በቦሌ ክፍለ ከተማ 66 የጨረቃ ቤቶች በቃጠሎ አደጋ ወደሙ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

በቦሌ ክፍለ ከተማ 66 የጨረቃ ቤቶች በቃጠሎ አደጋ ወደሙ

Unread post by ኦሽንoc » 04 Nov 2009 17:18

በቦሌ ክፍለ ከተማ 66 የጨረቃ ቤቶች በቃጠሎ ወደሙ
(በኃይሌ ሙሉ)
Wednesday, 04 November 2009

Image
በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 03/05 ተገንብተው የነበሩ 66 የጨረቃ ቤቶች በኤሌክትሪክ ሽቦ መነካካት (ኮንታክት) ምክንያት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ድጋፍ የሥራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ከበደ ለገሰ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ገርጂ ጨረቃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰኞ እለት ማታ የተከሰተው የእሳት አደጋ 66 ቤቶችን ካወደመ በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ሰኞ ምሽት 12፡30 ላይ የአደጋ ጥሪ የደረሰው እሳት አደጋ መከላከል በከተማዋ ከሚገኙ ስድስት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ዘጠኝ የእሳት አደጋ መኪናዎችንና ሶስት አምቡላንሶችን አደጋ ወደተከሰተበት አካባቢ በመላክ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት መደረጉን ያስታወሱት አቶ ከበደ 59 የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ሰራተኞችና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ለ4፡37 ሰዓት ያህል 108 ሺህ ሊትር ውሃ ረጭተው እሳቱን ማጥፋት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

አቶ ከበደ እንዳሉት አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የተሰሩት የጨረቃ ቤቶች በፕላን የተሰሩ ባለመሆናቸው ቤቶቹም ከቀርከሃ፣ ከኮምፖርሳቶና ከፕላስቲክ በመስራታቸው እሳቱ በቀላሉ ሊቀጣጠልና ሊባባስ ችሏል፡፡

Image

የእሳት አደጋ ቅድመ መከላከል የጥናት ቡድን ከዚህ ቀደም ባካሄደው ጥናት በገርጂ በተገነቡ የጨረቃ ቤቶች የእሳት አደጋ እብደሚከሰት፣ አደጋው ከተከሰተም በቀላሉ በቁጥጥር ስር መዋል እንደማይቻል ግምቱን ያሰፈረ መሆኑንና ይህ ችግር እንዳይከሰትም ነዋሪው ቤቱን ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እንዲሰራ ለነዋሪዎቹና ለቀበሌው ጽ/ቤት ከአንድም ሁለት ጊዜ የጠቆመ መሆኑን የገለፁት አቶ ከበደ አስፈላጊው እርምጃ በወቅቱ ባለመወሰዱ የአሁኑ አደጋ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

በእሳት አደጋው የወደመው ንብረት ግምት እስከ ትላንት ማታ ድረስ አለመታወቁን አቶ ከበደ ገልጸዋል፡፡ ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ቤታቸው የተቃጠለባቸው ግለሰቦች ወደመብን ብለው ያስመዘገቡት ንብረት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ እሳት አደጋ መከላከል መ/ቤትና ተጎጂዎቹ መግባባት ላይ አልደረሱም፡፡

"አብዛኛዎቹ የአደጋው ሰላባዎች ያስመዘገቡት የወደመ ንብረት ግምት አንድ ቤት ሊያስገነባ የሚችል ነው" ያሉት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የእሳት አደጋ መከላከል ኃላፊ ተጎጂዎቹ ያልወደመባቸውን ንብረት ያስመዘገቡት ካሳ እናገኛለን በሚል የተሳሳተ ግምት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፡ሪፖርተር

Read More Ethiopian News

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”