"አንተ ነህ የሞትከው" የታገል ሰይፉ ምርጥ ግጥም ሊቢያ ላይ ስለተሰውት ኢትዮጵያውያን

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 558
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

"አንተ ነህ የሞትከው" የታገል ሰይፉ ምርጥ ግጥም ሊቢያ ላይ ስለተሰውት ኢትዮጵያውያን

Unread post by selam sew » 24 Apr 2015 00:06

"አንተ ነህ የሞትከው" በሚል ታገል ሰይፉ የሚያቀርበውን ምርጥ ግጥም በምስል ተቀናብሯል።

ፀፀቱ ይግደልህ! በታገል ሰይፉ

እንደኔው መሰደድ አባትህ ተሰዶ
መጠጊያ ፍለጋ ወደኛ አገር ሄዶ
ይቺን ጉረስ ካሉት አባቴ ፈትፍተው
እዚህ ስገድ ካሉት መስጊድ አሰርተው
ምን ይለኛል አምላክ ያንተን ነገር ብተው?
ብሎ እንደመቀበል ወዳጅን አክብሮ
አወኩ አወኩ ስትል አላወከው ኖሮ
የቁርዓኑን ፍቅር የዲኑን ሰላምታ
የሰውንም ክብር የኛንም ውለታ
በምን ልክፈል ብለህ ተጠበህ ተጨንቀህ
የት ነው የምትወስደኝ ማጅራቴን አንቀህ?

እኔ በባዶ እግር የሱ እግር በጫማ
እየለበለበኝ ሙቀት እንደ ሳማ
ከዚህ ጥቁር ጭንብል ከፊቱ ጭለማ
ምህረት አለመንኩም።
ማረኝ ብዬ ላልድን ከህይወት የራቀ
ሁለመናው በድን
ሁለመናው ድንጋይ ሁለመናው ብረት
ያለምንም ፍቅር ያላንዳች ምህረት
ያለርህራሄ ሙት አስከሬን እንጂ
.............ምኑን ሰው ነው ይኼ

አባቴ እንደሚለው ሰው ከወጣ ካገር
ጋላቢው ፊት ፈረስ አናጢው ፊት ማገር
ጫኙ ፊት አጋስስ የመሆኑን ነገር
ዛሬ በሰው ምድር ገብቶኝ ሳለ ገና
የኔን ህያውነት የኔን ትህትና
ገደልኩኝ ያልክ ማነህ? አንተ ነህ የሞትከው
ውለታ ቢስ ሆነህ ፍቅርን የገደልከው።

ዋናው ነገርማ መገኘት ነው ቆሞ
የሚሉህን ሰዎች አትስማ ፈጽሞ
ቆሞ መወዛወዝ መኖር ቢሆን ኖሮ
ያው ይወዛወዛል ያገርህ ጭራሮ
ያንተም ንቅናቄ ያንተም ደፋ ቀና
ለመኖር ጥያቄ መልስ አይሆንምና
ካለ ርህራሄ ካለ አዛኝ ልቦና
ልክ እንደ ጭራሮ ፍሬ አልባ ቁመና
ከጭራሮው በታች አንተም ጭራሮ ነህ
በሰብዓዊነት ላይ አፈሙዝ ደግነህ
ምንም አይደል ላንተ ይህ ሁሉ ጭከና
የምትንጎማለል አስከሬን ነህና
ካንተ እሱ ተሻለ የምድርህ አቧራ
ብድግ አለ ጨሶ ካፈሙዝህ ጋራ
እያጥወለወለው የሰራኸው ስራ።

የኛ አይን በረሃ መንገድ የሚያጠፋ
ያንተ ጀርባ ውሃው ካገር የሚሰፋ
የተንጣለለ አለም የለም...የለም....የለም
ምንም ውሃ የለም ከቆምክበት ጀርባ
ፍቅርን አንበርክከህ አንተ ስታደባ
ባህሩን የሞላው ውሃ አይደለም አባ
ያለም ህዝብ አዘን ነው የደሃ እናት እንባ

እስኪ ሰው ፈልጉ ከተንበረከኩት
ይናገሩ እንደሆን ምኑን እንደነኩት
ምን እንዳስቀየሙት ከዝምታው ተርታ
ወንድሜን ወንድሜን ለምትል ወዮታ
ምን አርጎት ነው እንበል
ከቶ ምን በደለው
ለዚህ እንኳን እኛ እራሱም መልስ የለው

ግን ላንተ አልመኝም እኔ እንደተበዳይ
እንዳንበረከከኝ አንበርክኮ ገዳይ
ከእኔ ላይ ላረፈው የጭካኔህ አይጣል
የሚመጥን ሞትስ ከወዴት ይመጣል?
እኔስ ሰው ነኝና እለያለሁ ካንተ
ድንገት ሞቼ ብገኝ ይባላል ሰው ሞተ
ማን ይላል ሰው ሞቷል አንተን ሰው ቢገድልህ?
ባይሆን ሰው ሁንና ጸጸቱ ይግደልህ


Image

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”