በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡ VOA Amharic

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 604
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡ VOA Amharic

Unread post by selam sew » 13 Sep 2016 13:18

በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡

ዋሺንግተን ዲ.ሲ. — በምዕራብ አማራ የተለያዩ አካባቢዎች እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡
በጎንደር፣ በአዴት፣ በዳንግላና ሌሎችም ሥፍራዎች የታሠሩ ሰዎች መኖራቸውንና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊም እየተፈለጉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ስለሁኔታው መረጃ እንደሌላቸው የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻገር የሚሠሩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፀጥታና የደኅንነት ኃላፊ አመልክተዋል፡፡
እንዲሁም ዳንግላ ላይ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ – መኢአድ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ዐይናለም ተይዘው ዳኛ ፊትም ሳይቀርቡ፣ ክሥም ሳይመሠረትባቸው ለአሥር ቀናት መታሠራቸውን ባለቤታቸው ገልፀዋል፡፡
አዴት ላይም የፓርቲው የይልማና ዴንሣ ወረዳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ስመኘው ገሠሠ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተኩል ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ተይዘው መታሠራቸውና ወደ ብር ሸለቆ መወሰዳቸውን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎችም በርከት ያሉ የጅምላ እሥራቶች እየተከናወኑ ሲሆን እንቅስቃሴዎቹ የተሣሣቱ ወጣቶችን ለማስተማር፤ በወንጀል ተጠያቂ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያለባቸውን ደግሞ ሕግ ፊት ለማቅረብ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አስረድተዋል፡፡
ለተጨማሪ ሙሉው ዘገባ የተካተበበትን እንዲሁም ሙሉ ቃለ-ምልልሶች የያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የምዕራብ አማራ የሰኞ ውሎ (14:02)
Listen The Audio Here


ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከአቶ ተሻገር ወልደሚካኤል ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ፤ ቪኦኤ - ሰኞ፣ መስከረም 2/2009 ዓ.ም (13:13)
Listen The Audio Here


ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ከአቶ ንጉሡ ጥላሁን ጋር በክልሉ ሁኔታ ላይ የተደረገ ቃለ-መጠይቅ፤ ቪኦኤ - ሰኞ፣ መስከረም 2/2009 ዓ.ም (18:43)
Listen The Audio Here

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”