ከአሥር ሺህ በላይ ሕዝብ በተገኘበት፣ «ጥቁር ሰው» እና «ያስተሰርያል» በድጋሚ እንዲዘፈን ተጠ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ከአሥር ሺህ በላይ ሕዝብ በተገኘበት፣ «ጥቁር ሰው» እና «ያስተሰርያል» በድጋሚ እንዲዘፈን ተጠ

Unread post by zeru » 29 Apr 2014 18:54

Image
አንጋፋዉ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ቅዳሜ ሚያዚያ 18፣ ቀን በጊዮን ሆቴል ከአስር ሺህ ህዝብ በላይ በተገኘበት ፣ የፍቅርና የኢትዮጳይዊነት ጣእም ዜማዎችን ሲያቀርብ እንዳመሸ ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ታዋቂዎቹ «ጥቁር ሰው» እና «ያስተሰርያል» የተባሉት ዘፈኖች በሕዝቡ ጥያቄ በድጋሚ እንደዘፈኑ የተደረገ ሲሆን፣ሕዝቡ ዘረኝነትና ክፍፍል፣ ጥላቻና ቂም በቀለ እንደመረረዉ በመገልጸ ፍቅርን፣ የሰላምን እና የአንድነት መልእክት ማስተላለፉን ለማየት ተችሏል።
በተለይም ጥቁር ሰው የተሰኘውን ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊ ዜማን የሚቃወሙ፣ አንዳንድ አክራሪዎች ፣ በዚህ ጣእመ ዜማ ምክንያት፣ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ላይ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርቶች ስፖንሰር እንዳየገኙ ከፍተኛ ግፊት ሲአይደርጉ እንደነበረም ይታወቃል።
እንደዚያም ሆኖ፣ ከ10 ሺሆች በላይ የሚሆን ሕዝብ በዚህ ኮንሰርት በመገኘት ለተዲ አፍሮና ለሚዘናቸው ዘፈኖች ያለዉን አክብሮትና አደናቆት ገልጿል። ብዙ ድምጹ በአደባባይ የማይሰማው ሰፊዉ ሕዝብ፣ በኮንሰሩ በመገኘት ፣ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን፣ ዘረኝነትን ሳይሆን አንድነትን እንደሚፈልግም ያረጋገጠበት ሁኔታ እንደሆነ ለማየት የተቻለው።
ጥቁር ሰው የተሰኘው ዜማ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ሁሉ ኩራት የሆነውን ታላቁን የአድዋ ድል በአል የሚያስታወስ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ አጼ ምንሊክ ፣ ሕዝቡን አስተባብረው የነጭን ኃይል ያንበረከኩ የመጀመሪያዉ ጥቁር መሪ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የጥቁር ሕዝብ ሁሉ አባት መሆናቸውን ያመላከተ ነው።
«ባልቻ አባቱ አባ ነፍሶ ፣
መድፉን ጣለው ተኩሶ»
ሲል የባልቻ አባ ነፍሶን ጀግንነት የሚያቀነቅነው የጥቁር ሰው ዜማ
«ዳኛው ያሉት አባ መላ ፊት ሃበቴ ቢነግዴ፤
ሰልፉን በጦር አሰመረው ፊት ሆኖ በዘዴ»
ሲል ስለጥበበኛዉ አባ መላም ይጠቅሳል።
የአድዋ ድል ባይኖርም ኖሮ፣ በፈረንጆች እጅ ወድቀን፣ አሁን ያለን መንነታችን አይኖረን እንደነበረ ለመገልጽ «ወይ ሳልለው ብቀር ያኔ፣ እኔን አልሆንም ነበር እኔ» በማለት የጠቁር ሰው ዜማ ይጠናቀቃል።
«ቅርብ ነው አይቀርም የኢትዮጵያ ትንሳኤ፣ በአንድነት ከገባን የፍቅር ሱባኤ
ፍቅር አጥተን እንጂ በርሃብ የተቀጣን፣ አፈሩ ገራገር ምድር መች አሳጣን
በተስፋዉ መሬት እንዲፈጸም ቃሉ፣ ሞፈርን ያዙና ይቅር ተባበሉ»
ሲል ደግሞ ሌላ በድጋሚ እንዲዘፈን በተጠየቀዉ በያስተሰርያል ዜማ የፍቅር፣ የተስፋ መልእክቶችም ተቀንቅነዋል።

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”