Page 1 of 1

የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማ

Posted: 25 Feb 2014 22:00
by Ethiopian News
[justify] Image
[/justify]
[justify]የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡[/justify]ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
[justify]ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡[/justify]ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
[justify]ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡[/justify]ናይጄሪያም ከአንድ ወር በፊት ተመሳሳይ ሕግ ያወጣች ሲሆን የዑጋንዳው ሕግ በረቂቅነት ከወጣ የዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ምዕራባውያን ከፍተኛ ተጽዕኖ በማድረግ ሕጉ ተግባራዊ እንዳይሆን፤ ከሆነም በአብዛኛው የህጉ ክፍል እንዲሸራረፍ በርካታ ሙከራዎችን፣ ማስፈራሪያዎችንና ውስወሳዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ