የሁለት መቶ ሁለት ነፍስ የታደገ ማስተዋል – ማህበራዊ ኑሮንም ያዳመጠ ብልህነት። (ከሥርጉተ ሥ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የሁለት መቶ ሁለት ነፍስ የታደገ ማስተዋል – ማህበራዊ ኑሮንም ያዳመጠ ብልህነት። (ከሥርጉተ ሥ

Unread post by zeru » 17 Apr 2014 20:23

Image

«ማስተዋልን ገንዘቡ የሚያደርግ፣ በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርሷ መነገድ ይሻላልና። ከቀይ ዕንቁም ትከብራላች፤ የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም። በቀኛዋ ረጅም ዘመን ነው፣ በግራዋም ባለጠጋነትና ክብር። እርስዋን ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት። የተመረኮዘባት ሁሉም ምስጉን ነው። እግዚአብሄር በጥበብ ምድርን መሠረተ በማስተዋልም አጸና። ምሳሌ ም.3 ቁ. 13 እስከ 19 »
በቅድሚያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምንያን እንኳን ለ2006 ፀሎተ ሃሙስ አደረሳችሁ – አደረሰን። ልክ የዛሬ ሁለት ወር በዚህች ዕለት የሰማይ ታምር በማስተዋል ተገለጠ። ዓለምም ታደመ – በአጽህኖት በአንክሮ ተደመመ። የወያኔ ገዢ መሬትም ተደፈረ – በጎጥ የጎረና የዘበጠ አስተዳደሩም አፈረ – ተመዘነ።
ማስተዋል የሰማይ ጸጋ ነው። ማስተዋልን እግዚአብሄር አምላክ መርቆ ሲሰጠን እንድናስተውለው ነው። ማስተዋል „ማስተዋልን“ አብክሮ የሚጠይቅ መክሊትና ክህሎት ነው። ክህሎት ነው ያልኩበት ምክንያት ሰው በዕድሜው ተመክሮ ያገኛቸው ትምርቶች ተግባሩን መካሪ እንዲሆኑ መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፤ ከዕድሜ ጋርም በርካታ ባህሪያት እዬሰከኑ ስለሚሄዱ ማስተዋል የበለጠ እያማረበት እዬተዋበ ይሄዳል ለማለት ነው። ማስተዋልን የሰነቀ ግለሰብ፣ ድርጅት ወድቆ አይወድቅም፤ ጉዞው ሁሉ መጪ ነገሮችን አስቀድሞ ዬሚይበት መሳሪያ በመንፈሱ ስላለው የተግባሩ ትልም ሆነ መቋጫው አቅም ያለው እርግጠኝነትን የጠጣ ይሆናል። የፈለገ ዓይነት ያልተጠበቀ ሁኔታ ቢመጣም ይቋቋመዋል። ማስተዋል እኛ እንደምናስበው ለተለዩ ፍጥረቶች አምላካችን የሸለማቸው ሳይሆን ሁላችንም ያለን ሀብት ሆኖ፤ ግን ያላዬነው መሪ ሥነ – ምግባር ነው። ማስተዋልን „የማስተዋል“ የመቻል አቅም ግን ተለይቶ መቀባት ይመሰለኛል።
በማስተዋል የተመራ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ካዬን ልክ ዛሬ ሁለት ወራችን ነው። „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ከባሩድ በስተቀር በማናቸውም በእጅ በገባ አምክንዮ ሊከወን ይችላል። ክወናው መስዋእትነቱን ሊያቀለው ወይንም ሊያከብደው ይችላል። የጀግናዬ የረ/ አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን ወይንም እንደ ሲዊዞቹ ረ/ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ኃይለመድህን የማስተዋል ልክ መለካት ያለበተ እጅግ በዳበረ ማስተዋል የተከወነ መሆኑ ነው። ካለምንም ንብረት ውድመትና ካለምንም ህይወት ጥፋት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ጫና ሳይፈበረክ የተከወነ ጉልበታም ደፋር „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ አብነት ነው። የታሪኩ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ከመሆኑ ጋር ይህን ተከትሎ በአለማችን በጉልህ የቀጠሉ ተግባራትን ስንመለከት እውነትም እርምጃውና ጥበቃው የአምላካችን የመዳህኒተአለም ስለመሆኑ እንገነዘባለን። 202 ነፍስን በማስተዋል የታደገው ይህ ድንቅ ተግባር ዘመናትን ሊያሻግር የሚችል የብቃት ልቅም – ልቅናም ነው።
ከዬካቲቱ የብልሁ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ በኋላ በአውረፕላን ዙሪያ ሰማይ ላይ ሆነ የብስ ላይ የተከሰቱ ተግባራት የእሱን የማስተዋል ብቃት እኛ ካለን የማስተዋል ሃብት ጋር ፍተሻ እንድናደርግበት በሚገባ ያስተምራል። በተጨማሪም ዓለም በሁለት ረዳት አውሮፕላን አብራሪዎች መሃከል ያለውን ብቃትና የብልህነት ደረጃ እንዲገመግም በራሱ ጊዜ በፈቃደ እግዚአብሄር አቅም እዬተለካ ነው። እኔን ስትሞግተኝ የነበረች ባልደረባዬ „ አበራ ሊደነቅ ይገባል“ አለችኝ። ለነገሩ ለእሷም ማስተዋሉ ተገልጦላት።
ሀ. የጀግናዬን ማስተዋል የበለጠ የሚያብራራ፤ የሚያበለጽግ አጋዢ ሰሞንተኛ የሰማይና የምድር „እንቢተኝነት“
  1. ወርኃ መጋቢት —- እኔ እንደማስበው ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ „ማስተዋሉ“ ያሰቀረውን ዓለም አቀፍ እንግልት፣ ጥፋት፤ የመንፈስ ጭንቀት፤ የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ፤ የፖለቲካ ትርምስ ማስተዋልን አለብን ባይ ነኝ። እኛ ብቻ አይደለም እያንዳንዱ ሰው ዓለም ዓቀፍ ድርጅትም። እኔ አስቀድሜ በጻፍኳቸው ጹሑፎች አንድ ነገር ተማጽኜ ነበር። „በአዎንታዊ“ እንድንመለከተው …. ይሄው የማላዥያ አውሮፕላን 26 ሀገሮች ቀንና ሌት በአውስትራልያ በፐርዝ ውቅያኖስ ማሰኑ … ስንት ገንዘብ? ስንት ነርብ? ስንት ሴል? ስንት ጊዜ? ስንት ዕንባ ፈሰሰበት? ስንት ቤተሰብ ተበተነበት? ሳይንስን ያሸነፈ ጥረት ባተለ። እንዲሁም የቀዝቃዛው ጦርነት አካል ሆኖ ዓለምን እያመሰ ነው። ከሁሉ በላይ „ከሞቱ አሟሟቱ“ ይላል የቀደመው ብሂል፤ ዬሂደቱን ወጥ መረጃ ለመስጠት እንኳን ያላስደፈረ በመሆኑ ተሳፋሪዎች የደረሰባቸው አለመታወቁ ብቻ ሳይሆን፤ ዬታላላቅ ሳይንቲስቶች ጠበብት ሊቃናተ – ሙሁራን የትንበያ ሆነ የጥበብ አቅም ፈተነ – ገመደ።
  2. ወርኃ ሚያዚያ — ከሚዚያ መግቢያ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በጎረቤት ሀገር በጀርመን ታዋቂው የሉፍታንዛ አውሮፕላን ከቱርክ አዬር መንገድ በእጥፍ፤ ከሌሎችም የተሸለ ትርፍን የሚዝቅ ድርጅት፤ ለአብራሪዎቹ የሚከፈለው ማህያ ጋር ሲነፃፀር አይመጥንም ሲሉ የኖሩ ኖረው በሚዚያ መግቢያ በ2014 ለተከታታይ ቀናት ሞተራቸውን ረ አድርገው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሉፍታንዛ ተጓዡን ሲያዘገይ እንኳን ድጎማ የሚያደርግ ሲሆን፤ ያ … ሁሉ በረራ ተጓጉሎ ቀጥ በማለቱ የጀርመን መንግሥት ስንት መዋለ ንዋይ ከሰረ? ስንት ቀጠሮ ተሰረዘ? የሚችሉ ወደ ፈረንሳይ፣ ወደ ኦስትራሽ ፣ ወደ ሲዊዝ በመሄድ ተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ አፈሰሱ። ይህ „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ በዚህ መልክ የተካሄደው ጀርመን ተቃውሞን ለማሰማት ዴሞክራሲ ያለበት ሀገር ስለሆነ ነው። የእኛ ግን ሃሳቡን ማሰብ እንኳን አይቻልም፤ እንኳንስ እንዲህ ለተከታታይ ቀናት አውሮፕላን አቁሞ አመጽ ማካሄድ ቀርቶ። አግባብነት ያለው ጥያቄ በግል ለማቅረብ እንኳን ጋዳ ነው። ከዚህ አንጻር ፈቃደ እግዚብሄር በሁሉም አቅጣጫ ሰማይ ላይ ሆነ ምድር ላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ ነገሮችን እዬፈጠረ ወጣቱ ፓይለት የወሰደውን ውሳኔ፣ የማስተዋልና የብልህነት ብቃት በአዎንታዊነት እያበሰለው ይገኛል። ትርፍ!
ለ. የወያኔ መደፈር እልህና ቁጣ ተከታይ እርምጃ።
ይህን በሚመለከት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ የተበራራ ቀዳሚ የማሳሰቢያ ጭብጥ አቅርቧል። ስለምን በሚስጢር ተያዘ ለሚለው እኔ እንደማስበው ከሆነ —
  1. የሲዊዝ መንግሥት ተጠይቆ አዎንታዊ መልስ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅ ግድ ይል ነበር። ፍርዱን ሊያከብድ የሚችል የወንጀል ክስ አስቀድሞ ወያኔ ቢያሳውቅ፤ የሲዊዝ መንግሥት „አሻም“ ሊል ስለሚችል፤ ምንም ያልተፈጠረ አድርጎ አለሳልሶ ለመስለብ ነበር የጫካው ተመክሮ – የመከረው። ግን ይህ አልተሳካም።
  2. ድርጊቱ ሲከወን በጓዳ ስላልነበር የክሱ መሰረት ተምታቶም ይሁን ቅጥፈት ተሸምቶ መቀነባበር ነበረበት። ለዚህም ወያኔ በቂ ጊዜ ያስፈልገው ነበር። ልክ ሄሮድስ መለስ ሲሞቱ እንደ ተሰራው ድንባስ ትእይንት ቀድሞ መዘጋጀት አለበት ወያኔ ገርድፎ ይሁን ሸርክቶ።
  3. የጀግናው የኃይለመድህን ተግባር ወያኔ ባላለመው፤ ባላሰበው፤ እጅግም ባልገመተው ነበር። ጥቃቱን ያደረሰበትን የመንፈስ ትርትርና ትርምስ መልሶ ለመቋቋም ገዢው ፓርቲ ወያኔ አቅሙ አልነበረውም። ስለሆነም ወያኔ ትንፋሽ መሰብሰብ ነበረበት። የሚርገበገብ መንፈሱ ተግ ማለት ነበረበት። ደፋር እርምጃ ያስታጠቀውን መንፈሳዊ ቁስለት ለማገገም ጊዜ ማግኘት ለወያኔ በእጅጉ ያስፈልገው ነበር። አዬር ላይ የተወሰደው እርምጃ እንዲህ በግልብ፤ በግብታዊነት የተከወነ አልነበረምና። ሲዊዝ ከገባ በኋላ እንኳን ፎቶውን ለማግኘት አልተቻለም። ስለዚህ ይህን ለመሞገት ልጥፍና ዝግ መሳናዶ አስፈለገው – ወያኔ
  4. አስተዋዩ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ሀይለመድህን መነሻውን፤ መድረሻውን ያወቀ፤ መሬት ላይ የሚጠብቀውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ ጠንቅቆ የተረዳ። ወቅት የሰጠውን ዕድልም ያላሾለከ የማስተዋል ፍሬ ነው። ክንውኖቹ ሁሉ የማስተዋል ማህጸነ – ሚስጢር ናቸው።
  5. ሐ. ለቤተሰቦቹ እኔ እምለው።
ውጬ ሀገር የሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች ሁሉ አስከ 18 ዓመት እስር፤ የእድሜ ልክ እስር፤ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አሉ። ይህ ወያኔ አቅሙን አለማዋቁን ነው የሚመለከተው እንጂ የሚያመጣው አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ የፈለገውን አይነት ክስ ወያኔ መስርቶ የሚፈልገውን አይነት ውሳኔ ቢሰጥ ወገኖቼ ቅጭጭ አይበላችሁ። ማስተዋልን ወልዳችሁ አሳደጋችሁ። ማስተዋሉ የሸለመው ደህንነት አለና አትስጉ – ለደቂቃ አደራ! ሲዊዝ እንደተፈለገ ተገብቶ የሚዛቅ ምንም ነገር የለም።
ይልቅ አራዊት ስለሆነ ወያኔ ለእናንተ ለራሳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ጥቃት ሊሰነዝርባቸው የሚችሉ እጅግ በርካታ መስኮች አሉት። ግንኙነትን መወሰን፤ ከተገኘው ቤት አለመመገብ፤ የተገኘውን ሥጦታ አለመቀበል። በፖስታ የሚላኩ ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ ማዬት ይገባል። በተረፈ „በማስተዋል“ ላይ የወያኔ ማናቸውም ዓይነት ፍርድ ሊያደርስ የሚችለው ምንም ነገር የለም። ከተጀመረ ጀምሮ ያለው የሂደቱ ጠረን ምላሽ ሆነ አዬሩም፤ እንዲሁም አካባቢውም፤ ተያያዥ ነገሮችም እርምጃውን – ውሳኔውን – ማስተዋሉን እንደ ታቦት የሚከበክቡ ናቸው።
አዬር ላይ ሳይቀር የጣሊያንና የፈረንሳይ አውሮፕላኖች እኮ አጀበውታል። ይህ በሰው ሃይል የተከወነ አይደለም። በሳምንቱ እትብቱ በተቀበረበት የተከናወነው ድንቁ የባህርዳሩ የመኢህድና የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ቀድሞ የተሰናዳ ግን የጄኔቡን ድል ያጀበ ነበር። በጣም ዕንቁ መረጃ ነበር። ከዚህ ሰልፍ በኋላ የሁለቱ ፓርቲዎች ሁኔታስ …? ይህም ሌላ ታምር ይነግረናል። ዙሪያ ገባው በአባታችን በመዳህኒአለም ጥበቃ የሚደረግበት ክንውን ሰለሆነ ጉዳዩን ለፈጣሪ መስጠት ነው። የእውነት ወላጆቹም ቅኖች ናችሁ። እንደገና በማህበራዊ ህይወትን ያቆሰለ ቋሳ አልተከለም። አንድ ነፍስ አልጠፋም። ደም አላጋባም። የማህበራዊ ኑሮን ሥነ -ምግባር በቅጡ ያደመጠ ብልህነት- ልዕለ ምህረት።
መ. ባለቤት ስላልነበረው ወቅታዊው ሲዊዛዊ ዘገባው ትንሽ ልበል።
መቼም ጀግናዬ ኃይለመድህነ አበራ በጣም ያስተማረን ነገር ማስተዋልና ትርፉን ነው። ስለዚህ በእሱ ዙሪያ የሚፈሱ መረጃዎች ሁሉ እጅግ በጣም የጥንቃቄን ጥበቃ ይሻሉ። አሁን ሀገር ቤት ያለውን በማስተዋልና በጥንቃቄ መረጃውን ያቀበለን የጋዜጠኛ ተመስገን ዘገባ ዘርጋ አድርጋችሁ ስትመልከቱት „የጉዳዩን ደህንነት“ በሚገባ ጠብቆለታል። ስሜቱን ለመግለጽ እንኳን እራሱን ቀጥቶ በተረጋጋ ቀለማዊ ስክነት ነበር ዕይታውን የገለጸው። ወሸኔ ነው ማለፊያ ወንድምዬ።
ወደ ጉዳዬ ስመጣ አሁን ሲዊዝ ላይ ስላለው ሁኔታ መረጃ ያቀበለን ዘገባ ባለቤት ቢኖረው መልካም በሆነ ነበር። ተጠያቂነት ሆነ ተመስጋኝነት ጥግ ይኖረዋል። ለማንኛውም ዘጋቢው ማን? መሆኑን ባላውቅም ሊስተካከሉ በሚገባችው ጉዳዮች ላይ ትንሽ ማለት ወደድኩኝ። ስለምን ነገም ሌላ ዘገባ ሊቀርብ ስለሚችል መስተካከል አለበት ብዬ ስለማምን። መነሻዬ ይህ ነው።
በቅድሚያ ግን የተከበሩ(ችሁ) የመረጃውምንጭዘጋቢ(ዎች) አመሰግናችኋለሁ – የወያኔህልምመክሰሩን፤የወያኔህልም ውሃበልቶትመቅረቱን፤የወያኔየበቀልቀጣይትልሙአከርካሪውእንኩትኩትማለቱን ስለነጋራችሁን ወይንም ስላበሰራችሁን እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። እግዚአብሄርም ይስጥልን። አሁን ወደ አስተያዬታዊ ማሳሰቪዬ።
1 በነገራችን ላይ ሚዲያ ላይ የሚወጣ ማናቸውም ዘገባ ባለቤት እንዲኖሩ የሚዲያ ህግ ያስገድዳል። ነገሩ የኃይልዬ ጉዳይ ሆኖ እንጂ እኔ እራሴ አላነበውም ነበር። የሆነ ሆኖ የእሱን ጉዳይ በባለቤትነት የሚከታተል ሰው ወይንም ቡድን የቆረጠ መሆን አለበት። ምንም ዓይነት ቅንጥብጣቢ ቅሬት ሊኖረው አይገባም። አቋሙ ግልጽና አንድና አንድ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ነገሮች የተከተቡበት በአጽህኖት የቆረጠ ብልጹግ እርምጃ ነውና። እውነት ለመናገር የዘገባው እርእስ ነርብ ይበጥስ ነበር። „ኢህድግ“ ይህ ቃል ጀግናችን ለወሰደው ለድርጊቱም ክብር የሚመጥን አልነበረም። የተጎመደ ጉድ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ላይ ያለው ህብረ ብሄር ፓርቲ አይደለም። የአንድ ጎሳ ድርጅት ቲፒኤልኤፍ ነው። ይህ ደግሞ አለም ያወቀው ነው። ይህ ወጋ ጠቀም ያለ አገላለጽ እኔ በግሌ ፈጽሞ አይመቸኝም። ጎሰኝነት መርዝ ነው። ወያኔ ስለሆነ ሳይሆን ሌላም ጎሳም እድሉን ቢገኝ የሚያድርገውን ነው ዛሬ ወያኔ እዬፈጸመ ያለው ዕንባን የመርገጥ ተግባር። የህግ ሆነ የተፈጥሮ ጥሰት መሰረቱ ይሄው ነው። አንድ ጎሳ ሥልጣን ከያዘ ጨቆነ ያለውን ይቀጠቅጣል፤ ተጨቆነ ያለውን ጥበቃ ያደርግለታል። አናሳዎችም ቢሆን ልክ ብዙ ቁጥር እንዳላቸው ይፈለጣሉ – ካለርህራሄ።
ይህ የሚመነጨው ደግሞ የዘር ፖሊሲዎቹ ከተነሱበት ከዞግ ማኒፌስቶው ነው። አንድ የጎሳ ድርጅት ወሳኝ የሆነውን የፖለቲካ ተቋማት በእጁ ካስገባ፤ ዜጎች በዜግነት በሐገራቸው የመኖር መብታቸው ይጠቀጠቃል። ዜግነት ዳር ደንበሩ ይጣሳል። የዜግነት መብት በግፍ ተጥቅልሎ ይጣላል፤ ዜግነት ይደፈራል። ዜግነት ዋጋው ይረክሳል – ይሰረዛል። ከዚህም ባለፈ ለዬጎሳው አጥር ተሰርቶ ግርዶሽ ይበጃል። ቅራኔውም እንዲፋፋም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።

ስለምን? ሥልጣን ላይ ያለው ገዢ ጎሳ ትንፋሹ ጥበቃ የሚያገኘው በዚህ ግጭት ውጤት ነውና። ሌላውን እያተራመሰ እሱ ንጹህ አዬሩን ለሽ ብሎ ይመገባል። አይደለም ሀገር ውስጥ ውጭ ሀገር ያለው የነፃነት ትግሉ ቤተሰብ በጠላታችን ላይ ተስማምተን፤ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ያለው መታመስ መስከን ያልቻለውም ለዚህ ነው። ይህ በግልብ ተሂዶ የሚደረስበት ሳይሆን፤ መሬት ዬያዘ የመንፈሳዊ ጥሪቶች አቅም በተጠና ሁኔታ መገንባትን ይጠይቃል። ድልዳል ያለው ተከታታይነት ያለው ተግባርን መከወን ይፈልጋል። ሳናውቀው እኛም የዚህ ኮስማና የጎሳ ፍቅር ሰለባ ስለሆን፤ እራስንም ታግሎ ማሸነፍ። የወያኔ ትልም ተጠቂ እኛ ብቻ ሳንሆን ዘመኑ እራሱ ሆኗል። አንዱን ዘለን ሌላው ላይ ስንደርስ፤ ቀጥ እንላለን። ምሳሌ በወያኔ አባገነንነት ላይ ተስማምተን ወደ ታሪክ ወይንም ወደ ሃይማኖት አሁን ደግሞ ወደ ፆታዊም እዬዘለቀ ነው ስንደርስ እራሳችን ከዋናው አስኳል ፍላጎታችን መንበር እናወርዳለን። ይህ ደግሞ ለጣሊያን የረጅም ጊዜ ትልም ላደረ ዬጎሳ ድርጅት ህይወቱና የሚፈልገውም ነው።
በጎሳ ማኒፌስቶ የዘር አድሎ፤ የዘር ግለት፤ የዘር ፍልሰት፤ የዘር መፈናቀል፤ በዘር መጥቃት፤ የዘር የበታችነት፤ የዜግነት ዋጋ ዕጦት መታዬታቸው ግድ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ እዬታመሰችበት ያለው ይህ ነው። ወያኔ ይህን ማራገቢያ ይዞ ያፋፍመዋል። የደጋፊዎችም መደበኛ ተግባር ይኽው ነው። ስለዚህ የመሰረታዊ ችግራችን ምንጩ አናቱ ጉዳይ የጎሳ አስተዳደር ዘረኛ ፋሽስታዊነት ወይንም ሌሎችን በኃይል መጫን ማድቀቅ ነው። (Diskrimnation + rascism = TPLF) ስለዚህ የጀግና ኃይለመድህን ጉዳይ የሚታዬውም ከዚህ አንጸር ነው። «ረዳትፓይለትሃይለመድህንአበራንለማስመለስየኢህአዴግልኡካንበጄኔቫ» ብሎ ርእስ መስጠት አያስኬድም የተዘጋ – የታነቀ መንገድ ነው፣ ለጉዳዩ ፍትህ አሰጣጥ። ለነጻነት ትግሉም ቢሆን ቦንብ የማጉረስ ያህል እጅግ አስጊ አካሄድ ነው። ለብልሁ አውሮፕላን አብራሪም ከጉዳዩ ጋር ያሉ ተያያዥ አንቀፆችን ካል ይግባኝ ይገድላል። አውነት ለመናገር ለዚህ ሥልጡን – ንጡር ድርጊትም እርእሱ ውስጥ ያለው ለወያኔ የህብረ ብሄር ፓርቲነት እውቅና መስጠት የተገባ ፈጽሞ አይደለም። ለቀጣይ ትግላችንም በዚህ መስማማት ካልቻልን የትም አንደርስም።
ለማንኛውም ጉልበት ሊሰጡ የሚችሉ (Siwiss Criminal Cod (STGB) Art. 173, 174, 177, 261) እነዚህአንቀፆችወያኔንበፍርድአደባባይሲዊዝላይሊሞግቱትየሚችሉናቸው። በእንግሊዘኛ እንዳለያቀርብኩት የህግ ባለሙያዎችለቃልቀርቶ ለአንድ ፊድልእንኳንያላቸውንየከበደየጥንቃቄ ዕይታስለምገነዘብነው “እኔ” ለሚለው አገናዛቢ ቃል „ለእኔ” ከእኔ” ተእኔ” „በእኔ“ አንዲት ፊደል ከፊት ስትታከል የትርጉሙ መልክ ሆነ አቅጣጫ ይቀዬራል። ስለሆነም ባለቤት ነን ካልን፤ ለምንጽፋቸው ማናቸውም ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ማደረግ ግድ ይላል። ሕይወትም ታሪክም ነው። ትርፍ የሚገኘው ከጠንቃቃነት ነው።
2 „ጀግና ሀይለመድህን በቤተሰብ እንደተጠዬቀ“ ዘገባው አመለክቶ ነበር። ይህ በ28.02.2014 የበርኑ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገልፆ ነበር። እኔ የሰላማዊ ሰልፉን ዘገባ ስሠራ መረጃውን ዘልዬ ነበር ሪፖርቱን ያጠናቀርኩት። ፖለቲካ ግርድፍ አይደለም ልም ነው። ደህንነት የሚባል ነገር አለ። ቤቱ ብቻ ሳይሆን ጓሮውና አካባቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ለእንሰሳ አስተዳደር ይህን መሰል መረጃ ማቀበል ሆነ መቀለብ አይገባም። ጊዜውን ቢጠብቅ መልካም በሆነ ነበር። መጠበቅ – ማሸነፍ ነው።
3. ውጭ ስለሚገኙ የህግ ባለሙያዎች በአሉታዊ አስተያዬት ዘገባው ነበረው። ቃሉን በትርጉም ላቃናውና እንዳለ ማቅረብ ስለሚከብደኝ። “ኢትዮጵያዊ የህግ ጠበቆች የሲዊዝ ጠበቆች ለጠዬቋቸው ጥያቄዎች አቅም ያነሰው መልስ እንደሰጡ።” ዘገባው ጠቁሟል። ይህን በሁለት መልክ ማዬት ይገባል።
3.1 መዘርዘር ባልፈልግም ጫና በሁሉም ላይ አለ። ይህን ጥሶ መውጣት መቻል መታደል ነው፤ ባይሆንም መብት ነውና ብዙ መጋፋት አያስፈልግም። የሥራ ክፍፍልም ስለአለ ለሥራው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተግተው በጀመሩት ይቀጥሉ ባይ ነኝ።
3.2 ወቀሳ ላይ ደፈር ብለን ከገባን ሁሉንም አካባቢ መዳሰስ ያስፈልጋል። ጉዳዩ የተፈጸመው ሲዊዝ ሆኖ በተመሳሳይ ቀን በ28.02.2014 ሁለቱም የኢሳት ስቲዲዮዎችና ሪፖርተሮች የተገኙት ኖርዎይ ነበር።
ፀሐፊ ገዛህኝ አበበ ከኖርዎይ እንደዘገበው ቅኒት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላና ጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ መገኘታቸውን ዘግቧል ሪፖርቱን ለኢሳት ያቀበለውም ጋዜጠኛ ደረጀ ስለመሆኑ አዳምጫለሁ። እኛስ ነው ጥያቄው? ማዳላት ጥሩ አይደለም።
ከዚህም ባለፈ “የሲዊዝ ሹሞኞቹ አክቲቢስቶች፤ የነፃነት ትግሉ ኤክስፐርቶች” አልነበሩም። ሁልጊዜም ታች ሆነው ሥራውን የሚጋፈጡትን ብቻ ነው ጉሮሯቸው እስከደርቅ ድረስ መፈክር ሲያስተገቡ ያዬሁት። እርግጥ የሰለጠነ መሳሪያና ታታሪ ቪዲዮ ቀራጭ አይቻለሁ። ሰላማዊ ሰልፉን ዬጠሩት ወገኖች ወንዝ ላይ፤ ዛፍ ጥላ ሥር፤ መንገድ ላይ ብቻ ከሆነ ቦታ በጋራ እንግዳችን እንቀበል ሲሉ መገኘት መልካም ነበር። ከሁሉም የላቀ ፈታኝ ጥሪ ነበር። ግን አልሆነም። ታሪክን ለሚጽፉት ይከብዳል። ስንት ቀንስ በትርጉም ተቃንቶ፤ ተሽፍኖ ሃቅን ከናንቦ ይዘለቃል?! እኔማ ያው ዬቤቴን የከረንትን እንዲሁም የአንድነትን ናፍቆቶቼን ስለአገኘሁ በመንፈሴ ላይ ምንም ዓይነት ግልምጫም ሆነ ፍጥጫ በሹም ሳይደርስብኝ በሰላም ተግባሬን ከውኜ ነበር የተመለስኩት።
እርግጥ ኖርወዬ ጥሩ እረኛ አባት ስላላቸው እድለኛ ናቸው። ለመታገል የወደዱ ሁሉ ፍቅርና እቅፍ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት ያለው ቋሚ ድርሻንም ለመወጣት ሆነ ለመታገል ይችሉ ዘንድ ተመርቀዋል። እኔም እማደንቀው አመራር ነው ኖሮይ ያለው። አጋጣሚ ሰጥቶኝም በ2009 የታህሳሱ የጂ20 ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ ላይ ሄሮድስ መለስ ተገኝተው ስለነበር ከኮፐን ሀገን የተቃውሞ ስልፍና ስብሰባ ላይ እናቱን ውስጡ ጽላቱ ያደረግ፤ ንቁ አሰባሳቢ እንዳላቸው ዓይኔ አይቷል፤ እንዴትም እንደሚደንከባከባቸው ተመልክቻለሁ። ያን ጊዜ አዎንታዊ ቅናትም ብልት አድርጎኝ ነበር የተመለስኩት። ዶር/ ሙሉአለም አዳሙ ወቅቱ ለሚጠይቀው የትግል መስመር አስቀድሞ የተሰናዳ ወርቅ ወንድም ነው። ለዚህም ነው የትግል መስመሩ ሁሉ በእኩልነት እንደ ወቅቱ ባህሪና ይዘት በነፃነት ቋሚ አድማጭ ኖሪዎይ ላይ ያለው። አቅማቸውም ጉልበታም የሆነው።
የሆነ ሆኖ ለ28.02.2014 ነገር ኃይለመድህን አበራ ግን ከዬትኛውም ቦታ የተፈጥሮ ጠረን ለኢሳትና ሆነ “ለኢሳት አክቲቢስቶቹ” ሲዊዝ ይቀርብ ነበር …. አስተካክሉ፣ እረሙ፣ ታዝበናችኋል እንላለን እኔና ብእሬ …. በስንት ወጨፎና ግርፋት ነው እኛ እንኳን ሥራ ያውጣው ብለን ሳንቀመጥ ሁሉንም ታግሰን እኔም ሆንኩ ብዕሬም እንዲሁም እምሳሳለት ጥንቁቅ ሰብዕናዬም እዬተረገጥን የምንታደመው —- እንኳንስ ፍቅርና ክብር፤ እልልታ በገፍ በሩን ቧ አድርጎ ፈክቶ የሚጠብቀው ኢሳት —- የእውነት መገኘት ነበረበት። ኢሳትም በስሚ ስሚ — ቀኑን አሾለከ —– ታሪክ ተከዘ።
4 የዘጋቢ ፊልሙም ጉዳይ የበለጠ ድንቅ ሊሆን የሚችለው ተከድኖ ቢቆይ ነበር። ሲዊዝ መኖር እኮ እጅግ ተዝቆ የማያልቅ ዕውቀት የሚሸመትበት ሀገር ነው። እጅ ስንሰጥ ወደ 8 ወር 300.00 የማይሞላ ወደ ሌላ ካንፕ ስንሸጋገር 400.00 መኖሪያ ፈቃድ ስናገኝ 960.00 ፍራንክ ለወር ይሰጠናል። ያው ከጤና ኢንሹራንሱና ከቤት ኪራዩ ሌላ። ደረጃ በደራጃ ኑሮን እንዴት መኖር እንደሚቻል በረቀቀ ሁኔታ ብልሆቹ ያስተምሩናል። ከካንፑ ውስጥ ልብስም በጣም በርካሽ ይሸጣል። በ1.00 በ5.00 የሲዊዝ ፍራንክ ወዘተ …. መንገድ ላይ ሆነ ገብያ ላይ ቀለል ያለ እቃ ለያዘ ቅድሚያ ይሰጣሉ። ሐብታቸው – ደስታው – ድሎታቸው ልክና ደንበር አለው። እኛም ያስተማሩንን በመተግበር በራችን እስከ አንቃሩ ሳንከፍት ስሜታቸውን እዬተከተልን መረጃውን ብናቀብል መልካም ነው።
5. ትእግስትን ገርገጭ ያደረገ አስተያዬታዊ ማሳሰቢያ – ለሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች።
- በሀገረ ሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ መጠዬቅ ሆነ የማሳወቅ ጉዳይ በደብዳቤ እንጂ በኢሜል የሚታሰብ አይደለም። መልሱም በደብዳቤ መሆን አለበት። አይደለም እኛ ሲዊዞች ከህጋቸው በታች በታች ናቸው። ስለዚህ መጀመሪያ መጨረስ የሚገባነን ሳንጨርስ በተደጋጋሚ ከሥራዓት አስጠባቂዎች ጋር መጋጨት ለሁልጊዜ ለኢትዮጵውያን ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ሊነሳ የሚችል ይሆናል። ተሳታፊውም ይቀራል። ይህ ትብስብስ ያለ ጉዳይ ፍርጥርጥ አድርጋችሁ ተወያይታችሁ መልክ ልታስይዙት የሚገባ ጉዳይ ነው።
- ጥሪው በኢሜል፤ በሁሉም ሆም ፔጆች፤ በኤስኤምኤስ በተጨማሪነት መጠቀሙ መሰረታዊ ነው። በኢሳትና በፌስ ቡክ እንደምትጠቀሙት ሁሉ። በአንዱ መረጃውን ማግኘት ይቻላል።
- ጥረው ሲተላለፍ ባለቤት ሊኖረው ይገባል፣ ቋሚ የመገናኛ ቦታ መታወቅ አለበት፤ ተሳታፊ ከዋናው ባቡር ጠቢያ ወርዶ የትኛውን አውቶብስ፣ ትራም፣ እንደሚይዝ መብራራት አለበት፤ የሚወርድበት ስቴሽንም ሆነ በእግር የሚያስኬድ ከሆነም ግልጽ መረጃ ሊሰጥ ይገባል። የአድራሻ ለውጥ ሲኖር ሲቀዬርም በ አስቸኳይ በማናቸውም መንገድ ለተጠሪው በሙሉ መረጃ የማሳወቅ ግዴታ ነው። እኔ በግሌ የስልክ ቁጥር አያሰኜኝም። ደጅ ጥናት ስለማልፈልግ። የምፈልገው ትክለኛ ግልጽ መረጃ ወረቀት ላይ የተጻፈ።
- ተሳታፊውን በሙዑሉ አክብሮትና ፍቅር “እንኳን ደህና መጣችሁ” ሰልፉ ሲያበቃ ደግሞ “እግዚአብሄር ይስጥልን፤ በሰላም ያግባችሁ” መባል አለበት። የመንፈስ ስንቅ አይነት – ለቀጣዩ ጥሪ ምቹ ሁኔታም ማሰናዳት ያስፈልጋል። ለአንድ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜው ገንዘቡ አቅሙ ጤናውም አለ —- በጣሙን አብዝቼ የምጠይቀው – ድካሙን ከብክነት የሚያድን የተደራጀ አቅም፤ ብቃታዊ አመራር።
- ስብሰባም ሲጠራ ማስታወቂያው ይወጣል የሚገኘው የፖለቲካ ሰው ግን አይገለጸም። ለምን? አይገባኝም። ጭራሽም የመረጃ ፍሳት ሳይኖር ይቀራል። ለምሳሌ ኢንጂነር ይልቃል ሲዊዝ መጡ ጄኔባን ብቻ አይተው ተመለሱ። ቢሰማ ቢያንስ እዛው አካበቢ ያሉ ወገኖች መገኘት ይችሉ ነበር።
- በርን ማዕከላዊ ቦታ ከመሆኑም በላይ ፍቅር ናቸው እዛ ያሉ ወገኖች። ሁሉንም ቀዳዳ በተግባር እዬሸፈኑ ያሉትም እነሱ ናቸው። ለማናቸውም ኃላፊነት በቂ ተከታይነት ያለው አቅምም አለ። ስለዚህ የሲዊዝ የነፃነት እንቅስቃሴ በርንን ማዕከል ቢያደረግ መልካም ይመስለኛል። የሲዊዝ ዋና ከተማም ነው።
- ጠሪው በሌለበት ተጠሪው የመገኘት ይህም ያዬሁት ነገር ነው። ከዚህ በላይ የወቅቱን የሰልፈኛውን ሙቀት፤ ፍላጎት፤ ቁጣ ሊያስተናገድ የሚችል አቅም ሊኖር ይገባል። ኤክለፕተስ ዛፍ ፍሬ ሲያፈራ ቅርንጫፉ ፍሬውን የመሸከም አቅም ስለማይኖረው ይዘነጠላል። የሳውዲ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ግልብጥ ብሎ ተወጥቶ ነበር በግምት ከ300 እስከ 400 ሊሆን የሚችሉ ቅኖች ነበሩ። ተሳትፎው ልባዊ ሀገራዊ – ፍቅራዊ ነበር። እኔ ሲዊዝ ውስጥ አይቼ አላውቅም። ግን ያን ፍል እንባ በሥርዓት መርቶ ለቀጣይ ኃይላፊነት በቋሚነት ለማቆዬት የሚችል የተደራጀ አመራር አልነበረም። በቀጣይ የረዳት አውሮፕላን አብራሪ ጉዳይ ጥሪ ቢኖር ለመሳተፍ እነዚህ ነጥቦች በአግባቡ ሊስተካከሉ ይገባል። በስተቀር ግን ለብክነት ጊዜ የሚሰጥ ሰው አይኖርም።
በመጨረሻ — ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ካሰኛችሁ የቀደምት አንድነቶችን በስተቀር ብሄራዊ ጉዳይን የማስተናገድ አቅም ያላቸው እንደ ሙንሽን፤ ኖርወዬ፤ ሲዊዲንና ፍራንክፈርት የዳበረ ልምድ ስላላቸው በዝግጃታችሁ ቅድሚ ምክር ጠይቁና እናንተ ካላችሁ ተመክሮ ጋር አጋባታችሁ ጥሪያችሁን አክብሮ የሚመጣውን ኃይል በብቃትና በፍቅር ብታስተናግዱ መልካም ነው። አልመለሰብተም ጨረስኩኝ።
በመጨረሻ – ለጀመርነው አጠቃላይ አቅጣጫ ጠላትን በስልት ሊረታ የሚችል ሥልጡን – ጥንቁቅ ዘገባዊ አቀራረብ ነበርው የነገረ ኃይለመድህን በወያኔ ጓዳ ያለውን ጭብጥ የጠቆመን የጋዜጠኛ ተመስገን ጥንቅር። እጅግ ለሚዲያ ሰዎች ይረዳልና ደግመን ብናነበው ምርጫዬ ነው ከትህትና ጋር።
እንደ መከወኛ። ናፍቆቶቼ የሀገሬ ልጆች ይሄውላችሁ በገባሁት ቃል መሰረት “የተስፋ ማህጸን” የመጀመሪያ ዝግጅትን በ10.04.2014 ደስ ብሎኝ ድልን እያሰላሁ ሰራሁት። የተላለፈውን አርኬቡ ላይ አለላችሁ። ቀጣዩ ደግሞ በ27.04.2014 ይሆናል። እያሰባችሁ በዬ15 ቀኑ በዕለተ ሃሙስ ከ15 እስከ 16 ሰዓት አዬር ላይ ከቻላችሁ፤ ካልቻላችሁ አርኬቡ ላይ አዳምጡ – ጀግና ፍለጋ ጋራ ሸንተረር ከምትጠብቁ ሲዊዝ ላይ የተገኘውን የጀግና ድጋፋዊ መንፈስ አዳምጡ በትህትና። ወይንም Aktuell Sendung።ይህንሊንክከአጀንዳችሁብትመዘግቡት አመሰግናለሁ። እኔአልመለሰበተም።የዘርፖለቲካናጦሱለጎረበጠውተቆርቋሪይህችን በመንፈሱ ሰሌዳ ማስቀመጥ ቀላሏ የቤት ሥራ ናትና። በተረፈ የጀግናችን ሁለተኛ ወር ምክንያት በማድረግ ጸልዩለት፤ በፌስ ቡካችሁ በቲተር አካውንታችሁ ላይ እሱን እሰቡት። ቀኑን ለእሱ ስጡት አሁንም ዝቅ ብሎ በሚለምን ትህትና። “ሰላማዊ እንቢተኝነትን በዝምታ የሞሸረ” የእኛ ልዩ ስጦታ ነው ረ/ አውረፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ።
መልካም የትንሳኤ በአል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማንያን ተመኘሁ። እንዲሁም መልካም በጸሎት የመረዳዳት የመተሳሰብ ጊዜ – ይሁንልን። የወንድማችን፤ የልጃችን፤ የጀግናችን፤ የሽልማታችን ቸር ወሬ አምላካችን ያሰማን። አሜን!
የጀግና ተግባሩ መንበሩ
የጀግና ውበቱ ተግባሩ!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 17.04.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)


Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”