ህወሓት ይቅርታ እየጠየቀ ነው!

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ህወሓት ይቅርታ እየጠየቀ ነው!

Unread post by zeru » 15 Apr 2014 18:30

ህወሓቶች ከትግራይ አከባቢዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት የትግራይን ህዝብ ልብ ሸፍቷል፤ የህወሓት የስልጣን ዕድሜ ከአንድ ዓመት እንደማያልፍ ታውቋል። አሁን ህወሓት በምንም ምክንያት የትግራይን ህዝብ ድጋፍ ማግኘት ስለማይችል ያለው ብቸኛ አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ነው። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት እነ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሓየ፣ ስዩም መስፍን፣ ፀጋይ በርሀና ሌሎች በህወሓት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በትግራይ ገጠር ወረዳዎች እየተዘዋወሩ በአርሶአደሩና ወጣቱ ላይ ለፈፀሙት በደል በግልፅ ቋንቋ ይቅርታ እየጠየቁ ነው። ይቅርታ መጠየቅ ጥሩ ነው። ግን ምነው ከረፈደ? በህወሓቶች የዐዞ እንባ የሚሸወድ ወጣት ካለ እስቲ እናያለን። ለማንኛውም ትዕቢተኞቹ ህወሓቶች ለይቅርታ የተዳረጉ ባሰማነው (ባጋለጥነው) ተቃውሞ ነው። በትግራይ የሚደርስ ዓፈና ላጋለጣችሁ ሁሉ ምስጋናየ ተቀበሉ

ከአብርሀ ደስታ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11217

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”