ሪፖርተር....የትንሿ ልብ ጭንቀት

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
Post Reply
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

ሪፖርተር....የትንሿ ልብ ጭንቀት

Unread post by selam » 06 Oct 2009 22:41

Postby selam on 06 Oct 2009 21:29
የትንሿ ልብ ጭንቀት
Monday, 05 October 2009

በምሕረት አስቻለው

"ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሜ ውስጥ መገኘቱን እንደቀላል ልመለከተው አልቻልኩም፡፡ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ትልልቅ እናትና አባቶች ስመለከት እንኳ የኔ ይለይብኛል፡፡ እኔ ገና ልጅ ነኝ፡፡ ሳድግ ወደፊት ምን እሆናለሁ? ብዬ አስባለሁኝ" ያለችን የአሥራ ሠባት ዓመት ታዳጊ ነች፡፡
የአስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳ በአድቫንስ ሰርቲፍኬት የሙያ ትምህርት መቀጠል የሚያስችላትን ነጥብ በማምጣት ትምህርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነች፡፡

እናቷ ከሞተች ስድስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ያኔ ታዳጊዋ የዘጠኝ አልያም የአስር ዓመት ሕፃን የነበረች ቢሆንም ህመሟ ምን እንደሆነ ያልታወቀውንና ለረዥም ጊዜአት አልጋ ላይ የዋለች እናቷን አስታማለች፡፡ "ምንም ዘመድ አልነበረንም፡፡ እናቴም ያሳደገችኝ በሠው ቤት እየዞረች ልብስ በማጠብ ነው፡፡ ታማ አልጋ ስትይዝ የምንበላው ነገር ጨርሶ አጣን፡፡ እናቴም ሠውነቷ ቆስሎ አንድ እግሯም አልንቀሳቀስ ብሎ ነበር"፡፡

ታዳጊ ሕፃን ብትሆንም ዘወትር እናቷን የምታቀና፣ የምታገላብጥና ገላ የምታጥበው እሷው ነበረች፡፡ ጐረቤቶች ምግብ እየያዙ እናቷን ይጠይቁ እንደነበር፤ ግን ቀርበው እናቷ ምኗን እንደሚያማት ለመጠየቅ ወይም ሐኪም ቤት እንድትሄድ ለመንገር ለአንድ አፍታ እንኳን ከደሳሳ ቤታቸው ገብተው አረፍ ማለት ይፈልጉ እንዳልነበር አስታውሳለች፡፡

አባቷ እዚያው አካባቢ ጥሩ ኑሮ የነበረው ሠው ቢሆንም በድብቅ አልፎ አልፎ ለመርዳት ከመሞከር ባለፈ በግልፅ ልጁ መሆኗ እንዲታወቅ አይፈልግም ነበር፡፡ እሱም ታሞ የሞተው እናቷ ከመሞቷ ከዓመት በፊት እንደሆነ፤ ታሞ አልጋ ላይ በነበረበት ወቅት እንኳ ልትጠይቀው ስትሄድ ይሰጣት የነበረውን ምግብ አንደኛዋን አልጋ ባትይዝም በህመም ትሰቃይ ለነበረችው እናቷ ደብቃ ይዛ ወደ ቤቷ ትመለስ እንደነበር ነግራናለች፡፡

የእናቷ ህመም ሲበረታ አለችን የሚሏት ብቸኛ ዘመዳቸው አክስቷ ከዝዋይ መጣች፡፡ ለወራት አልጋ ላይ የዋለችው እህቷን ወደ ሆስፒታል ወስዳ ሕክምና እንድታገኝ አደረገች፡፡ እናቷ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሟ ውስጥ እንዳለ ታወቀ፡፡ ይህ በሆነ በሳምንቱም ህይወቷ አለፈ፡፡ "ስለ ኤች.አይ.ቪ ሲወራ ብሰማና ባውቅም እናቴ ስትሞት በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ፈራሁም፡፡ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ፣ የእናቴ መሞትና ብቻዬን መቅረቴ ሁሉንም ነገር የልጅ ጭንቅላቴ አልቻለውም፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ አክስቴ ሆስፒታል ወስዳ ስታስመረምረኝ ለምን? ብዬ ጠየቅኳት፡፡ አሁን አይደለም በጊዜው እነግርሻለሁ አለችኝ"

በድህነት እንደ ልጅ ጠግባ ያልቦረቀችው፣ የአባትነት ፍቅርና እንክብካቤ በወጉ ያላየችውና፣ በብቸኝነት ያሳደገቻት እናቷን በሞት የተነጠቀችው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን እናቷ ከሞተች ከሦስት ወራት በኋላ ሌላ አሳዛኝ ፈተና ገጠማት፡፡ የእናቷን ሞት ተከትሎ በተደረገላት የደም ምርመራ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሟ ውስጥ መኖሩ ታወቀ፡፡ ፣አሁን አይደለም በጊዜው እነግርሻለሁ፣ ብላት የነበረችው አክስቷም በአቋሟ አልፀናችም፡፡ የግድ ለሕፃኗ መንገር እንዳለባት አምና ነገረቻት፡፡ "እሷም እኔም ተቃቅፈን መላቀስ ጀመርን፡፡ ሠውነቴ እያሳከከኝ አንዳንድ ስሜቶችም ነበሩኝ፡፡ ፍርሀቴ ልክ አጣ፡፡ እያንዳንዱን ሠዓትና ቀን የማሳልፈው በፍርሀት ሆነ፡፡ አክስቴ ቤቷን ትዳሯን ትታ ከኔ ጋ ብትሆንም ማንም የሚያስጥለኝ እንደሌለ ይሰማኝ ነበር" በማለት ቫይረሱ በደሟ ውስጥ መኖሩን ያወቀችበትን ወቅት አስታውሳዋለች፡፡

በትምህርቷ ጐበዝ ተማሪ ነበረች፡፡ እናቷ በጠና ታማ በነበረበት ዓመት የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ በዚያ ጊዜ እናቷን ለማስታመም እቤት የምትቀርባቸው ቀናት ወደ ትምህርት ቤት ከምትሄድባቸው ይበልጡ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በትምህርቷ ደከም ማለት ጀመረች፡፡ ብቸኝነት፣ ድህነትና ህመም ትንሿን ልቧን ያስጨንቋት ተስፋም ያስቆርጧት ጀመሩ፡፡ የልጅ አእምሮዋ ሊመልሳቸው በማይችሉ ጥያቄዎች ህይወቷ የተወጠረውን ሕፃን ልንከባከብ በማለቷ ትዳሯ የፈረሰባት አክስቷ ግን ተስፋ በመቁረጥ መኖር እንደማይኖርባት መክራ አሳመነቻት፡፡ ሃሳቧን ሰብስባም ትኩረቷን ትምህርቷ ላይ እንድታደርግ የመሰላትን ሁሉ ሞከረች፡፡

"አሁን እኔ ያለ አክስቴ የማውቀው ዘመድ የለኝም፡፡ በአንድ ወቅት ላይ አሞኝ መድሀኒት መግዣ ስለሌላት እዚያው የተመረመርኩበት ሆስፒታል ነጠላዋን አንጥፋ ለምናለች፡፡ ባሏ ሌላ ሚስት አግብቶ የጠበቃት እኔን እኔን ስትል ነው"

በምትኖርበት አካባቢ በጆሮዋ የሰማችው ወይም ፊት ለፊት ያየችው ነገር ባይኖርም "ያው ሹክሹክታ መኖሩ ያስታውቃል" በማለት ከልጆች ጋር መቀራረብም መጨዋወትም ከተወች እንደቆየች አጫወተችን፡፡ "ጥሩ ቤተሰብ ያላት ልብስ ሲገዛላት ለኔም ታስገዛልኝ የነበረች የልጅነት ጓደኛዬ እንኳ አያቷ ከእኔ ጋር እንዳትሆን ስለነገሯት ትታኛለች፡፡ ለምን? ብዬ መጠየቁ ለእኔ ዋጋ ስለሌለው ምንም ሳልል እንደ እሩቅ ሠው ሠላም ሠላም እየተባባልን መተላለፍ ከጀመርን አንድ ዓመታችን" በማለት እናቷን ምግብ ይዘው ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው ይሄዱ የነበሩ ጐረቤቶች እቤታቸው ይገቡ ያልነበረው፣ እናቷንም ቀርበው ያላናገሯትና ያላዋይዋት ለምን እንደሆነ የገባት ዛሬ የራሷን ህይወት ስትመለከት እንደሆነ ገልፃልናለች፡፡

አክስቷና እሷ ጐርሰው የሚያድሩት የሚኖሩበትን የቀበሌ ቤት ከፍለው በማከራየት ነው፡፡በዚህ የሚያገኙት ብር ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ከቀናት በኋላ ለሚኖራት የትምህርት ቤት ምዝገባ ከዚያም የሚቀጥለው ወርሀዊ ክፍያ አስጨንቋቸዋል፡፡ "ነገሮችን በመቀበል ተረጋግቼ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት የመልቀቂያ ፈተና ላይ ከመቀመጤ ከሦስት ወር በፊት መድሀኒት መጀመር እንዳለብኝ ተነገረኝ፡፡ ፍርሀቴ እንደገና ተቀሰቀሰ፡፡ ተስፋ መቁረጥ እንደገና አስጨነቀኝ፡፡ ትምህርትና ጥናት የሚባል ነገር እርግፍ አድርጌ ተውኩኝ፡፡ ሳላጠና በመፈተኔም ነው ጥሩ ውጤት ማምጣት ያልቻልኩት፡፡ መድሃኒት ምግብ ይፈልጋል፡፡ የግድ ሥጋ አይደለም ባቄላ እንኳ ንፍሮ አድርጐ መብላት ቀላል አይደለም"

selam

Posts: 41
Joined: 25 Aug 2009 00:59

* Private message

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: ሪፖርተር....የትንሿ ልብ ጭንቀት

Unread post by selam » 09 Oct 2009 23:14

"አሙቀው" E-mail
Wednesday, 07 October 2009

Image(በምሕረት አስቻው)

ቤተሰቦቹ ላሞች ነበሯቸው፡፡ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ወተት ያከራዩ ነበር፡፡ ወተት ለማደል ዘወትር ንጋት አሥራ አንድ ሰዓት ላይ በወተት የተሞሉ ፕላስቲክ ጀሪካኖችን ይዞ ይወጣል፡፡ ረዥሙን መንገድና ድቅድቁን ጨለማ የሚያቋርጠው የተለያዩ ዜማዎችን እያንጎራጎረ እንደነበር፤ ከአሥር ዓመታት በፊትም አንድ የአካባቢው ኗሪ ሠርግ ላይ ዘፈን አውጭ ለመሆን ያስቻለውም የንጋት ላይ እንጉርጉሮው እንደሆነ አስታውሷል፡፡


ለመጀመሪያ ጊዜ ሠርግ ላይ የሠርግ ዘፈን ለመዝፈን ሲሞክር ሰው ፊት ዘፍኖ ባለማወቁ እንደፈራና እንዳፈረ አጫውቶናል፡፡ "ቤታችን ከከተማ ወጣ ያለ ስለነበር በእግሬ የምጓዘው በጨለማ ሩቅ የእግር መንገድ ነበር፡፡ ልጅም ስለነበርኩ የማንጎራጉረው ፍርሃቴን ለማስወገድ ነበር፡፡"

ዘፈን ማውጣት ከተቸገረበት የሠፈር ሠርግ በኋላ ግን የዘወትር የንጋት ላይ እንጉርጉሮው ፍርሃቱን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሰርጎች ላይ በሰዎች ፊት መጫወትንና ማስጨፈርን በማሰብ ሆነ፡፡

አቶ ብርሃኑ ያደቴን ብዙዎች "አሙቀው ብርሃኑ" እያሉ ይጠሩታል፡፡ ቋሚ ሥራዬ የሚለው በሰርግ ላይ ተገኝቶ ማድመቅና፤ ከሠርግ ቀን ቀደም ባሉት ቀናት ማታ ማታ ሰርግ ቤት እየተመላለሰ ማስጨፈርን ነው፡፡ ፣አሙቀው፣ የሚለው ቅጽል ስምም የወጣለት በዚሁ ነው፡፡

በተለያዩ ሆቴሎችና መናፈሻዎች እየተከፈላቸው ሠርግ የሚያደምቁ ቢኖሩም አቶ ብርሃኑ "የእኔ የተለየ ነው፡፡ በሠርግ እለት ብቻ ሳይሆን ሰርጉ ከመድረሱ በፊት ለተወሰኑ ቀናት ማታ ማታ ወደ ሙሽሮች ቤት እየሄድኩ አስጨፍራለሁ፡፡ ይህንንም ከሳምንት ወይም ከአስር ቀን በፊት እጀምራለሁ" ብሎናል፡፡

የሠርግ እለት ከመድረሱ ከቀናት በፊት በሙሽሮች ቤት ማታማታ መጨፈር አዲስ ነገር ባይሆንም ለቀናት የሠርግ ዘፈኖች እንዳይሰለቹ ዘወትር እየተዘጋጁ መሄድ ቀላል እንዳልሆነ ይናገራል፡፡

አቶ ብርሃኑ እንዳጫወተን የሠፈር ሰርግ ላይ የሠርግ ዘፈኖችን እያወጣ ሲያስጨፍር ባየው ሚዜ ለራሱ ሠርግ እንዲሰራለት መጠየቅ በገንዘብ መስራት እንዲችል በር የከፈተለት አጋጣሚ ነበር፡፡ በክፍያ ሲሰራ የመጀመሪያው በመሆኑ የሚጠይቀውን ብር ከፍ ቢያደርግ እድሉን አጣለሁ በሚል ስጋት ራሱ ሙሽራው አስቦ እንዲከፍለው ተናገረ፡፡ ይሄ እንደማይሆን ሙሽራው ሲገልጽለት ሃምሳ ብር እንዲከፈለው ጠይቆ በሰርጉ፣ በምስራችና በመልሱ እለት ሰርቶ ሁለት መቶ ብር ተከፍሎታል፡፡

የተለያዩ የባህልና የሠርግ ዘፈን ካሴቶችን እየገዛ በማዳመጥ ሥራውን በስፋት መሥራት ቀጠለ፡፡ ጀማሪ በነበረበት ወቅትም ሐምሌ 19 መናፈሻ በመመላለስ ሰርጎች ላይ የሚደረገውን ጭፈራና ዘፈን ይመለከት ነበር፡፡ በአንድ ሠርግ ላይ ሲሰራ የተመለከቱት ግለሰብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ድምጽ አወጣጥ እንዲሁም ማሲንቆ እንዲለማመድ እድል ሰጥተውት እንደነበርም ነግሮናል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት በየአካባቢው ሠርግ ባለበት ቤት የሠርጉ እለት ከመድረሱ (ከጥንስሱ) ጀምሮ ለረዥም ቀናት ማታ ማታ ላይ ሲጨፍሩ ማምሸት የተለመደ እንደነበር፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጊዜ በማጣት ወይም በፍላጎት መቀነስ ይህ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን ከንግግሩ ለመረዳት ችለናል፡፡ "ለጭፈራና ለሠርግ ዘፈን ብዙም ግድ የሌላቸው ሙሽሮችም አይቻለሁ፡፡ ለሠርግ ቀን ተነጋግሬ ጠዋት ላይ ሙሽራው ቤት ስደርስ ምንም ዓይነት ጭፈራ ወይም ግርግር ያልተመለከትኩበት አጋጣሚ አለ፡፡ በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ሻይ ጠጥቼ ልመለስ ብዬ የወጣሁባቸው የሠርግ ቤቶች ጥቂት አይደሉም" በማለት ይህ ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ከአካባቢ አካባቢ እንደሚለያይ መመልከቱን ገልጿል፡፡ "አያት፣ ቦሌና ሌሎች አካባቢዎች በተለያየ አጋጣሚ ከሠርግ እለት በፊት ማታ ማታ ሲጨፈር አላየሁም፡፡ በተቃራኒው ሠርጉ ከመድረሱ ከአሥራ አምስት ቀናት በፊት ክፍለ አገር ያሉ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጥተው ለቀናት የተጨፈረበት ሰርግም አይቻለሁ"

ከቅርብ ጊዜአት ወዲህ የሠርግ ስነ ስርዓቶች ላይ ሠርግ አድማቂዎች በሳክስፎን፣ በማሲንቆ አንዳንዴም በአኮርዲዮን ታጅበው ሲዘፍኑ ይታያል፡፡ ከአቶ ብርሃኑ እንደተረዳነውም እንደ አሰሪዎች የማጀቢያ መሣሪያ ምርጫና አድማቂው እንዲገኝላቸው እንደሚፈልጉት ቀን ክፍያ ይለያያል፡፡ በአኮርዲዮን የሚሰራው አልፎ አልፎ ሲሆን በሳክስፎን ማሰራት ከሌሎቹ ጋር ሲነፃፀር ውድ ይሆናል፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይል በፈረቃ ይታደል በነበረበት ወቅት የጋብቻ ሥነስርዓታቸውን ለማድመቅ የሙዚቃ ባንድ ቢቀጥሩም መብራት ሊቋረጥ ይችላል በሚል ስጋት ብዙ ሙሽሮች እንደ አቶ ብርሃኑ ያሉ ሠርግ አሟቂዎችንም ይቀጥሩ እነደነበር ነግሮናል፡፡ በዚህም የእሱና የጓደኞቹ ገበያ ደርቶ እንደነበር ገልፆልናል፡፡

"የታዳሚዎችን ትኩረት ለመሳብ ሃይሎጋ ብለን በመጀመር ተበላ ወይ ጮማው ተበላ ወይ፣ ጨፈረ ወይ ሚዜው ጨፈረ ወይ፤ መች ጨፈረና እያልን ለመሸለም ስንፈልግ ሸለመ ወይ ሚዜው ሸለመ ወይ እያልን እንቀጥላለን"

ብዙዎች የሠርግ አሟቂዎቻቸው በሥራ ላይ እስካሉ መጠጥ እንዳይቀምሱ እንደሚያስጠነቅቁ፤ እሱም ፕሮግራሞች ሳይጠናቀቁ ምንም ዓይነት መጠጥ እንደማይቀምስ ገልጾልናል፡፡ ትንሽ መጠጥ ቀምሶ በነበረባቸው የሠርግ አጋጣሚዎች ድካም ተሰምቶት ያውቃል፡፡ በሥራ ላይ ሆነው መጠጥ በጠጡ ሌሎች ሠርግ አድማቂዎች ላይ ደግሞ ዘፈን ሲጠፋቸው፣ ግጥምም ሲበላሽና ዘለፋ ሲሆንባቸው መመልከቱን አልደበቀንም፡፡

ከወራት በኋላ ወንድሙ እንደሚያገባ በሠርጉ ላይ አሟቂ ከመሆን ይልቅ እንደ ቤተሰብና ታዳሚ ለመጫወትና ለመታደም በማሰብ ሌላ ሠርግ አሟቂ መቅጠራቸውን፣ እሱም አሁን ቤት በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ሲጠናቀቅም የማግባት እቅድ እንዳለው ነግሮናል፡፡

፣ለማሞቅ፣ ፕሮግራም በያዙበት ተመሳሳይ ቀን ሌላ ሥራ ሲገጥማቸው ለሌላ ጓደኛ አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ እንደዚህ ያለ ውለታ የተደረገለት አሟቂም ሥራውን ላመጣለት ጓደኛው የሃምሳ ብር የሞባይል ካርድ በስልክ የጽሑፍ መልዕክት እንደሚልክለት፤ የዚህ አይነቱ አሰራርም በሠርግ አሟቂዎች ዘንድ የተለመደ እንደሆነ አቶ ብርሃኑ አጫውቶናል፡፡

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”