ቆይታ ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል ጋር

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ቆይታ ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል ጋር

Unread post by selam sew »

የቢቢሲ ጋዜጠኛ ቃልኪዳን ይበልጣል የኢትዮጵያና የኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ፤ እንዲሁም ወደፊት ኤርትራ ውስጥ ሊኖር ስለሚችለው ለውጥ ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ጋር አሥመራ ውስጥ ቃለ-ምልልስ አድርጓል።
Image
ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ወደ አሥመራ በመጡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ህዝቡ ደስታውን ሲገልፅ ነበር። አሁንም ቢሆን ደስታው እንደቀጠለ ነው። ይህ ለእናንተ የሚሰጠው ትምህርት ምንድን ነው?

አቶ የማነ ፦ ከ1960 ጀምረን ካሰብን ያለፉት 53 ዓመታት የጦርነት ወይም የመሳሳብ ዓመታት ነበሩ። በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል አንፃራዊ ሰላም የተገኘው ለሰባት ዓመታት ብቻ ነበር። ይህን ምዕራፍ ወደ ጎን በመተው እንደ ሁለት ሃገራት፣ የታሪክ የባህልና ሌሎች ዝምድናዎችም እንዳሏቸው ህዝቦች አብረን ለልማት እንድንሰራ ህዝብ ይፈልጋል።

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ወደ አሥመራ እንደመጣ፤ የህዝቡ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር ሁሉም አይቶታል። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወደ አዲስ አበባ በሄደበት ወቅትም የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜት ታይቷል።

ባጭሩ ስገልፀው፤ ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ሁለቱም መሪዎች ጥሩ ራዕይ ስላላቸው፣ አስፈላጊና ደፋር ውሳኔ ስለወሰኑ፣ ሁለቱ ህዝቦችም ቢሆኑ የጦርነትን አስከፊነት ስለሚያውቁ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው። መጪው ግዜ ደግሞ ጥሩ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።

ቢቢሲ፦ ባለፉት ሦስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን ለውጦች እየተደረጉ በመሆናቸው ከኤርትራ ጋርም እንደገና ግንኙነት ተጀምሯል። ይህ ግንኙነት ኤርትራ ውስጥ ተመሳሳይ ለውጦችን ሊያመጣ ይችላል? ከኤርትራ ወገን ምን ዓይነት ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ?

አቶ የማነ፦ የኤርትራ ህዝብ ሲታገል ለመብቱ ነው የታገለው። መብት ደግሞ ብዙ ነው። የመልማት፣ ዜግነት የማግኘት እና እንደህዝብ የመኖር መብቶችን ያጠቃልላል። ምናልባት ጦርነት ካለ ከጦርነቱ ጋር የሚዛመዱ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። በሰላሙ ጊዜ ግን ለሀገሪቷ ብልፅግና፣ ለሰብአዊ መብቶችና ለዜጎች ደህንነት መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ ይደረጋል ማለት ነው።

ቢቢሲ፦ የሃይማኖት እስረኞች ተፈትተዋል የሚል ዜና ሰምተናልና. . . . .

አቶ የማነ፦ ይህን በተመለከተ አላውቅም። ነገር ግን ኤርትራ ላይ የተሳሳተ አመለካከት ስላለ ነውን'ጂ፤ ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች። ኢትዮጵያ ውስጥም ተመሳሳይ ይመስለኛል።

ክርስትና ወደ ኤርትራ የገባው በ320ኛው ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነው። ክርስትና፣ እስልምናና ካቶሊክ እንዲሁም ወንጌላውያን ተፋቅረው ነው የኖሩት። መንግሥት ደግሞ ሃይማኖት ውስጥ እጁን አያስገባም።

ማንኛውም ሰው የእምነት ነፃነት አለው። ምናልባት በቅርብ ጊዚያት ያየነው ግን፤ በውጭ ኃይሎች የሚደገፍና ህብረተሰቡን የሚረብሽ ነገር ስለመጣ በሃገሪቱ ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚኖረው ነገር ሲኖር መንግሥት እጁን ያስገባል፤ ሰው ሲፈልግ አማኝ ሲፈልግ ኢ-አማኝ መሆን ይችላል።

ስለዚህ፤ ይህ አንዳንድ ስለኤርትራ የሚፃፈው ነገር ሌላ ፍላጎት ያላቸው የሚያራግቡት ካልሆነ በስተቀር፤ አሥመራ ውስጥ ተንቀሳቅሰህ አይተህ ይሆናል፤ የተለያዩ ቤተ-ክርስትያናትና መስጊዶች ጎን ለ ጎን ነው ያሉት።

አሁን አሁን ብዙ የሉም እንጂ፤ አይሁዳውያንም ስለነበሩ፤ ቤተ-መቅደሳቸውም ሳይቀር አለ። ስለዚህ የሃይማኖቶች መዋደድ እና መቻቻል አለ። መንግሥትም እጁን አያስገባም። እኔ ብፈልግ አምናለሁ ባልፈልግ አላምንም።

መንግሥት ይሄን እመን ይሄን አትመን ሊለኝ አይችልም። እንዳልኩህ፤ አክራሪነት በዚህም በዚያም ስለሚመጣ፤ በህብረተሰቡም ላይ ችግር ስለሚያመጣ አንዳች ሥርዓት ያስፈልገዋል።

ይህ ሲባልም፤ ይከልከል ማለት ሳይሆን ሥርዓት ግን ያስፈልገዋል። እንዴት ነው የሚመዘገበው? እምነት ላይ የተመረኮዘ ነው ወይስ ሌላም ዓላማ አለው? የሚለውን የሚመለከቱ ህጎች አሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።
Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”