ከሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በየሃይማኖታችሁ ጣልቃ ለተገባባችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በየሃይማኖታችሁ ጣልቃ ለተገባባችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

Unread post by zeru » 26 Apr 2014 15:18

ቀን 18/08/ 2006 ዓ.ም
ውድ ሃይማኖታችሁ ላይ ጣልቃ እየተገባባችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን በነጻነት የፈለጉትን ሃይማኖት እንዲከተሉ፣ የፈለጉትን እምነት እንዲይዙ ባለው የጸና አቋም ገዥው ፓርቲ በሙስሊሙና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እያደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት ሲቃወም ቆይቷል፡፡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ገዥው ፓርቲ በሐይማኖቱ ጣልቃ መግባቱን ተቃውሞ የሚያደርገውን ፍጹም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በማድነቅ ገዥው ፓርቲ ከህገ ወጥ ተግባሩ እጁን እንዲሰበስብ ምክር ከመለገስ አልፎ በሰላማዊ ሰልፍም ድምጹን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተወሰደው ህገ ወጥ እርምጃ እና በእስር ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይም በጽኑ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ወደፊትም በዚሁ አቋሙ እንደሚቀጥል ይገልጻል፡፡
በተመሳሳይ በክርስቲያኖች በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ያለውን ጣልቃ ገብነትም በተመሳሳይ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህል በዋልድባ ገዳም ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ ተግባር በግልጽ ተቃውሟል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለይም በማህበረ ቅዱሳን ላይ ጫና እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በማህበሩ ላይ ሊደረግ የታሰበው ሴራ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም ሆነ በማህበሩ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫናም በጽኑ ይቃወማል፡፡
ውድ የሁለቱም እምነት ተከታዮች፡- ሰማያዊ ፓርቲ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያደርገውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት በጽኑ እየተቃወመ፣ ማንኛውም በሐይማኖታችሁ ላይ የሚደረግን ጫና በግልጽ እንድትቃወሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የሁለቱም የእምነት መጽሃፍቶች በአንዳችን ላይ የሚደርሰው ግፍ በሌላኛው ላይም እንዳይሆን መፈለግ እንዳለብን እንደሚገልጹት የእናንተ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫናም በመቃወም ለመርህ እንድትቆሙ ማሳሰብ ይፈልጋል፡፡
ሃይማኖት ለአንድ ማህበረሰብ ማንነት መሰረት እንደመሆኑ በአገር ግንባታ ቀላል የማይባል ሚና እንዳለው እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሐይማኖታች ሳይገድበን ተረዳድተን፣ ተባብረንና ተፈቃቅረን ኖረናል፡፡ ለዚህ አብሮ መኖርና መቻቻልም ሃይማኖታችን የራሱ የሆነ ሚና እንዳለው እናምናለን፡፡ ገዥው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ብቻ ሳይሆን አንድ ሐይማኖት ውስጥ የሚገኙትን የአገራችን ዜጎች በጠላትና በወዳጅነት በመከፋፈል ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳቸው እንዲጠራጠሩ፣ ግጭት ውስጥ እንዲገቡና ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዳይከተሉ እያደረገ ነው፡፡ ይህም ለቀጣይ የአገራችን ሁኔታ አሉታዊ አስተዋጽኦው የጎላ በመሆኑ ፓርቲያችን በጽናት ይቃወማል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ጽኑ አቋሙ አግባብ ያልሆኑ የተለያዩ ስሞች ተሰትቶታል፡፡ አመራሮቹና አባላቱም ታስረዋል፡፡ ተደብድበዋል፡፡ ከተነጠቁት መብቶች መካከል ይህን የእምነት ነጻነት መብት እንዲከበር የሚጠይቁ ጥያቄ ባነሳበት በአሁኑ ወቅት እንኳ ከ50 በላይ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ማጎሪያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያውያን መብት ይከበር ዘንድ የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈልም ቁርጠኛ መሆናችንን መግለጽ እንወዳለን፡፡
ገዥው ፓርቲ በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ በመግባት የዜጎቻችን አንዱንና ዋነኛውን መብት ቀምቷል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የኢትዮጵያውያን መብት ለማስመለስ ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በመሆኑም ይህን የተቀማችሁትን መብት ለማስመለስ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ እንድትሳተፉ ጥሪውን ያቀርብላችኋል፡፡
ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፋንታ እንወስን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ይኑር!

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”