የዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 አበይት ዜናዎች

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 አበይት ዜናዎች

Unread post by selam sew »

የዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 አበይት ዜናዎች

1. የኢትዮ-ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ የተለያዩ የድርጅቱ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ዝርዝሩን ዋዜማ ድረ ገፅ ላይ እናቀርባለን።

2. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሐምሌ 12 አድርጎት የነበረውን የተናጠል ተኩስ አቁም መተውን አሳወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ለተኩስ አቁም እርምጃው ተመሳሳይና ገንቢ ምላሽ ካለመስጠቱም ባሻገር… በምዕራብ ኦሮሚያ ሠፊ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ… የጦር ኃይሉን ከነቀምቴ፣ ከአሶሳና ከጋምቤላ በብዛት ወደ ኦሮሚያ በማሰማራት ላይ መሆኑን በመግለጫው የጠቀሰው ኦነግ “በአካባቢው የሚገኘው ኃይላችን እና ሕዝባችን ይሕንን ጦርነት ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም፤ ሊደርስ ለሚችለው ጉዳት ሁሉ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ነው” ብሏል፡፡

3. ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ፣ ከመጅሊስ እና ከገለልተኛ ወገኖች የተውጣጣ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ ዛሬ ጧት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት ሲወያይ ውሏል፡፡ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ውሎው የደረሰባቸውን ስምምነቶች ከነገ በስቲያ ሐሙስ በጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚያሳውቅ ተጠቁሟል፡፡

4. የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ሠራተኞችና ኃላፊዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ የፖለቲካ አስተሳሰብንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ እንደሚሰሩ የገለጹት የደሕንነት መስሪያ ቤቱ ዳይሬክተር ጄኔራል አደም መሐመድ “የደሕንነት አባላት ከፓርቲ አባልነት መውጣት አለያም ተቋሙን መልቀቅ ይኖርባቸዋል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፤ ሁለቱንም ይዞ መጓዝ እንደማይቻል አስምረውበታል፡፡ ተቋሙ እንደ ማንኛውም መንግስታዊ ተቋም ተጠያቂ የሚሆንበት አሰራር እንደሚኖረውና በሕግ በተሰጠው ሥልጣን ብቻ እንደሚሰራ ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

5. የቀድሞው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) አባል ታከለ ኡማ ዛሬ ሐምሌ 10/2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ አዲስ ከንቲባ ሆነዋል፡፡ ታከለ ኡማ እና ቶሎሳ ተስፋዬ በመረራ ጉዲና (ዶ/ር) ይመራ የነበረውን ኦብኮን ለሁለት በመክፈል ረገድ ዋና ሚና እንደነበራቸው ይታወሳል፡፡ ታከለ (ኢንጂነር) የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በከንቲባነት ባይሾሙም በከንቲባ ማዕረግ የድሪባ ኩማን ወንበር ተረክበው የከተማዋ ኃላፊ ሆነዋል፡፡ ዳግማዊት ሞገስ እና ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) በምክትል ከንቲባነት ማዕረግ ተሹመዋል፡፡ ተሰናባቹ ድሪባ ኩማ የትንስፖርት ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት የወረዳ፣ የዞንና የኦሮሚያ ክልል ግብርና ኃላፊ ነበሩ፡፡


6. ኢትዮጵያ በቅርብ ቀናት ኤምባሲዋን በአስመራ እንደምትከፍት ተነገረ፡፡ ኤምባሲውን ለመክፈት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ነው ተብሏል፡፡ የአየር መስመሩ ከ20 ዓመት በኋላ የከፈተ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 465 መንገደኞችን በመያዝ በነገው ዕለት በቀጥታ ወደ አስመራ በረራ ያደርጋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳምንቱን ሙሉ በየቀኑ በረራ እንዲኖር በማቀድ በአስመራ የቲኬት ቢሮ ከፍቷል፡፡ የአሰብ ወደብን ለመጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት ለመተግበር በሁለቱም ሀገራት በኩል የመንገድ ጠረጋ እና ጥገና እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የማሪታይም አገልግሎት ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቶች የጋራ ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡ በደርግ ዘመን በአሰብ የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣን የነበረውን መስሪያ ቤት ግብረ ኃይሉ በቢሮነት ይጠቀምበታል፡፡

7. የዛሬ አንድ ወር ገደማ በተደራቢነት ለሰሜን ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት የተሾሙበትን ደብዳቤ ያቀረቡት ብርሀነ ገብረክርስቶስ ከቻይና አምባሳደርነት ተነስተዋል፡፡ ለአምባሳደሩ ከኃላፊነት መነሳት መንግስት አሳማኝ ምክንያት ባይሰጥም፣ በአጭር ጊዜ ተሹመው እንዲነሱ መደረጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አካሄድን ካለመቀበል ጋር የሚያያይዙት አሉ፡፡

8. የኬንያው ቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም “ኤምፔሳ” የተሰኘውን በሞባይል ስልክ ገንዘብ የማዘዋወር አገልግሎትን ለማስጀምር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመደራደር ላይ ነው፡፡ የሳፋሪኮም እናት ኩባንያ የሆነው የብሪታንያው ቮዳፎን የአገልግሎቱ ንግድ ስም ስያሜን ሲይዝ፣ ሳፋሪኮም ደደግሞ ናይሮቢ በሚገኘው ሰርቨር አማካይነት አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

ለሌሎችም ያጋሩ SHARE SHARE
Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”