በአባይ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር እየተነጋገርኩ ነው አለች

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

በአባይ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር እየተነጋገርኩ ነው አለች

Unread post by zeru » 25 Feb 2014 21:19

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 18/2006 (ቢቢኤን) ፦አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለዉ ግድብን እንገነባለን በማለት የኢትዮጵያ መንግስት በቦንድ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ ያደረገዉ ሙከራ እምብዛም አለመሳካቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት የግንባታዉ ፕሮጀክት ሰላሳ አራት ከመቶ ተጠናቋል ቢልም ግብጽ ባሰማችዉ ተቃዉሞ የግድቡ ግንባታ መስተጓጎሉን የመገናኛ ብዙሗን ዘግበዋል።
የኢትዮጵያ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ኢትዮጵያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሱዳን ጋር ዉይይት ጀምራለች” ሲሉ ገለጸዋል። ግብጽን ወደ ዉይይቱ ሒደት ለማምጣት እየተጣረ መሆኑን የገለጹት ሚኒስቴር ሒደቱ ምን እንደሚመስል ግን ያመላከቱት ነገር የለም።
ሱዳንና ግብጽ ከግድቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ኢትዮጵያ ብትገልጽም፤ ሁለቱ አገራት ግን ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ አልተስተዋልም። ግብጽ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነዉ የዉሃ ሐብቷ ከአባይ እንደሚመጣ ይታወቃል፤ የአባይን ጉዳይ እንደ ህልዉና ስለምትመለከትዉ የህዝብ ድጋፍ የሌለዉ የመላኒየሙ ግድብ እንደምን ዉጤታማ ይሆናል የሚለዉ ጉዳይም አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።
ግድቡን ለመገንባት እስከ ሐያ ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን መፈናቀላቸው የታወቀ ሲሆን 70 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ዉሃን ያከማቻል ተብሎ የተነገረት ግድብ ከፈነዳ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ።
ኢትዮጵያ ግድቡ በአዉሮፒያኑ ቀመር 2017 ሲጠናቀቅ እስከ ስድስት ሺ ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤለክትሪክ ሐይልን ለማመንጨት ብቃት ይኖረዋል ትላለች። ይህ ዉጥን ከግድቡ ባላንጣዎች ከሱዳናን ግብጽ ብቻ ሳይሆን” አባይ ከመገደቡ በፊት የመብት …
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”