
Re: መማማሪያ ቪዲዮ በአማርኛ .... Tutorial Videos in Amharic
Selam Awash,
እንዴት ሰንብተሃል? 2 ሰ ዓት ሙሉ ?..

አይ እንዲያው ትንሽ ስታጋንነው ነው እንጂ መቼም አንተ ይህንን አጠቃቀም አታጣውም
ዋርካ ላይ የምንጽፍበት መንገድ እና ይህኛው ብዙም አይራራቅም እኮ.. እስኪ ትንሽ ጊዜ ተለማመደው እና እንዴት ቀላል እንደሆነ ታየዋለህ። ሶፍት ዌሩን የሚሰሩት ሰዎች እነሱ እንዲህ ቢሆን ይሻላል ብለው ባሰቡት መንገድ ስለሚጽፉት እኛ ሁሉንም እንደልብ ለመልመድ ተቸገርን።
ወደፊት አንድ መስፈርት ወጥቶለት እስኪሰራ ድረስ በዚሁ መንገዛገዝ ነው እንግዲህ
ሌላው ነገር የማይክሮሶፍት ኦፊስ ሶፈት ዌሩ አንተ እንዳልከው ከ60 ቀን በሁዋላ የነጻ አገልግሎቱን ይጨርስና ካለገዛህ ወይም ቁጥር ካላስገባህ አልከፈትም ይልሃል።
ይህንን ፕሮግራም በነጻ ዳውንሎድ ማድረግ የሚቻልባቸው ሳይቶች አሉ ያው ስርቆት ነው እንግዲህ...

እናም ፕሮግራሙን አፕዴት ለማድረግ እስካልሞከርክ ደረስ በደንብ ይሰራል...( መላኪያ መንገዱን ካስተካከልን ልልክልህ እችላለሁ)
ፕሮግራሙን ከ60 ቀን በሁዋላ እንዳያቆም ማድረግ የሚቻልበትም መንገድ አለው ይህን ማጣቀሻ ተመልከተው
http://www.mydigitallife.info/2007/05/21/hack-to-activate-microsoft-office-2007-evaluation-trial-version/የትኛው እንደሚሻልህ መወሰን ትችላለህ
ለጉዋደኛህ የላከውን መልክት ሊከፍተው ያልቻለው ምናልባት እሱ 2007 ወርድ ስለሌለው ይሆናል ነገር ግን ሁለት አማራጮች አሉት
-- አንተ በ 2007 የጻፍከውን ሴቭ ስታደርግ ከ2007 በፊት ለተሰሩትም ጭምር ( 97 እና 03 ) እንዲከፈት በሚያስችል መንገድ ሴቭ ማድረግ ( ልክ ምስሉ ላይ እንደሚታየው)

-- ጉዋደኛህ በ2007 የተጻፉ ዶክሜንቶችን ማየት እንዲያስቸለው የሚያደርግ ማስተካከያ ከማይክሮሶፍት ዳውንሎድ ማድረግ
( ይህንን ማጣቀሻ መከተል ይቻላል)
Open a Word 2007 document in an earlier version of Word ከዚህ ከማይክሮሶፍት በተጨማሪ
ኦፕን ኦፊስ openoffice.orgየሚባልም ወርድ እና ሌሎችንም ነገሮች ሊያሰራህ የሚችል ፕሮግራም አለ። ነገር ግን አንተ በዚህ ፕሮግራም የጻፍከውን ወርድ ማይክሮሶፍት ወርድ አይከፍተውም።
በል አንጠፋፋ... ፕሮግራሙን ከፈለከው ጣፍልኝ እና እንደሚሆን እናደርጋለን።
መልካም ሰንበት።