ከኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት የኮበለሉ የስፖርት ጋዜጠኞች ቁጥር ሰባት ደረሰ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
Ethiopians
Site Admin
Site Admin
Posts: 97
Joined: 07 Aug 2009 10:13
Contact:

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት የኮበለሉ የስፖርት ጋዜጠኞች ቁጥር ሰባት ደረሰ

Unread post by Ethiopians » 23 Sep 2009 15:34

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት የኮበለሉ የስፖርት ጋዜጠኞች ቁጥር ሰባት ደረሰ

(እሁድ መስከረም 10 ቀን 2002 ዓ.ም. September 20, 2009)፦ ብዙውን ጊዜ "ሙያዊ ነፃነትን በመጫን" ከሚታወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠንና ራዲዮ ድርጅት በተለያዩ አስተዳደራዊ፣ ፖለቲካዊና በዘመድ የቅጥር ጫናዎች ምክንያት ሥራቸውን እየለቀቁ ወደ ግሉ የሥራ መስክ የሚሠማሩ የመንግሥት ጋዜጠኞች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑ ታወቀ። ጥቂት የማይባሉትም ሀገር ለቀው መሰደዱን ምርጫቸው አድርገዋል።

Image

በዚሁ መሠረት ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና ራዲዮ ድርጅት ከምርጫ 97 በኋላ ከሀገር እንደወጡ የቀሩ የስፖርት ጋዜጠኞች ቁጥር ብቻ ሰባት ደርሷል። የስፖርት ጋዜጠኞቹን ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ያደረጋቸው በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተገኝታ ለመዘገብ ወደ ጀርመን አምርታ የነበረችው ሒሩት ገብረ-አምላክ ነች። ሒሩት ለዘገባ ከሄደችበት ጀርመን እስከ መስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. ምሽት ድረስ ወደ ሀገርዋ አልተመለሰችም።

ከእሷ በፊት ከአማርኛው የስፖርት ዝግጅት ክፍል ስዊዘርላንድ ተጉዛ የቀረችውን ሐናን እና ወደ ጀርመን አመርቶ በዛው የከተመውን ኢዘዲን ከድርን ጨምሮ ሦስት ጋዜጠኞች እንደወጡ ቀርተዋል። ከኦሮምኛ እና ከትግርኛው ቋንቋ የስፖርት ዝግጅት ክፍልም እንደዚሁ 3 ጋዜጠኞች መኮብለላቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ድርጅት ምንጮች ገልጸዋል።

Source:ethiopianzare
የሁላችን ፎረም Our forum. Enjoy!
ethiopiaforums.com

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”