የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፋሲል ከነማ ያቀረበውን የወዳጅነት ጨዋታ ጥያቄ ተቀበለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፋሲል ከነማ በኤርትራ ፕሪምየርሊግ ውስጥ ከሚጫወት የእግር ኳስ ክለግ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀበለ።
ፌዴሬሽኑ በፃፈው የመልስ ደብዳቤም የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ለመጫወት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቋል።
የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአስመራ ላይ በቅርቡ ለማካሄድ የተሰበውን የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ መጀመሩንም አስታውቋል።
የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታው የሚካሄድበት ቀንም በቅርቡ እንደሚያስታውቅ ነው ፌዴሬሽኑ ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በላከው ደብዳቤ ያስታወቀው።
የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ያቀረበው የወዳጅነት የእግር ኳስ ጥያቄም የሀገራቱ መሪዎች ሰላምን ለማስፈን የጀመሩትን ስራ የሚያጠናክር ነው ሲልም አድንቆታል።
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ከሚጫወት ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሰኔ 30 2010 ዓ.ም ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፋሲል ከነማ ያቀረበውን የወዳጅነት ጨዋታ ጥያቄ ተቀበለ
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
-
- Leader
- Posts: 692
- Joined: 08 Feb 2011 11:14
- Contact: