ኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊዎቹን አባረረ - ዋዜማ ራዲዮ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 592
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊዎቹን አባረረ - ዋዜማ ራዲዮ

Unread post by selam sew » 18 Jul 2018 13:41

የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በመሰለል መረጃው ለሶስተኛ ወገን ይተላለፍ ነበር
Image
ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮ-ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ የተለያዩ የድርጅቱ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
የግዥ፣ የሰው ሀይልና የኦፐሬሽን ሀላፊዎችም ተነስተዋል።
ሀላፊዎቹ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በተፃፈ ደብዳቤ እንዲሰናበቱ መደረጉንም ለመረዳት ችለናል።
ዶ/ር አድማሴ በሀላፊነት በቆዩበት ወቅት ድርጅቱን ህገ ወጥ ለሆነ ተግባር ክፍት በማድረግና የአንድ አካባቢ ሰዎች የድርጅቱን አገልግሎት ለወንጀል እንዲጠቀሙበት አድርገዋል በሚል ሲወነጀሉ ቆይተዋል።
በድርጅቱ ላይ ምዝበራ ሲፈፀም ማስቆም አለመቻላቸው፣ የደህንነት መስሪያቤቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ግለሰቦች ከድርጅቱ የደንበኞችን ምስጢር እንዲያወጡ መንገድ ማመቻቸታቸው በድክመት ይነሳባቸዋል።
የኦፐሬሽን ሀላፊ የነበሩት አቶ ኢሳይያስ ዳኘው ከሀላፊነታቸው የተነሱት ቀደም ባሉት ቀናት ሲሆን ከሕወሐት ጋር በመመሳጠር የድርጅቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በቁጥጥር ስር አውለው እንደነበር የድርጅቱ ባልደረቦች ይናገራሉ።
አቶ ኢሳያስ የሜቴክ ሀላፊ የነበሩት ክንፈ ዳኘው ወንድም ናቸው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ በኢትዮቴሌኮም ትብብር የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮና የሌሎች ባለስልጣናትን የስልክ ግንኙነቶች በመጥለፍ መረጃውን ለሶስተኛ ወገን የማቀበል ስራ ሲሰራ እንደነበረም በድርጅቱ የቴክኒክ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል። ...

ሙሉውን ዜና እዚህ ተጭነው ያንብቡ


Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”