ቂርቆስ በኀዘን ማቅ በዳንኤል ክብረት

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 558
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ቂርቆስ በኀዘን ማቅ በዳንኤል ክብረት

Unread post by selam sew » 21 Apr 2015 22:33

ቂርቆስ በኀዘን ማቅ


ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከፖኤቲክ ጃዝ አባላትና ከሌሎች የኪነ ጥበብ ሰዎች ጋር ወደ ቂርቆስ ሄጄ ነበር፡፡ ያቺ ሳቂታዋና ተጫዋቿ ቂርቆስ ኀዘን ወርሯታል፡፡ የቂርቆስን ልጆች አውቃቸዋለሁ፡፡ ማልታ፣ ግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ስ
ዊዘርላንድ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ መሳቅ ነው፣ መጨዋት ነው፡፡ መቀለድ ነው፡፡ ችግር እነርሱ ጋር የለም፡፡ ካገኙ ተካፍለው ካጡ ተሳስቀው ያልፉታል፡፡ መተዛዘን፣ መረዳዳት፣ ነገር ማቅለል ማን ይችላቸዋል፡፡ እንግሊዝ ሀገር የደረሱት በመንገድ ያለቁትን የሚያስቡበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀን አላቸው፡፡
ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ
ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ
ይላሉ የማልታ ልጆች፡፡

ዛሬ ያ ሁሉ ሳቅና ጨዋታ በኀዘን ተቀይሯል፡፡ የልጆቻቸውን መሞት በቪዲዮ በተመለከቱ ወላጆች፣ ማንነታቸውን ከቪዲዮው ለመለየት አቅቷቸው በሰቀቀን ውስጥ በሚገኙ ወላጆች፣ የልጆቻቸውን መረጃ ፈልገው መልስ ባጡ ወላጆች ቂርቆስ ተሞልታለች፡፡ ትጠይቃለች፤ መልስ ግን አላገኘችም፡፡ እንዴት ያለው ትምህርት፣ እንዴት ያለው ጥበብ፣ እንዴት ያለው ብልሃት እንደሚያጽናናት እንጃ፡፡
እኔ በልቅሶ ቤት ሄጄ ብዙም አላለቅስም፡፡ ዛሬ ግን አለቀስኩ፡፡ በተለይ የባልቻ እናት ‹ፍቅር እስከ መቃብር› እያሉ ሲያለቅሱ ስሰማ ዕንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ኢያሱና ባልቻ ሲበሉም፣ ሲጠጡም፣ ሲሄዱም፣ ሲቀመጡም የማይለያዩ አብሮ አደጎች ናቸው፡፡ ሲሰደዱም አብረው ነው የተሰደዱት፤ መሥዋዕት የሆኑትም አብረው ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹ፍቅር እስከ መቃብር› የሚሉት የባልቻ እናት፡፡ እናቱን ሊረዳ እንደሄደ፣ ድሮም በእምነቱ ቀልድ እንደማያውቅ፣ ብዙ ተስፋ ሰጥቷቸው እንደነበረ እያነሡ ያለቅሳሉ፡፡ ‹‹እኔ ሲሞት እንዳላየው ብሎ አንገቱን ዘንበል አደረገ›› ይላሉ፡፡
አያሌ የከተማው ሕዝብ ለእግር መቆሚያ እስኪጠብ ድረስ ሠፈሩን አጨናንቆታል፡፡ ኡኡታ፣ እሪታ፣ ሰቆቃ፣ ቁጭት፣ ሰቀቀን፣ ይነበባል፡፡ የባልቻ እናት ከልጃቸው ሞት በላይ አሁንም በሊቢያ የሚገኙ ሌሎች ወገኖቻችን ያሳስቧቸዋል፡፡ ስለ እነርሱም ያለቅሳሉ፣ ይወዘወዛሉ፡፡

አይ ኢትዮጵያዊት እናት፡፡
Image

Image

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”