የአኖሌ ሃውልት በኦህዴዶች መካከል ክፍፍል መፍጠሩ እየተሰማ ነው።

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የአኖሌ ሃውልት በኦህዴዶች መካከል ክፍፍል መፍጠሩ እየተሰማ ነው።

Unread post by zeru » 12 Apr 2014 14:58

አንደኛው ወገን “ሃውልቱ የአሩሲን የበላይነት ለማሳየትና የሌሎች የኦሮምያ አካባቢዎችን ታሪክ ለማንኳሰስ ተብሎ የተሰራ ነው” ብሎ ትችት ሲያቀርብ፣ ሌላው ወገን ደግ
ሞ “ህዝቡ ትኩረቱ በኑሮ ውድነቱና በመልካም አስተዳደር ችግር ላይ ሆኖ እያለ ለሃውልቱት ግንባታ ተብሎ የወጣው ወጪ ከተገኘው የፖለቲካ ትርፍ ጋር አይመጣጠንም”ብሎ እየተቸነ ነው። አነስተኛ ቢሆኑም የተወሰኑት ኦህዴዶች ደግሞ “ኦሮምያ ክልልን አስፈሪ ክልል አድርጎ ማሳየቱ የክልሉን እድገት የሚጎዳና ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የውጭ ኢንቨስተሮች በክልሉ እንደልብ ተንቀሳቅሰው ስራ እንዳይሰሩ የሚያደርግ ነው” በማለት ተቃውመውታል።
የክልሉ ህዝብ ለሃውልቱ ግንባታ የሰጠው መልስ እጅግ የተቀዛቀዘ መሆኑ የኦህዴድ ባለስልጣኖችን አበሳጭቷል።
የኦሮሞ ህዝብ አሁን በከፍተኛ የኑሮና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተሰቃየ ነው። የኦህዴድ አመራሮች እንኳ በህዝቡ ተሳትፎ መዳከም ተስፋ እየቆረጡ ነው።
“የፕሮፓጋንዳ ስራ ረቂቅ ሳይንስ ነው። እንዴት እና መቼ እንደምትጠቀምበት ካላወቅህ አንተኑ መልሶ ይበላሃል” የሚለው በኦህዴድ ላይ እየደረሰ ያለ ይመስላል።Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”