ቲማቲም የመመገብ 10 የጤና በረከቶች

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ቲማቲም የመመገብ 10 የጤና በረከቶች

Unread post by zeru » 12 Apr 2014 18:47

1. ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ላይኮፔን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡
ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ…ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡

ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡

2. ቲማቲም በርካታ የካንሰር አይነቶችን ይከላከላል፡፡ በርካታ የጥናት ውጤቶች እንዳመለከቱት በቲማቲም ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው ላይኮፔን ፕሮስቴት፣ ኮሎሬክታል እና የሆድ ውስጥ ካንሰሮችን ይከላከላል፡፡
ላይኮፔን የካንሰር ህዋሳትን እድገት የመግታት ብቃት አለው፡፡ ቲማቲምን መቀቀልም በውስጡ የሚገኘው ላይኮፔን እንዲጨምር እንጂ እንዲቀንስ ስለማያደርገው ቲማቲምን ቀቅሎ መመገብ ከዚህ አንጻር ምንም ችግር የለውም፡፡
3. ቲማቲም ለአጥንት ጥንካሬ ወሳኝ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ካልሲየምና ቫይታሚን ኬ በውስጡ ያለው ሲሆን እነዚህ ንጥረ ነገሮችም አጥንትን ለማጠንከርና በአጥንት ላይ በተወሰነ መልኩ የመጠገን ባህሪ አላቸው፡፡
4. ቲማቲም በማጨስ ሳቢያ የሚከሰት ጉዳትን ይጠግናል፡፡ በቲማቲም ውስጥ የሚገኙት ከውማሪክ እና ክሎሮጂኒክ አሲዶች አካልን በሲጋራ ጭስ ውስጥ ከሚገኙት ካንሰር አምጪ ኬሚካሎች (ካርሲኖጂን) ይከላከላል፡፡


5. ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤ እና ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ እነዚህ ቫይታሚኖችም በሴሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱትን ጎጂ ʻፍሪ ራዲካሎችʼ ያስወግዳሉ፡፡ ቲማቲምን መቀቀል በውስጡ የሚገኘውን ቫይታሚን ሲ ስለሚያጠፋው ከዚህ አንጻር ቀቅሎ መመገቡ አይመከርም፡፡
6. ቲማቲም ለልብ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡ በቲማቲም ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚን ቢ እና ፖታሲየም በደም ውስጥ ያለውን የኮልስትሮል መጠንና የደም ግፊት እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም ቲማቲምን ከምግብ ዝርዝራችን ውስጥ በማስገባት የልብ ህመም፣ የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስና ሌሎች ከልብ ህመም ጋር የተያያዙ የጤና እክሎችን መከላከል ይቻላል፡፡
7. ቲማቲም ለጸጉር ጤንነት ይረዳል፡፡ በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ጸጉርን አብረቅራቂና ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለአይን፣ ቆዳ፣ አጥንትና ጥርስ ጤንነት ወሳኝ ነው፡፡
8. ቲማቲም ለኩላሊት ጤንነት ይረዳል፡፡ በአንዳንድ ጥናቶች ላይ እንደተረጋገጠው ፍሬውን ሳይጨምሩ ቲማቲምን ምግብ ውስጥ ጨምሮ መመገብ በኩላሊት ጠጠር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል፡፡
9. ቲማቲም ለአይን ጤንነት ይረዳል፡፡ በቲማቲም ውስጥ ያለው ቫይታሚን ኤ ለአይን የእይታ ብቃት ከመርዳቱም በተጨማሪ ʻNight Blindnessʼ የሚሰኘው በምሽት የማየት ችግር እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡
10. ቲማቲም በስኳር በሽተኞች ዘንድ ተመራጭ ምግብ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በውስጡ የሚገኘው ክሮሚየም የተሰኘው ማዕድን የስኳር በሽተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዳይዋዥቅ ስለሚያደርግ ነው፡፡Image

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”