“ሕዋስ” የ2002 የኢህአዲግ የምርጫ መሐንዲስ እንደሚሆን ተጠቆመ ።

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

“ሕዋስ” የ2002 የኢህአዲግ የምርጫ መሐንዲስ እንደሚሆን ተጠቆመ ።

Unread post by ኦሽንoc » 18 Oct 2009 02:08

“ሕዋስ” የ2002 የኢህአዲግ የምርጫ መሐንዲስ እንደሚሆን ተጠቆመ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2002 ዓ.ም. October 17, 2009)

በቅርቡ የተቋቋው “ሕዋስ” በያዝነው ዓመት ለሚከናወነው ምርጫ የኢህአዲግ የምርጫ ስልት ቀያሽ መሐንዲስ እንደሚሆን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ።

የኢህአዲግ የብሔር ብሔረሰብ ፖሊሲ ችግር መፍትሔ ተብሎ ከወር በፊት የተፈጠረው "ሕዋስ" አንድነትንና ሕብረትን በመስበክ የምርጫ ማስፈጸሚያ ስልት ይጠቀማል። እንደምንጮቻችን ጥቆማ "ሕዋስ" ሥራውን የጀመረው በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሚገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ ሲሆን፣ በጋምቤላ ሦስት የብሔር ፓርቲዎችን ወደ አንድነት ለማምጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ታውቋል።

በየመ/ቤቶቹና በየወረዳው በተፈጠረው የኢህአዲግ አባላት የብሔር ግጭት ምክንያት የኢህአዲግ ከፍተኛ አመራሮች እንደ መሠረት ያደረጉት ሕዋስ የብሔር ተዋጽዖዎች ያሉት ስብስብ ሲሆን፤ ወደፊት የብሔር አደረጃጀትን በማፍረስ ብሔራዊ አንድነትን ለማምጣት የተዋቀረ ነው ተብሏል።

“የባንዲራ ቀንን” በከፍተኛ ድምቀት እንዲከበር አስትዋጽዖ አበርክቷል የተባለለት ይኸው "ሕዋስ" በመባል የሚታወቀው አካል ክልሎች ከብሔር ብሔረሰቦች ባንዲራ ይልቅ ዓርማ ያለውን ባንዲራ እንዲያስቀድሙ ግፊት እንዳደረገ ተጠቁሟል።

የህወሓት የበላይነትን ያስቀራል፣ በየመ/ቤቱ ከዝቅተኛ ሠራተኛ እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣንነት በብሔረ ጥላ ሥር ብቻ የተቀመጡትን ያጠራል፣ ኢህአዲግ በህዝብ የደረሰበትን ጥላቻ በመቅረፍ ስለአንዲት ኢትዮጵያ ያቀነቅናል ሲሉ ምንጮቹ የሕዋስን ሚና ገልጸዋል።

በየመ/ቤቱ ምልመላ እየተደረገ ነው ያሉት እነዚሁ ምንጮች የሕዋስ አባል ለመሆን የሚቻለው የብሔር ድርጅት አባል ሆኖ የቆየ ብቻ እንደሆነም ጠቁመዋል።

source:Ethiopiazare

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”