Page 1 of 1

በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት አለመብረዱ

Posted: 14 Jul 2016 16:10
by selam sew
Image
በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት እስከ ምሽት ድረስ አለመብረዱን፤ በዚህም የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙንና በከተማው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መቋረጡን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ዋሽንግተን —
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በተፈጠረው ግጭት ከመንግሥት ታጣቂዎችና ከነዋሪዎች በኩል የሰው ሕይወት መጥፋቱን እና መቁሰሉን፣ እንዲሁም አራቱን የኮሚቴ አባላት ጨምሮ ሰዎች ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

የጠፋውን የሰው ሕይወት ቁጥር በተመለከተ የተረጋገጠ ቁጥር በእጃቸው እንደሌለ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ቤታቸው በታጣቂዎች ተከቦ የነበረው የኮሚቴው አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ከተከበቡበት ወጥተው ሰሜን ልዩ ኃይል አዛዥ ከንቲባ ጽ/ቤት በእነሱ አጠራር (ፖሊስ መምሪያ) በአደራ መቀመጣቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

የብሔራዊ የመረጃና የደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ድርጊቱ አሸባሪዎችና የፀረ ሰላም ኃይሎች የፈጠሩት ረብሻ ነው ሲል ሀገር ውስጥ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል የወልቃይት ተወላጅ እንደሆኑ እና በዛው ዕለት ፒያሳ በተባለው አካባቢ እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ዋሲሁን አንበሴ፤ “.. ልጅ የሚያሳድግ ሰው ቤት እየመራ ቀን ወጥቶ ማታ ቤቱ እየገባ ያለ ሰላማዊ ሰው አሸባሪ ይባላል?” ሲሉ ይጠይቃሉ።

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆችና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በማነጋገር የተጠናከረ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
[jmp3]http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/07 ... bc4061.mp3[/jmp3]