ጾም ራስን በመግዛት ከእግዚአብሔር ጋራ ልዩ ግንኙነትና አንድነት ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ መሣር

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ጾም ራስን በመግዛት ከእግዚአብሔር ጋራ ልዩ ግንኙነትና አንድነት ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ መሣር

Unread post by zeru » 23 Feb 2014 21:24

Image
መልእክት ዘእም ኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእንተ በዓለ ጾም ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡ [center]በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡[/center]በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ፡-
እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለ፳፻፮ ዓ.ም. የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኁ፡፡
‹‹ወእመሰ በምግባረ መንፈስ ቀተልክምዎ ለምግባረ ነፍስትክሙ ተሐይዉ ለዓለም፤ በመንፈሳዊ ሥራ ሥጋዊ ሥራችኹን ብትገድሉ ለዘላለሙ ትድናላችኹ፡፡›› /ሮሜ ፰÷፲፫/
ጾም ከጥንት ጀምሮ በዘመነ ብሉይም በዘመነ ሐዲስ የተወደደ፣ የፈቃደ ሥጋ መቆጣጠሪያ፣ የፈቃደ ነፍስ ማበልጸጊያ መሣርያ ነው፤ እነሙሴ፣ እነኤልያስ እና እነዳንኤል ከእግዚአብሔር ጋራ በቀጥታ ይገናኙ የነበረው ራሳቸውን በጾም ለእግዚአብሔር በማስገዛት ነው፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዓርባ መዓልትና ዓርባ ሌሊት ጾሞ፣ በሰይጣን የቀረበለትን ፈተና አሸንፎ፣ የጾምን ድል አድራጊነት በተግባርና በትምህርት አሳይቶናል፤ (ማቴ. ፬÷፩ -፲፩)
ቅዱሳን ሐዋርያትም እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዲያቃናላቸው፣ ኃይለ መዊዕ (የአሸናፊነት ኃይል) እንዲሰጣቸው በየጊዜው ይጸልዩ ነበር፤ (ግብ. ሐዋ. ፲÷፳፫)
ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊትና ህልውት በኵሉ የኾነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ከነቢያት፣ ከጌታችንና ከሐዋርያት በተማረችው ትምህርትና በተቀበለችው ትውፊት መሠረት ከእግዚአብሔር ጋራ ለመገናኘት፣ ኃይለ አጋንንትን ድል ለማድረግ፣ ከእግዚአብሔር በረከትንና ረድኤትን ለማግኘት ጾምን ትጾማለች፡፡

ሰው በተፈጥሮው እርስ በርስ የሚጋጩ ኹለት ፍላጎቶች በውስጡ እንዳሉ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል፤ እነዚኽ ፍላጎቶች ሥጋዊና መንፈሳዊ ተብለው የሚታወቁ ሲኾን፣ የሥጋ ፍላጎት ለነፍስ ፍላጎት፣ የነፍስ ፍላጎትም ለሥጋ ፍላጎት ተቃራኒ እንደኾነ በቅዱሳት መጻሕፍት ተብራርቶና ተገልጾ ተቀምጦአል፡፡ (ገላ. ፭÷፲፮-፲፰)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በተመለከተ ሲያስተምር ‹‹የሥጋ ፍላጎት ሞትን ያመጣል፤ የነፍስ ፍላጎት ግን ሰላምንና ሕይወትን ይሰጠናል፤›› ብሏል፤ (ሮሜ ፮÷፮-፰)
የጾም አስፈላጊነት የሚመነጨውም ከዚኽ መሠረታዊ ትምህርት ነው፡፡ ሥጋ ኃይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦችን አብዝቶ በተመገበ ቁጥር ኃይል ይሰማዋል፤ በዚኽ ጊዜ ለእግዚአብሔር መታዘዝን ይዘነጋል፤ ወንድሙን ለመበደል ይፈጥናል፤ ማመዛዘን አይችልም፤ ብዙ ስሕተትንም ይፈጽማል፤ በመጨረሻም ይሞታል ማለትም ከእግዚአብሔር ጋራ አንድነትን ያጣል፤ በመንፈሳዊ እይታ ከእግዚአብሔር አንድነት መለየት እጅግ በጣም የከፋ ሞት ነው፡፡
በአንጻሩ ደግሞ ሰው ከምግብ በታቀበ ጊዜ ረጋ ብሎ ማሰብን፣ ማስተዋልን፣ ማመዛዘንን፣ ለእግዚአብሔር መታዘዝን፣ ራስን መግዛትን፣ ርኅራኄንና ቸርነትን፣ ለወንድም አዛኝነትን ገንዘብ ያደርጋል፤ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ጋራ አንድነቱን ያጠነክራል፤ በዚኽም የሞት አሸናፊ ኾኖ በእግዚአብሔር መንግሥት በዘላለማዊ ሕይወትና ክብር ተደስቶ ይኖራል፤
ከዚኽ አኳያ ጾም ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት፣ ራስን በመግዛት ከእግዚአብሔር ጋራ ልዩ ግንኙነትና አንድነት ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ ኾኖ ይገኛል፡፡
ጾማችን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አግኝቶ ሙሉ ዋጋ ሊያሰጠን የሚችለው ከፍቅር፣ ከምጽዋት፣ ከሰላም፣ ከጸሎትና ራስን ለእግዚአብሔር ከማስገዛት ጋራ ሲኾን ነው፡፡
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”