ለሐኪም ለመንገር የምንቸገራቸው ቀላል ችግሮች

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 592
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ለሐኪም ለመንገር የምንቸገራቸው ቀላል ችግሮች

Unread post by selam sew » 03 Sep 2014 17:32

ወደ ጤና ባለሙያ ከምንሔድባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለ ግል የጤና ችግሮቻችን ለመናገር ነው፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ የጤና ቸግሮች ከሌሎች የበለጠ ሌሎች ሰዎች ሊያውቋቸው አይገባም የምንላቸው አይነት ናቸው፡፡ ያም ሆኖ የወሲብ ችግር፣ በግልፅ የማይታይ ሽፍታ፣ መጥፎ የአካል ጠረን፣ አሉየም ለከባድ ጠረን የሚያጋልጠን የስሜት ቁስል ቢኖርብንም እንኳን እረዳት ለመፈለግ በሃፍረት መሸማቀቅ የለብንም፡፡ ለምሳሌም፡-

የአባላዘር በሽታ

ሰዎች የአባላዘር በሽታ እንዳለባቸው ለማወቅ በየጊዜው ወደ ሐኪም ቤት ይሄዳሉ፡፡ የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኛችን ለአባላዘር በሽታ መጋለጣችንን ከነገሩንና ምንም አይነት ምልክት ካልታየብን ወደ ሐኪም መሄዱን ትተን ነገሮች ጥሩ ይሆናሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡ ዳሩ ግን ለመዳንም ሆነ በሽታውን ወደ ሌሎች ላለማስተላለፍ መመርመሩ ጠቃሚ ነው፡፡

እንደ ጨብጥ ያሉ በሽታዎች በግልፅ የሚታዩ ምልክቶች ሲኖሯቸው ሌሎች መሰል በሽታዎች እንዳለብን እንኳ ለማወቅ እንቸገራለን፡፡ የብልት ሀርፐስ ሲጀመር ቢታወቅም አንዳንድ ጊዜ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት ከማይታይበት ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡

Image

ከመጠን ያለፈ ላብ

በጋለ ፀሐይ ስር ስንቆም ወይም በህዝብ ፊት ንግግር ስናደርግ ሰውነታችን ላብ ማመንጨቱ የተለመደ ነው፡፡ ሊያልበን በማይገባ ጊዜ ካላበን ግን Hyperhidrosis የተሰኘ የጤና ችግር እንዳለብን ሊያመላክት ይችላል፡፡

በላብ ምክንያት ልብሳችንን ቶሎ ቶሎ ከቀየርን፤ በቀን ከአንዴና ሁለቴ በላይ ሻወር ከወሰድን፤ ስንጨነቅ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስንሰራ እጆቻችን ከረጠቡ፤ አሊያም እቃዎችን መያዝ ካቻልን ወደ ጤና ባለሙያ ዘንድ መሄድ ይኖርብናል፡፡

ከመጠን ያለፈ ላብ ለችግሩ ህክምና ስላለው ችግሩን ለጤና ባለሞያ መግለፅ ጠቃሚ ነው፡፡ ችግሩ ያለብን እኛ ብቻ እንዳልሆንን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ Hyperhidrosis ከሌለብን እንኳ ከመጠን ያለፈ ላብ የሌሎች ጤና ችግሮች የጎንዮሽ ምልክት ሊሆን ስለሚችል መመርመሩ ይመከራል፡፡

ከልብ ድካም በኋላ ወሲብን መፍራት

ከልብ ድካም ህመም የሚያገግሙ ሰዎች ብዙ ጊዜ ወሲብ መፈፀም አለመቻላቸው ያሳስባቸዋል፡፡ የልብ ችግር ካብን የጤና ባለሙያው ስለ ወሲብ እስከሚያወራ መጠበቅ የለብንም፡፡ ይልቁንም ስለሚያሳስበን ነገር ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ መጠየቅ ካሉብን ጥያቄዎች መካከል ‹‹ቀስ በቀስ ወሲብ መፈፀም የምንችለው እንዴት ነው?››፤ ‹‹ምን አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እችላለሁ?›› እንዲሁም ‹‹ችግሩን ቀላል ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?›› የሚሉት ይገኙባዋል፡፡ ለምሳሌ የመተንፈስ ችግር ያለበት የልብ ህመምተኛ ወሲብ ቀጥ ብሎ እንደቆመ እንዲፈፅም ሊመከር ይችላል፡፡

አንዳንድ ህሙማን ወሲብ በድጋሚ መፈፀም አልችልም በሚል ይጨነቃሉ፡፡ አብዛኞቹ የልብ ህሙማን ግን ይህ አይነቱ ጭንቀት ሊያሳስባቸው አይገባም፡፡

የብቸኝነት ስሜት

በርካታ የስነ ልቡና ባለሞያዎች እንደሚሉት ለአብዛኛዎቹ ታካሚዎቻቸው ስለወሲብ ማውራቱ አያስቸግራቸውም ይልቁንም ይበልጥ የሚያሳስባቸው ከሌሎች ሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች የማህበረሰቡ አካል እንደሆኑ አይሰማቸውም፡፡ የሆነ አይነት ችግር እንዳለባቸው ያው ቃሉ፡፡ ስለዚህ ህይወታቸው ውስን ነው፡፡ ጥቂት ጓደኛ ቢኖራቸውም እንኳ ጥልቀት ያለው ግንኙነት አይመሰርቱም፡፡ ፍላጎቱ እያላቸውም በብቸኝነት ይጠቃሉ፡፡ ችግራቸውን ለመናገርም ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል፡፡ ቀስ በቀስ ግን ያለባቸውን ችግር ማውጣታቸው አይቀርም፡፡

ለረጅም ጊዜ የብልት መቆም

ለረጅም ጊዜ የብልት መቆም (priapism) በህመም ስሜት የታጀበ ከመሆኑም ሌላ በጊዜው ካልታከመ ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ስንፈተ ወሲብን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ደግነቱ እንደዚህ አይነት ችግር ሊገጥም የሚችለው በመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥመው ለእንቅልፍና እንዲታሹ ጭምር የሚታዘዘው ፀረ- ድብታ ስሜት የሆነው tragadone የተባለውን መድሃኒት ሲጠቀሙ ነው፡፡

ሀኪም መድሃኒት ሲያዝልን ፋርማሲስቱን ስለ አጠቃቀሙ ለመጠየቅ ማፈር የለብንም፡፡ በግልፅ እንዲያብራራልን ካስፈለገ ሰዎች ገለል ሲሉ ጥያቄ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡

የብልት ሽፍታ

በወንድ ወይም በሴት ብልት እንዲሁም መቀመጫ አካባቢ የሚወጣ ሽፍታ ምቾት የሚነሳ ነው፡፡ ፈንገስ፣ በተባይ መወረር ወይም ሌላ አይነት የቆዳ ችግር በማንኛውም የሰውነታችን ክፍል ላይ ቢታይ በፍጥነት ሀኪም ብናማክር መፍትሄ አግኝተን ችግሩ ሊቆም ይችላል፡፡

የሚያሳፍር ጥርስ

በጥርሳቸው የሚያሳፍር የሚመስላቸው ሰዎች ሲስቁ ፈገግታቸውን በእጃቸው መዳፍ የመሸፈን ልማድ አላቸው፡፡ አሊያም ከንፈራቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ በተፈጥሮም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች የፊት ጥርሳቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሀፍረታቸውን ገፍፈው ወደ ሀኪም ጎራ ቢሉ መፍትሄ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረን

ሁሉም ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳለውና እንደሌለው ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያው ጭምብል አጥልቆ እንኳ ዘልቆ የሚሰማ የአፍ ጠረን ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ የአንዳንድ ሰዎች የአፍ ጠረን ደግሞ ከሌሎች ይበልጥ አስከፊው ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ባክቴሪ የሚከማችበትን ምላስ በመፋቅ ወይም በመቦረሽ ችግሩን ማስወገድ ይቻላል፡፡

ከፍቱን መፅሔት

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”