አርቲስት ቻቺ ታደሠን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ...

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
ኦሽንoc
Leader
Leader
Posts: 1129
Joined: 07 Aug 2009 14:20
Contact:

አርቲስት ቻቺ ታደሠን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ...

Unread post by ኦሽንoc » 03 Nov 2009 00:02

አርቲስት ቻቺ ታደሠን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መሠረቱ

(በታምሩ ጽጌ)

"ሆሕተ ተስፋ" የሚባል ድርጅት በማቋቋም ወላጅ አልባ ሕፃናትና ጐዳና ላይ ተዳዳሪዎችን በማሰባሰብና በመርዳት የምትታወቀው አርቲስት ቻቺ ታደሠን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን "አልያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር" በሚል ስያሜ ዘመናዊ የትራንስፖርት ድርጅት ማቋቋማቸውን ጥቅምት 19 ቀን 2002 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

Image
ቻቺ ታደሰ

በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለ16 ወራቶች የዓለም ባንክ አዲስ አበባን ጨምሮ በ14 የአፍሪካ ከተሞች ላይ ያደረገውን ጥናት፣ በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ ትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር እና አንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅትን በግብአትነት በመጠቀም ከፍተኛጥናት ካደረጉ በኋላ ማህበሩን ለመመስረት መቻላቸውን የቦርዱ ዳይሬክተር አቶ አዲል አብደላ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለልና ችግሩን ለመሙላት ብቻ ሣይሆን ብቃት፣ ጥራትና ፍጥነት ያለው አገልግሎት የሚሰጥ ትራንስፖርት ለማቅረብ በማሰብ አውሮጳ ሠራሽ የሆኑና በአንድ ጊዜ 100 ሰዎችን መጫን የሚችሉ ዘመናዊ አውቶብሶችን እንደሚያስገቡ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ከአዲስ አበባ መንገዶች ጋር ተመሳሳይነት ባላቸው የአፍሪካ ከተሞች ተሞክረው ከ50 እስከ 60 ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን ተመሳሳይ አውቶብሶች ከየትኛው የአውሮፓ አገር መግዛት እንዳለባቸው አጥንተው መጨረሳቸውን የተናገሩት አቶ አዲል፣ "ለቢዝነሱ ሲባል የአገሩን ስም ለጊዜው ባልናገርም፤ በዱባይና በተለያዩ አገሮች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የመለዋወጫ ዕቃዎች ያሏቸውና በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ ናቸው" ብለዋል፡፡

አልያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የሚያስመጣቸው አውቶብሶች ዘመናዊ የኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኦን ላይን ባስ ትራኪንግ ሲስተም) የተገጠመላቸው በመሆኑ እያንዳንዱ አውቶቡስ በተመደበለት ሰዓትና ፌርማታ መድረሱን ከማዕከል ቁጥጥር እንደሚደረግ አቶ አዲል ገልፀዋል፡፡

ማህበሩ የፓርኪንግ ሕንፃናዎችን እንደሚገነባና ባሁኑ ሰዓት የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚያስቀር የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ ሁለት መቶ ለሚሆኑ አውቶብሶች ማቆሚያ ፌርማታዎች ለማዘጋጀት ማቀዱንም አስታውቀዋል፡፡

አንድ መቶ ሰው እስከሚሞላ ድረስ ቆሞ መጠበቅ እንዴት ጊዜ ይቆጥባል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ የትራንስፖርት አጠቃቀሙን ለሕብረተሰቡ ማስተማር እንደሚጠበቅባቸው (በስንት በስንት ሰዓት እንደሚነሳና እንደሚደርስ) አቶ አዲል ተናግረው፣ ጥራቱን ጠብቀው መቅረብ ያሳስባቸው እንደሆነ እንጂ ተሳፋሪ ሰው እንደማያጡ እርግጠኛ በመሆናቸው አውቶብሱ የጫናቸውን ብቻ ይዞ በሰዓት እንዲጓዝ ማድረግና ሌላው ዓለም የደረሰበት የትራንስፖርት አጠቃቀም ስርዓት ላይ ለመድረስ አስበውበት መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡

የሚያስመጧቸው ባለ አንድና ባለ ሁለት ደረጃ አውቶብሶች ለማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል አገልግሎት መስጠት የሚችሉና የግል ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ሁሉ በአውቶብሶቹ መጠቀም እንደሚጀምሩ በእርግጠኝነት የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፣ የካርቦን ልቀትንና የነዳጅ እጥረትን እንደሚያቃልልም ገልፀዋል፡፡

በንግድ፣ በምህንድስና፣ በባንክ፣ በአርቲስትነት፣ በማማከር፣ በፋብሪካ ሥራና ከተለያዩ የሙያ ዘርፍ በተውጣጡ የተመሰረተው አልያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የፊታችን ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚጀምር የተናገሩት አቶ አዲል፣ የአንድ አክሲዮን ዋጋ አንድ ሺ ብር ሆኖ አንድ ሰው ከ10 አክሲዮኖች በታች መግዛት እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

የአክሲዮን ሽያጩን በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ በማጠናቀቅ ወደ ሥራ ለመግባት ከባለድርሻ አካላት ጋር (አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ ትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር) ተነጋግረው መጨረሳቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አርቲስት ቻቺ ታደሠ በበኩሏ ሌሎች አርቲስቶች ሕዝብ ከሕዝብ ጋር የሚያገናኝ ሥራ እንዲሰሩ ጥሪዋን አስተላልፋ፣ ባለፉት ዓመታት ስትሰራቸው ከቆየችው የበጐ ሥራ አድራጐት በተጨማሪ በትራንስፖርቱ ዘርፍ የተሰማራችው የሕብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ስትወጣና ስትገባ በማስተዋሏ መሆኑን ተናግራለች፡፡

Source:ሪፖርተር

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”