ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ

Unread post by selam sew »

ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ

Image

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት በፍጥነት ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ሃገር ወደ ሃገር ውስጥ እየገባ በመሆኑ ምንዛሪ ያከማቹ አካላት ገቢ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የውጭ ምንዛሪውን ያከማቹ አካላት ችግር ከመከሰቱ በፊት ገቢ በማድረግ ከኪሳራ እንዲድኑም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በቅርቡም የውጭ ምንዛሪ ህገ ወጥ ዝውውርና ክምችትን ለመከላከል ሃገር አቀፍ ዘመቻ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ይህ ከመሆኑ በፊትና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሲባልም እነዚህ አካላት በእጃቸው ያለውን ምንዛሪ ወደ ባንክ በመሄድ እንዲመነዝሩም ነው ያሳሰቡት።

የግልና የመንግስት ባንኮችም ይህን ለማድረግ የሚመጡ አካላትን ያልምንም ውጣ ውረድ እንዲያስተናግዱም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እየተከሰቱ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህም የዜጎች ህይዎት መጥፋትና መፈናቀል እየተከሰተ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ አንጻርም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላት እንዲሁም በጉዳዩ በቀጥታ ባይሆንም በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብለዋል።

እነዚህ አካላት ከጥፋት ድርጊት በመታቀብም ህዝብና ህዝብን የሚያቀራርቡና የሚያፋቅሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው።

ጊዜ ያለፈበትን አካሄድ በመተውም ለህዝብና ለሃገር አንድነት የሚከፈልን ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት እንደሚኖርባቸውም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ አካላት ስሜታቸውን አሸንፈው ለሰላም መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ ህዝብና ህዝብን ለማቀራረብ መስራት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አመራሮችም እርስ በርስ በመወያየት ህዝብን የማቀራረብ ስራ እንዲሰሩም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ መዋቅር አካላትም፥ መሰል ድርጊቶችን እልባት ለመስጠት ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

ግጭትን ለማስቆም በሚደረግ ሂደት ወቅትም ህገ መንግስቱን በሚጻረር መልኩ በሰው ህይዎትም ሆነ ንብረት ላይ ጉዳት ሊደርስ እንደማይገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህን መሰሉ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ድርጊቱ እንዳይሰፋም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የተጀመረውን ሃገራዊ የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ የሚጥሩ አካላትን ድርጊትና ተግባር በመዋጋት ሂደት ውስጥም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”