ሐሙስ ሰኔ 28/2010 አበይት የሀገር ውስጥ ዜናዎች - Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ሐሙስ ሰኔ 28/2010 አበይት የሀገር ውስጥ ዜናዎች - Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ

Unread post by selam sew »

ሐሙስ ሰኔ 28/2010 አበይት የሀገር ውስጥ ዜናዎች

1. በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን አስከሬን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ሶስት አርሶ አደሮችና ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸው ተጠቁሟል፡፡ መጀመሪያ ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ቦታ ሠላም የሠፈነ እንደሚመስል የጠቆሙ የዜና ምንጮች በሌሎች ተጎራባች አካባቢዎች ግን የሱዳን ወታደሮች እየፈጸሙት ባለው ትንኮሳ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የግብርና ሥራ ማቋረጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ግጭቱን በተመለከተ የሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት ውይይት አድርገዋል፡፡ ለፕረዝዳንት አልበሽር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን መልዕክት ይዘው ወደ ካርቱም ያመሩት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በዚሁ የድንበር ጉዳይ ከሱዳኑ አቻቸው ኤል ዲርደሪ መሐመድ ጋር መወያየታቸው ተዘግቧል፡፡

2. የትምሕርት ሚኒስቴር ለሁለት ሊከፈል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት 50 ዩኒቨርሲቲዎች፣ 30 ሚሊየን ተማሪዎች፣ 40 ሺህ ትምሕርት ቤቶች፣ ከ1500 በላይ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት በሀገሪቱ የሚገኙ እንደመሆኑ መጠን ሚኒስቴሩ ባለው አደረጃጀትና የሰው ኃይል ተልዕኮውን ማስፈጸም አልቻለም ተብሏል፡፡ ችግሩን ለመፍታት በተካሄደ ጥናት መሰረት ትምሕርት ሚኒስቴር በሁለት አደረጃጀት ይከፈላል፡፡ የአጠቃላይ ትምሕርትና የቴክኒክ ሙያ ስልጠና በአንድ ሚኒስቴር ሥር እንዲሆኑ፣ የከፍተኛ ትምሕርት ዘርፍ ደግሞ ለብቻው በሌላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እንዲዋቀር ረቂቅ ተዘጋጅቶ በቀጣዩ ሳምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚላክ ታውቋል፡፡

3. ግንቦት 7፣ ኦነግ እና ኦብነግ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር ተሰረዙ። በዛሬው ዕለት ፓርላማው ይህንን የሚኒስትሮች ምክር ቤትን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ፍጋፍ አጽድቆታል ተብሏል። ድርጅቶቹ በአሸባሪነት የተፈረጁት በ2003 ነበር።

4. ለኦሮሚያ ክልል አዲስ የጸጥታ ኃላፊ ተሹሟል፡፡ የክልሉ ካቢኔ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ግርማ ኃይሉን የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ጥላሁን ወርቁን የኦሕዴድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አድርጓል፡፡ በሹመቱ መሰረት መስፍን አሰፋ የአዳማ ከንቲባ፣ አሕመድ ኢድሪስ የአዳማ ምክትል ከንቲባ፣ ሰለሞን ፈዬ የቡራዩ ከንቲባ፣ ጌታቸው ታምራት የምስራቅ ሸዋ አስተዳዳሪ፣ ሙና አሕመድ የክልሉ ሴቶችና ሕጻናት ቢሮ ኃላፊ፣ እልፍነሽ በዬቻ የኮሙኒኬሽን ምክትል ኃላፊ ሆነዋል፡፡

5. የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ኢንተርፕራይዝ ኃላፊዎች ከሀገር እንደወጡ ቀርተዋል፡፡ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስፋወሰን አለነ እና ምክትላቸው አባይ ከበደ የዓመት ፈቃድ ጠይቀው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከሄዱ ሶስት ወራት አልፏቸዋል፡፡ የኃላፊዎቹ በሕገወጥ ድርጊት ውስጥ መሳተፋቸው ከሀገር ኮብልለው ቤተሰቦቻቸው ባሉበት ሀገር እንዲቀሩ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ቀድሞ የጅምላና ገቢ ንግድ ኢንተርፕራይዝ ይባል የነበረው ነው፡፡

6.የኢትዮጵያ መርከበኞች ከመርከብ ላይ እየኮበለሉ መጥፋት ለሀገሪቱ ከባድ ፈተና ከመሆን አልፎ በደብረዘይት የሚገኘው የማሪን ኢንጂነሪንግ ሥልጠና እንዲቋረጥ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ በሥራቸው ላይ የነበሩ ሠማንያ ያሕል ኢትዮጵያውያን መርከበኞች በመጥፋታቸው የተነሳ 10 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ አዳዲስ መርከበኞችን መቅጠር አቁመዋል፤ 1050 መርከቦች ያሏቸው 30 ካምፓኒዎች የሥራ ግንኙነት አቋርጠዋል፤ 200 የሀገራችን ባሕረኞች ከሥራ ተባርረዋል፤ አመኔታ በማጣት 340 አዳዲስ ተመራቂዎች ሥራ ማግኘት አልቻሉም፤ ኢትዮጵያም ከባሕረኞቹ በየወሩ ታገኝ የነበረውን 450 ሺህ ዶላር የውጪ ምንዛሪ አጥታለች፡፡

7. በአፍሪካ ትልቁ ዓለምአቀፍ ነጻ የንግድ ቀጠና ዛሬ ተመርቋል፡፡ የጂቡቲ ዓለም አቀፍ የንግድ ቀጠናን ለማስመረቅ በሥፍራው የተገኙት ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ “…ለቀጠናው ሀገራት የጋራ ሀብት በመሆኑ ኢትዮጵያም እንደ ራሷ ፕሮጀክት ትቆጥረዋለች” ብለዋል፡፡ በቻይና መንግስት ድጋፍ የተሠራውና 340 ሚሊየን ዶላር የፈሰሰበት ማዕከሉ በ“ሮድ ኤንድ ቤልት” ፕሮጀክት የሚካተት ነው፡፡ ይሕ ፕሮጀክት ቻይና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመር የምትዘረጋበት መሆኑ ይታወቃል፡፡

8. ፓርላማው ዛሬ በበጀት ጉዳይ በተወያየበት ወቅት ከአባላቱ ለቀረቡ ጥያቄዎች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትር ምላሽ ሠጥተዋል፡፡ ሚኒስትሩ አብርሀም ተከስተ በሰጡት ምላሽ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በመደበኛ በጀትና ካፒታል በጀት ላይ ቅናሽ እንደተደረገ አረጋግጠዋል፡፡ የበጀት ቅናሽ የተደረገው የመንግስት ገቢ አቅም በመቀነሱ መሆኑን ያስረዱት ሚኒስትሩ በቀጣዩ ዓመት ታክስ የመሰብሰብ አቅምን ማሻሻል ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚገኙበት ፓርላማው በነገው ዕለት በሚያካሂደው ልዩ ስብሰባ የ2011 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል፡፡

9. የሀዋሳከተማ ከንቲባና የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ሥልጣን ለቀቁ። ከንቲባ ቴዎድሮስ ገቢባ እና የዞኑ አስተዳዳሪ የነበሩት አክሊሉ አዱላ በሀዋሳ ከተማ በቅርቡ ተከስቶ ለነበረው ሁከትና ጉዳት "ኃላፊነት በመውሰድ" ከዛሬ ሰኔ 28 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት መልቀቃቸው ተገልጿል። ከግጭቱ በኋላ ወደ አካባቢው የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሁከቱን ማስቀረት ያልቻሉ ሹማምንት በፈቃዳቸው እንዲለቁ ማሳሰባቸው አይዘነጋም።

ለወዳጅዎ ያጋሩ SHARE

Source: Facebook
Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”