Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
Post Reply
User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Unread post by morefun » 06 Oct 2009 01:42

መስከረም፡- ከረመ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ቀዳማይ፣ ለዓለም ሁሉ መጀመሪያ፣ ርእሰ ክራማት፣ መቅድመ አውራኅ ማለት ነው፡፡ መስከረም፡- ዐውደ ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው ማለትም ይሆናል፡፡

መስከረም በክረምት ውስጥ የሚካተት ቢሆንም የጨለማው ጊዜ አልፎ ብርሃን የሚታይበት፣ ዕፅዋትና አዝርእት የሚያብቡበትና የሚያፈሩበት፣ እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሣር እየነጩ የሚቦሩቁበት፣ በአጠቃላይ ምድር በአበቦች የምታጌጥበት፣ ሰማይ የደመና ቡሉኮውን (ጋቢዋን) ጥሎ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊት በከዋክብት ማጌጥ የሚጀምርበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ወር ናት፡፡

የመስከረም ስም ሲነሣ በግንባር ቀደምነት የሚወሱት አበባና እሸት ናቸው፡፡ በተለይ አበባ ከመስከረም ጋር ያላት ትስስር የተለየ ነው፡፡ አበባ በጥቅምትም ያለ ቢሆንም መስከረምን ያለ አበባ፣ አበባን ያለ መስከረም ማሰብ ያለ ደመና ዝናብ ለማግኘት የመመኘት ያህል ነው የሚሆነው፡፡ ከነተረቱ "መስረከረም በአበባው ሰርግ በጭብጨባው" እንዲሉ፡፡

"እንቁጣጣሽ" በኢትዮጵያ ብቻ የምትገኝ (የምትበቅል) ከመስከረም መጀመሪያ እስከ መስቀል ባለው ጊዜ የምታብብ ውቡ አበባ ናት፡፡ በትግራይ "ገልገለ መስቀል" እየተባለች ነው የምትጠራው፡፡ ደቡብ ጐንደሮች ደግሞ "አጐሮጐምባሽ" እያሉም ይጠሩዋታል፡፡ በመስከረም የምታብበው ግን እንቁጣጣሽ ብቻ አይደለችም፡፡ የድመት ዐይን፣ የጅብ ጫማ፣ አደይ አበባ፣ የልጃገረድ ኩል የመሳሰሉት በመስከረም ወር ብቻ ከሚያብቡ የአበባ ዓይነቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ሌላው የመስከረም መለያ፣ እሸት ነው፡፡ በሀገራችን ቆላማ አካባቢዎች እሸት የሚደርሰው ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ እሸት ከቅዱስ ዮሐንስ (እንቁጣጣሽ) በፊት አይቀመስም፡፡ ከዚሁ ከእሸት ጋር በተያያዘ መረሳት የሌለበት ጉዳይም አለ፡፡ በሀገር ቤት አዲስ ተጋቢዎች (ጐጆ ወጪዎች) በእንቁጣጣሽ የበቆሎ እሸት በስልቻ ሞልተው ለወላጆቻቸው ይወስዳሉ፡፡ ሌላውም ቢሆን እሸት ያለው ለሌላው "ዓመት ዓመት ይድገመን" እያለ ለጐረቤቱ እሸት ያድላል፡፡ ተቀባዮችም "እህል ይታፈስ ይርከስ፣ ሳቢ በሬውን አራሽ ገበሬውን ይባርክ፣ ኑሮአችሁ፣ ሕይወታችሁ እንደ እሸት የለመለመ ይሁን ወልዳችሁ ሳሙ ዘርታችሁ ቃሙ" እያሉ ይመርቁዋቸዋል፡፡
"እንቁጣጣሽ-አጐሮጐምባሽ"

ልጃገረዶች በእንቁጣጣሽ ማለዳ በየቤቱ እየዞሩና "እንቁጣጣሽ-አጐሮጐምባሽ" እያሉ የሚያድሉትን እንግጫና አበባ የሚቀጩት (የሚነቅሉት) በእንቁጣጣሽ ዋዜማ ምሽት ነው፡፡ ልጃገረዶቹ እንግጫ ነቀላ ወደ መስክ ሲሔዱ ወንዶች ችቦ ይዘው ያጅቡዋቸዋል፡፡ መስክ አንደ ደረሱ ለልጃገረዶቹ "አበባየሁ አበባየሁ አደይ" እያሉ እንግጫ መንቀል ሲጀምሩ ወንዶች ችቦዎቻቸውን ይዘው ፊት ለፊታቸው ቆመው ያበሩላቸዋል፡፡
(ካህሣይ ገ/እግዚአብሔር፤ ኅብር ብዕር፣ 1996)

--------------------------------------------------------------------------------
ጥቂት ስለ ቀለማት

ቀለማት እንደየ አካባቢው ባህል የራሳቸው መገለጫዎችና ትርጓሜዎች አንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ሰዎችን በቀለማቸው ቀይ፣ ጥቁር እና ጠይም እያልን በመክፈላችን መልካቸውን ለመለየት እንችላለን፡፡ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ታዲያ እንስሳቶች ከዝርያቸው ጋር በተዛመደ መልኩ የተለያዩ ቀለማት (መልክ) መገለጫዎች አሉዋቸው፡፡
ጓድ - ለሁሉም ነጭ የእንስሳት ዝርያዎች መጠሪያና መለያ ነው፡፡
ገምበና - ለሁሉም ጥቁር የእንስሳት ዝርያዎች መጠሪያና መለያ ነው፡፡
ብሻ - የቀይ ከብቶችና በሬዎች መለያ ነው፡፡
ዳማ - ለቀይ የፈረስ ዝርያዎች መለያነት ያገለግላል፡፡
ደማየት - የቀይ በጎችና ፍየሎች መለያና መገለጫ ነው፡፡
ዋአታ - ለቢጫ መሰል ከብቶችና በሬዎች መለያነት ያገለግል፡፡
ዶንግ - ለቢጫ መሰል ፈረሶች መለያነት ያገለግላል፡፡
አመጫ - ለተመሳሳይና ቀለማቸውም ቢጫ መሰል በጎች መጠሪያነትና መለያነት ይውላል፡፡
ገና - ለቢጫ መሰል ፍየሎችና ዶሮዎች መለያ ይውላል፡፡
ጊላ - የጥቁር ቡናማ ፈረስ መለያ ነው፡፡
ዘኸራ - ለጥቁር ቡናማ ላሞችና በሬዎች መለያነት ይውላል፡፡
ገኸራቤት - ለጥቁር ቡናማ በጎች መለያ የሚያገለግል መልክ ነው፡፡
(የጉራጌ ዞን ማስታወቂያ መምሪያ፤ አልፍኝ፣2001)
__________________________________________________________
Go to http://morefun.niceboard.net" onclick="window.open(this.href);return false for more.

Image


User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Unread post by selam » 06 Oct 2009 21:24

Once upon a time in a village in India, a man announced to the villagers that he would buy monkeys for $10.The villagers seeing there were many monkeys around, went out to the forest and started catching them.The man bought thousands at $10, but, as the supply started to diminish, the villagers stopped their efforts.The man further announced that he would now buy at $20. This renewed the efforts of the villagers and they started catching monkeys again.Soon the supply diminished even further and people started going back to their farms. The offer rate increased to $25 and the supply of monkeys became so little that it was an effort to even see a monkey, let alone catch it!The man now announced that he would buy monkeys at $50! However, since he had to go to the city on some business, his assistant would now act as buyer, on his behalf.In the absence of the man, the assistant told the villagers: 'Look at all these monkeys in the big cage that the man has collected. I will sell them to you at $35 and when he returns from the city, you can sell them back to him for $50.'The villagers squeezed together their savings and bought all the monkeys.Then they never saw the man or his assistant again, only monkeys everywhere!

players on wall street - to understand the current world financial situation!!!!!!!!!!

Welcome to WALL STREET.

User avatar
morefun
Leader
Leader
Posts: 152
Joined: 06 Sep 2009 01:52
Contact:

Re: Did you know this? ይህን ያውቁ ኖርዋል ?

Unread post by morefun » 07 Oct 2009 01:41

የአክሱም የንግድ መረብ

ፊሊፕሰን የተሰኙ ፀሐፊ አንድ የአክሱሞች ንጉሥ ምናልባትም ኢዛና ሊሆን ይችላል፡፡ በ340 ዓ.ም. አካባቢ ከምዕራብ አክሱም እስከ ሽሬ ግዛት ወደ ግብጽ መንገድ መዘርጋቱንና ይህንንም ያደረገው መውጫውን ለማስከበር ንግድን ለመቆጣጠርና የንግድን መስመር ወደ ምዕራብና ሰሜን ለመዘርጋት አስቦ እንደሆነ በ2002 ጽፈዋል፡፡ ይህ የንግድ መረብ አክሱምን በተጨማሪ ትልቅ ከተማ እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ለማየት ያስችላል፡፡

(የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት፣ አክሱም ለምን?፣ 2000)

-------------------------------------------------------------------

የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ

በየጊዜው የሚሠሩት አውሮፕላኖች በፍጥነታቸው፣ በሚያቋርጡት ርቀት በሚጭኑት መሣሪያ እየላቁና እየተራራቁ ሄደው በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የነበሩት አውሮፕላኖች ከ500 ኪ.ሜ በላይ ፍጥነት ያልነበራቸው ሲሆኑ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ግን ከ6500 ኪ.ሜ በላይ አቋርጠው የሚሄዱ፣ ከ10"000 ኪሎ ግራም የማያንስ መሣሪያ የሚጭኑና ከ500-800 ኪ.ሜ በሰዓት የሚጓዙ ሆነው ተሠሩ፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለቂያ አንስቶ እስካሁን አለንበት ጊዜ ደግሞ ማለትም የመጀመሪያው በረራ በተደረገ በ77 ዓመት የሚጭኑት መሣሪያ በቶን የሚቆጠር፣ ለሚያቋርጡት ርቀት ወሰን የሌላቸው (አየር ላይ ነዳጅ በመሙላት) ፍጥነታቸው ከድምጽ ፍጥነት በሦስት እጅ የሚበልጡ. በሬዲዮ የሚመሩ መሣሪያዎች ያሏቸውና የአንደኛው ወገን የሌላውን ከኢላማው ሳይደርስ ለማጨናገፍ የሚያስችሉ ናቸው፡፡

(መኮንን በሪ፣ አቪየሽን፣ 1995)

Image


Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”