የኢትዮጵያ ባለ አንድ ብር ኖት ሊቀር ነው።

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

የኢትዮጵያ ባለ አንድ ብር ኖት ሊቀር ነው።

Unread post by ኦሽንoc » 06 Dec 2009 15:22

የ ኢትዮጵያ ባለ አንድ ብር ኖት ሊቀር ነው።


ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 51 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ባለ አንድ ብሩ የወረቀት ኖት ቀርቶ በምትኩ ሳንቲም እንዲቀረጽለት ተወስኖ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተዘገቧል።
በዝውውር ላይ ከ አንድ ብር ይልቅ የ አንድ ሳንቲም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው እምነት መኖሩም ተገልጿል። የ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጋር መነጋገሩና በጉዳዩ ዙሪያም ባለፉት ሁለት አመታት ያህል ጥናት ማካሄዱን ገልጿል። አንድ ብር ለሶስት አመታት ብቻ በዝውውር ላይ የሚቆይ ሲሆን ባለ አንድ ብር ሳንቲም ግን
ለ 20 አመታት ሊቆይ ይችላል ተብሏል። እረኛው ልጅ፡ ወፍና ፏፏቴውን በፊትና ጀርባው የሚታይበት አንድ ብር በ እንዴት አይነት መንገድ እንደሚለወጥ አሳሳቢ ሆኗል።
and birr አንድ ብር.jpg
and birr አንድ ብር.jpg (43.75 KiB) Viewed 1333 times
አዲሱን የብር ሳንቲም ለመቅረጽ ባለፈው ኦክቶበር ማጫረት የተጀመረ ሲሆን አሸናፊው ማን እንደሆነ አልተገለጸም።ተጫራቾቹ ከ አውስትራሊያ ፡ ካናዳ፡ ፈረንሳይና ጀርመን እንደሂኑም ተነግሯል።
አሁን ስራ ላይ ያሉት የ ባለ 50 እና 100 ብር ኖቶች የሚታተሙት ፈረንሳይ ሲሆን ባለ አንድና አምስት ብር ኖቶች ደግሞ እንግሊዝ ሃገር እንደሚታተሙ ተገልጿል።
አዲስ፡የባለ አንድ ብር ኖት ከ እንግዲህ በሁዋላ እንደማይታተም ግን ተረጋግጧል።
አንድ ብር ዛሬ የሚገዛቸው ብዙ ነገሮች የሌሉ በመሆኑም አንድ ብሎ ከመጀመር ምናልባት አምስት ብሎ መጀመርም ያዋጣ ይሆናል።

ምንጭ፡ ዘ ኢትዮጵያ ጋዜጣ

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”