብ ፍንዳታ እራሴን እንድጠብቅ ነግረውኝ... ተለየኃቸው (ምን ማለት እንደሆነ የሚገባቹ ይመስለኛል.... ኢትዮጵያን ቪሌጅ አትሂድ ነው.... ያኔ እሱ ነበር የፈነዳው)
> አብሽር አታስቡ ብያቸው....
ወደ-ካባላጋላ...
ከሹፌሬ ጋራ
................//...........
የት ልብላ ግን? ካባላጋላን ብዙ አላውቀውም....
ብዙ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ .... ባውቅም... ብዙ ሬስቶራንት እንዳለ ባይም... ከኢትዮጵያን ቪሌጅ ውጪ ሌላ ቦታ ገብቼ አላውቅም
ፋሲካ ሬስቶራንት የሚል ያነበብኩ ይመስለኛል
እዛ ልሂድ ይሆን
ቆይ ቆይ... አንድ ጓደኛ አለኝ እኮ..... አምቼ (ከኤርትራ)
ደወልኩለት
አያነሳም ስልኩን....
ሚስቱ ትዝ አለችኝ... ደወልኩላት
> ከመይ... ፅቡቕ... ናይ ሰሜናይ ቆንጆ
+ ውይ አንተ.... በህይወት አለህ... በናትህ... የት ጠፍተህ ነው... በሀሳብ ገደልከን እኮ
> አሁን ወሬ አታብዢ... ምሳ እንብላ
+ ካምፓላ ነህ እንዴ
> አዎን ሰውዬሽ ጋር ብደውል አያነሳም.... ምሳ ልጋብዝሽ
+ ውይ እሱ እኮ ቀን ቀን ይተኛል.... ስራው ሌሊት ስለሆነ
> እንዴ ካንቺ በተጨማሪ ሌላ የሌሊት ስራ አለው እንዴ
+ ሂድ... ባለጌ... እንደሱ ማለቴ አይደለም
> እህሳ!
+ በቃ ማታ ማታ ነው ሚሰራው... ስለዚህ እስከ-ቀን ድረስ ይተኛል
> አንቺን ጥሎ?
+ ሂድ ፈዛዛ.... ቆይ አሁን የት ነህ
> ወደ-ካባላ ጋላ እየሄድኩ ነው... ፕሊስ ምሳ እንብላ
+ ኖ እኔ ስራ ላይ ነኝ... አመሰግናለሁ ግን.... የት ልትበላ ነው
> አንዱም የደወልኩት ለዚያ ነው... እስኪ የት ልብላ
+ እ..... ቆይ ጠብቀኝ እንደገና እደውልልሀለሁ
> እሺ የኔ ቆንጆ... ማለቴ የጓደኛዬ ቆንጆ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ተሳሳቅን እና ስልኩን ዘጋነው
አቤት የመኪናው ብዛት ካምፓላ ውስጥ
ቦዳ-ቦዳው (ሞተር ብስክሊሊት) ሲያስፈራ ደሞ
የትራፊክ ህግ አያከብሩ
ሹልክ ሹልክ ሲሉ... ስቅጥጥ ይላል...
በየቀኑ ስንትና-ስንት አደጋ ይሆን ሚደርሰው
ደሞ የትራፊኮቹ ሲገርም
ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው... ቆመው እንጂ.. ስራ ሲሰሩ አይቻቸው አላውቅም
እረ ባለመኪናውም ይጋቸውን ሚያከብር አይመስለኝም
ብቻ ያናድዳል
ከናካሴሮ አካባቢ.. እስከ-ካባላጋላ ቢበዛ 7 ወይም 10ኪሎ ሜትር ቢሆን ነው
የሚፈጀው ጊዜ ግን ከ30 ደቂቃ በላይ
እያሰብኩ... እየተናደድኩ... ውጪ ውጪውን እያየሁ ሳለ... ቂሊሊ ቂሊሊ... አለች ስልኬ
> ዋው ፍጥነት.... ሪዘርቭ ልታደርጊልኝ ነው እንዴ ያስጠበቅሽኝ
+ ሂድ... ጨምላቃ... ደሞ ላንተ... ይልቅ... አብነት ሂድ... አሪፍ ምግብ አላቸው
> የት አካባቢ ነው
+ ካባላጋላ እና ካታንጋ መጋጠሚያው ጋር,,, ፋሲካ ሆቴል የሚል አለ አይደል... እሱን እልፍ ስትል ቀጭን መንገድ አለ... በሱ ወደ-ውስጥ ጉራንጉር ውስጥ ስትገባ ታገኘዋለህ.... ለማንኛውም እዛ አካባቢ ስትደርስ... አብነት ብለህ ጠይቅ
> እሺ ይኔ (ማለቴ) የሱ ቆንጆ.... ውለታ መላሽ ያድርገኝ
+ ሂድ... አስቀያሚ.... ደሞ ማታ ደውል!
> ፅቡቕ... ፅቡቕ
..........................................//.....................
መጣሁ

Dole
Starter
Starter
Posts: 19
Joined: 04 Jan 2012 20:47
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Dole » 17 Feb 2012 03:17

ሀሳቤ ሳይበተን ልድገም ዛሬውኑ
ሀይሉሻ... እንዴት ነው ይህች ተረት.... አደቆርሳ ያውቃት ይሆን
የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል.... ህምምምም.... ታዲያ ከማን ሊወልድ ነው.... እንደኔ ከጎረቤት?
ህምምምምምም
አያድርስ ነው
በል አሁን ወደ-ነገሬ
..............................//....................
ፋሲካ ሬስቶራንት ስደርስ አንድ አበሻ ሚመስል ልጅ አየሁ
መኪናዋን አስቆምኩና ልጠይቀው ስል ፈጥኖ መጣና
በፈረንጅኛ (ያበሻ ፈረንጅኛ ደሞ የትም ቢኮን ያስታውቃል እኮ)
> ለኮንፍረንስ ነው የመጣኸው... አለኝ ፈጥኖ
አንገቴ ላይ የተንጠለጠለ መታወቂያ ቢጤ እንዳደረኩ የታየኝ ቆይቶ ነው
+ አዎን አልኩት.... ውሸቴን
> እኔም ለኮንፍረንስ ነው የመጣሁት... ከሴኔጋል..... ሲለኝ
ድንግጥ ነው ያልኩት... ለምን መዋሸት አስፈለገ
ወዲያው ባማርኛ
+ እባክህ ወንድሜ.... አብነት ምግብ ቤት የት እንደሆነ ልታሳየኝ ትችላለህ... አልኩት
ደንግጦ....
> ነቅቻለሁ.... እንግዳ ነሽ አይደል... እየውልሽ ምን መሰለሽ.. ነፍሴ..... እኔ እዚህ አገር ከመጣሁ ቆይቻለሁ.....
ወሬውን መቅደድ ጀመረ
ከኃላ ለኛ ብለው የቆሙት መኪኖች... ጡሩንባ ማሰማት ጀመሩ
ምንም እድል ልሰጠው አልቻልኩም
ስለምን ማውራት እንደፈለገ ሳላውቅ... መኪናችን ተንቀሳቀሰች
በእጁ እየጠቆመኝ....
> ሳትፀድቅብኝ ልትሄድ ነው? .... በል እዛ ታች ስትደርስ ሰው ጠይቅ
አለኝና መልስ ሳይጠብቅ ሄደ...
ወደ-ሰው ጫካ ውስጥ ገብቶ ጠፋብኝ
የነገረኝ ቦታ ደርሼ... ሰው ስጠይቅ ... አሳዩኝ.... ወደ-ታች .. ወደ-ቁልቁለቱ
መኪና ያስገባል..ግን .. ጠባብ ስለሆነ መንገዱ... በእግርህ ብትሄድ ይሻላል አሉኝ
በእግር.. ወደ- አብነት ምግብ ቤት
..............................//...........................
ስገባ.. ጢም ብሏል
በብዛት የሚታዩት ግን... የጋምቤላ... ወይም የደቡብ ሱዳን ወጣቶችና ሴቶች ናቸው
የኢትዮጵያ ቲቪ ከፍ ባለ ድምፅ ተለቆአል... ዜና ላይ ነው
በእናርጅና እናውጋ ቀበሌ ያሉ ገበሬዎች... ለህዳሴው ግድብ መዋጮ አዋጡ
በጋራሙለታ የሚገኙ መምህራን የአመት ደሞዛቸውን....
በሀሳቤ....
እዚህም መጡ!... ነው ያልኩት
እነማን እንዳትሉኝ
የምሳ ሰአት ዜና ነው አሉኝ
ከወዲያ ጎን አንድ 6 የሚሆኑ ያበሻ መልክ ያላቸው ወጣቶች ምሳቸውን ይጠስቃሉ
> አብነት! ብዬ ተጣራሁ... እቤቱ መሀል ስደርስ
አንድ ወፍራም ወጣት ወንድ እና... አንዲት በ40ዎቹ የምትገመት ወጣት ሴት ዞር ብለው አዩኝ
> አብነት ነሽ
+ አዎን ምን ልታዘዝ
> አይ ሰው ልኮኝ ነው የመጣሁት.... አሪፍ ምሳ አለ ተብዬ
+ ጎሽ... ምን ይምጣለህ
> ምንድነው አሪፉ ምግብ እዚህ
+ ሁሉ አሪፍ ነው... በቅድሚያ ግን አትቀመጥም?
> ኦህ... የት ልቀመጥ .... እያልኩ ቦታ ሳማርጥ
+ ና እዚህ ጋር ተቀመጥ አለችኝ
ሁለት ወጣት ሴቶች .. አንዲት ክብ ጠረጵዛ ከበው ተቀምጠዋል
የኢትዮጵያን ቲቪ ያያሉ
ደስ አለኝ
ከሴት አጠገብ መቀመጥ.... ለወሬ ይመቻል
ምንም እየተመገቡ አይደለም.... ለስላሳ የያዘች መሰለኝ አንደኛዋ... ኮካ-ኮላ
ለመቀመጥ እየተስተካከልኩ... ወደ-አብነት ዞሬ....
> እስኪ አሪፍ ምግብ አንቺው እዘዥልኝ... ርቦኛል............ አልኳት
እና ዞር ስል... አንደኛዋ ልጅ ከወንበሯ ተነስታ መውጣት ጀመረች
> ውይ ጓደኛሽ የት ልትሄድ ነው?.... አልኳት እየተቀመጥኩ
+ ምን አልክ... አለችኝ... በደከመ ድምፅ
ፊቷ የተቦጫጨረ... የሚመስል.... አማርኛዋ የሚኮላተፍ.... ድክምምምምምምምምም ያላት.... ፀሀዩ ያጠወለጋት.... ምስኪን ለግላጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት
> አይ... ጓደኛሽ ስትወጣ አይቼ እኮ ነው....
+ ጓደኛዬ አይደለችም...
> ኦህ ሶሪ... አብራቹ ስትቀመጡ
+ ኖ አላውቃትም... ኡጋንዳዊ ናት... ምሳዋን በልታ መሰለኝ
> አንቺስ በልተሻል
+ አዎን
> የበላሽ አትመስይም... አብረን ብንበላ ምን ይመስልሻል
+ በውነት በልቻለሁ
> ፊትሽ ግን የበላ አይመስልም... ድክም ያለሽ ትመስያለሽ
+ አዎን ከፀሀይ ላይ መግባቴ ነው.... ወደ-ቤት ከመሄዴ በፊት ትንሽ ልረፍ ብዬ ነው
> ታዲያ ምሳ አብረን ብንበላ ምን ይላል
+ ኖ እበት ሰው ይጠብቀኛል... እንጀራ ገዝቼ... ወደቤት ለመሄድ ነው እዚህ የመጣሁት
አለችኝ በጥቁር ካቬራ (ሚካ- በሀረርኛ... የእቃ መያዣ ላስቲክ በ-አዲሳብኛ) የያዘችውን ደረቅ እንጀራ እያሳየችኝ
> እንዴ አንቺም ሴት ሆነሽ እየገዛሽ ነው እንዴ ምትበይው... ለምን እቤት አትጋግሪም
+ አይ.... ከመጣሁ ገባ ሶስት ወሬ ነው... ምኑንም አላውቅም
> ኦህ.. ነው ለካስ.... አዲሳባ እንዴት ናት
+ አይ... እኔ ካስመራ ነው የመጣሁት
> ዋው... ናይ ሰመናይ ፅብቅቲ ነሻ
ቅቅቅቅቅቅ...
+ ጥሩ ተጫዋች ነህ
> አምቼ ነሽ
አካካካካካካ....
+ እንዴት አወክ... አምቼ የሚለውን ስም
> አይ ብዙ አምቼ ጓደኞች ስላሉኝ ነው
+ አይደለሁም
> ተይ እንጂ...
+ አዎን አስመራ ተወልጄ ያደኩ ነኝ
የጨፈገገው ፊቷ ሲፍታታ... ቁንጅናዋ ሳቋ ላይ ሲወጣ ይታያል
> ታዲያ አማርኛ ከየት ለመድሽ
+ በጣም ስለምወድ... ከጓደኞቼ... ከአምቼዎች
> እንዴ እናንተ አስመሪኖች... አማርኛ ትወዳላቹ እንዴ?...
በመገረም ነበር የምጠይቃት
+ በጣም.... እንደምትሰማው አይደለም... የምናዳምጠው ሙዚቃ... የምንፃፃፈው ... የምናወራው... ባማርኛ ነው....
> ለምን ግን
+ እንጃ.... በቃ ደስ ይለናል
> አንድነታችንን ለማቅረብ እየታገላቹ ነው ማለት ነው
+ ምን አለበት......
> ደስስ ይለኛል.... እንዳንቺ ያሉ ሰዎች ቢበዙ.... እንዴት መልካም ነበር
+ ብዙ ነን
> አሀ... እናንተ እነማን ናቹ
+ እንዴ ጥያቄ አበዛህ..... በል ብላ ምሳህ መጥቷል
> ኖ አብረን ነው ምንበላው... አለበለዚያ ንክች አላደርጋትም
+ እረ!... እነ በልቻለሁ ስልህ
> አልበላሽም.... አትግደርደሪ... የቤቱ እቤት ይደርሳል... አሁን እየበላሽ አውሪኝ
+ ምን ላውራህ
> ስለራስሽ
+ ዋእ.... ሳላውቅ ብዙ አወራሁም አይደል
> በሞቴ ብይና አባይኝ.. ርቦኛል.... ከመጣሁ ስንት ጊዜ ሆነኝ ነው ያልሽው
+ ሶስት ወር... ሊሞላኝ ነው መሰለኝ
> እየበላሽ... እየበላሽ..... ላጉርስሽ እንዴ
+ ዋእ.... ኢሂሂሂ
አቤት ስታፍር ማማሯ
> በናትሽ ስምሽን ንገሪኝ
+ ፊአ..ሜታ
> ምን?
አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ
+ ምነው
> ፊያሜታ ነሽ እንዴ?
+ ኖ ኖ እንደሱ አይደለም ሚባለው... ፊአ..ሜታ... ነው
> ትንሿ ነበልባል
+ ምንድነው እሱ ደሞ
> ኦሮማይ የሚባል መፃፍ ታውቂያለሽ
+ ዋእ አላውቅም.. መፃፍ
> ከምር ግን ስምሽ ነው?
+ እንዴ... አው....ን ስልህ... ለምን ዋሻለህ.... በል ያንተን ስምን ንገር
> ባለሱቅ.... እባላለሁ.... እውነት ግን የስምሽ ትርጉም ምንድነው
+ እንጃ..... እናቴን ጠይቃት.... አንተ ብላ እንጂ
> ጠገብኩ
+ እንዴ ሳትበላ
> እንጃ ለካስ ሆዴ አልነበረም የተራበው
+ እህሳ... ወይ ጉ....ድ
> መንፈሴ ሳይሆን አይቀርም .... ከምር ጠገብኩ
+ ምንም እኮ አልበላህም
> በናትሽ ይልቅ አጫውቺኝ.... እንዴት ነው የመጣሽው
+ እንዴት ማለት
> በየት በኩል ነው የወጣሽው ካገርሽ.... እናትሽ ለምን ይህንን ስም አወጡልሽ... እውነት ትርጉሙን አታውቂም.... ምንድነው የምትሰሪው.... ከማን ጋር ነው ምትኖሪው
አጣደፍኳት
+ ሌላ ቀን እንጫወታለን... አለችኝ ጥያቄዬ ሲበዛባት
> ሌላ ቀን ብንገናኝ ደስ ይለኛል.... ሳወራሽ መንፈሴን ደስ አላት
+ እኔም ደስ ነው ያለኝ... እንጃ ለምን እንደሆነ....
> በይ ስልክሽን አምጪ
+ 0758.....
አቤት ደስ ሲል.... ሰው እንዲህ ቶሎ ተግባብቶ ቶሎ እሺ ሲል
እንዳበሻ መግደርደር የለ.... ለምነኝ የል.... መገላመጥ የለ... ... መጠርጠር የለ
የአስመራ ልጅ ይግደለኝ አቦ
እንደሀረሮቹ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
የመሀል አገር ልጆች አዋሶችና አዲሳቦች ናዝሬቶችና ባህርዳሮች ገደሉኝ
ያኔ አዋሳ ያገኘሀት የአስመራ ልጅም ልክ እንደዚሁ ነበረች.... ... ትዝ አለችኝ አቦ
...................................//.......................
ፊአ-ሜታን ይዤላቹ መጣለሁ...
ጠብቁኝ
አደቆርሳ እና ያዶላ ልጆች...
ዋርካ ፀድቷልና... ኑ ትባላላቹ
ሁለቱንም ቤት ማሞቅ አያቅተንም
በተረፈ
በቸር እንሰንብት
እመለሳለሁ ከፊያመቴ ጋር
ባለሱቅ

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”