በሙስና በተጠረጠሩት የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

በሙስና በተጠረጠሩት የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

Unread post by selam sew »

በሙስና በተጠረጠሩት የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

18 July 2018
ታምሩ ጽጌ

Image

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የኢትዮጵያ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ ቢንያም ተወልደ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆ ተፈቀደ፡፡

ተጠርጣሪው የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በሚሠሩበት ወቅት፣ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ቤታቸው ተፈትሿል፡፡ ቤታቸው ሲፈተሽ የተለያዩ አገሮች ገንዘቦች፣ የኤጀንሲው ሚስጥራዊ ሰነዶች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ የአይቲና የባንክ ሰነዶች፣ 3.2 ሚሊዮን ዶላር ያላግባብ ክፍያ መፈጸማቸውንና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማከማቸታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤት ገልጾ አሥር ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለት ነበር፡፡

መርማሪ ቡድኑ በተፈቀደለት አሥር ቀናት ውስጥ በተጠርጣሪው ባለቤት ወ/ሮ ጽጌ ተክሉና አንድ ሌላ ግለሰብ ስም የተቋቋመ ኮላን ባርና ሬስቶራንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ያቋቋሙበትን ሰነድ መሰብሰቡን፣ በተጠርጣሪውና ሌላ አንድ ግለሰብ ስም ኮላን አካዳሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ያቋቋሙበትን ማስረጃ መሰብሰቡን፣ የተጠርጣሪው ባለቤት ወ/ሮ ጽጌ ተክሉና ሌሎች ሦስት ግለሰቦች ስም የተቋቋመ አርክ የኅትመትና ማስታወቂያ ድርጅት የተቋቋመበትን ሰነድ መሰብሰቡን አስረድቷል፡፡ በአቶ ተወልደ ባለቤት ወ/ሮ ጽጌ ስም በ600 ሺሕ ብር የተገዛ መኪና፣ በለገጣፎ ከተማ በ500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተጀመረ ቤት፣ በመቀሌ ከተማ ባለሁለት ፎቅ ጅምር ቤት፣ ሰነድ መሰብሰቡንና የሦስት ሰዎችንም ምስክርነት ቃል መቀበሉንም አክሏል፡፡

ከኤጀንስው ወጪ ተደርጓል የተባለና ያግላባብ አፎሚች ቴክኖሎጂ ለሚባል ድርጅት ለሥልጠና በሚል 3.2 ሚሊዮን ዶላር ወይም 71,727,040 ብር የሚመለከት ሰነድ ለማግኘት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ መጻፉን፣ ተጠርጣሪው ሥልጠናው መጠናቀቁን ለኤጀንሲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ አመራር ዘርፍ የጻፉትን ደብዳቤና ዘርፉ ደብዳቤውን መነሻ በማደረግ ሒሳብ እንዲወራረድ ለፋይናንስና ዘርፍ የጻፈውን ደብዳቤ መሰብሰቡን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪ ኢንሳ ከተቀጠሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ ለቀቁበት ጊዜ ይከፈላቸው የነበረውን የደመወዝ መጠን የሚያስረዳ ሰነድ መሰብሰቡንና ስለሥልጠናው ኦዲት ተሠርቶ እንዲላክለት ደብዳቤ መጻፉንም መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡ ሥልጠና ሰጥቷል የተባለው ደርጅት ኤልሲ የከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ቅርንጫፍ መሆኑ ስለተገለጸ፣ ባንኩ ማስረጃ እንዲልክለትና ብሔራዊ ባንክ ከኤጀንሲው ሒሳብ 3.2 ሚሊዮን ዶላር መቀነሱን የሚያሳይ ሰነድ እንዲሰጠው መጠየቁንም አክሏል፡፡ ተጠርጣሪው ሥልጠናው ተጠናቋል ቢሉም አለመጠናቀቁን ከኤጀንሲው የሚገልጽ ደብዳቤ መሰብሰቡንም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ በቀጣዩ የሚያከናውናቸውን ሥራዎችን በሚመለከት የኦዲት ሪፖርት ውጤት መሰብሰብ፣ የኦዲት ባለሙያዎችን የምስክርነት ቃል መቀበል፣ ከኤጀንሲው የሕግ ክፍል ስለሥልጠናው የተደረገውን ውል በሚመለከት የምስክርነት ቃል መቀበል፣ ከብሔራዊ ባንክ ማስረጃ መሰብሰብና በእግሊዝኛ የተጻፉ በርካታ ሰነዶችን ወደ አማርኛ ማስተርጎም፣ በተጠርጣሪውና ባለቤታቸው ስም ሌሎች ድርጅቶችና መኖሪያ ቤቶች መኖር አለመኖራቸውን ለየክፍላተ ከተሞች ደብዳቤ በመስጠት ማጣራት፣ ተጠርጣሪው በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ስም በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ካለ ባንኮቹን ጠይቆ የማስረጃ ሰነድ መሰብሰብና የቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እንደሚቀረው ገልጾ፣ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪው በበኩላቸው መርማሪ ቡድኑ የሚፈልገውን ማስረጃም ሆነ መረጃ ተቀብሎ መጨረሱን፣ ቀረኝ የሚላቸው ሰነዶችም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ያሉ መሆናቸውን በማስረዳት ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ መርማሪ በድኑ በተፈቀደለት ጊዜ በርካታ ሥራዎችን መሥራቱን ገልጾ፣ ቀረኝ ያለውንም ሥራ መኖሩን በማረጋገጥና የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ፣ ለመርማሪ ቡድኑ አሥር ተጨማሪ ቀናት በመፍቀድ ለሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Source: Reporter Ethiopia
Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”