Page 1 of 1

ለአይ ሲ ጂም ያለን ግምት ንቀትና ንቀት ብቻ ነው...መለስ

Posted: 20 Sep 2009 15:12
by ኦሽንoc
ለአይ ሲ ጂም ያለን ግምት ንቀትና ንቀት ብቻ ነው"

Image
"ከአሜሪካንሪ ጋር ከፀሐይ በታች ባለ በሁሉም ነገር እንስማማለን? በጭራሽ፤ እንኳንስ ከኦባማ ጋር ቀርቶ፣ ከፀሐይ በታች ባለ ሁሉም ነገር ከኔም ከራሴም ጋር አልስማማም፡፡" በማለት አሁን ስላለው የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሴት ልጃቸው ወደ ፖለቲካ እንደምትገባ ተጠይቀው " . . . ጥናቱና ብርታቱ ካለሽ ቀጥይ አለዚያ ግን ርቀሽው ኑሪ" ብለው እንደሚመክሯት ተናግረዋል፡፡


የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዳማ ሊያደርጉት አስበው ስለተቋረጠው ስብሰባ " . . . የፓርቲያቸን ደጋፊዎች በማያገባቸው ገብተው ስብሰባ በባህላዊ የኦሮሞ ምርቃት መጀመር አለበት ያሉበትን ጉዳይ ነው፡፡" ብለዋል፡፡

ፖለቲከኝነት ለማንምና ለሁሉም የማይመኙት ሥራ ስለመሆኑ

አቶ መለስ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱና ከተለመደውና ከመደበኛው የታወቀ ወቅታዊ ጥያቄ ወጣ ያለው ልጃቸው የአባቷን ፈለግ ተከትላ ፖለቲከኛ ትሆን እንደሁ የፖለቲካ ሰው ትሆን ዘንድ ይመክርዋት፣ ያበረታትዋት ይገፋፉት አንደሆነ ነው፡፡

እንደመታደል ሆኖና ደግነቱ እንዲህ ያለ ግዳጅ የለብኝም ብለው የጀመሩት አቶ መለስ በዚህ ረገድ ልጃቸውን የመምከር፣ የእሷን ጥያቄ እንደ አባት የመመለስ ግዳጅ ገና ያለባቸው ቢሆን ኖሮ ደግሞ ልጃቸውን የሚሏት ፖለቲከኛ መሆን የሚጠይቀው "". ጥናቱ፣ ብርታቱ ካለሽ ቀጥይ አለዚያ ግን ርቀሽው ኑሪ"". ብለው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
Image
Semhal Meles source:ethioplanet


በመካከል አቋርጦ ይህ የተባለው "ጥናት፣ ብርታት ችሎታ" ልጃቸው ያላት እንደሆነ መልሶ ለጠየቃቸው ጋዜጠኛ አቶ መለስ የሰጡት መልስ አይመስለኝም የሚል ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለልጃቸው ብቻ ሳይሆን ፖለቲከኛ ለመሆን ለሚመኙ ወጣት ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚያስተላልፉት መልዕክትና የሚሰጡት ምክር በተመሳሳይ ሁኔታ "ጥናቱ፣ ብርታቱ ካላችሁ ብቻ፣ አለዚያ ለጤንነታችሁ ስትሉ ከዚህ ሥራ፣ ከዚህ ሙያ ራቁ፡፡ እሱ ጥግ ድረሽ አትበሉ" የሚል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ-ዩኤስ አሜሪካ ግንኙነት

ከወቅቱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ያለንን ግንኙነት በተመለከተ ምናልባትም ታውቁታላችሁ ተብሎ እንደሚገመተው ከቀድሞው አስተዳደር ከነበረን ይልቅ በአዲሱ አስተዳደር ውስጥ ብዙ ነበር ወዳጆች ያሉን፡፡

ስለዚህም ከእርስ በርስ በይነ ሰብአዊ ውይይቶች አኳያ ከዚህ በፊት ለብዙ ዓመታት ከነበረው ይልቅ አሁን ሁኔታው ቀናና የቀለለ ነው፡፡ የዚህ ዝምድና መሠረታውያን ደግሞ በጣም ጠንካሮች ናቸው፡፡

ከአሜሪከ ጋር ያለን የአጋርነትም ቡድኑ መሰረት ላይ ያለ ነው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ እና በእኛ መካከል አንድን ወይም ሌላ ጉዳይን በተመለከተ የአመለካከት ልዩነቶች አሉን ወይ? አዎ፣ በጣም እንጂ፡፡ ሁሌም ልዩነቶች አሉ፡፡

ያወጡትን የሰብዊ መብት ሪፖርት ለምሳሌ እንውሰድ፤ በእኛ በኩል ይህ ስራ በጣም ሲበዛ የገረፍ ገረፍና ያለተገቢው ጥንቃቄ የተሰራ ስራ ነበር፡፡ እጅግ በጣም ግዙፍ ኤምባሲ እዚህ አላቸው፡፡ ሌላው ቢቀር እዚሁ . . . አፍንጫቸው ስር የሚከናወኑ ናቸው የሚባሉትን ጉዳዮች እውነትነት ሊያጣሩና ሊያረጋግጡ ይገባቸው ነበር፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚከፍሏቸውን ሰዎች ድምፅ የገደል ማሚቶ ሆነው ማስተጋባት መረጡ፡፡ ስለዚህም በሪፖርቱ ላይ ያለንን ቅሬታ/ተቃውሞ፣ ነገር ግን በንቃት ሳይሆን በአክብሮት፣ አስታወቀን፡፡

እናም፣ ከፀሀይ በታች ባለ በሁሉም ነገር እንስማማለን? በጭራሽ፣ እንኳንስ ከኦባማ ጋር ቀርቶ፣ ከፀሐይ በታች ባለ ሁሉም ነገር ላይ ከኔም ከራሴም ጋር አልስማማም፡፡

ሳንስማማ ስንቀር የተለያየንበትን በግልፅ በግላጭ እንገልጻለን? አዎ፡፡ ይህ ታዲያ አንዳንዴ ከጊዜ ወደ ጊዜ የውጥረት ስሜት ይፈጥራል ወይ? ምናልባት አዎ፡፡ ይህ ማለት ግንኙነቶችን መሰረታዊ ድክመት አለበት ማለት ነው? በጭራሽ

ስለዚህም ረጠያቂውሪ ያስተዋልካቸው በመሰለህ ቅሬታዎች (መቃቃሮች) ውስጥ አዲስ ነገር የለባቸውም፤ አዲስ ነገርም አይደሉም፡፡ ከኦባማ አስተዳደር ጋር በተለይና በግል የተያያዘ ምንም ነገር የላቸውም፡፡ እንዲያውም አዲስ ነገር አለ የሚባል ከሆነ የኦባማ አስተዳደር መምጣት ቅሬታዎችን አለዝቧል፡፡ የተወጠረውን አላልቷል የሚለው ነው፡፡

አይ ሲ ጂ (ICG) ስለተነበየው የኢትዮጵያ ጉዳይ

የአይ ሲ ጄ (የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ) ትንታኔ የተጻፈበት ወረቀት ያህል፣ ፋይዳ ያለው ያን ያህል ዋጋ የሚያወጣ አይደለም፡፡ አይሲጂ ኢትዮጰያ ላይ መዓት ይወርዳል ብሎ ሲተነብይ ይህ ስንትና ስንት ጊዜው መሆኑን ነው፡፡

ከአመታት በፊት ብራስልስ በሚገኘው ኤርትራዊው አምባሳደር የተፃፈ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሪፖርቱ እንደወጣ ወዲያውኑ ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል ጽሑፍ ተጽፎ የነበረ መሆኑ እውነት ነው፡፡

ይህ ማለት አይሲጂ በኤርትራ መዳፍ ውስጥ ነው ማለት አይደለም፡፡ የዚህ ትርጉም አይ ሲ ጂ ፋይናንስ አድራጊዎቹ ቀለብ ሰፋሪዎቹ በእያንዳንዱ እና በሁሉም ላይ ካልጫን ሞተን እንገኛለን ከሚሉት ፖሊሲ ጋር አልስማማ ያሏቸውን ሌሎች አማራጮች አፈር ድሜ የማስገባት አላማውን ለማራመድ ያልሆኑ የትንታኔ ዘዴዎችን የኢንፎርሜሽን ምንጮችን ሁሉ መጠቀም ይችላል ማለት ነው፡፡

በመሆኑም ብዙ አልተደነቅንም፤ ተገቢ ያልሆነ ጭንቀት ውስጥም አልገባንም፡፡
አጋጣሚ ሆኖ ጥቃቶች የሚያዙበት እጅግ በጣም ብዙ ቢልዮን ዶላሮች አሏቸው፡፡ ስለዚህም ሌሎች በተለይም በታዳጊ ዓለም ያሉት እንደምን አድርገው የራሳቸውን የውስጥ ጉዳይ ማካሄድ እንዳለባቸው በቀጭን ትዕዛዝ የማስገደድ ከሰማይ ከወረደ ከ"ፈጣሪ" ከተሰጣቸው ገንዘብና ሀብት ጋር የሚስማማ ከሰማይ የወረደ ከ"ፈጣሪ" የተሰጠ መብት አለን ብለው ያስባሉ፡፡ ያንን ገንዘብና ሀብት ለዚህ አላማ ሊገለገሉበት ይሻሉ፡፡

እነሱም እንደዚያ ብለው ማሰብ የመሰላቸውን አመለካከት መያዝ መብታቸው ነው፣ ልክ እኛ የመሰለንን አመለካከት ለመያዝ ባለመብት እንደሆን ሁሉ እኛ ለሆነ ሰው መልስ መስጠት ያስፈልገን ዘንድ አስቀድሞ ነገር ያንን የሆነ ሰው አክብረን ለዚያ ሰው ክብር ሰጥተን መጀመር አለብን፡፡ እናም ለምሳሌ ያህል ለረአሜሪካሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት ምላሽ ሰጥተናል፡፡

ይህንን ያደረግነው መጀመሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አክብረን ለሱ ክብር ሰጥተን በመነሳታችን ነው፡፡ ስለዚህም ለሪፖረቱ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው፣ ይገባልም ብለን አመንን፡፡ ለሚንቁት መልስ አያሰጡም፤ ለአይ ሲ ጂም ያለን ግምት ንቀትና ንቀት ብቻ ነው፡፡ አንጓጠው ለሚያዩት ወራዳ ሪፖርት መልስ አይሰጡም፡፡

ስለመንግሥት የአድማ ብተና የአቋም ግንባታ

"አድማ መቋቁምን እና ምርጫ 97ን ተከትሎ የተከሰውን ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የመንግሥት የራሱ ግምገማም የተገቢው መሳሪያና ሥልጠና አለመኖር በእርግጥም ከችግሮቹ አንዱ እንደነበር ያሳያል፡፡ ይህ ችግር ሊቀረፍ የሚገባው ነው፡፡ ስለዚህም ከ97 ጀምሮ ፌዴራል ፖሊስን በተሻለ ሁኔታ ለማስታጠቅና ይበልጥ ለማሰልጠን መንግሥት የአቅሙን የተቻለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ 1997 ዓ.ም. ከነበረው በጣም በተሻለ የታጠቁ እዚያ የበለጡ የሰለጠኑ ስለመሆናቻው እርግጠኛ ነኝ፡፡"
በቅርቡ ወደ አገር ቤት ስለተጠሩት በርካታ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች

አምባሳደሮች ወደ አገር ቤት የተጠሩት በከፊል መደበኛ በሆነ የተለመደና የዘወትር አሰራር ነው፡፡ በከፊል ደግሞ በአገር ቤትም በውጭ አገርም ከሚኖረው የሰው ኃይል ድህረ ምርጫ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የሚታሰበውና የሚጠበቀው ከምርጫው በኋላ ፓርቲው የቀየሰው ኘላን አካል ተደርጐ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም ያለው እያንዳንዱ ሹመትና ምደባ ላይ ዙሪያ መለስ የሆነ ግምገማ እንደሚኖር ነው፡፡

ፓርቲው በምርጫው ካሸነፈ ያንን በመንግሥት ውስጥም መተባበር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም በቁልፍ ኤምባሲዎችም ጨምሮ በመላውና ዳር እስከ ዳር ባሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች ዙሪያ መለስ አዲስ ምደባና የአሰላለፍ ለውጥ ይደረጋል፡፡

እነዚህ ኤምባሲዎች ይህን የመሰለው መሠረታዊ ብወዛ እውንና አስፈላጊ ስለመሆኑ፣ ሲሆንም ያወቁት ዘንድ ሁሌም ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡

ለውጭ የግብርና ኢንቬስተሮች ሰፊ መሬት ስለመስጠት

ከኢህአዴግ "አሰቃቂ" ፖሊሲዎች አንዱ አድርገው መሬት ይሸጣሉ ብለው ለሚከሱን ሰዎች መሬት የግል አለመሆኑን፣ የማይሸጥ፣ የማይለወጥ መሆኑን፣ በሊዝ ብቻ የሚሰጥ መሆኑን ማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡

የተጠየቅሁት ለኢንቬስተሮች መሬት በሊዝ ስለመስጠት ከሆነ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላ ወይም በሌላ የትም ቦታ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ባከራየሁ ደስታውን አልችለውም፡፡ ምክንያቱም በጥቅም ላይ ያልዋሉ፣ በጥቅም ላይ ሊውሉ ያልቻሉ (በሄክታር) ሚልዮኖችና ሚሊዮኖች መሬት አሉን በነዚህ የአገሪቱ ክፍሎች አሉንና ነው፡፡

አዎ እውነት ነው በነዚህ ቦታዎች ኢትዮጵያውያንን ለማሰፈር ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ ሆኖም ግን የእኛ ለጋሾች "በቀደሞው መንደሮቻቸው ሆነው የምግብ እርዳታ የሚያገኙ ሰዎች ወደ ሰፈራ መንደር አንዲት ስንዝር ከተራመዱ የምግብ እርዳታውን ያጣሉ" እስከ ማለት ድረስ በተግባር ላይ ልናውለው የሞከርነውን እያንዳንዱን የሰፈራ ፕሮግራም ተቃውመውናል፡፡

የሰፈራ ፐሮግራማችን ቆሟል፡፡ ለማንኛውም ግን ኢትዮጵያውያንን አስፍረንም ለኢንቨስተሮች መስጠት የምንችለው ከበቂ በላይ መሬት አለን፡፡ እናም ኢንቬስተሮች ወደ አትዮጵያ ቢመጡ፣ በእርሻ ላይ ኢንቬስት ቢያደርጉ ለአገሪቱም፣ ለዓለም አቀፍ ገበያውም ተጨማሪ ምግብ ቢያመርቱ ነው ትርጉም ያለው፣ ይበልጥ ስሜት የሚሰጥ የሚሆነው፡፡

ብቸኛው ችግር እየሆነ አለመሆኑ፣ በሚፈለገው ፍጥነት አለመደረጉ ነው፡፡

ኢህአዴግ ተቃዋሚ ፓርዎችን
"አላስቆም አላስቀምጥ" ይላል ስለሚባለው ክስ

እነዚህ "ቁምስቅል" እያየን ተቸገርን ብለው እሱ የሚያሳስባቸው ፓርቲዎች ይህ ችግር ካለ ችግሩን ስለሚያስቀረው ችግሩ ከሌለ ደግሞ እንዳይኖር ስለሚያደርገው ስለፓርቲዎች የስነ ምግባር ደንብ ያን ያህል ሲጨነቁና ሲጠበቡ አይታይም፡፡

እኔ እንደሚሰማኝ የእነዚህ ግለሰቦች ፍላጎት በምርጫቸው ውስጥ ከምር መወዳደር አይደለም፡፡ የእነሱ ፍላጎት በምርጫው ትርጉም ባለው አኳኋን መሳተፍ ሳይሆን የምርጫውን ሂደት ገና ከአንደኛው ቀን ጀምሮ ማራከስና ማጣጣል ነው፡፡

በአንዱ ፓርቲ ወይም በሌላው አማካኝነት የሚፈፀም "ሀራስመንት" በጭራሽ የሌለበት የምርጫ ሂደት የሚመኝ ካለ እንግዲያውስ ያ ሰው ወደ ሌላ ፕላኔት መሄድ አለበት፡፡

ምክንያቱም አሜሪካን ምርጫ ጨምሮ አካትቶ ለምሳሌ አሁን በቅርቡ እንደተደረገው አክራሪ ቀኝ መንገደኛው "ሀራስ" የማያደርግበት ምንም አይነት ምርጫ ልብ አድርጌ አላውቅም፡፡

የነፃ እና የትክክለኛ ምርጫ የመኖር ቁልፍ ጉዳይ መጀመሪያ እንደዚህ አይነት ድንገቶች (ኤንሲደንትስ) በድንገቶች ደረጃ መቅረት እና እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ብቻ የሚያጋጥሙ የማይለመዱ መሆን ያለባቸው መሆኑ ሁለተኛ ደግሞ እነዚህ ድንገቶች ሲያጋጥሙ በቀጥታና በግልፅ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ መሆኑ ነው፡፡
እዚህ አገር በመሆን ላይ ያለው እቅጩን ይኼ ነው፡፡

እኔ እስከማውቀው ድረስ ያጋጠመ አንድ ድንገት የሆኑ የፓርቲያችን ደጋፊዎች በማያገባቸው ገብተው ረየአዳማውሪ ስብሰባ በባህላዊው የኦሮሞ ምርቃት መጀመር አለበት ያሉበትን ጉዳይ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ድንገቶችም በየትም አገር ሊያጋጥሙ የማይችሉ በጭራሽ ያልተለመዱ መሆናቸውን ልብ ያደረግነው በደስታ ነው እንደዚህ ያሉ ሲበዛ ያልተለመዱ ድንገቶችም በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ ረተቃውመንሪ በማስተናገዳችንም እንኮራለን፡፡ እናወግዛለን በጭራሽ የማይደገም መሆኑንም እናረጋጣለን፡፡
Riporter amharic

VOA መለስ የአይ ሲ ጂን ሪፖርት በተመለከተ ዘገባ

Posted: 20 Sep 2009 15:21
by ኦሽንoc
VOA መለስ የአይ ሲ ጂን ሪፖርት በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ያዳምጡ።

የ አይጥ ምስክሯ ድምቢጥ...መለስ